TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#YouTube

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዩትዩብ ቻናል የለውም!

ከሰሞኑን በTIKVAH-ETH (Tikvah-Ethiopia) ስም ዩትዩብ ላይ እውቅና የሌላቸው፣ ሰዎችን የሚያሸብሩና የሚያስደነግጡ የተለያዩ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆኑ እየተመለከትን ነው።

እነዚህ የሚሰራጩት መረጃዎች በቀን ውስጥ ከ50,000 በላይ ሰዎች አንዳንዴም በመቶ ሺ የሚጠጉ ሰዎች ጋር እየደረሱ በርካቶችን እያሳሳቱ ነው።

የቲክቫህ ባለቤቶች ከ895,000 በላይ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ናቸውና ማንኛውም ስራ ያለእናተ እውቅና እንደማይሰራ እንድትገነዘቡልን እንፈልጋለን።

እስካሁን በፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ዩትዩብ፣ ትዊተር ላይ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እያደረጋግን አይደለም።

ምናልባት ከቴሌግራም ውጭ በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች መንቀሳቀስ እንኳን አስፈላጊ ከሆነ ለእናተ አሳውቀን የምንጀምረው እንጂ ያለእናተ እውቅና የምንሰራው ስራ አይሆንም።

በተረፈ በዩትዩብ ላይ በTIKVAH ስም ሀሰተኛ እንዲሁም ከእኛ ያልሆኑ መልዕክቶችን የሚያሰራጩትን አካላት እነማን እንደሆኑ የማጣራት ስራ እየሰራን ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#YouTube ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዩትዩብ ቻናል የለውም! ከሰሞኑን በTIKVAH-ETH (Tikvah-Ethiopia) ስም ዩትዩብ ላይ እውቅና የሌላቸው፣ ሰዎችን የሚያሸብሩና የሚያስደነግጡ የተለያዩ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆኑ እየተመለከትን ነው። እነዚህ የሚሰራጩት መረጃዎች በቀን ውስጥ ከ50,000 በላይ ሰዎች አንዳንዴም በመቶ ሺ የሚጠጉ ሰዎች ጋር እየደረሱ በርካቶችን እያሳሳቱ ነው። የቲክቫህ ባለቤቶች…
#YouTube

ዩትዩብ ላይ በTIKVAH-ETH ስም ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩ አካላት አጠቃላይ መረጃዎችን ከገፁ ላይ አጥፍተውታል ፤ በተጨማሪ ስሙን ከTIKVAH-ETH ወደ "Hagere Ethiopia ሀገሬ ኢትዮጵያ" ቀይረውታል።

በTIKVAH-ETH የቤተሰብ አባላት ስም የዩትዩብ ገፅ ከፍተው ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩት አካላት ላይ አስፈላጊው የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው።

ምንም እንኳን ከዚህ ቀደም ያሰራጯቸውን ሀሰተስኛና ሰዎችን ሚያሸበሩ መረጃዎች ከገፃቸው ቢያጠፉም በአንድ እና በሁለት ቀን በመቶ ሺ ለሚቆጠር የዩትዩት ተጠቃሚ ደርሰዋል ፤ እኛም እኚህ አካላት ማንነታቸውን እንደደረስንበት #በህግ የምናስጠይቃቸው ይሆናል።

በድጋሚ #ለማስታወስ TIKVAH-ETHIOPIA ዩትዩብ ላይ ምንም አይነት ቻናል #የለውም። አሁንም በቲክቫህ ስም ዩትዩብ ቻናል ከፍተው #ገንዘብ ለመሰብሰብ ሲሉ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Youtube

ዩቲዩብ (YouTube) ብዙ ቪዲዮዎች ላይ ማስታወቂያዎች ማሳየት እንደሚጀምር እና ለሁሉም ማስታወቂያ ግን ክፍያ ላይፈጽም እንደሚችል አስታውቋል።

ኩባንያው በአሁኑ ወቅት የማስታወቂያ ገቢውን በሽርክና መርሃ ግብሩ ላይ ከተመዘገቡ ቪዲዮ ሠሪዎች ጋር ይጋራል።

ከዚህ በኋላ ግን ዩቲዩብ የሽርክና መርሃ ግብሩ አካል ያልሆኑ በአንዳንድ ቪዲዮዎች ላይም ማስታወቂያዎችን ማስገባት እጀምራለሁ ብሏል።

በአገልግሎት ውሉ ላይ በተደረጉ ለውጦች ምክንያት ዩቲዩብ ከማስታወቂያዎቹ የሚገኘውን ገቢ ለቪዲዮ ሠሪዎች ላያጋራ ይችላል።

ከዚህ በተጨማሪ ተመልካቾች ከፍተኛ የሆነ ቁጥር ያላቸውን ማስታወቂያዎችን እንዲያዩ ሊገደዱ ይችላሉ መባሉን BBC አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TikvahFamily

ስለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ፦

• ቲክቫህ/ተስፋ ኢትዮጵያ ሰውነትን ያስቀደሙ ሁሉንም የሰው ፍጡር፣ ህዝብን እና ሀገርን የሚያከብሩ ፣ በማንኛውም ጉዳይ ሚዛናዊ አመለካከት ያዳበሩ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ ቤት ነው።

• የቤተሰቡ አባላት መረጃ ማካፈል፣ አንዱ ያልሰማውን ሌላው እንዲሰማው መጠቆም ፣ በሚዲያ ላይ የሚከታተሉትን ሌላው የቤተሰቡ አባል እንዲያውቀው ማድረግ ይችላሉ። በአጭሩ የቤተሰብ አባላቱ እርስ በእርስ መረጃ ልውውጥ የሚያደርጉበት ነው። (ምንጭ በመጥቀስ)

• በቤተሰቡ / አባላት በማንኛውም ጉዳይ ላይ ሀሳብን በነፃነት መግለፅ የሚቻል ሲሆን አንዲት ቃል ስድብ ሆነ የሰዎችን ክብር ፣ ሃይማኖት፣ ብሄር ማንነትን የሚነካ መልዕክት መላክ ከቤተሰቡ ወዲያው በቀጥታ ያስቀንሳል።

• ቲክቫህ ኢትዮ. ከተመሰረተ አንስቶ ከማንም ወገን ፣ ከየትኛውም አካል (የመንግስት ሆነ ተቃዋሚ፣ አልያም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት) ጋር ግንኙነት የሌለው ሲሆን በየትኛውም አካል አይደግፍም፤ አይታግዘም። ለስራ በሚል ከቤተሰቡ ገንዘብ አይጠይቅም አያሰባስብም።

ተቋርጠው የነበሩ የቤተሰቡን ስራዎች ስለማስቀጠል ፦

- ባለፉት ሁለት ክረምቶች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በጦርነት ሳቢያ ዓመታዊ ለገጠር ት/ቤቶች የሚደረገው የመፅሀፍ ማሰባሰብ ዘመቻ እና የፀረ ጥላቻ ንግግር ዘመቻ ተቋርጦ ቆይቷል። በዚህ አመት ለማስቀጠል ዝግጅት ተደርጓል።

- ሲቆራረጥ የነበረው ለግለሰቦች የሚደረግ የህክምና ድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻም በዚህ ዓመት የሚጀምር ሲሆን ከዚህ በፊት በተለየ ሁኔታ ስራው ይሰራ የሚለውን ሃሳብ ያላችሁ የቤተሰባችን አባላት ማሳወቅ ትችላላችሁ።

- ከዚህ ቀደም በቤተሰቡ አባላት የሚተላለፉ አጭር የቅሬታ ፣ የጥቆማ፣ የፀጥታ ችግር ማሳወቂያ ፣ ትችት፣ ጥያቄ በስፋት መላክ ይቻላል። እንደከዚህ ቀደሙ መልዕክት ሲላክ አጭር ከጥላቻ ሃሳብ የፀዳ እና የመፍትሄ ሃሳብንም የሚጠቁም ሊሆን ይገባል።

- ለጀማሪ ወጣቶች ላለፉት ዓመታት ክፍት የተደረገው የነፃ ማስታወቂያ ስራም በዚህ ዓመት ይቀጥላል። በግል ሆነ ተደራጅተው እራስን ሆነ ሀገርን ለመቀየር የሚንቀሳቀሱ ወጣት የቤተሰቡ አባላት ስራቸውን ሆነ አገልግሎታቸው በነፃ ያለምንም ክፍያ ለሌሎች የቤተሰቡ አባላት ማስተዋወቅ ይችላሉ መብታቸውም ጭምር ነው። ነገር ግን በሚሰሩት ስራ ፍቃድ ያስፈልጋቸዋል።

- በጋዜጠኝነት ሞያ ውስጥ ያሉ የቤተሰባችን አባላት እንዲሁም ደራስያን መፅሀፍቶቻቸውን በነፃ ለቤተሰባችን እንዲያስተዋውቁ የተጀመረው ስራ በዚህ ዓመት የሚቀጥል ይሆናል።

#ማሳወቂያ፦ የ "ዕርቅ ሀሳብ አለኝ" በሚል በቲክቫህ አስተባባሪነት የተካሄደው ሀገር አቀፍ በሀገር በቀል ባህላዊ የዕርቅ ስነስርዓት ላይ ባተኮረው ውድድር ላይ የቀረቡ ፅሁፎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደቤተሰቡ ይላካል።

#ማሳሰቢያ ፦ ማስታወቂያን በተመለከተ በቀን እጅግ ውስን ማስታወቂያ ለቤተሰቡ ይላካል ፤ የሚላከው ማስታወቂያ ጠቃሚ እና ህጋዊ ሲሆን ብቻ ነው። ማስታወቂያውን የሚያስነግሩትም የቤተሰቡ አባላት በመሆናቸው የእርስ በእርስ ተውውቅን ያጎለብታል። በዚህ መሃል ችግር ቢፈጠር በማስታወቂያ ስም ማጭበርበር ቢሰራ ድርጅቱን ከነስሙ የምናጋልጥ ይሆናል። የቤተሰቡ አባላትን ገንዘባቸው እንዲመለስ ይደረጋል። ድርጅቱም ከቤተሰቡ ይቀነሳል።

#ከአጭበርባሪዎች_ተጠንቀቁ ፦ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት
- " Tikvah Mart "
- " Tikvah Market "
- " Tikvah Business " በሚሉ አድራሻዎች/ቦታዎች አይሰባሰቡም። በእነዚህ ገፆች የሚተላለፉ ሁሉ ሀሰተኛ መልዕክቶች ናቸው። በማስታወቂያ ስም ገንዘብም እንደሚቀበሉ ደርሰንበታል ፤ ከዚህ በፊትም እንዳልነው ተጠንቅቋቸው። ቻናሎቹንና ግሩፖቹን ለቴሌግራም ሪፖርት አድርጉ ፤ ይህን ስራ ለመስራት የሚጠቀሙበትን የስልክ ቁጥር ካላቸውም ላኩልን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ ምንም አይነት የ #Youtube#TikTok#Facebook አካውንት የለም።

መልዕክት ማስቀመጫ ፦ @tikvahethiopiaBOT

@tikvahethiopia