TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.2K photos
1.45K videos
208 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አብን #አቶ_ክርስቲያን_ታደለ

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሩና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ፤ የአብን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ አመራሮች ፣ አባላት፣ ደጋፊዎች ማዋከብ እና አፈና እየደረሰባቸው መሆኑን በመግለፅ ይህ ድርጊት በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል አሉ።

ደርሷል ስላሉት ማዋከብ እና አፈና ፣ መቼ ? የት ? እንዴት ? እነማንን ? ስለሚሉ ዝርዝር ጉዳዮችን በግልፅ የሰጡት ማብራሪያ የለም።

አቶ ክርስቲያን በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " አብን ዝቅ ሲል የአባላቱና ደጋፊዎች፥ ከፍ ሲልም የንቅናቄውን ዓላማ የሚጋሩ ኢትዮጵያውያን ንብረት መሆኑን ገዥው የብልጽግና ፓርቲና ያዋቀረው መንግስት በውል ሊያውቁት ይገባል " ብለዋል።

አክለውም " የተፎካካሪ ፓርቲ የውስጥ ጉዳይ የፓርቲው አባላትና በየደረጃው ያለው ሕጋዊ መዋቅር ጉዳይ ነው። የአብን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ አመራሮችን፣ አባላትንና ደጋፊዎችን ማዋከቡ በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል " ሲሉ ገልፀዋል።

" እየተደረገ ያለው አፈናና ውርክቢያ ማንንም አይጠቅምም፤ በተለይ ደግሞ ገዥውን ፓርቲ አይጠቅምም " ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

አቶ ክርስቲያን ፤ " አብን በሕዝብ ምርጫ በራሱ መንግስት ለመሆን የሚታገል ፓርቲ እንጂ የገዥው ፓርቲ ሁሉንም የመጠቅለል ስካር መደገፊያ ምርኩዝ አይደለም " ሲሉ ፅፈዋል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ከጥቂት ቀናት በፊት የፓርቲያቸው ስራ አስፈፃሚ ከህገደንብ እና አሰራር ውጭ በመሆን አፍራሽ ድርጊቶችን እና የዲሲፕሊን ጥሰቶችን ፈፅመዋል በሚል የመጨረሻ ያለውን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷቸው እንደነበር ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ አቶ ክርስቲያን ፤ መሰል ውሳኔዎችን ለመወሰን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሥልጣን የሌለው መሆኑን መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ነው። የም/ ቤቱ አባላት ጥያቄዎችን እየቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጠያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። እስካሁን ፦ - ከኦነግ ሸኔ፣ - ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ፣ - ከሰሜኑ የሰላም ስምምነት፣ - ከዜጎች መፈናቀልና ግድያ፣ - ወደ አዲስ…
#ፓርላማ

" እርስዎስ ስልጣንዎን በመልቀቅ የመፍትሄው አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ ? በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀሙ እንዲሁም በማንነት ተኮር የዘር ማጥፋት ፣ የዘር ማፅዳት እና የማንነት ማሳሳት ወንጀሎች ተጠያቂ ለመሆን ምን ያህል ዝግጁ ኖት ?

#አቶ_ክርስቲያን_ታደለ (የህ/ተ/ም/ቤት አባል) ጠቅላይ ሚኒስትሩን ምን ጠየቁ ?

" የጥያቄዬ መንደርደሪያ የሚሆን ማስታወሻ ብዬ ወደ ጥያቄዬ አመራለሁ።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በዚህ ምክር ቤት እና በተለያዩ መድረኮች ስለ እርሶ እና ስለሚመሩት የአስፈፃሚ መንግስት ተጠየቅ ሲቀርብቦት ለተጠየቁ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ጠያቂዎችን የሚያጥላላ አስተያየት ሲያራምዱ አለፍ ሲል ተጠየቅ የቀረበቦት የወጡበትን ብሄር በመጥላት እንደሆነ አድርገው ምላሽ ሲሰጡ የቅርብ ትዝታችን ነው።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጥያቄ የማቀርብልዎ እኔ በብሄሬ አይደለም፤ ይህን ጥያቄ ሳቀርብልዎ እርሶ የሚወክሉትን ብሄር በመጥላት አይደለም ምላሽ እና ማብራሪያ ሲሰጡም ለጥያቄዬ ብሄርዎን እና ምናልባት የመንግስት ግልበጣ ሴራ ነው ከሚል ምላሽ እና ማብራሪያ እንዳይሰጡ ከወዲሁ አደራ ማለት እፈልጋለሁ።

ወደ ጥያቄዬ አመራለሁ ...

የዜጎችን ደህንነት እና የሀገርን ሉዓላዊነት መጠበቅ ዝቅተኛው የመንግስት ኃላፊነት ሆኖ ሳለ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ይገደላሉ፤ ይፈናቀላሉ፣ ቤታቸው ይፈርሳል፣ ንብረታቸው ይወድማል የሀገር ሉዓላዊነትን በሚዳፈር መልኩ የጎረቤት ሀገራት ሰራዊቶች በኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብ፣ እና ደቡብ ምዕራብ ወሰኖች በርከታ ኪሎ ሜትሮችን ዘልቀው በመግባት ወረራ ፈፅመዋል።

... የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በሪፖርቱ ደጋግሞ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ስለሚገደሉ ዜጎች፣ ስለሚፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ወንጀሎች ፣ መፈናቀሎች፣ ግድያዎች ፣ ቤት መፍረሶች በሪፖርቱ ያቀረበው ነው።

አሁን ላይ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የዜጎች ደህንነት እና የሀገር ልዑላዊነት ዋና ስጋት ምንጭ ሆኖ የምናየው እርሶ የሚመሩት መንግስትን ነው።

እርሶ በአፍዎ ኢትዮጵያ አትፈርስም ቢሉንም በተግባር ግን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት በመንግስትዎ እየተናዱ ነው።

የበርካታ ሀገራት መሪዎች መሰል ኃላፊነትን በወጉ አለመወጣት ጉድለት ሲያሳዩ ህዝብን ይቅርታ ጠይቀው ስልጣናቸውን ሲለቁ ይታያል፤ በሀገራችንም የቀድሞ ጠ/ሚ ክቡር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተመሳሳይ ህዝባዊ ተጠየቅነት ሲቀርብባቸው ስልጣን መልቀቃቸውን እናስታውሳለን እርስዎም ወደ ስልጣን የመጡት በዚሁ ተጠየቅ ምክንያት ነው፤ እርስዎስ ስልጣንዎን በመልቀቅ የመፍትሄው አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ ? በሰብዓዊነት ላይ በተፈፀሙ እንዲሁም በማንነት ተኮር የዘር ማጥፋት ፣ የዘር ማፅዳት እና የማንነት ማሳሳት ወንጀሎች ተጠያቂ ለመሆን ምን ያህል ዝግጁ ኖት ? አመሰግናለሁ !! "

@tikvahethiopia