TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58K photos
1.44K videos
208 files
4.01K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው #ለመመለስ ከአካባቢው ነዋሪዎችና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ለመስራት በዝግጅት ላይ መሆኑን የብሔራዊ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የአካባቢው ነዋሪዎችና ለጋሽ ድርጅቶች የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት ያሳዩት ተነሳሽነት ከፍተኛ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አንጻር #ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢዜአ እንደተናገሩት የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ #በባህላዊና #ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓት ዕርቅ ለማውረድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ነው።

በተለይ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ የየአካባቢው ነዋሪዎችና የመንግስት አካላት በተገኙበት እርቅና ሰላም የማውረድ ስራ ይሰራል ብለዋል።

ኮሚሽኑ ተፈናቃዮቹ ከሚገኙበት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ ሲሆን ድጋፉን ለማጠናከር ተጨማሪ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መላኩንም ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ እስካሁን ከአካባቢው ለተፈናቀሉ ዜጎች 17 ሺህ 468 ኩንታል ስንዴ ሩዝና አልሚ ምግብ፣ 146 ሺህ 194 የመመገቢያ ቁሳቁስ መጠለያና አልባሳትና 1 ሺህ 101 ካርቶን የዱቄት ወተት ወደ ስፍራው መላኩን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከዳሸን ባንክ አምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሲደረግ ከቡራዩና አካባቢዋ ለተፈናቀሉም እንዲሁ በሲውዘርላንድ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን 600 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው ሰሞኑን ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈናቅለው በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ 10 ወረዳዎች የሚገኙ ሰዎች ቁጥር 91 ሺህ 348 ደርሷል።

▪️በተጨማሪ በመላው አገሪቱ በመደበኛነት #በድርቅ አደጋ የሚረዱ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ያሉ ሲሆን ለጋሽ አካላት የተለመደ ትብብራቸው እንዲያደርጉ ጠይቋል።

በተለይ ዲያስፖራው፣ ባለሃብቶችና ሌሎችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን ይህንን ለመምራት የሚያስችል ኮሚቴ መዋቀሩንም ገልጸዋል።

በቅርቡ በምዕራብ ጉጂ፣ በጌዲኦ፣ በሶማሌና በቡራዩ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በባህላዊ ስነ-ስርዓት የሕዝብ ለሕዝብ ስራ መሰራቱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከፋ ዞን‼️

በካፋ ዞን ስለ ቡና መገኛነት በድረ-ገጽ በተላለፈ መረጃ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ወደ ነበረበት #ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት በካፋ ዞን የተፈጠረው አለመረጋጋት ከቡና መገኛነት ጋር በተያያዘ በድረ-ገጾች በተላለፈ መረጃ አማካኝነት ነው።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዓለም አቀፍ የቡና ኮንፍረንስ በቅርቡ ለማዘጋጀት በሚያደርገው ሂደት በድረ-ገጹ የተላለፈው መረጃ የካፋን ወጣቶችና ህዝቡን አስቆጥቶ በአካባቢው አለመረጋጋት ተፈጥሯል።

“የቡና ባለቤትነት ጥያቄን በሚመለከትም የባለቤትን ጉዳይን የሚመራና እውቅና የሚሰጥ ራሱን የቻለ ተቋም በሃገር ደረጃ ያለ በመሆኑ ጥያቄው አሰራሩን ተከትሎ ምላሽ ያገኛል”ብለዋል፡፡

ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ያቀረበው የካፋ ህዝብና ወጣት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሲገታ የሚያሳድረውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና በመረዳት የተዘጉ መንገዶችን እንዲከፍት ጠይቀዋል፡፡

በአካባቢው ያሉ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ይህንን በማስተባበርና ወጣቱም ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በመተባበር የአካባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት እንዲመልስ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችም አሁን ላይ ወደ ሰላም እየተመለሱ መሆናቸውን ገልጸው የአብዛኛዎቹ መንስኤም ከመዋቅር ጋር የተያያዙ እንደነበሩ ጠቁመዋል።

በቅርቡ የክልሉ ምክር ቤት 44 ወረዳዎችንና 3 ዞኖችን በአዲስ መልክ ማዋቀሩን ተከትሎ አዳዲስ ፍላጎቶች የፈጠሩት ስሜትና የሚጠበቅ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

“ችግሮቹን በቀጣይ ከህዝቡ ጋር በሚደረግ ጥልቅ ውይይት መስመር የሚይዙ ናቸው” በማለት  በየደረጃው ያለ አመራር ከህዝቡ ጋር በሚያደርጋቸው ሰፊ የውይይት መድረኮች እንደሚኖሩ ገልጸው በዚህም የሰላም ግንባታ ስራው እንደሚጠናከር ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ‼️

አሶሳ ዩኒቨርሲቲን ወደ ቀድሞ ሰላሙ #ለመመለስ እየተሠራ መሆኑን ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ካለፈው እሑድ ጀምሮ ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሰላማዊ መማር ማስተማሩ ተስተጓጉሏል፡፡ ተማሪዎች እና ተወካይ ፕሬዝዳንቱ እንደነገሩን የግጭቱ መነሻ የሁለት ተማሪዎች አለመግባባት ነው፡፡ ይህም እየተስፋፋ ሄዶ ወደ ቡድን ፀብ ተቀይሮ ነበር፡፡

ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ዶክተር #ሃይማኖት_ዲሳሳ ችግሩን ለመፍታት ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ከተማሪዎች ጋር ምክክር ተደርጎ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በውይይቱም መግባባት ላይ መደረሱ ተማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡

ይሁን እንጂ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት ትናንት ጠዋት ላይ ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሽ ሲገቡ እንደገና #ረብሻ ተጀምሮ ነበር፡፡

እንደ ተማሪዎቹ መረጃ የግጭቱ ዋነኛ ምክንያት የተማሪዎች መማክርት በወቅቱ አለመመረጥ ኢ-ፍትሐዊ አሠራር ፈጥሯል የሚል ነው፡፡

ተማሪዎቹ ምርጫው ‹‹ባለፈው ዓመት ሰኔ ላይ መካሄድ ነበረበት፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት አልተካሄደም፤ እስካሁን ግን መቆየት አልነበረበትም›› የሚል አቋም አላቸው፡፡

አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ችግሮችን ተወካዮቻቸው በወቅቱ አለመፍታታቸውም ለችግሩ መከሰት ምክንያት መሆኑን ነው ተማሪዎቹ የተናገሩት፡፡

ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ግን ‹‹በውይይቱ ለከፋ ግጭት የሚዳርግ ችግር አላገኘንም›› ነው ያሉት፡፡

በረብሻው ምክንያት ‹‹34 ተማሪዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸውም ይገኛል ብለዋል
ዶክተር ሃይማኖት፡፡

በተከሰተው ግጭት የሶስት ተማሪዎች ህይወት አልፏል፡፡ የጸጥታ ኃይሎች ግቢውን ወደ ቀድሞ ሰላሙ ለመመለስ እየሠሩ መሆናቸውን ተወካይ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎችም ይህን መመልከታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ ተረጋግተው ለመኖር እና ለመንቀሳቀስም ስጋት ውስጥ መሆናቸውንና ለሰላማቸው #ዋስትና እንደሚፈልጉ ነው የተናገሩት፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደቡብ ክልል‼️

በኢትዮጵያ ደቡብ ክልል የሚነሱ የክልል፣ የዞን እና የልዩ ወረዳ ጥያቄዎችን #ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ #ለመመለስ የሚያስችል ጥናት ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ።

ጥናቱ የሚጀመረውም የደቡብ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ባለፈው መስከረም ወር ባካሄደው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ እየተነሱ ያሉት ጥያቄዎች ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እንዲፈቱ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት መሆኑ ነው የተገለፀው።

በዚህ መሰረትም ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችለውን ጥናት ለማካሄድ ከምሁራን፣ከወጣቶች እና ከመንግስት ሰራተኞች የተውጣጡ 20 አባላትን የያዘ ኮሚቴ መቋቋሙን የጥናት ቡድኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶክተር ያኒአ ሰይድ መክይ ተናግረዋል።

የጥናት ቡድኑ በዋናነትም እየተነሱ ያሉትን ጥያቄዎች ከክልሉ ህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና ዘላቂ ልማት አንፃር በመመርመር፥ ህዝቦቹ በጋራ በኖሩባቸው ጊዜያት ያተረፉትንና ያጡትን አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ የሚያጠና መሆኑ ተነግሯል።

በሚቀጥለው ሳምንት የሚጀምረው የጥናት ሂደት ከአምስት እስከ ስድስት  ወራት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ተጠናቆ የክልሉ መንግስት ውሳኔ እንዲሰጥበት ይደረጋል ነው የተባለው ።

ጥናቱ እስኪጠናቀቅ እና ጥያቄዎች በሰለጠነ እና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ምላሽ እስኪያገኙ ድረስም፥የክልሉ ህዝብ ሰላም እና አንድነቱን ጠብቆ እንዲቀጥል የጥናት ቡድኑ  የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የክልል እና የዞን ጥያቄዎችን በተመለከተ‼️

በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ የዞንና የክልል ጥያቄዎችን በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ #ለመመለስ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ተናገሩ።

በአሁኑ ወቅት በርካታ የማንነት ጥያቄዎች እየቀረቡ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን በህጋዊ መንገድ ማቅረብና መደመጥ መቻል በራሱ የዴሞክራሲ መብት አካል መሆኑን አስገንዝበዋል።

ይሁን እንጂ ዞን ወይም ክልል የሚለው ጥያቄ ከመመለሱ በፊት የጥያቄዎቹ ዋና ዓላማ፤ እንዲሁም ጥቅምና ጉዳቱን መታየት አለበት ብለዋል።

የአንድ አካባቢ የዞን ወይም የክልል ጥያቄ ሲመለስ በአካባቢው ካሉ ጎረቤት ክልሎች ጋር በሰላም፣ በኢኮኖሚና በሌሎች ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደማይኖረው መረጋገጥም ይኖርበታል ብለዋል።

ይሁን እንጂ የክልልና የዞን ጥያቄዎች በህጋዊ መንገድ መቅረብ እንዳለባቸው፤ የጥያቄው አግባብነት እስከሚታይ #መታገስ እንጂ በህገ-ወጥ መንገድ ይመለሳል ብሎ መንቀሳቀስ #አዋጭነት_የለውም ብለዋል።

መንግስት ይህንኑ ጉዳይ የሚከታተል ኮሚሽን አዋቅሮ እየሰራ መሆኑንና በቀጣይ ጥናት ላይ ተመስርቶ በህጋዊ መንገድ ለመፍታት የምናየው ይሆናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ።

“የሚወሰነው ውሳኔም የሚያዋድደን፣ አንድ የሚያደርገን እንጂ የሚያጣላን መሆን የለበትም” ሲሉም ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውም ጫፍ ከሌላው ጋር ተሳስሮና ተደጋግፎ መሄድ ካልቻለ #መቀጠል አይችልም፣ ህይወታችን በራሱ #ተደጋግፈን እንድንቀጥል ያደርገናል” ሲሉም ነው መልዕክት ያስተላለፉት።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 24/2011 ዓ.ም.

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከጅቢቲ ወደ የመን በማምራት ላይ ሳሉ በሰጠሙት ሁለት ጀልባዎች ውስጥ ከተጫኑት #ኢትዮጵያውያን ናቸው ከተባሉ ስደተኞች መካከል #የሞቱት ቁጥር ወደ 52 ከፍ ማለቱ ተነገረ።
.
.
የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሰድስት ወራት ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ መያዙን ገልጿል።
.
.
ኢትዮጵያዊው ሌተናል ጀነራል #ጥጋቡ_ይልማ_ወንድማገኝ በሶማልያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ አዛዥ በመሆን ተሹመዋል።
.
.
32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ከጥር 30 2011 ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል #ግብር አሰባሰብ ችግር በፈጠሩ 75 ባለሙያዎች ላይ ሕጋዊ #እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን አስታውቋል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በተለያየ ጊዜ ለልማት መሬት ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ122 ኢንተርፕራይዞች ላይ #እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።
.
.
በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚነሱ የዞንና የክልል ጥያቄዎችን በጥናትና ህግ በሚፈቅደው መንገድ #ለመመለስ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር #አብይ_አህመድ ተናግረዋል።
.
.
ባለፉት 6 ወራት 7ሺህ 8 መቶ ባለቤት አልባ ውሾችን ማስወገዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
.
.
የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታን #ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ #በተጠናከረ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
.
.
24 የአልሸባብ ቡድን አባላት በአየር ድብደባ #መሞታቸውን የአሜሪካ ጦር ኃይል አስታውቋል።
.
.
በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ የተገነባው የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መታሰቢያ ኀውልት የካቲት 3 ቀን 2011 የሚመረቅ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
.
.
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ነጋዴዎች #መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።
.
.
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ #ሊከለስ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው እንደገለጹት አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ፖሊሲ በማስፈለጉ ነው ክለሳ የሚደረግበት፡፡
.
.
16ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ "ቅድሚያ ለሴቶች" ከመጋቢት 1 ጀምሮ ይካሄዳል።
.
.

ጉዞ ሉሲ የአንድነት እና የፍቅር ፕሮጀክት የካቲት 14 ይጀምራል፡፡ ጉዞ ሉሲ የሰላምና የፍቅር ጉዞ ነው፡፡
.
.
የሀገሪቱ መደበኛ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናግረዋል።
.
.
ከጥረት ኮርፖሬት፣ ላፓልማ እና ባህርዳር ሞተርስ አክሲዮን ማህበር #የሙስና_ወንጀል ጋር በተያያዘ ከጠረጠሩት አምስት ግለሰቦች መካከል አራቱ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
.
.
በቴፒ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ #ግጭት ሰባት ሰዎች #መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ #የሽዋስ_አለሙ ለቢቢሲ ገልፀዋል።
.
.
የኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል ከተመረቀ #የመጀመሪያውን አመታዊ የኮካኮላ የሽያጭና ግብይት ስብሰባ ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በ450 ተሳታፊዎች በሚያምረው ግዙፍ አዳራሽ ያስተናግዳል።
.
.
የቀድሞው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አምባሳደር #ዳዊት_ዮሐንስ የቀብር ስነ ስርዓት የፊታችን እሁድ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክረስቲያን ይፈፀማል፡፡
.
.
የጎፋ ዞን ዛሬ #በይፋ ተመስርቷል። የዞኑ ይፋዊ የምስረታ በዓል በሳውላ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና የዞኑ ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ተከብሯል፡፡
.
.
ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው የመኪና መንገድ #ባቢሌ ከተማ ላይ #በመዘጋቱ መቸገራቸውን አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ አሽከርካሪዎች ተናግረዋል።
.
.
ምንጭ፦ ኢዜአ፣etv፣fbc፣ ዋዜማ ራድዮ፣ BBC አማርኛ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የጀርመን ድምፅ ራድዮ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፓይለቱ ችግር ገጥሞት ነበር‼️

የአውሮፕላኑ አብራሪ #ችግር ስላጋጠመው ወደ አዲስ አበባ #ለመመለስ ጠይቆ እንዲመለስ ተነግሮት እንደነበር የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም ተናግረዋል። አውሮፕላኑ ከጆሃንስበርግ በረራው ሲመለስ ምንም አይነት የበረራ ችግርን የሚመለከት መረጃ እንዳልነበርና ከሶስት ሰዓት በላይም መሬት ላይ ቆይቶ እንደነበር አቶ #ተወልደ ገልፀዋል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የ4 አብያተ ክርስቲያናትና ሚኒስትሪዎች ሠርተፍኬት #እንዲሰረዝ መወሰኑን አሳውቋል።

ሠርተፍኬታቸው የተሰረዘው ፦

1ኛ. ጋድስ ላይት ግሎሪ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ ነብይ ኢዮብ ጭሮ

2ኛ. ገዥዋ ዓለም አቀፍ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መጋቢ ካሳ ኪራጋ

3ኛ. የሰማይቱ ጽዮን ማኅበርተኞች የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መጋቢ ሚስጥሩ መዝገቡ

4ኛ. የእግዚአብሔር መንግስት እውነት ዓለም አቀፍ ሚኒስትሪ መጋቢ  ቢንያም ሽታዬ ... ናቸው።

ውሳኔው የተለለፈባቸው በስህተት ትምህርትና ልምምዶች ምክንያት ነው።

ካውንስሉ እነዚህ አካላት የተሰጣቸውን የሕግ ከለላ በመጠቀም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሮና ጤናማ ሥነ ምግባር ውጭ የሆነ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበሩ ገልጿል።

ከዚህ ተግባራቸው ይመለሱ ዘንድም አስፈላጊውን ትምህርትና ምክር ሲሰጥ ቆይቷል።

ይሁን እንጂ ምክሩ ተቀበለው ሕዝብን ከሚያሳስት ተግባራቸው #ለመመለስ ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው ሠርተፍኬታቸው እንዲሰረዝ ወስኗል።

(ካንውስሉ ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia