TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የማህበራዊ ሚዲያ ህግ እየተዘጋጀ ነው‼️

በማህበራዊ ድረ ገጾች የሚለጠፉ መረጃዎች #ትክክለኛነታቸውንና በህዝቦች መካከል #ግጭት የማይፈጥሩ መሆናቸውን #ለማረጋገጥ መንግስት ህጋዊ አሰራርን ሊተገብር ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ አክለውም ህጉ ትክክለኛነታቸው ሳይረጋገጥ በማህበራዊ ድረ ገጽ በሚሰራጩ መረጃዎች ምክንያት የሚከሰቱ ግጭቶችና #አለመግባባቶችን ከማስቀረቱም ባሻገር የዜጎችን #ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ እድል ይፈጥራልም ብለዋል።

ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ወይዘሮ ተቋምወርቅ አሰፋ ይህን ብለዋል፦

"ፌስቡክ እውነትም ውሸትም አለው፤ በአሁኑ ሰዓት አልጠቀምም ብትል ከሚዲያ #ትርቃለህ እጠቀማለሁ ስትል ደግሞ #እውነታነቱ የቱ ጋር ነው ፌስቡክ አዘጋጆቹ ራሳቸው እነርሱ ናቸው የሚያውቁት መረጃውን የሚሰጠው አካል እውነታነቱ የቱጋ ነው ብሎ ሲያበቃ ሀሰተኛ መረጃ የሚያስተላልፉትን መንግስት #በህግ ሊከታተላቸው ይገባል˝ ብለዋል።
.
.
በሌላ በኩል...

በኢትዮጵያ ከማህበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ስርዓት ያለው አሰራር ለመፍጠር የሚያስችል ህግ #እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አበይ አህመድ በዚህ ሳምንት በህዝበ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “የሚዲያ ነጻነት ሲባል በውሸት ስም ገፅ በመክፈት፣ ማንነትን በመደበቅ፣ ያልተገቡ ተግባራትን በማከናወን አይደለም” ሳይሆን ለአገርና ለህዝብ ግንባታ የሚውሉ ቁምነገሮችን በማሰራጨት መሆን ይገባልም ብለዋል።

ህጉ “በተደራጀ መልኩ ደመወዝ እየተከፈላቸው፤ አንዴ ኦሮሞ ሌላ ጊዜ ደግሞ አማራ፤ አንዱ ቦታ ሴት ፣ ሌላ ቦታ ደግሞ ወንድ ሌላም ሌላም በመሆን የሚሰሩ ሰዎችንም” #ተጠያቂ ለማድረግ ያለመ እንደሆነም ተናግረዋል።

የዚህ ዓይነቱን የማሕበራዊ ሚዲያ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ለመከላከልም ዋነኛው መፍትሔ ዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን ትክክለኛውን መረጃ ፈጥነው ለህዝብ ማድረስ መቻል መሆኑንም በአጽንኦት ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#YouTube ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዩትዩብ ቻናል የለውም! ከሰሞኑን በTIKVAH-ETH (Tikvah-Ethiopia) ስም ዩትዩብ ላይ እውቅና የሌላቸው፣ ሰዎችን የሚያሸብሩና የሚያስደነግጡ የተለያዩ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆኑ እየተመለከትን ነው። እነዚህ የሚሰራጩት መረጃዎች በቀን ውስጥ ከ50,000 በላይ ሰዎች አንዳንዴም በመቶ ሺ የሚጠጉ ሰዎች ጋር እየደረሱ በርካቶችን እያሳሳቱ ነው። የቲክቫህ ባለቤቶች…
#YouTube

ዩትዩብ ላይ በTIKVAH-ETH ስም ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩ አካላት አጠቃላይ መረጃዎችን ከገፁ ላይ አጥፍተውታል ፤ በተጨማሪ ስሙን ከTIKVAH-ETH ወደ "Hagere Ethiopia ሀገሬ ኢትዮጵያ" ቀይረውታል።

በTIKVAH-ETH የቤተሰብ አባላት ስም የዩትዩብ ገፅ ከፍተው ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩት አካላት ላይ አስፈላጊው የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው።

ምንም እንኳን ከዚህ ቀደም ያሰራጯቸውን ሀሰተስኛና ሰዎችን ሚያሸበሩ መረጃዎች ከገፃቸው ቢያጠፉም በአንድ እና በሁለት ቀን በመቶ ሺ ለሚቆጠር የዩትዩት ተጠቃሚ ደርሰዋል ፤ እኛም እኚህ አካላት ማንነታቸውን እንደደረስንበት #በህግ የምናስጠይቃቸው ይሆናል።

በድጋሚ #ለማስታወስ TIKVAH-ETHIOPIA ዩትዩብ ላይ ምንም አይነት ቻናል #የለውም። አሁንም በቲክቫህ ስም ዩትዩብ ቻናል ከፍተው #ገንዘብ ለመሰብሰብ ሲሉ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትምህርት_ሚኒስቴር የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል። ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ…
#NationalExam

የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ ይሰጣል።

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ፈተናው ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የፈተና ደንብ ጥሰቶች #በህግ ያስጠይቃሉም ተብሏል።

የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠት ባለፈ የፈተና ኩረጀ እና ስርቆትን ለመከላከል በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ከቀናት በፊት መገለፁ ይታወሳል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን ለማድረግ የታሰበ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የተሳሳቱ መረጃዎችን በመልቀቅ ተማሪዎች የስነ ልቦና ጫና እንዲደርስባቸው የሚያደርጉ አካላትን #በህግ_ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ ነው " - ዶ/ር እሸቱ ከበደ

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ስራ ሙሉ በሙሉ በመጠናቅ ላይ መሆኑን የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የፈተና ዝግጅቱም የተማሪዎችን ልፋት ሊለካ በሚችል ከደህንነት ስጋት ነፃ እንዲሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ለፈተና አሰጣጡ ውጤታማነት ከመፈተኛ ቦታ መረጣ ጀምሮ የፈተና ኮዶችን ብዛት ከፍ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

ይህንን ተከትሎ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ የራሳቸው ጥረት ውጤት ለማግኘት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የተሳሳቱ መረጃዎችን በመልቀቅ ተማሪዎች የስነ ልቦና ጫና እንዲደርስባቸው የሚያደርጉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ዋና ዳይሬክተሩ ያሳሰቡ ሲሆን ለዚህም የህግ ተጠያቂነት እንዲኖር እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ተማሪዎችና ወላጆችም መረጃዎችን ከተቋሙ እና ከታማኝ የመረጃ ምንጮች ብቻ እንዲከታተሉም ጠይቀዋል።

የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል " - ብልፅግና ፓርቲ

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ኢብራሂም በ" ጅግጅጋ ኤርፖርት " ውስጥ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ብልፅግና ፓርቲ አሳውቋል።

" ጉዳዩ #በህግ_አግባብ ተይዞ እየተጣራ ነው " ያለው ፓርቲው " በቀጣይ ሁኔታው የደረሰበት ደረጃ በሚመለከተው አካል ይገለፃል " ብሏል።

ፓርቲው በማእከላዊ ኮሚቴ አባሉ ላይ በደረሰው ህልፈት ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ተጨማሪ መረጃዎች ፦ (ኢትዮ ቴሌኮም) #DevicePenetration 📱 በኢትዮጵያ 31 ሚሊየን (46%) ዜጎች የዘመናዊ ስልክ ( SmartPhone) ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል። ከዚህ ውጭ ያሉ (Basic Feature Phone) ተጠቃሚዎች ደግሞ 47.5 ሚሊዮን መድረሳቸውን ነው የተገለጸው። ዳታ የሚጠቀሙ መሳሪያዎች (Data Devices) ደግሞ 1.2 ሚሊዮን መድረሱን ገልጿል።…
" ከቀናት በፊት ኔትዎርክ ተቋርጦ የነበረው #በፋይበር ላይ በደረሰ ጉዳት ነው " - ኢትዮ ቴሌኮም

በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ጉዳት የደረሰባቸው እንዲሁም የተጠገኑ የኔትወርክ ሳይቶች ስንት ናቸው ?

በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት ኢትዮ ቴሌኮም በግጭት በግንባታ ሥራ፤ የዓለም አቀፍ መስመሮች መቋረጥና ብልሽት፤ በተፈጥሮ አደጋ እንዲሁም በኃይል መቆራረጥ ምክንያት ወደ 2,716 የሞባይል ኔትዎርክ ሳይቶቹ እንዲሁም 145 የመደበኛ ሳይቶቹ ሥራ ያቋረጡ መሆኑን ገልጿል።

እነዚህም በአብዛኛው በሰሜን እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ናቸው። (🔴ከላይ በካርታው ተያይዟል)

በአንጻሩ በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት 413 የሞባይል ኔትወርክ ሳይቶች ጥገና ተደርጎላቸው ወደ አገልግሎት የገቡ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር የሚይዘው ጥገና በትግራይ ክልል በ174 ሳይቶች (28 ወረዳዎች/ከተማዎች) ወደ ላይ ተደርጎ ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል።

በአጠቃላይ አገልግሎት በተቋረጠባቸው በ80 ወረዳዎችና ዋና ከተሞች የአገልግሎት ጥገና ተደርጎባቸዋል ተብሏል። [መሰረተ ልማቱን ለመጠገን የወጣው ወጪ እንዲሁም የደረሰው የጉዳት መጠን ከመግለጽ ተቆጥበዋል]

#FYI

- ኢትዮ ቴሌኮም፤ከሰሞኑ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ዳግም የኔትወርክ አገልግሎት ከጀመረ በኋላ ከቀናት በፊት የተቋረጠው #በፋይበር ላይ በደረሰ ጉዳት መሆኑን ገልጿል።

- በሰሜን ሪጅን (በአብዛኛው በትግራይ ክልል) ካሉ ከ700 በላይ ሰራተኞቹ ወደ 500 የሚጠጉት ዳግም ሥራ ለመጀመር አመልክተዋል ተብሏል።

- ከሰሞኑ በሰመራ የደረሰው የኔትወርክ መቆራረጥ በተወዳዳሪው [ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ] የመሰረተ ልማት ግንባታ መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ የገለፁ ሲሆን በኩባንያው ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠየቅ ጉዳዩ #በህግ_ተይዟል ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ... የቤተሰብ ዋነኛ ፍላጎት ፍትህን ማግኘትና እውነቱን ማወቅ ነው " - የአቶ በቴ ኡርጌሳ ቤተሰብ

የአቶ በቴ ኡርጌሳ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈፅሟል።

ስርዓተ ቀብራቸው ቤተሰቦቻቸው ፣ ዘመዶቻቸው በርካታ ሰዎች ፣ ወዳጆቻቸው በተገኙበት ዛሬ በመቂ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ነው የተፈፀመው።

አንድ ቀላቸውን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ የሰጡ የቤተሰብ አባል ፤ " ያው እንደ በቴ ከዚህ በላይ ብጠበቅም ብዙ ሰው ከሩቅም ከቅርብም መጥተው ስርዓተ ቀብራቸው ላይ ተገኝተው ቤተሰብም ቀብሩን ፈጽመው በሰላም ወደ ቤት ተመልሰዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

በትውልድ ከተማቸው መቂ ስርዓተ ቀብራቸው የተፈጸመው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ማክሰኞ ሌሊት ተገድለው ትናንት ማለዳውን አስከሬናቸው ከመቂ ወደ ባቱ መውጫ መንገድ ላይ ተጥሎ መገኘቱ ይታወቃል።

የቤተሰቡ አባል ፤ " የበቴ አስክሬን ትናንት ጠዋት በአከባቢው ማህበረሰብ እና ቤተሰቦቻቸው ከመንገድ ተነስቶ ወደ ቤት ከተወሰደ በኋላ፤ ዛሬ ጠዋት ወደ አከባቢው ሆስፒታል በመውሰድ የአስከሬን ምርመራ ተደርጎለት ነበር፡፡ " ብለዋል።

" ቤተሰብ እንደ ትልቅ ነገር ያየው አንዴ የሞተውን ልጃቸውን ወስደው በስርዓቱ ቀብሩን መፈጸም ነው፡፡ ዛሬ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ አስከሬኑ እንዲመረመር የሆነው #በህግ_አዋቂዎች ምክር ነበር፡፡ ፖሊስ አስከሬኑን ወደ ምርመራ ባይወስድም ትናንት ጠዋት መረጃዎችን አሰባስቦ ሄዷል " ሲሉ ገልጸዋል።

እኚህ የቤተሰብ አባል በአቶ ቤተ አስከሬን የተለያዩ የሰውነት አካል ላይ በርካታ ያሉት ቦታ ላይ በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የሚያመላክት ብዙ ቁስሎች በአይናቸው መመልከታቸውን አስረድተዋል፡፡

" የቤተሰብ ዋነኛ ፍላጎት ፍትህን ማግኘት እና እውነቱን ማወቅ ነው " ብለዋል።

" ቤተሰብ የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ማወቅ ይፈልጋል፡፡ በፍርድ ሂደት ፍትህ ቢገኝ ቤተሰቡንም የአከባቢውንም ማህበረሰብ የሚያረካ ጉዳይ ነው " ሲሉ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

በግፍ ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ተጥሎ የተገኘው የኦነግ ከፍተኛ አመራር አቶ በቴ ኡርጌሳ ባለትዳርና የ4 ልጆች አባት ነበሩ።

@tikvahethiopia