TIKVAH-ETHIOPIA
" የቅልጥ ዓለቱ እንቅስቀሴ እስከቀጠለ ድረስ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቱ የመቀጠል እድል አለው " - ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ከቀኑ 6 ሰዓት አከባቢ በ 'አዋሽ ፈንታሌ' የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። ንዝረቱ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ተሰምቷል፡፡ ትናንት ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት መሰማቱ ይታወሳል። አሁንም ዳግም የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ መከሰቱ ታውቋል። በአዲስ…
#አፋር
በአፋር ክልል ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል።
በቦታው የባለሙያ ቲም አዋቅሮ የላከው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው እንደተከሰተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጦ ለአካባቢው ማህበረሰብ ልዩ ትኩረት እንዲደረግ በአጽንኦት አሳስቧል።
ህዝቡ ላይ የከፋ ከደጋ እንዳይደርስ የሚመለከታቸው አካላት ሊያደርጉት የሚገባው ርብርብ ምንድን ነው ? ስንል የጠየቅናቸው ዩኒቨርሲቲው የጂኦሎጂ ትምህርት ክፍል ተመራማሪና መምህር ኖራ ያኒሚኦ ምላሽ ሰጥተዋል።
ምን አሉ ?
“ የአደጋው ምክንያት ምንነት አሁን ታውቋል። አደጋው የተፈጠረው የቀለጠ አለት በሚያደርገው እንስቃሴ ነው።
ስለዚህ የከሰም ግድብ የሚባል ስኳር ፋብሪካ አካበቢ አለ። አደጋው እዛ አካባቢ ላይ የሚከሰት ከሆነ የከፋ ጉዳት ሊያከተል ይችላል። ምክንያቱም የመሬት መንቀጥቀጡ በተከታታይ እየተፈጠረ ነው።
አደጋው ካልቆመና የግድቡ አካል የሚነካ ከሆነ ከግድቡ ቁልቁለት አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።
ስለዚህ በተለይ የአዋሽ ፈንታሌ የወረዳ ካቢኔዎች፣ የዞን አስተዳዳሪዎች ህብረተሰቡን ከቁልቁለታማው ቦታ የውሃ ፍስት ወደማይደርስበት ወደ ሌላ ቦታ ያውርዱ።
ተራራ ስር አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ታዝበናልና እነዛ ሰዎች ወደ ሜዳ የሚመጡበት መንገድ ቢፈጠር ሊከሰት የሚችለውን ጉዳት ሊቀንስ ይችላል ” ሲሉ አስገንዝበዋል።
የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተጠባባቂ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም አሊ በበኩላቸው፣ ወደ ቦታው ባለሙዎችን እንደላኩ ገልጸው፣ “ በአካባቢው የግድብ ስራዎች አሉ። አደጋው ከጨመረ ቀፈን ቀበና ያለው ግድብ ትልቅ ፋክተር ተደርጎ ተፈርቷል ” ብለዋል።
“ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ሊደረግለት ይገባል ግድቡ። አንዴ ጉዳት ከደረሰበት ህዝቡን ጠራርጎ ነው የሚወስደው። ከፍተኛ ቦታ ላይ ነው ያለው። በጣም ብዙ መሬትን ሊያካልል የሚችልም ነው ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
አደጋው የሚጨምር ነው የሚቀንስ ? ምን እየተሰራ ነው ? አደጋው ሊያስከትለው የሚችለው ጉዳትስ በምን ደረጃ ነው ? ስንል የጠየቅናቸው ተመራማሪና መምህር ኖራ በበኩላቸው ተከታዩ ማብራሪያ ችረዋል።
“ የመሬት መንቀጥቀጡ እየተፈጠረ ያለው በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ነው። ከሦስት ሳምንታት ወዲህ የትላንት ስድስት ሰዓቱን ጨምሮ አደጋው ሦስት ጊዜ ተከስቷል።
መነሻው በክልሉ ሳቡሪ ቀበሌ ነው። ከዛ ተነስቶ ነው እስከ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ አዋሽ አካባቢዎች ላይ ንዝረቱ የሚሰማው።
በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አማካኝነት አንድ ቲም ተዋቅሮ ለሁለት ሳምንታት በቦታው ተገኝተን ምልከታዎችን እያደረግን ነው። ሙያዊ ሥራዎችን እየሰራን ነው። ለህዝቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ እየሰጠንም ነው።
የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሚከሰትበትን ቦታ መለየት ይቻላል። በዚህ ሰዓት ሊከሰት ይችላል ተብሎ የሚገመት ግን አይደለም። አሁን ባለን ቴክኖሎጂና እውቀት ቦታዎቹን መለየት ብቻ ነው የሚቻለው።
የመሬት መንቀጥቀጥ ዋናው ምክንያቱ ከሥር የቀለጠው አለት ከፍተኛ እንቅስቃሴ ነው። ስለዚህ ማግማው ወደላይ ሰንጥቆ መውጣት እስከሚያቆም ድረስ አደጋው ቀጣይነት ሊኖረው ይችላል።
እስካሁን ድረስ እየተመዘገበ ያለው ከ4.5 እስከ 4.9 ሬክተር ስኬል አካባቢ ነው፤ ይሄም ያን ያክል ጉዳት የሚያደርስ አይደለም መካከለኛ ስኬል ነው። 7 እና ከዚያ በላይ ከሆነ ነው አደጋው ከፍተኛ ሊሆን የሚችለው ” ብለዋል።
በመጀመሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ በተከሰተበት ቦታ ፍል ውሃ መፍለቁ፤ ነዋሪውም ውሃውን ከመጠቀም እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ መሰጠቱ ይታወሳል፤ የተገኘ የምርምር ውጤት አለ እንዴ ? ለሚለው ጥያቄ ምላሻቸው፣ “ አሰስመንት ላይ ነን። ካጠናቀቅን በኋላ ሙሉ መረጃ እናጋራለን ” የሚል ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

" በህክምና ሞያ ብቻ 10 ዓመት በላይ ተምረናል እድሜያችን ወደ ጎልማሳነት ተጠግቷል ቤተሰብ ማስተዳደር ፣ ለልጆቻችን ወተት እና ዳይፕር መግዣ እስከማጣት ድረስ ነው ያቃተን " - ሐኪም
በማዕከላዊ የኢትዮጵያ ክልል፣ ሃዲያ ዞን የሚገኘው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ የሚያስተምሩ ሐኪሞች ፦
➡️ የ4 ወር ዲዩቲ (የትርፍ ሰዓት ስራ ክፍያ)፣
➡️ የ14 ወር የኦቨር ሎድ ክፍያ (Over load)
➡️ የ2016 የአንዋላይዜሽን (Annualization) ክፍያ ስላልተከፈላቸው ማስተማራቸውን ለመቀጠል እንደሚቸገሩ ለዩኒቨርሲቲው በጻፉት ደብዳቤ አሳውቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተውና ለዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች የተጻፈው ደብዳቤ በቁጥር 48 የሚሆኑ መምህራን ሐኪሞች ፊርማቸውን አስፍረውበታል።
ከማህጸንና ጽንስ፣ ከውስጥ ደዌ ፣ ከሰርጀሪ እና ከህጻናት ህክምና ክፍል የተወጣጡ ናቸው።
በጻፉት ደብዳቤ ሐኪሞቹ የማስተማር ሂደቱ ላይና የተጠራቀሙ ልዩ ልዩ ክፍያዎችን በሚመለከት ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትና ሌሎች ከሚመለከታቸው አመራሮች ጋር የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች በተገኙበት ተደጋጋሚ ውይይቶችን ቢያደርጉም መፍትሄ ባለማግኘታቸው እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን ይገልጸል።
በመሆኑም ከ05/02/17 ጀምሮ የማስተማር ስራቸውን በጊዜያዊነት እንዳቆሙና ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ሃላፊነት እንደማይወስዱ ለዩኒቨርሲቲው አሳውቀዋል።
ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ ለመምህራኑ ደብዳቤ ምላሹን በደብዳቤ የሰጠ ሲሆን የማስተማር ስራቸውን በመደበኛነት እንዲቀጥሉ እና ይህን የማያደርጉ መምህራን ሐኪሞች ላይ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታ አቅራቢ ሐኪሞችን በስልክ በማነጋገር ሃሳባቸውን ተቀብሏል።
በሆስፒታሉ የሚያስተምሩ የጤና ባለሞያዎች " የዲዩቲ ወይም የትርፍ ሰዓት ክፍያው ጨምሮ ሌሎችም ክፍያዎች እንዲከፈላቸው ተደጋጋሚ የሆነ ሙከራ ቢያደርጉም ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ማስፈራሪያ እየደረሰን ይገኛል " ብለዋል።
የህክምና ሞያ በባህሪው ከመደበኛ የስራ ሰዓት በተጨማሪ የምሽት እና የአዳር ሰዓትን ጨምሮ ለተጨማሪ ሰዓታት እንዲሰሩ የሚያስገድድ ሲሆን በሆስፒታሉ የሚያስተምሩ ሲኒየር ሐኪሞች ባለፉት 4 ወራት የሰሩበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈላቸው ለከባድ የኢኮኖሚ ጫና መዳረጋቸውን ነግረውናል።
ካነጋገርናቸው መካከል አንደኛው ሐኪም ፦
" በህክምና ሞያ ብቻ 10 ዓመት በላይ ተምረናል እድሜያችን ወደ ጎልማሳነት ተጠግቷል ቤተሰብ ማስተዳደር ፣ለልጆቻችን ወተት እና ዳይፕር መግዣ እስከ ማጣት ድረስ ነው ያቃተን።
እኛ ትርፍ ነገር አልጠየቅንም ኑሮ ውድነቱ የሚታወቅ ነው በደሞዝ ብቻ መኖር አልቻልንም ለልጆቻችን የምንቋጥረው ምግብ ከአቅም በላይ ሆኖብናል።
መሰረታዊ ፍላጎታችንን እናሟላ የሰራንበተን ክፈሉን ነው ያልነው " ብለዋል።
እንደ ሐኪሙ ገለጸ የኑሮ ውድነቱ በተለይም አነስ ያለ ደሞዝ በሚከፈላቸው ነርሶች ላይ ከፍቷል።
ምግብ ሳይበላ መጥቶ በስራ ላይ ሳለ ራሱን ስቶ የወደቀና የቤት ኪራይ የሚከፍለው አጥቶ ቴሌቪዥኑን ያስያዘ ነርስ በሆስፒታል አለ ነው ያሉት።
በሚሰሩበት እና በሚያስተምሩበት በዋቻሞ ዪኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው የንግሥት እሊኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕረንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አመራሮችን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲውን ሃላፊዎችን ቢያናግሩም መፍትሄ እንዳጡ ነግረውናል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ የሰጡ ሐኪሞች " መኖር አልቻልንም " ሲሉ ክብደቱን አስረድተዋል።
ከተጠራቀመው የትርፍ ሰዓት ክፍያ ውስጥ የአንድ ወር ክፍያ ባለፈው ወር እንደተከፈላቸው ገልጸው ነገር ግን ዘግይቶ ስለተከፈለ " ከብድራችን አላለፈም ሁላችንም በብድር ነው የምንኖረው " ብለዋል።
" የብድር አዙሪት ውስጥ ገብተናል ደሞዝ እንቀበላለን ያልቃል ከዛ እንበደራለን፣ ብድር እንከፍላለን እንደዚህ ነው እየኖርን ያለነው " ሲሉ አስረድተዋል።
በተጨማሪ ሐኪሞቹ ፦
- የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ችግራቸውን ከመፍታት ይልቅ ሰዎችን ለይቶ ማስፈራራት ላይ እንደተጠመዱ ፤ የዲፓርትመንት ሃላፊዎችን ለይቶ በማስፈራራት " እናንተ ናችሁ እያሳመጻቹ ያላቹት የሙያ ፈቃዳቹ ይነጠቃል " እስከማለት እንደደረሱ፤
- ለሆስፒታሉ፣ ለተማሪው ፣ለማህበረሰቡ እና ለሰራተኞች የሚያስብ ሃላፊ እንዳጡ ፤
- ተወካዮች ከዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሃየሶ ጋር በተነጋገሩበት ወቅት ፕሬዝዳንቱ " ችግሩ ያለው ግቢያቹ ውስጥ ነው የሆስፒታሉ የውስጥ ገቢ የት እንደሚሄድ አላውቅም የውስጥ ገቢው የተጠየቀውን ክፍያ መክፈል መቻል አለበት " ማለታቸውን፤
- ለቀድሞው የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሐብታሙ አበበ ቅሬታቸውን በተደጋጋሚ ቢያቀርቡም ችግራቸው ሳይፈታ ፕሬዝዳንቱ በሙስና እና ሐብት ምዝበራ ወንጀል ተጠርጥረው ሐምሌ 15/2016 ዓም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን፤
- ከትምህርት ሚኒስቴር ሊያማክሩ የመጡ በትምህርት ሚኒስትር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የተወከሉ ሰዎች ባሉበት ስብሰባ ላይ አዲስ ፕሬዝዳንት ስለሆነ ጊዜ እንዲሰጠው ፣ ነገሮችን አስተካክሎ እና አይቶ የእነሱን ክፍያ በቅድሚያ እንዲከፈል እንደሚያደርጉ እንደነገሯቸው እና እስካሁን መታገሳቸውን ጠቁመዋል።
ነገር ግን እስካሁን ከመፍትሄ ይልቅ ማስፈራሪያ እና ዛቻ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጻዋል።
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አያኖ ሻንቆ ምን ምላሽ ሰጡ ?
ስራ አስኪያጁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃን ፥ መምህራኑ የጠየቁት ክፍያ ያልተከፈላቸው መሆኑን አምነዋል።
" አልከፍልም ያለ ሰው የለም ለምንድነው ስራ የሚያቆሙት ? የዲዩቲ እና ኦቨርሎድ ክፍያ ከደሞዝ ጋር አይገናኝም ለደሞዛቸው መስራት አለባቸው የትርፍ ሰዓት ክፍያ ግን ሲሰሩ ብቻ ነው መክፈል የሚቻለው አሁን ላለመግባት ከወሰኑ በቀጣይ ያልሰሩበት ይቆረጥባቸዋል " ብለዋል።
" በአንድ ጊዜ ያልተከፈለውን ክፍያ ሁሉ ለመክፈል የሆስፒታሉ በጀት የማይበቃ በመሆኑና ተጨማሪ የገንዘብ ምንጭ ስለሌለ የሚመጣውን ገንዘብ ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ ሰጥተን ነው የምንከፍለው በጀቱን እየጠየቅን ነው ሲፈቀድ እንከፍላለን አንከፍልም ያለ የለም " ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም " ይህን መሰል ችግር እኛ ጋር ብቻ አይደለም ያለው እናንተ ጋር ስለደረሰ ነው እንጂ በሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ ችግር አለ " ያሉ ሲሆን " በእኛ በኩል በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ችግሩ ይፈታል ብለን እናስባለን " ብለዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
“ የሞቷ ምክንያት ምን እንደሆነ ፓሊስ እያጣራ ነው ” - ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጂ የቱሪዝም ትምህርት ክፍል ሁለተኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ሩት ማርሻ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየች ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከቀናት በፊት አሳውቋል።
ዩኒቨርሲቲው በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ተማሪዋን፣ “ በድንገት ከዚህ ዓለም ድካም አርፋለች ” ከማለት ውጪ ስለአሟሟቷ የጠቀሰው ግልጽ ማብራሪያ የለም።
ይህ በእንዲህ እያለ “ ተማሪዋ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በመጣላቷ ከፎቆ ተወርውራ ነው የተገደለችው ” የሚሉ ወሬዎች እየተዘዋወሩ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ያሰራጫችሁት ፅሑፍ ተማሪዋ በድንገት ከዚህ ዓለም ድካም እንዳረፈች ከመግለጽ ውጪ ስለአሟሟቷ አያብራራም፤ በሌላ ወገን ደግሞ ተማሪዋ የሞተችው “ ከፎቅ ተወርውራ ” እንደሆነ እየተገገረ ነው፣ እውነታው ምንድን ነው ? ሲል ዩኒቨርሲቲውን ጠይቋል።
ከዩኒቨርሲቲው የሕዝብና ዓለም ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ምላሽ የሰጡን አቶ ማቲዎስ ጪናሾ፣ “ በፃፍነው ላይ ድንገት ሕይወቷ አለፈ ነው የሚለው። አሁን ደግሞ የሞቷ ምክንያት ምን እንደሆነ ፓሊስ እያጣራ ነው ያለው ” ብለዋል።
“ እርሷ ጋር የነበረ ልጅም አለና ከእርሱ ኢንቬስቲጌት እያደረጉ ስለሆነ መረጃውን ፓሊስ ይፋ ሲያደርግ እኛም ይፋ እናደርጋለን ብለን ነው እየጠበቅን ያለነው ” ነው ያሉት።
እስካሁን የተገኘ ፍንጭ አለ ? ከፎቅ ተወርውራ ስለመገደሏ አመላካች ጉዳዮች፤ የአሟሟቷ ሂደት እንዴት ነው ? ሲል ቲክቫህ ላቀረበው ጥያቄ ፣ “ የአሟሟት ሂደቱን እኛ አሁን ይሄ ነው ብለን መናገር አንችልም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“ ምክንያቱም ጉዳዩን የያዘው ፓሊስ ነው። የሞቷ ምክንያት ይሄ ነው ብሎ ይፋ ሲያደርግ ነው ይፋ ማድረግ የምንችለውና አሁን እኛም የተረዳነው ነገር የለም ” ሲሉም አክለዋል።
“ ዝም ብለው ወሬዎቹ አሉ። ወሬዎቹ የተለያዩ ናቸው” ያሉት አቶ ማቲዎስ፣ “ ‘ከ4ኛና 5ኛ ፎቅ ወድቃም’ ይባላል፤ ‘ሰው አንቋትም’ ይባላል፤ የተለያዬ ወሬ ነው ያለውና ያንን አሁን እንደ ምክንያት አንቀበልም። መቀበል የምንችለው የተጣራ መረጃ ሲገኝ ነው ” ብለዋል።
አደጋው የደረሰው ከቀናት በፊት ከምሽቱ 4 ሰዓት ገደማ እንደሆነ፣ አስከሬኑ አዲስ አበባ ወደሚመለከተው ሆስፒታል ሌሊት ተወስዶ፣ በማግስቱ ሀዋሳ ከቤተሰብ እንደደረሰ፣ ቤተሰብ የቀብር ሥነ ሥርዓት እንደፈጸመ፣ ዩኒቨርሲቲውም ትላንት የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት እንዳካሄደ አቶ ማቲዎስ ተናግረዋል።
በተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለጉዳዩ የጠየቀው የወላይታ ሶዶ ዞን ፓሊስ ለጊዜው ማብራሪያ ከመስጠት የተቆጠበ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ህብረት ደግሞ ጉዳዩን እንደሚያጣራ ገልጿልናል።
(ጉዳዩን እስከመጨረሻው በመከታተል ተጨማሪ መረጃ እናደርሳችኋለን)

" በግቢ ውስጥ ብዙ የአእምሮ ህሙማን ፤ አረጋውያን አሉ በእነሱ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም " - አቶ ንጋቱ ማሞ
ዛሬ ቀን ላይ አዲስ አበባ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 " መቄዶኒያ የአእምሮ ህሙማንና የአረጋዊያን መርጃ ማህበር " እያስገነባ ባለዉ አዲስ ህንጻ ስር ባለ መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ " በደረሰን ጥሪ መሰረት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞቻችን ከሁለት ቅርንጫፍ ወደ ቦታዉ ፈጥነዉ በመድረስ እሳቱ ሳይስፋፋ በፍጥነት ተቆጣጥረውታል " ብለዋል።
በእሳት አደጋዉ በመጋዘን ዉስጥ የነበሩ ልዩ ቁሳቁሶች ላይ መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ በስተቀር በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ ተናግረዋል።
አቶ ንጋቱ ማሞ ፤ " ግቢ ውስጥ ብዙ የአእምሮ ህሙማን፣ አረጋውያን አሉበት በእነሱ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም። አካባቢው ላይ ካሉ ፀጥታ ኃይሎች፣ ከግቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን እሳቱን በቀላሉ መቆጣጠር ተችሏል " ሲሉ አስረድተዋል።
መጋዘን ውስጥ የነበሩ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ላይ ግን መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰ ጠቁመዋል።
የአደጋውን ምክንያት ፖሊስ እያጣራው ነው።

#AddisAbaba #Education
“ በሂሳብና እንግሊዘኛ መፅሐፍት ላይ እጥረት በመታየቱ ተጨማሪ ህትመት እየተካሄደ ነው ” - አ/አ ትምህርት ቢሮ
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት መፅሐፍ ማሳተም ላይ እንደ አገር በተለያዩ ትምህርት ቢሮዎች ክፍተቶች እንዳሉ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲገለጽ መቆየቱ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት በ2017 የትምህርት ዘመን መፅሐፍትን አሳትሞ ለተማሪዎች ማዳረስ ተቻለ ? ሲል ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጥያቄ አቅርቧል።
የቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) በሰጡት ቃል፣ “ በተወሰኑ ትምህርቶች ላይ፤ ሂሳብና እንግሊዘኛ መፅሐፍት እጥረት በመታየቱ ምክንያት ተጨማሪ ህትመት እየተካሄደ ነው። ሪዘርቭም እያደረግን እንገኛለን ” ሲሉ ተናግረዋል።
የመፅሐፍት እጥረቱ በምን ደረጃ ነው ? ሲል ቲክቫህ ላቀረባቸው ጥያቄ በምላሻቸው፣ “ ይህንን ሬሽዎ በተለይ ከግል ትምህርት ቤቶች አካባቢ ላይ ያለ ችግር ነው ” ብለዋል።
“ እነርሱም መፅሐፉን ወስዶ ለማሰራጨት ፍላጎት ማጣት፣ ይሄ ደግሞ የራሳቸው መፅሐጽት አትመው ለመሸጥ ከሚመነጭ ነገር ስለሆነ እሱ ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እየወሰድን ትምህርት ቤቶች ወስደው ለተማሪዎቻቸው ተደራሽ እንዲያደርጉ አድርገናል ” ነው ያሉት።
“ ከሁለተኛ ደረጃና ቅድመ አንደኛ ደረጃ በስተቀር ለሁሉም አንድ ለአንድ ተዳርሷል ” ሲሉም ተናግረዋል።
“ ለሁለተኛ ደረጃም ትምህርት ሚኒስቴር አሳትሞ ሰሞኑን ባስገባው መሠረት ለሁሉም ተማሪዎች ማዳረስ ተችሏል" ያሉት ኃላፊው፣ " ባለፉት ሁለት ዓመታት በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ተማሪዎቻችን ጋር ተደራሽ ለማድረግ ተሞክሯል” ብለዋል።
በሌላ በኩል፣ ከተማሪዎች ምገባ ጋር በተያያዘ መጋቢ እናቶች ከኑሮ ውድነቱ ጋር በተያያዘ የሚከፈላቸው ገንዘብ አነስተኛ መሆኑን ይገልጻሉ።
ይህንኑ በተመለከተ ምን እየተሰራ እንደሆነ ማብራሪያ የጠየቅናቸው ዘላለም (ዶ/ር)፣ “ በተማሪ 22 ብር የነበረው በዚህ ዓመት ወደ 32 ብር አሳድጎላቸዋል። ስለዚህ ያ ጥያቄ ተመልሷል ማለት ነው ” ብለዋል።
“ በቀን 800 ሺሕ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ ይመገባሉ ” ሲሉ ተናግረዋል።
በተያያዘም በትምህርት ቤት አካባቢዎች ያሉ ሱስን የሚያበረታቱ ቤቶች እንዳሉ፣ ይህም ተማሪዎችን ከዓላማቸው የሚያደናቅፍ ከመሆኑ አንጻር በቂ ትኩረት ተሰጥቷል? ሲልም ቲክቫህ ጥያቄ አቅርቧል።
ዘላለም (ዶ/ር) በምላሻቸው፣ “ትክክል ነው። የተማሪዎችን ሀሳብ፣ ልቦና የሚሰርቁ ጉዳዮች በትምህርት ቤት አካባቢዎች እንዳይኖሩ ባለፉት ዓመታት ጠንካራ እርምጃ ወስደናል” ብለዋል።
“ ከ3000 በላይ የሚደርሱ የተለያዩ መማር ማስተማር ሂደቱን ሊያውኩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ እርጃ ተወስዷል ” ብለው፣ “ አሁንም እንደዛ አይነት ፍላጎቶች በትምህርት ቤቶች ብቅ ብቅ እንዳይሉ መልሶ ጠንካራ እርምጃና ክትትል ያስፈልጋል ” ሲሉ አስገንዝበዋል።

#Update በመርካቶ ' ሸማ ተራ ' የተነሳው እሳት እስካሁን ሊጠፋ አልቻለም። እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም ከእሳቱ መፋፋምና ከቦታው አለመመቸት የተነሳ ሁኔታውን እንዳከበደው በስፍራው የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት ጠቁመዋል። እሳቱ ያልደረሰባቸው ሱቆች እቃቸውን ከስፍራው እያሸሹ ናቸው። እስካሁን የጉዳቱ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቀም በርከት ያሉ ሱቆች ግን እየተቃጠሉ ናቸው።…
#Update
“ አደጋውን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ” - አቶ ንጋቱ ማሞ
መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ መከሰቱን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ኮሚሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ከኮሚሽኑ ቃላቸውን የሰጡትን አቶ ንጋቱ ማሞ፣“ አደጋውን ለመቆጣጠር እርብርብ እየተደረገ ነው ” ብለዋል።
“ ከመሸ ነው ጥሪ የመጣው። ጥሪው እንደመጣ በአቅራቢያው ካሉ የአዲስ ከተማ፣ አራዳ ክፍለ ከተሞች ልከን ነበር ” ብለዋል።
“ ነገር ግን በእነርሱ የሚሸፈን ስላልሆነ ከሁሉም ቅርንጫፍ ጣቢያ የአደጋ መቆጣጠር ማሽነሪዎች፣ አደጋ ጊዜ ሠራተኞች፣ አምቡባንሶች፣ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች፣ አመራሮች ጭምር ቦታው ላይ ሆነው አመራር እየሰጡ ነው እሳቱን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ” ሲሉ አክለዋል።
“ የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች እሳቱ ወደተነሳበህ ቦታ ላይ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ቦታው ትንሽ አስቸጋሪ አድርጎታል ” ያሉት አቶ ንጋቱ፣ “ ዞሮ ዞሮ ርብርብ እየተደገ ነው ” ብለዋል።
“ በዚህ ሂደት የጸጥታ ኃይሎች የአካባቢው ማህበረሰብ አሉ። አደጋውን በቁጥጥር ሥር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።
ያሉትን ሂደቶች እንደሚያደርሱን የገለጹ ሲሆን፣ መረጃው እንደደረሰን የምናጋራ ይሆናል።
ቪድዮ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

#ሶማሌክልል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ካለፈው ሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በሱማሌ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰቢያ የምክክር መድረክ እያደረገ ይገኛል፡፡ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ፥ ከጥቅምት 4-6/2017 ዓ.ም በክልሉ ሶስት ማዕከላት ፦ - በጅግጅጋ ፣ - በጎዴ - በዶሎ አዶ ማዕከላት ከ 1 ሺ በላይ የማህበረሰብ ወኪሎችን በማመካከር አጀንዳዎቻቸውን እንዲለዩ ማድረግ…
#ሶማሌክልል
" መሳሪያ አንግበው በጫካ እየታገሉ ያሉ ሰዎች በሌሉበት ምክክሩ የተሳካ ይሆናል የሚል ግምት የለንም "- ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በሶማሌ ክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር አጀንዳ የመሰብሰብ የምክክር ምዕራፍ እያደረገ ነው።
ከባለድርሻ አካላት መካከል የፓለቲካ ፓርቲዎች ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ በውይይት መድረኩ የተገኘው ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ከቲክቫህ ኢትዮጵያና ሌሎች ሚዲያዎች ጋር ቆይታ አድርጓል።
ስለውይይቱን ሂደት፣ የኮሚሽኑን አካታችነት፣ የታጠቁ ኃይሎች፣ የባሕር በርን በተመለከተ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ኢሴ ባናሃጂ አቡቦከር ምላሽ ሰጥተዋል።
ምን አሉ?
" የኢትዮጵያዊያን ግጭትን የምናስወግድበት የራሳችን ባህሎች አሉን። ባህሎቻችንን ባለመከተል በአገራችን ብዙ ችግሮች እየተከሰቱ ስለሆነ እነዚህን ችግሮች ይቀርፋል ተብሎ ነው መድረኩ የተዘጋጀው።
በመድረኩ የሶማሌ ህዝብን ወክለን መጠየቅ ያለብንን ነገር እየተወያዬን ነው።
(ለምሳሌ ህዝቡ ከዚህ በፊት በነበሩት መንግስታት የደረሰበት በደል፤ ቅሬታ፣ ቁስል አለው)፤ በቅድሚያ ህዝቡ ያለበት ቁስል ይታከም። ብዙ አጀንዳዎች አሉ።
ከአካታችነት አንጻር እኛ እንደ ፓለቲካ ፓርቲ አገራዊ ውይይቱ የበለጠ ውጤታማ ይሆናል ብለን የምንጠብቀው በመድረኩ ያልተካተቱ ሰዎች ቢካተቱበት ነው።
መሳሪያ አንግበው በጫካ እየታገሉ ያሉ ሰዎች በሌሉበት ምክክሩ ሰክሰስፉል ይሆናል የሚል ግምት የለንም።
እነርሱ እንዲካተቱ ነው እንደ ፓለቲካ ፓርቲ ደጋግመን እየጠየቅን ያለነው። መድረኩ ለማንም የሚጠቅም እንጂ ማንም የሚከስርበት አይደለም።
መሳሪያ አንግበው በጫካ እየታገሉ ያሉ አካላትም ወደ መድረኩ መጥተው ሀሳባቸውን አቅርበው በሚያግባባን ሀሳብ እንድንግባባ፣ በማያግባባ ሀሳብ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ተሰብስቦ ሪፈረንደም እንዲያደርግ ነው አስተያየት የምንሰጠው " ብለዋል።
በመድረኩ የተዳሰሱ ጉዳዮችን በተመለከተም፣ " የፓለቲካ ፓርቲዎች እንደ ጥያቄ ያቀረቡት አጀንዳ፣ ለምላሌ የኛ ፓርቲ፣ አሁንም አገራችን እየተመራችበት ያለውን ፌደራሊዝም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ሌላው የኢትዮጵያ ባንዲራን በተመለከተ ነው። ስለኢትዮጵያ ባንዲራ የኛ ፓርቲ ያለው አመለካከት ባንዲራው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ አይወክልም የሚል ነው " ብለዋል።
" ስለዚህ አሁን ያለው ባንዲራ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ አንድ ላይ በመሆን ሁሉንም የሚወክል ምልክት ተደርጎበት ባንዲራ ላይ ለውጥ እንዲደረግ የሚል አስተያየት ነው ያቀረብነው " ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ መንግስት ከሶማሌላንድ ጋር የተፈራረመችውን የባሕር ወደብ በተመለከተ ተጠይቀው ባደረጉት ገለጻ፣ " እንደ ሶማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ ኢትዮጵያ የባሕር ወደብ እንድታገኝ በጣም እንፈልጋለን " ብለዋል።
" ግን እንደ ፓርቲነት ይሄን ባሕር የምንፈልገው ከዚህ በፊት የባሕር በር የሌላቸው ብዙ የአፍሪካ አገሮች ባሕር ያገኙበትን መንገድ ተከትለን ኢንተርናሽናል ሕግ በሚፈቅደው ሁኔታ እንዲሆን ነው " ሲሉ አክለዋል።
ኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ ጋር ባደረገችው የባሕር በር ሥምምነት ክልሉ ያደረበት ስጋት አለ? ተብሎ ለቀረበላቸው በምላሻቸው፣ " አዎ። ኢትዮጵያ መንግስት ከሱማሌላንድ ጋር ያደረገው ሥምምነት እኛ ላይ አንዳንድ ስጋት ፈጥሮብናል " ነው ያሉት።
" ባሕር ያልነበራቸው አገሮች ከጎረቤት አገሮች ጋር ኢንተርናሽናል ሕግን መሠረት ባደረገ መንገድ ተፈራርመው ባሕር እየተጠቀሙ ነው። የነርሱን ልምድ በተከተለ መንገድ የባሕር በር ብናገኝ ፍላጎታችን ነው " ብለዋል።
የኦጋዴን ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) ከሀገራዊ ምክክሩ እንዳገለለ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ያስታወቀ ሲሆን፣ ፓርቲው በዝርዝር ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ ያደረግነው ጥረት ፓርቲው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለጊዜው አልተሳካም።

“ አንድ እንጀራ 30 ብር በገባበት ወቅት 450 ብር ለምን ይጠቅማል ? ለቤት ኪራይ፣ ወይስ ለቀለብ ነው የሚሆነው? ” - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር።
የመምህራን የስልጠና ክፍያ እጅግ አነስተኛ መሆን ከኑሮ ውደነት ጋር ተያይዞ ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ሲሰጡት የነበረውን የሙያ ስልጠና አለመስጠታቸው የትምህርት ጥራት ቀውስ ውስጥ እንዲገባ እያደረገ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጠየቀ።
ከማኀበሩ የተሰነዘሩ ቅሬታዎች ምንድን ናቸው ?
“ ከትምህርት ሥርዓት አንጻር በአሁኑ ሰዓት የትምህርት ጥራት ችግር ብቻ ልንለው አንችልም። የትምህርት ቀውስ ነው። ቀውስ ውስጥ ገብተናል። ወደ መምህራን ችግሩን የመግፋት ነገር ይታያል። ይሄ ትክክል አይደለም።
ሲጀመር የመምህርት ስልጠና ዋጋ አልተሰጠውም። ለምላሌ ፦ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት እጩ መምህራን ከተወሰኑ ኮሌጆች ውጪ 450 ብር ተሰጥቷቸው ውጪ ሆነው እንዲማሩ የሚደረጉት።
አንድ እንጀራ 30 ብር በገባበት ወቅት 450 ብር ለምን ይጠቅማል ? ለቤት ኪራይ ወይስ ለቀለብ ነው የሚሆነው ? ችግሩ እዚያ ጋ ነው የሚጀምረው።
እጩ መምህራን ወደ ኮሌጅ ውስጥ ሲገቡ 450 ብር ይከፈላቸዋል። ፍላጎታቸውን ስለማይሟላ ትምህርት ላይ ትኩረት ሳያደርጉ ፍላጎታቸውን ለሟሟላት ይንቀሳቀሳሉ። ይሄ የመምህርነትን ሙያ ጥራቱን ቀንሶታል። ስለዚህ ጉዳዩ ሊታረብበት ይገባል።
የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ጥናት አጥንቷል። በዚያ መልኩ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል።
በሌላ በኩል ፥ ወደ መምህርነት ሙያ ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንሲ ተብለው እነዚህ የመቐለ ፣ ባሕር ዳር፣ የአዲስ አበባ፣ ጅማና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንን የሚያሰለጥኑ ነበሩ ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች።
ነገር ግን ላለፉት ሦስትና አራት ዓመታት ምንም አይነት ተማሪ ወደ መምህርነት ሙያ እንዲገባ እያሰለጠኑ አይደለም።
ይሄ ደግሞ በቀጣይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችንን በድጎማ መምህር ልናስይዝ አይደለም ወይ ! ይሄ ወዴት እየሄደ ነው ?
በተያያዘ፣ የመፅሐፍት ስርጭት ችግሮች አሉ። ችግር መኖር ብቻ ሳንሆን አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ በአንድ ላይ ኮምባይን የሆኑ ትምህርት ቤቶች አሉ።
ለምላሌ ፦ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስና ባይሎጂ አንድ ላይ ናቸው። በአንድ መምህር ነው የሚሰጡት። ይህም መምህራን ኬሚስትሪውን ፓርት ያስተምሩና ፊዚክስና ባይሎጂው የተመረቁበት ስለማይሆን ለማስተማር እየተቸገሩ ነው።
በሌሎች የትምህርት አይነቶችም ተመሳሳይ ችግር አለ። መምህር ያልተዘጋጀባቸው ሥርዓተ ትምህርቶች አሉ። የትምህርት ጥራቱን እየጎዳው ያለው አንዱ ችግር ይሄ ነው። አጠቃላይ ትምህርቱ ሴክተሩ በቂ ትኩረት አላገኘም። በቂ ፋይናንስ እየተመደበለት አይደለምና ሊመደብለት ይገባል።
መምህራንም የተለያዬ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሲፈጠሩ መብታቸውን ለማስከበር ወደ ሕግ ተቋማት ስለሚሄዱ የትምህርት ጊዜ ይዘጋል። ይሄ ደግሞ የትምህርት ጥራት ላይ ችግር አምጥቷል። ”
እነዚህ ቅሬታዎች የትምህርት ሚኒስቴር በተገኘበት መድረክ እንደቀረቡ ማኀበርሩ ገልጾልናል።
የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዲሰጡ ያሳሰበው ማኀበሩ፣ ትምህርት ሚኒስቴር በተነሱት ቅሬታዎች ዙሪያ መፍትሄ ለማምጣት አሳይመንት ይዞ እንደሄደ አመላክቷል።

“ ጡረታ፣ ህክምና ይከበርልን። እኛ ወድቀናል፤ ከስረናል፤ ከሽፈናል። ቢያንስ እንደ ዜጋ እንታከም ” - የሶማሌ ክልል ቀድሞ ሰራዊት አባላት
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶማሌ ክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር የአጀንዳ ማሰባሰብ የውይይት መድረክ አድርጎ ነበር።
በዚህ መድረክ ከተሳተፉት ባለድርሻ አካላት መካከል አንዱ የሶማሌ ክልል የቀድሞ ሰራዊት አባላት ነው።
ኮሚሽኑ ስለቀድሞ ሰራዊት ጉዳይ ምን ማተኮር እንዳለበት፣ ስለታጠቁ ኃይሎችና የመንግስት አካሄድ የተመለከቱ ጥያቄዎች ያቀረብንላቸው የክልሉ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ሊቀመንበር ሻለቃ ሴባ ቶንጃ ምላሽ ሰጥተዋል።
ምን አሉ ?
“ ሥርዓት ሲወድቅ የሚወድቅ ሥርዓት ሲነሳ የሚነሳ ሰራዊት ካለ ሀገርና ሕዝብ ዋስትና የለውም። ማንም እንደገባ ከዚያም ከዚህም ያዋክበዋል፤ ህዝብ ጉዳት ያደርስበታል።
ቀጣዩ ትውልድ እንዴት ይኑር? ለምን በባንዲራ እንጨቃጨቃለን? ከጥንት ጀምሮ ቅድመ አያቶቻችን ያወረሱን ነው እዚህ ላይ ያለው ስህተት ምንድን ነው? ለምን በአድዋ ድል እንጨቃጨለን? ስህተት ካለ ተመካክረን እናስተካክል እንጂ ለምን እንጋደላለን ?... በሚል ለሀገር የሚጠቅም አጀንዳ እየቀረጽን ነው።
ጡረታ ያልተከበረልን ነን፤ ጡረታ ይከበርልን፤ እንደዜጋ ለሀገር አገልግለናል፤ ሜዳ ላይ መውደቅ የለብንም። አሁንም እየተጠራን እየተሳተፍን ነው።
እኛ ለሀገር አሁንም ዝግጁ ነን፤ አላኮረፍንም፡፡ ሁሉም በእኩልነት ይታይ፡፡ የተወሰኑትን ብቻ መዞ ይዞ የተወሰነው ጭራሽ እስከነመፈጠሩም ይረሳል፡፡
ጡረታ ይከበርልን፤ ህክምና ይከበርልን፤ እኛ ሁሉን ትተን ለሀገር ብለን ስለንዘምት የነበረ ተማሪ አሁን ዶክተር ፕሮፌሰር ነው። እኛ ወድቀናል፤ ከስረናል፤ ከሽፈናል። ቢያንስ እንደ ዜጋ እንታከም። እኛ ስንዋጋ ተምረው ዶክተር የሆኑ ያክሙን።
መንግስት የሕክምና፣ የጡረታ ዋስትና ይስጠን። ከራሳችን ገንዘብ ተቆርጦ ገቢ ሲሆን የነበረውን ተከልክለናል። ይህ ይስተካከል።
እንደዜጋ በክብር እንኑር። በመስሪያ ቤቶች ተቀጥረን ጥበቃ ለመስራት እንኳ የታገደበት ሁኔታ ነበር፤ ‘እንዳይቀጠሩ’ የሚል። ዜጋ ነን፣ ይሄ ያሳምጻል ነገር ግን አላመጽም በሀገራችን አናምጽም፤ ህዝብ ይበጠበጣል ብለን።
ችግራችንን አምቀን ይዘን አሁንም ለህዝባችን ደኀንነት እየታገልን ነው።
ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ግጭቶች በአያያዝ ስህተት የተፈጠሩ እንደሆኑ እናምናለን። በአጠቃላይ የእርስ በእርስ ግጭት የወንድማማቾች እልቂት አንደግፍም።
እገሌ እገሌ የሚል ስያሜ መንግስት ይስጠው እኛ የወንደማማቾች ግጭት አንደግፍም፡፡ ግን መጥተው ህዝቡን እንዲጨፈጭፉና ተቋም እንዲያወድሙም አንፈልግም፡፡
ይልቁንም ወደ መድረክ እንዲመጡ እንፈልጋለን፡፡ ለዚያ ደግሞ መንግስት በሆደ ሰፊነት ቀረብ ብሎ መሳብ ያስፈልጋል። ግጭት እስከወዲያኛው ይቁም።
አሁን የተፈጠረው ግጭት በአያያዝ ስህተትነው የተፈጠረው አይፈጠርም ነበር፡፡ ለምሳሌ ጊዜውን መጠበቅ ሲገባ ያልበሰለ አጀንዳ ወደ ህዝብ ይለቀቃል፡፡
በሚስጥር ተይዞ ቆይቶ በኋላ ሁኔታው ሲፈቅድ መልቀቅ ነው እንጂ ጊዜውን ያልጠበቀ አጀንዳ ከለተለቀቀ ግጭት ይፈጥራል፡፡ ጊዜውን ያልጠበቀ አጀንዳ መዓት ነገር ነው፡፡
ለምሳሌ ፦ ለመጥቀስ የፋኖም ራሱ ጊዜውን ያልጠበቀ አጀንዳ ሆኖ በግድ ስለተኬደበት እንጂ አይዋጉም ነበር፡፡ ትላንትና ራቁቱን የተባረረውን መካላከያ ሰራዊትን ያዳኑ እነርሱ አይደሉምን ?
አሁን የተፈጠረውን ብቻ ኮንነን መንግስት ይውደደን ብዬ አልናገርም፡፡ ሚዛናዊ ህሊና አለኝ፡፡ አሁን የሚሰሩት ሥራ ጥሩ ነው እያልኩ ሳይሆን ወደ መጥፎ ተገፋፍተው በእልህ የተገፉት ነገር ጥሩ ስላልሆነ ነው፡፡
በእርግጥ አሁን መንግስት ጥረት እያደረገ ነው በዚሁ ይቀጥል፡፡ ወደ ሰላም ቢያመጣቸው ጥሩ ነው፡፡
መጪው ትውልድ በሰላም እንዲኖር ከእንግዲህ በአገራችን የወንድማማቾች ጦርነት እንድናይ፣ እኛ ያየነው ችግር በእነርሱ ላይ እንዲደርስ አንፈልግም፡፡
ሁሉም የበኩል ድርሻ ተቀብሎ መንግስትም ያለውን ስህተት አርሞ ብለድርሻ አካላት በሙሉ ለሰላም አስተቃጽኦ አድርገው ከተንቀሳቀሱ ሰላም ይመጣል፡፡ ይህ ካልሆነ ከዚህ በባሰ እንጠፋፋለን፡፡ አሁን በዚህ ውይይት መፈታት አለበት ከዚህ ካለፈ አካሄዱ አያምርም፡፡
ከተሞክሯችን ተነስተን ነው መልዕከት የምናስተላልፈው፡፡ እሳት የጎረሰ መሳሪያ ይዘን ውሃ ጠምቶን ለምነን እየጠጣን ነበር፡፡
ከደረሰብን ጉዳት አንጸር እኛ ለመሸፈት ነበርን ቅርብ፡፡ አሁንም ቢሆን አኩርፈን ለመሄድ እኛ ነን ቅርብ፡፡ ጸጉራችንን ተላጭተን እድሜያችንን የጨረስነው በርሃ ውስጥ ነው፡፡
በውጊያ አውድ ያሉ አካላት እርግጥ ምክንያት ኖሯቸው ትግል ቢጀምሩም የትኛውም ግጭት ሂዶ ሂዶ በስምምነት መጠቃለሉ አይቀርም፡፡ ዞሮ ዞሮ ሰላም ይመጣል፤ በእድሜያችን እያየን ያለነው ይሄው ስለሆነ፡፡ ከብዙ መተላለቅ ይልቅ ለስምምነቱ፣ ለእርቁ፣ ለውይይቱ እድል ቢሰጡ ጥሩ ነው" ብለዋል።
ምን ያክል ቀድሞ ሰራዊት አባላት አሉ ለሚለው የቲክቫህ ጥያቄ በምላሻቸው “ ባለንበት አካባቢ በርካታ የቀድሞ ሰራዊት አባላት አሉ፡፡ ወደ 5 ሺሕ የሚሆኑ አሉ ” ብለዋል።

“ አንድ እንጀራ 30 ብር በገባበት ወቅት 450 ብር ለምን ይጠቅማል ? ለቤት ኪራይ፣ ወይስ ለቀለብ ነው የሚሆነው? ” - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር። የመምህራን የስልጠና ክፍያ እጅግ አነስተኛ መሆን ከኑሮ ውደነት ጋር ተያይዞ ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ሲሰጡት የነበረውን የሙያ ስልጠና አለመስጠታቸው የትምህርት ጥራት ቀውስ ውስጥ እንዲገባ እያደረገ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር በቲክቫህ…
“ የመምህራን ደመወዝ በዘመቻ በሚባል መልኩ ይቆረጣል ” - ማኀበሩ
“ በተለይ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል ክልሎች የመምህራን ደመወዝ በዘመቻ በሚባል መልኩ ይቆረጣል ” ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ማኅበሩ 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባ በአዳማ ከተማ ከጥቅምት 7 እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ/ም አካሂዶ የነበረ ሲሆን፣ የመምህራን ቅሬታዎች ትምህርት ሚኒስቴር በተገኘት መቅረባቸውን ገልጿል።
መምህራን እየገጠሟቸው ያሉ በርካታ ችግሮች መኖራቸውን የገለጹት የማኀበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አበበ ችግሩ በወቅቱ እንዲፈታ አሳስበዋል።
ማኀበሩ በዝርዝር ምን አለ ?
“ ክልሎችና ዩኒቨርሲቲዎች በተገኙበት የተለያዩ አጀንዳዎች ተነስተዋል። የተነሱት አጀንዳዎችም እንደ ክልል የመልካም አስተዳደር ችግሮች አሉ የሚሉ ናቸው።
በየክልሎች የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አሉ፡፡ ከመልካም አስተዳደር ችግር ደግሞ የጸዱ አካባቢዎች አሉ፡፡ በተለይ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሀረር አካባቢ የከፋ የመልካም አስተዳደር ችግር የለም።
ጦርነቱ በአማራ ክልል መምህራን ተረጋግተው እንዲሰሩ፣ ተማሪዎቹም ተረጋግተው እንዲማሩ እያደረገ አይደለም፡፡ ወደ 3,000 የሚሆኑ ት/ቤቶች ከሥራ ውጪ ናቸው፡፡
በዛው ልክ ደግሞ በእነዚህ ት/ቤቶች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎችና መምህራን ከሥራ ውጪ እንደሆኑ ተገጿል።
እንደ ኦሮሚያ ክልልም ብዙ ቃል የተገቡ ነገሮች ነበሩ ነገር ግን አልተተገበሩም (በተለይም ከመኖሪያ ቤት አንጻር)፤ ይሄ መስተካከል አለበት፡፡ የተሻለ ነበረ ኦሮሚያ አፈጻጸሙ ግን በዚህ ዓመት ብዙ ርቀት አልሄደም።
ከእነዚህ ክልሎች ውጪ ያሉት ደግሞ በተለይ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ፣ ቤንሻንጉል ክልሎች የመምህራን ደመወዝ በዘመቻ በሚባል መልኩ ይቆረጣል።
ይሄ በጣም የከፋ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ ነው የተነሳው።
በአፋር ክልልም ለረዥም ጊዜ የደረጃ እድገት፣ የትምህርት ማሻሻያ ያልተከፈለበት ሁኔታ አለ።
በትግራይ ክልል የ17 ወራት የመምህራን ደመወዝ አልተከፈለም። የአምስት ወሩን ክልሉ እከፍላለሁ ብሎ ነበር እስካሁን አልከፈለም።
የክልሉ መምህራን ማኀበር ጠበቃ ቀጥሮ ክስ መስርቷል። በሕግ ሂደት ላይ ነው ” የሚሉ ቅሬታዎች ተነስተው መፍትሄ እንዲሰጥ መጠየቁን ገልጿል።
ከትምህርት ሚኒስቴር ባለድርሻ አካላት ባሉበት ለተነሳው ቅሬታ ታዲያ ምን የመፍትሄ አቅጣጫ ተቀመጠ ? ለሚለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ጉዳዩን እንዳዳመጠ፣ በቀጣይ ለመፍትሄ እንደሚሰራ መጠቆሙን ማኅበሩ አስረድቷል።
ማኀበሩ በመጨረሻም የተነሱት ቅሬታዎች ምላሽ እንዲያገኙ በአንክሮ ጠይቋል።