TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ነገ ከሚወጣው "በተስፋ ቢሱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ተስፋ ያጡት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች" በሚል ርእስ የአለም አቀፍ ስፖርት ፀሀፊው ፍሬው አስራት ከሰራው ትንታኔ የተወሰደ . . .

" ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ይመጥናሉ ብለን ያመናቸውን ትውልደ ኢትዮጵያን በመዘርዘር እና ለብሄራዊ ቡድኑ እንዲጫወቱ በማግባባት እንዲሁም ስለ እነርሱ ሙሉ መረጃ በማዘጋጀት ለብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኞች ለምርጫ ያለ ምንም ክፍያ እናቅርብ ብለን ከፌዴሬሽኑ አመራሮች ጋር ብንወያይም ምላሻቸው በጣም አስከፊ ነበር" የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ዴቪድ በሻ

በዚህ ትንታኔ ላይ የ Ethio-KickOff መስራች ጋዜጠኛ ማርታ በላይ ፤ የተጫዋቾች ወኪል በመሆን የሚያገለግለው ጢሞቲዎስ ባዬ እንዲሁም የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች እና ወኪል ዴቪድ በሻ እናም ሌሎች በጉዳዩ ላይ የሚመለከታቸውን አካላት ሀሳባቸውን አጋርተውታል ::

#FirewAsrat #TikvahSport

Join👇@tikvahethsport

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
#TikvahSport

አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ሆላንድ ሄንግሎ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር ውድድር በአንደኝነት አሸንፏል።

በሌላ በኩል በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር ሲፋን ሀሰን በፓውላ ራድ ክሊፍ የተያዘውን የአውሮፓ ሪከርድ በመስበር በበላይነት አጠናቃለች።

ኢትዮጵያዊቷ ፀሀይ ገመቹ ውድድሯን በሁለተኝነት ማጠናቀቅ ችላለች።

@tikvahethiopia @tikvahethsport
#TikvahSport

ቲክቫህ ስፖርት እና ዘራፍ ቶርናመንት ከጋስት ኢንተርቴመንት እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር #በጋስትሞል ላይ ያዘጋጁት " #FIFA 22 " ውድድር ምዝገባው ተጀምሯል ።

ውድድሩ ለመጫወት ምቹ በሆነው ጋስት ሞል በPS4 የሚካሄድ ይሆናል። የውድድሩ ተሳታፊዎች በተለያዩ ዙሮች በርካታ ሽልማቶችን ይሸለማሉ።

የውድድሩ የፍፃሜ ተጫዋቾቻችን ውድድራቸውን በኩሪፍቱ ሪዞርት ላይ ያካሂዳሉ።

ለመመዝገብ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት https://zeraftournament.com/ ወይም በቴሌግራም @Zeraf_Tournament ላይ ማግኘት ይችላሉ።

ቻናል :- https://t.iss.one/ZerafTournament
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sport ተጋጣሚውን 9 ለ 0 ያሸነፈው የኢትዮጵያ ክለብ ! ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው በ #CECAFA ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የኢትዮጵያው ንግድ ባንክ ቡድን ተጋጣሚውን ዋሪየርስ ኩዊን በሰፊ የግብ ልዩነት 9 ለ 0 አሸንፏል። መዲና አዎል 4 ግቦችን እንዲሁም ሎዛ አበራ 5 ግቦችን ማስቆጠር ችለዋል ። More : @tikvahethsport
#TikvahSport | በተጋጣሚዎቻቸው ላይ የጎል ናዳ ያወረዱት 2ቱ ኢትዮጵያውያን !

በታንዛንያ ሀገር ፤ ዳሬሰላም ከተማ የ #CECAFA የሴቶች ሻሚዮንስ ሊግ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል።

በዚሁ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ በመሳተፍ ላይ ሲሆን የዚሁ ክለብ ተጫዋቾች የሆኑት ሎዛ አበራ እና መዲና አዎል በታጋጣሚ ቡድኖች ላይ የጎል ናዳ አውርደውባቸዋል።

እስከሁን ባለው ከ3 ክለቦች ጋር በተደረገ ጨዋታ ሎዛ አበራ 9 ጎሎችን እንዲሁም መዲና አዎል 6 ጎሎችን አስቆጥረዋል።

የጎል ናዳው የወረደው በየትኞቹ ክለቦች ላይ ነው ?

👉 ዋሪየርስ ኩዊን በተባለው የእግር ኳስ ክለብ ላይ ሎዛ ብቻዋን 5 ጎል ፤ መዲና 4 ጎል አስቆጥረውባቸዋል።

👉 ፎፊላ በተባለው የእግር ኳስ ክለብ ላይ ደግሞ ሎዛ 3 ጎሎችን መዲና 1 ጎል አስቆጥረዋል።

👉 ኤፒ አር ኪጋሊ በሚባለው ክለብ ላይ ሎዛም መዲናም አንድ አንድ ጎል አስቆጥረዋል (ይሄ ጨዋታ ዛሬ የተካሄደ ነው)

በድምሩ ሁለቱ ተጫዋቾች ብቻ በውድድሩ 15 ጎሎችን አስቆጥረዋል።

ቲክቫህ ስፖርት👇
https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ኢትዮጵያውያን በፀሎት እንዳይለዩን " - ጉዳፍ ፀጋይ

የዓለም የወርቅ እና ብር ሻምፒዮኗ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ዛሬ ምሽት በ10,000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ለሀገራችን የመጀመሪያ ሜዳሊያን ለማስገኘት ከቡድን አጋሮቿ ጋር በመሆን ብርቱ ፉክክር ታደርጋለች።

ከውድድሩ አስቀድሞ ሀሳቧን ያካፈለችው ጉዳፍ ፤ " የራሳችን ጥረት እና ልፋት እንዳለ ሆኖ ሁሉም ነገር የሚያምረው ፈጣሪ ሲጨመርበት ነው ፣ ህዝባችን ሁሌም ከጎናችን ነው አሁንም እንዲሆን እንፈልጋለን ፤ በፀሎት አይለየን " ብላለች።

" የኢትዮጵያ ህዝብ የተለየ ነው መግለፅ ያቅተኛል ፤ በየትኛውም ቦታ የተለየ ክብር ነው የሚሰጠኝ ፣ ከዚህ በላይ መስራት እንዳለብኝ የቤት ስራ ሰጥቶኛል። የህዝቡን ፍቅር ለመግለፅ እቸገራለሁ " ስትል ገልጻለች።

ዛሬ ምሽት 3:55 ላይ በ10,000 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ለተሰንበት ግደይ፣ ጉዳፍ ፀጋይ ፣ እጅጋየሁ ታዬ ፣ ለምለም ሀይሉ ተካፋይ ይሆናሉ።

#TikvahSport

More 👇
https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport