TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
A_HRC_54_55_AdvanceUneditedVersion.docx
79.2 KB
#ETHIOPIA #UN

ኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት እንዲቆም ስምምነት ከተፈረመ አንድ አመት ሊሞላው ቢቃረብም አሁንም ግፍ፣ የጦር ወንጀሎች እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እየተፈፀሙ ነው ሲል በተመድ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አሳወቀ።

ኮሚሽኑ የሰላሙ ሁኔታ አሁንም ያልተረጋገጠ መሆኑን ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ ባወጣው ባለ 21 ገጽ ሪፖርቱ ከህዳር 3 ቀን 2020 ጀምሮ በግጭቱ ውስጥ በተሳተፉ #ሁሉም_አካላት የተፈፀሙ መጠነ ሰፊ አሰቃቂ ድርጊቶችን አስፍሯል።

ከእነዚህም ውስጥ ፦
- የጅምላ ግድያ፣
- አስገድዶ መድፈር፣
- ረሃብ፣
- የትምህርት ቤቶች እና የህክምና ተቋማት ውድመት፣
- የግዳጅ / በኃይል ማፈናቀል እና የዘፈቀደ እስራት ይገኙበታል።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር መሀመድ ቻንዴ ኦትማን ፤ " የሰላም ስምምነቱ መፈረሙ በአብዛኛው የመሳሪያ ድምፅ ጸጥ ያሰኘው ቢሆንም ፤ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተለይም በትግራይ ያለውን ግጭት አልፈታም ወይም ምንም አይነት አጠቃላይ የተሟላ ሰላም አላመጣም " ብለዋል።

" በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በአማራ ክልል በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርስ የመብት ጥሰት እና በትግራይ እየተፈጸመ ያለ ግፍን የሚገልጹ ሪፖርቶች እንዳሉት ኮሚሽኑ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ያፋ ባደረገው ሪፖርት፤ የኤርትራ ወታደሮች እና የአማራ ሚሊሻ አባላት ትግራይ ውስጥ ከፍተኛ ጥሰቶችን መፈፀም መቀጠላቸውን አመልክቷል። ይህም ስልታዊ የሆኑ አስገድዶ መድፈር፣ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃቶችን እንደሚያካትት አመልክቷል።

ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በመንግስት ሃይሎች ይፈፀማል ስላለው የሰላማዊ ዜጎች እስራት እና የማሰቃየት ድርጊትን በተመለከተ በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል።

በተጨማሪም ፤ በቅርቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ በአማራ ተወላጅ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን የሚያሳዩ በርካታ ሪፖርቶችን እንዳገኘ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ፤ የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መምጣቱ እና ለጭካኔ ወንጀሎች የሚያጋልጡ ሁኔታዎች መኖራቸው በእጅጉ እንደሚያሳስበው አመልክቷል።

ይህ ሁኔት በኢትዮጵያ እንዲሁም በሰፊው ቀጣና መረጋጋት ላይ እንዲሁም በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሴቶች፣ ወንዶች፣ ህፃናት ላይ እንድምታ እንዳለው ገልጿል።

https://www.ohchr.org/en/press-releases/2023/09/ethiopia-nearly-one-year-after-ceasefire-un-experts-warn-ongoing-atrocities

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

➡️ " በሃገራዊ ምክክሩ #ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

➡️ " ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ #ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ ሀገራት #ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው " - ኮሚሽኑ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት እየተደረጉ ያሉ ግጭቶች ቆመው ሁሉም አካላት ወደ ንግግር አንዲመጡ ጠይቋል

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጫካ የሚገኙት ታጠቂዎች በምክክሩ ላይ እንዲሳተፉ ከለላ እንዲደረግላቸው መንግስትን የመጠየቅ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ " በሃገራዊ ምክክሩ ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ብለዋል፡፡

በጫካ ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ አንዲሳተፉ ለዚህ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ  ምክር ቤቱ የጠየቀ ሲሆን ፥ " ይህ ካልሆነ ግን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ሲል የጋራ ም/ቤቱ ስጋቱን ተናግሯል።

#ሌላው_ስጋት ብሎ ያነሳው ደግሞ የምክክር ኮሚሽኑ የተቋቋመበት አዋጅ  ግጭቶችን የማስቆም ሃላፊነት አልተሰጠውም ግጭት ሳይቆም በግጭት ውስጥ የሚደረግ ምክክር ደግሞ ውጤት ላያመጣ ይችላል ብሏል፡፡

የጋራ ም/ቤቱ ከጅምሩ ጀምሮ " በምክክሩ አንሳተፍም " ያሉ ፓርቲዎችን፣ በተለያየ ክልሎች ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ እንዲሳተፉ እንዲደርግ ኮሚሽኑን ጠይቋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዶክተር ዮናስ አዳዬ ምክክሩ አሳታፊ እንዲሆን፣ ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ አለም ሀገራት ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

" ጫካ የገቡ አካላት በምክክሩ እንዲሳተፉ በመገናኛ ብዙሃን ተደጋጋሚ ጥሪዎችን እያደረግን ነው " ያሉት ዶ/ር ዮናስ " ሕጋዊ የሆነ መስሪያ ቤት ስለሌላቸው ጥሪ ለማድረግ ተቸግረናል፣ እዚህ ነን  አለን የሚሉ ከሆነ የተመካከሩ ጥሪ ወረቀት ይዘን ለመሄድ ዝግጁ ነን " ብለዋል፡፡

Credit - Sheger FM 102.1

@tikvahethiopia