TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፉን ይጀምራል።

ለ7 ቀናት ያህል በሚቆየው የአዲስ አበባው ምክክር ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉ ኮሚሽኑ ገልጿል።

በምክክሩ የውይይት የአጀንዳ ሀሳቦችን የሚያመጡ ለምክክሩ የሚቀርቡ ተሳታፊዎች ሲሆኑ ፤ እነዚሁ ተሳታፊዎች በተስማሙባቸው የጋራ አጀንዳዎች ላይ የመፍትሔ ሀሳቦችን እንደሚያቀርቡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመልክቷል። #DW

@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

የመጅሊሱ ቅሬታ ምንድነው ?

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህዝበ ሙስሊሙ ሀገራዊ ምክክሩን እጅግ እንደሚደግፈው ነገር ግን ከምክክሩ ተሳታፊዎች ጋር በተያያዘ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንዳልተሰጠው በዚህም ምክንያት ቅሬታ እንዳደረበት ገልጿል።

ም/ቤቱ ያደረበት ቅሬታ " በምክክሩ ላይ የሙስሊሞች ውክልና አነስተኛ ነው ፤ ይህ ደግሞ በምክክር ውጤቱ ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር ስጋት አለኝ " የሚል ነው።

" #ከወረዳ እስከ #ክልል ድረስ የሚሳተፉት ተወካይ ሙስሊሞች ቁጥር እጅግ አነስተኛ ነው " የሚለው ም/ቤቱ ፥ " እንደ ሙስሊም በጋራ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ መግባባት ላይ ለመድረስ በቂ ተወካዮች አልተወከሉም " ብሏል።

የምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ከማል ሀሩን ምን አሉ ? (ለሃሩን ሚዲያ)

- ሙስሊሙ ከምንም በላይ ምክክሩን ይፈልገዋል።

- ሙስሊሙ የቆዩ ችግሮች ስላሉበት ይሄን ምክክር እንዲሳካ በጣም ከሚደግፉት ማህበረሰብ ክፍሎች ዋነኛው ነው።

- ከሌሎች እምነቶች ሲነጻጸር ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለዚህ ምክክር ያለው ድጋፍ ፈጽሞ ሊወዳደር የሚችል አይደለም። ሙስሊሙ ይህንን ምክክር የሚፈልገው ያልተመለሱለት ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ነው።

- ተወካዮች ከታች ሲመረጡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ተሳታፊ እንዲሆን ያስፈልጋል። ኮሚሽኑም check and balance ማድረግ አለበት ፤ በትክክልም የዚህን ማህበረሰብ ጥያቄዎች የሚያነሱ ተወካዮች ተወክለዋል የሚለውን።

- የተሳታፊዎች ልየታ ከታች ጀምሮ ሲመጣ በትክክል ሁሉም ማህበረሰብ መወከሉን ማረጋገጥ ይገባል። ኮሚሽኑም ከሌሎች እምነቶች ጋር balance የማድረግ ስራ ይጠበቅበታል።

- ተሳትፎ ላይ ቁጥሩ የተዛባ ከሆነ፣ በጣም አነስተኛ ከሆነ ቅሬታ ስለሚያስከትል ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

- ኮሚሽኑ አካሄድ የነበረው ሲቪል ማህበራት፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ መምህራን ፣ አርብቶ አደሮች፣ እድሮች፣ የፍትህ አካላት፣ የመንግሥት ሰራተኞች፣ ፖለቲከኞች የያዘ ነው በሃይማኖት መልክ ግን የቀረበ ነገር የለም። እነዚህ አደረጃጀቶች ምን ያህል ሙስሊሙ ተሳትፎ አለው ? የሚለው ያሳስበናል፤ ስጋትም አድሮብናል።

- የተነሱ ጥያቄዎችን እና ያሉትን ስጋቶች በተደጋጋሚ ለኮሚሽኑ ቀርበው የጋራ ኮሚቴ ጭምር እንዲቋቋም መረጃዎችም እንዲሰጡ ተጠይቆ በተለያየ ምክንያት ሊሳካ አልቻለም።

- ውይይቶች አድርገናል በተደጋጋሚ ፤ በውጤቱ ላይ የሙስሊሙን ተሳትፎ የሚያሳዩ መረጃዎች (ዳታ) ማግኘት አልተቻለንም።

- እንደ አጀንዳ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥያቄዎች በ9 አጀንዳዎች ተካተው ፣ በ47 ጥያቄ ቀርቦ የካቲት 2 ላይ ለኮሚሽኑ ቀርቧል። መጨረሻ ላይ ኮሚሽኑ ያንን የማስፈጸም ኃላፊት አለበት።

- ታች ያለው የማህበረሰቡ ውክልና በተሻለ ሁኔታ ሁሉ የሃይማኖት ተቋማት ባገናዘበ፣ ሃይማኖት ተቋማትን balanced ባደረገ ሁኔታ መታየት አለበት ቁጥሩ። ለምሳሌ ፦ ከ12 ሺህ ምን ያህል ሙስሊም ተካቷል ፤ ከአዲስ አበባም ከ2500 ተሳታፊ ካለ ምን ያህል ሙስሊም ተሳታፊ ነው ? የሚለው ነው የማህበረሰቡ ጥያቄ።

- እኛ በቂ መረጃዎች የሉንም ለማህበረሰቡ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አስቸጋሪ ነው። በአንዳንድ ሁኔታ ስናጣራ በጣም አነስተኛ ቁጥር ያለበት ስለሆነ የተሻለ ውጤት እንዲገኝ ጥያቄ በማያስነሳ መንገድ እንዲሄድ ማድረግ ይገባል።

- የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተሳታፊ ቁጥር አነስተኛ ከሆነ የሚቀርበው አጀንዳ ይቀራል ፤ ያ ደግሞ እጅጉን ያሳስበናል።

- በእኛ በኩል አሁንም ምላሽ እየጠበቅን ነው።

#EthiopianMuslims
#HarunMedia
#NationalDialogue

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፉን ይጀምራል። ለ7 ቀናት ያህል በሚቆየው የአዲስ አበባው ምክክር ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉ ኮሚሽኑ ገልጿል። በምክክሩ የውይይት የአጀንዳ ሀሳቦችን የሚያመጡ ለምክክሩ የሚቀርቡ ተሳታፊዎች ሲሆኑ ፤ እነዚሁ ተሳታፊዎች በተስማሙባቸው…
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

ከነገ ግንቦት 21 ጀምሮ ለ7 ቀናት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፉን ይጀምራል። ከ2 ሺህ በላይ ሰዎችም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃን።

የስብሰባው ሥርዓቶች ምንድናቸው ?

1. ማንኛውም ተሳታፊ #በነጻነት ሀሳቡን የመግለጽ መብት አለው። ሆኖም ተሳታፊዎች ከጥላቻ፣ ከአዋራጅ እና ከተንኳሽ ንግግሮችመቆጠብ፤

2. በምክክሩ ጊዜ መደማመጥን ከሚያውኩ፣ ሁከትን ከሚፈጥሩ እና መረጋጋትን ከሚነፍጉ ድርጊቶች እና ንግግሮች መቆጠብ፤

3. በጽሁፍ፣ ምልክት ወይም ድምጽ የጎንዮሽ ንግግር አለማድረግ እና ከተሳታፊዎች የሚቀርበውን ሃሳብ በአክብሮትና በጥሞና ማዳመጥ፤

4. እያንዳንዱ የምክክሩ ተሳታፊ የሚሰጠውን ሃሳብና የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ማክበር፣ በቅንነትና በታጋሽነት ማዳመጥ ፤

5. ሌላው ተሳታፊ ያቀረበውን ሃሳብ የመደገፍ ወይም የመቃወም ሁኔታ ሲኖር የሌሎች ተሳታፊዎችን መብት በሚያከብር መልኩ ማቅረብ፣

6. ተሳታፊው እድል ተሰጥቶት ሃሳቡን በመግለጽ ሂደት ላይ እያለ በማንኛውም ሁኔታ ያለማቋረጥ፤

7. የሰውን ክብር ከሚነኩ ነቀፌታዎች ፣ ዘለፋዎች ፣ ስብዕናን ከሚነኩ ንግግሮችና ድርጊቶች መቆጠብ፤

8. ሰዎች በሚያቀርቡት ሃሳብ እንዲሁም አስተሳሰብ ባይስማሙ እንኳ ሃሳባቸውን እና አስተሳሰባቸውን ማክበር፤

9. የሚሰጠውን ሀሳብ በቅን ልቦና ላይ የተመሠረተ ሆኖ ከውይይቱ  አጀንዳ ጋር አግባብነት ያለው አጭር፣ ግልጽ ያልተደጋገመ እና የተፈቀደውን ጊዜ ባከበረ መልኩ መግለጽ፤

10. በሂደቱ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ማብራሪያ እንዲሰጥ መጠየቅ ናቸው፡፡

#የኢትዮጵያ_ሀገራዊ_ምክክር_ኮሚሽን
#NationalDialogue

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹 ከነገ ግንቦት 21 ጀምሮ ለ7 ቀናት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፉን ይጀምራል። ከ2 ሺህ በላይ ሰዎችም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃን። የስብሰባው ሥርዓቶች ምንድናቸው ? 1. ማንኛውም ተሳታፊ #በነጻነት ሀሳቡን የመግለጽ መብት አለው። ሆኖም ተሳታፊዎች ከጥላቻ፣ ከአዋራጅ እና ከተንኳሽ ንግግሮችመቆጠብ፤ 2. በምክክሩ ጊዜ መደማመጥን…
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

በአዲስ አበባ የተጀመረው የአጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ምን መልክ አለው?

በአዲስ አበባ የተጀመረው የአጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ከዛሬ ግንቦት 21 ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል። በሂደቱ ከ2,500 በላይ ተሳታፊዎች ይሳተፋሉ።

በዋናነት ከዚህ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ምን ይጠበቃል?

- 2,500 ከሚሆኑት ተሳታፊዎች በቀጣይ ለሚደረገው ሀገራዊ ምክክር አዲስ አበባን ወክለው የሚሳተፉ ተወካዮች ይመረጣሉ

- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክክር ጉባኤ ይሰየማል

- በአዲስ አበባ ደረጃ በሀገራዊ ምክክሩ ላይ መቅረብ አለባቸው የሚባሉ አጀንዳዎች ይዘጋጃሉ።

በእነዚህ 7 ቀናት ምክክር ኮሚሽኑ ምን ሊያከናውን አቅዷል?

#ቀን_1 እና #ቀን_2

- በመጀመሪያው ቀን በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ የምክክር ምዕራፉ መክፈቻ ሥነ-ስርአት ይካሄዳል። (ይሄ መርሐግብር ዛሬ ጠዋት በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ተካሂዷል)

ከመጀመሪያው ቀን የከሰዓቱ መርሐግብር ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ቀን መጨረሻ ድረስ፦

- 11 የሚሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች  ከ100 በማይበልጥ ቡድን ተከፍለው ይወያያሉ።

- እያንዳንዱ ቡድን ህበረተሰቡን ወክሎ በሚቀጥሉት የምክክር ሂደቶች ሊሳተፉ
የሚችሉ 22 እጩዎችን ይለያሉ።

#ቀን_3

- በቡድን ሲደረግ የነበረው ምክክር ውጤት በየተራ ለቤቱ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይካሄድበታል።

- ከተለዩ እጩዎች ውስጥ 11 የህብረተሰቡ ወኪሎች በሚስጥር ድምጽ አሰጣጥ ይመርጣሉ፡፡

በዚሁ ቀን በተጓዳኝ በከተማ አስተዳደር ደረጃ የተወከሉ ቁጥራቸው 1,220 የሚደርሱ ባለድርሻ አካላት ውይይት ይደረጋል። (ባለድርሻ አካላት የሚባሉት ታዋቂ ሰዎች፤ ፖለቲከኞች ከተቋማትና ማኅበራት የሚሳተፉ አካላት ናቸው።)

#ቀን_4

ዋናው የመክፈቻ  ሥነ-ስርዓት (Launching Ceremony) ይከናወናል

- ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዲፕሎማቶችና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችን ጨምሮ 3,500 ተሳታፊዎች በዋናው የመክፈቻ  ሥነ-ስርዓት ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ።

#ቀን_5

- ተሳታፊዎቹ በ5 ቡድን ( ከወረዳ የተወከሉ (ብዛት 121 )፤ መንግስት፤ የፖለቲካ ፖርቲዎች፤ መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት፤ ታዋቂ ሰዎች (ብዛት 1220) ተከፍለው የአጀንዳ ምክክራቸውን ይቀጥላሉ፤ አጀንዳዎቻቸውን ይለያሉ።

በተጨማሪ ከአምስቱ ቡድኖች በተናጠል የምክክር ውጤቶችን የሚያጠናክሩና የሚያዳዳብሩ 5 ተወካዮች በድምሩ 25 ተወካዮች ይመረጣሉ።

#ቀን_6

- ጠዋት 1,340 ተሳታፊዎችን የያዘ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክክር ጉባኤ ይሰየማል፡፡ 

- 5ቱም ቡድኖች ለጉባኤው የምክክራቸውን ውጤት ሪፖርት ያቀርባሉ፤ በሪፖርቱ ላይም ውይይት ይደረጋል።

- ከየቡድኑ የተመረጡ 25ቱ ሰዎች በጋራ የ5ቱን ቡድኖች አጀንዳ አንድ ላይ በማምጣት ኮሚሽኑ ባስቀመጠው መሰፈርት መሰረት ያደራጃሉ፡፡

#ቀን_7

- 25ቱ ወኪሎች ያደራጆቸውን አጀንዳዎች ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርቡና ሙሉ ቀን ውይይት ይደረግበታል፡፡  

- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አጀንዳ ግብዓት ተለይቶ ለኮሚሽኑ ይሰጣል፡፡

- 25ቱ ተወካዮች የከተማ አስተዳደሩን የተጠቃለለ እጀንዳ ለማደራጀት ሦስት መስፈርቶች ይጠቀማሉ። እነዚህም አስቸኳይ ፤ አስፈላጊ እና  ከፍተኛ ውክልና ያለው በሚል የሚለዩ ይሆናሉ።

#TIKVAHETHIOPIA

@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

እናት ፓርቲ ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ግልጽ ደብዳቤ ጻፈ።

ፓርቲው ለኮሚሽኑ በጻፈው ደብዳቤ ፤ " ኢትዮጵያ ሕልውናዋን በመፈታተን ደረጃ ላይ ከደረሰው ቀውስ ብቸኛው መውጫ መንገድ ሁሉን አቀፍ #አገራዊ_ምክክር ማድረግ ፤ እንደ አገር በዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሆነ በጽኑ እናምናለን " ብሏል።

" የምክክር ኮሚሽኑ በክልል ደረጃ የአጀንዳ ልየታ ውይይቶችን ለማድረግ ዝግጅት እያደረገ መሆኑንና ለዚሁ በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተከታታይ ቀናት በሚደረጉ ስብሰባዎች የአጀንዳ ልየታ የሚያደርግ ጉባዔ መጥራቱ ይፋ ተድርጓል ፤ ጥሪው ለእኛም ደርሷል " ብሏል።

" የሚደረገው ምክክር ስልጣንን የጨበጠ አካል #በቀጥታም ሆነ #በስውር የሚመራው ውይይት መሆን እንደሌለበት እናምናለን " ሲል አስገንዝቧል።

ፓርቲው ፤ " በእኛ እሳቤ ይህ ምክክር በሥራ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥት በመሠረታዊ መልኩ እስከ ማሻሻል አስፈላጊ ከሆነ እስከ መለወጥ ድረስ የሚያዘልቅ እንደሆነ ብናምንም በሥራ ላይ ያለው የአሸናፊዎች ሕገ መንግሥት ዓይነት ተግባር እንዳይፈጸም እና እንደ አገር ዳግም ስህተት እንዳንሠራ ከፍተኛ ሥጋት አለን " ሲል አሳውቋል።

" አገር ልትመክርበት ይገባል ብለን የምናስባቸው የምክክር አጀንዳዎች ፦
➡️ ወቅት የማይለውጣቸውና ወጥነት ያላቸው፣
➡️ መንግሥት ብንሆን ልንተገብራቸው ይገባል ብለን ያስቀመጥናቸው ነጥቦች ስለሆኑ ከአጀንዳ ልየታው ጋር ምንም ችግር የሌለንና ይህንኑ ያቀረብን መሆናችንን ኮሚሽኑ እንዲያውቀው የአገራችን ሕዝብም እንዲረዳልን እንወዳለን " ብሏል።

እናት ፓርቲ ፥ " አጀንዳዎቻችንን የማቅረቡ ሂደት እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚደረገው የምክክር መድረክ ፦

1ኛ. አገር በከፍተኛ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባለችበት ሁኔታ ምክክርም ጦርነትም በአንዴ ማድረግ የማይቻል መሆኑ፣ ከአገራት ተሞክሮ እንዲህ ባለ ሁኔታ የሚደረግ ምክክር ውጤታማ እንደማይሆን ታውቆ በተቃራኒ ወገን የተሰለፉ ወንድማማቾችን እያጨራረሰ የሚገኘው የእርስ በርስ ጦርነት በድርድር ፖለቲካዊ መፍትሄ ሳይበጅለት ፤

2ኛ. በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በየእሥር ቤቱ ታጉረው ባሉበትና ፍትሕ ተነፍጓቸው የሰቆቃ ሕይወት በሚገፉበት፤

3. የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ለምክክሩ ጭምር ጉልህ አስተዋጽዖ ማድረግ የሚችሉ ወገኖቻችን ያለ ፍርድ በየእሥር ቤቱ በሚማቅቁበት፤

4ኛ. አገር በአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ባለችበት፤

5ኛ. በምክክሩ ከመሳተፍ ራሳቸውን ከመጀመሪያ ጀምሮ ከሂደቱ ያገለሉትን የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ምክክር ማምጣት ባልተቻለበትና በመሳሰሉ ምክንያቶች ምክክሩ አገራችን በእጅጉ የምትሻውን አገራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም ያስገኝላታል ብለን አናምንም። " ሲል አሳውቋል።

" እነዚህ ሁኔታዎች አጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ምክክር እስከሚደረግበት ባለው ጊዜ በቀዳሚነት መፍትሄ አግኝተው ሊፈቱ ካልቻሉና ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት ካልተቻለ በምክክሩ ለመሳተፍ እንቸገረለን " ሲል ገልጿል።

(ፓርቲው ለኮሚሽኑ የላከው ሙሉ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

➡️ " በሃገራዊ ምክክሩ #ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

➡️ " ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ #ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ ሀገራት #ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው " - ኮሚሽኑ

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት እየተደረጉ ያሉ ግጭቶች ቆመው ሁሉም አካላት ወደ ንግግር አንዲመጡ ጠይቋል

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጫካ የሚገኙት ታጠቂዎች በምክክሩ ላይ እንዲሳተፉ ከለላ እንዲደረግላቸው መንግስትን የመጠየቅ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ ደስታ ዲንቃ " በሃገራዊ ምክክሩ ሁሉም አካላት ካልተሳተፉ ምክክሩ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ብለዋል፡፡

በጫካ ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ አንዲሳተፉ ለዚህ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ  ምክር ቤቱ የጠየቀ ሲሆን ፥ " ይህ ካልሆነ ግን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ውጤት ላያመጣ ይችላል " ሲል የጋራ ም/ቤቱ ስጋቱን ተናግሯል።

#ሌላው_ስጋት ብሎ ያነሳው ደግሞ የምክክር ኮሚሽኑ የተቋቋመበት አዋጅ  ግጭቶችን የማስቆም ሃላፊነት አልተሰጠውም ግጭት ሳይቆም በግጭት ውስጥ የሚደረግ ምክክር ደግሞ ውጤት ላያመጣ ይችላል ብሏል፡፡

የጋራ ም/ቤቱ ከጅምሩ ጀምሮ " በምክክሩ አንሳተፍም " ያሉ ፓርቲዎችን፣ በተለያየ ክልሎች ያሉ ታጣቂዎች በምክክሩ እንዲሳተፉ እንዲደርግ ኮሚሽኑን ጠይቋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዶክተር ዮናስ አዳዬ ምክክሩ አሳታፊ እንዲሆን፣ ያኮረፉ እና ጫካ የገቡ ታጣቂዎች በምክከሩ እንዲሳተፉ ከሲቪል ማህበረስብ  እና ከተለያዩ አለም ሀገራት ኤምባሲዎች ጋር እየሰራን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

" ጫካ የገቡ አካላት በምክክሩ እንዲሳተፉ በመገናኛ ብዙሃን ተደጋጋሚ ጥሪዎችን እያደረግን ነው " ያሉት ዶ/ር ዮናስ " ሕጋዊ የሆነ መስሪያ ቤት ስለሌላቸው ጥሪ ለማድረግ ተቸግረናል፣ እዚህ ነን  አለን የሚሉ ከሆነ የተመካከሩ ጥሪ ወረቀት ይዘን ለመሄድ ዝግጁ ነን " ብለዋል፡፡

Credit - Sheger FM 102.1

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር  ፕ/ር መስፍን ዓርዓያ ፦
° እናት ፓርቲ ፣
° ኢሕአፓ ፣
° የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ፓርቲዎች በምክክሩ ዙሪያ ቅሬታ አላቸው።

አንዳንዶቹ እኛ እየሰማን ያለነው በመገናኛ ብዙሃን ነው የሚሉ አሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ እርሶ ምን ይላሉ ? ሲል ጠይቋል።

ፕ/ር መስፍን አርአያ ፦

“ በጣም የሚያደክሙ ጥሪዎች አድርገናል። በደብዳቤ ሳይቀር፣ ለኦነግ፣ ለኦፌኮ ለሁሉም ፓርቲዎች ጽፈናል።

የፓለቲካ ፓርቲዎች ከእኛ ጋር እንዳውም ውስጣችን ገብተው እየሰሩ ነው።

በእርግጥ በአሁኑ ሰዓት በአንዳንዶቹ የደረሱ ክስተቶች አሉ። እነዚህን ክስተቶች በጽሞና እያየናቸው ነው በአቅማችን።

እናት ፓርቲም መግለጫ አውጥተዋል ፤ አጀንዳዎቻቸውን ቀደም ብለው ሰጥተውናል።

እናም ያ ሀገራዊ ምክክሩ እስኪደርስ ድረስ መቼም ጥቂት ወራት መፍጀቱ አይቀርም። እነዛ ሁሉም ነገሮች በአምላክ ፈቃድ ይስተካከሉ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

ወደ 50 የሚሆኑ ፓርቲዎች አብረውን እየሰሩ ነው። ሁሉንም እናካትታለን፤ ዝም ያሉትንም #ዱር ያሉትንም። ”

#NationalDialogue
#Ethiopia
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🇪🇹 #NationalDialogue 🇪🇹

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን #በአዲስ_አበባ ደረጃ ለ7 ቀናት አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደትን ትላንት አጠናቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘም  ፥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ጥያቄ እያቀረበ ፤ ማብራሪያም እየጠየቀ ይገኛል።

በብዛት ከሚነሱት ጉዳዮች መካከል አንዱ ፥ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የተመረጡ 25 ተወካዮች እውነት የወከሏቸውን የአዲስ አበባ ማህበረሰብ ክፍሎች ፍላጎት እና ሀሳብ የማንጸባረቅ ብቃቱ አላቸው ወይ ? የሚል ነው።

እንዲህ ላሉት ጥያቄ አዘል ትችቶች የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምን ይላል ? 

ዶ/ር ዮናስ አዳዬ (ኮሚሽነር) ፦

“ ትችቶቹን #እናከብራቸዋለን። ተችዎቹ በራሳቸው አመለካከት ልክ ናቸው።

እኛ ግን በሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ላይ የሚሳተፉ ብለን ያቀድነው 3,500 ሰዎችን ነው በአጠቃላይ።

25 ተመረጡ የተባሉት #አጀንዳውን_የሚያቀርቡልን እንጂ ተመርጠው ወደ #National_dialogue የሚሄዱ አይደሉም።

➡️ አንደበተ ርቱዕ ናቸው ?
➡️ የህብረተሰቡን ጥያቄ ያንጸባርቃሉ ? ለሚለው ጥያቄ ህዝቡ ‘ በአንጻራዊነት እነዚህ #ይሻሉኛል ’ ብሎ ከመረጣቸው መቀበል ነው ” ሲሉ መልሰዋል።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-05

@tikvahethiopia