TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.44K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሟቾች ቁጥር 19 ደርሷል‼️

በሱዳን የነዳጅና የዳቦ ዋጋ #መጨመርን ተከትሎ በተከሰተው የኑሮ ውድነት ምክንያት በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ #የሞቱት ሰዎች ቁጥር 19 መድረሱ ተገለፀ።ለተቃውሞ በወጡ ሰልፈኞችና በፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭትም እስካሁን ሁለት የፖሊስ አባላትን ጨምሮ የ19 ሰዎች ህይዎት ማለፉን የሱዳን መንግስት ቃል አቀባይ ቦሻራ ጁማ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ አፍሪካ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከጅቢቲ ወደ የመን በማምራት ላይ ሳሉ በሰጠሙት ሁለት ጀልባዎች ውስጥ ከተጫኑት #ኢትዮጵያውያን ናቸው ከተባሉ ስደተኞች መካከል #የሞቱት ቁጥር ወደ 52 ከፍ ማለቱ ተነገረ። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት በምህጻሩ IOM እንዳስታወቀው የህይወት አድን ሠራተኞች ከሁለቱ ጀልባዎች ተጨማሪ አስከሬኖችን በማግኘታቸው ትናንት 43 የነበረው የሟቾቹ ቁጥር ዛሬ ወደ 52 ከፍ ብሏል። 16 ሰዎች ከአደጋው መትረፋቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። በአደጋው የሞቱት ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር እስካሁን በግልጽ አልታወቀም። ድርጅቱ አንደኛዋ ጀልባ 130 ሰዎችን አሳፍራ ነበር የሚል እምነት አለው። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ያነጋገረው አንድ ከአደጋው የተረፈ የ15 ዓመት ወጣት ቁጥራቸው 80 ከሚሆን ኢትዮጵያውያን ጋር በአንደኛው #ጀልባ ተጭኖ እንደነበር ገልጿል። የጀልባዋ ነጂ ሞተሩ ከባድ #ችግር እንዳጋጠመው ከተናገረ በኋላ ጀልባዋ መስመጠም መጀመሯን እርሱ ግን ከባህር ውስጥ በጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጠባቂ #ተጎትቶ መውጣቱን ወጣቱ ተናግሯል። ጦርነት እየተካሄደባት ቢሆንም ወደ #የመን የሚደረገው ስደት እንደቀጠለ ነው።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 24/2011 ዓ.ም.

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከጅቢቲ ወደ የመን በማምራት ላይ ሳሉ በሰጠሙት ሁለት ጀልባዎች ውስጥ ከተጫኑት #ኢትዮጵያውያን ናቸው ከተባሉ ስደተኞች መካከል #የሞቱት ቁጥር ወደ 52 ከፍ ማለቱ ተነገረ።
.
.
የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሰድስት ወራት ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ መያዙን ገልጿል።
.
.
ኢትዮጵያዊው ሌተናል ጀነራል #ጥጋቡ_ይልማ_ወንድማገኝ በሶማልያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ አዛዥ በመሆን ተሹመዋል።
.
.
32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ከጥር 30 2011 ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል #ግብር አሰባሰብ ችግር በፈጠሩ 75 ባለሙያዎች ላይ ሕጋዊ #እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን አስታውቋል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በተለያየ ጊዜ ለልማት መሬት ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ122 ኢንተርፕራይዞች ላይ #እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
.
.
በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ የዞንና የክልል ጥያቄዎችን በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ #ለመመለስ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ተናግረዋል።
.
.
ባለፉት 6 ወራት 7ሺህ 8 መቶ ባለቤት አልባ ውሾችን ማስወገዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
.
.
የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታን #ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ #በተጠናከረ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
.
.
24 የአልሸባብ ቡድን አባላት በአየር ድብደባ #መሞታቸውን የአሜሪካ ጦር ኃይል አስታውቋል።
.
.
በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ የተገነባው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መታሰቢያ ኀውልት የካቲት 3 ቀን 2011 የሚመረቅ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
.
.
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ነጋዴዎች #መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።
.
.
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ #ሊከለስ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው እንደገለጹት አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ፖሊሲ በማስፈለጉ ነው ክለሳ የሚደረግበት፡፡
.
.
16ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ "ቅድሚያ ለሴቶች" ከመጋቢት 1 ጀምሮ ይካሄዳል።
.
.

ጉዞ ሉሲ የአንድነት እና የፍቅር ፕሮጀክት የካቲት 14 ይጀምራል፡፡ ጉዞ ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ ነው፡፡
.
.
የሀገሪቱ መደበኛ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናግረዋል።
.
.
ከጥረት ኮርፖሬት፣ ላፓልማ እና ባህርዳር ሞተርስ አክሲዮን ማህበር #የሙስና_ወንጀል ጋር በተያያዘ ከጠረጠሩት አምስት ግለሰቦች መካከል አራቱ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
.
.
በቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ #ግጭት ሰባት ሰዎች #መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #የሽዋስ_አለሙ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
.
.
የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ከተመረቀ #የመጀመሪያውን አመታዊ የኮካኮላ የሽያጭና ግብይት ስብሰባ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በ450 ተሳታፊዎች በሚያምረው ግዙፍ አዳራሽ ያስተናግዳል።
.
.
የቀድሞው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አምባሳደር #ዳዊት_ዮሐንስ የቀብር ስነ ስርዓት የፊታችን እሁድ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክረስቲያን ይፈፀማል፡፡
.
.
የጎፋ ዞን ዛሬ #በይፋ ተመስርቷል። የዞኑ ይፋዊ የምስረታ በዓል በሳውላ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የዞኑ ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ተከብሯል፡፡
.
.
ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው የመኪና መንገድ #ባቢሌ ከተማ ላይ #በመዘጋቱ መቸገራቸውን አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ አሽከርካሪዎች ተናግረዋል።
.
.
ምንጭ፦ ኢዜአ፣etv፣fbc፣ ዋዜማ ራድዮ፣ BBC አማርኛ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የጀርመን ድምፅ ራድዮ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia