TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ተስፋዎች👆

#ሰውነት ያስተሳሰራቸው፤ #ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች #የተሰባሰቡ፤ ሀገራችንን ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ለማውጣት በየዩኒቨርሲቲው እየተጓዙ የሚገኙት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት #ኑ ኢትዮጵያን #ከጥላቻ አላቀን #ታላቅ እናድርጋት የሚል #ሀገራዊ ጥሪ አቅርበዋል።

ፎቶ: የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት #ለእንግዶቹ ያደረገው #የእራት እና #የምሳ ግብዣ #WKU

Photo: @Dura_pic

ደማችን #አንድ ነው!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech #wku ልዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅትም ተካሂዶ ነበር። ከAMUU, WSU(ትሩ ላይፍ) የተውጣጡት አባላት ያሉበት!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድ የማጠቀለያው ዝግጅት🔝የክብር እንግዶች በተገኙበት #StopHateSpeech #WKU
@tsegabwlde @tikvahethiopia
#WKU እጅግ በጣም እናመሰግናለን፤ ያደረጋቹልን ታሪካዊው የአቀባበል ሁሌም በአባላቶቻችን ዘንድ ሲታወስ ይኖራል። የመጣንበትን አላማ እንዲሰካ ለማድረግ የደከማችሁ ቅን ሰዎች እናመሰግናለን!! መላው የተቋሙን አመራሮች፤ ሰራተኞች እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጠቅላላ #እናመሰግናለን!! የተማሪዎች ህብረቱ በ3 ቀን የእንመጣለን መልዕክት ዝግጅት አድርጎ በትልቅ ክብር ስለተቀበለን እናመሰግናለን!!

#ፍቅር_አሸንፏል!!
የጥላቻ ንግግር ይቁም!!
የጥላቻ ንግግር ሀገር ያፈርሳል!!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ሳምንት🔁 #StopHateSpeech!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምድብ ሶስት!

ወደሰላም አምባሳደር ተቋም #ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ የሚጓዙ የTIKVAH-ETH #የሰላም እና #የፍቅር አምባሳደሮች #ምድብ_3

•አሸናፊ በቀለ
•መዝገቡ ተስፋዬ
•መሀመድ ሚፍታ
•አበበ በላቸው
•አብዱረዛቅ ኑርሰፋ
•አቤል እርቅ ይሁን
•አዳነ ለገሰ
•ናትናኤል ሰለሞን
•ዳዊት ፍቅሩ
•ፍሬው ጌታቸው
•ተምኪን ኑረዲን
•እሱባለው መረጃ
•ቃለአብ ዘበነ
•ደሳለኝ ንዳ
•እስከዳር ታደሰ
•ዮሴፍ ኃይሉ
•አስቻለው ጌቱ
•ይትባረክ አለባቸው
•ዮሃንስ አበራ
•ታዲዮስ ደጉ
•ብርሀኑ አወቀ
•ናትናኤል መርከቡ
•በእምት ሰሎሞን
•ታምራት በሻዳ
•ኑርሁሴን ከማል
•አላዛር ሲሳይ
•ሀናን በድሩ
•ማህሌት ተፈራ
•መቅደስ መሰለ
•ፌቨን ሻውል
•ሜሮን ረዳይ
•ምኞት ወርቁ
•ሰሚራ ሸረፍ
•ሀያት ሳቢር
•ፎዚያ መካ
•ፊሩዛ ሙሀበድ
•ራሄል በላቸው
•ራሄል ሰው መሆን
•ሲትሬላ ሙሀመድ
•ሰሚራ ሸረፋ
•ፈቲያ አሚን
•ሰሚራ ተሸመ
•ሰሚራ ከድር
•ሰዓዳ ሙሳ
•ግዛት ማሞ

√26 ወንድ
√19 ሴት

#WKU #StopHateSpeech
@tsegabwolde @tikvahethiopia
125 የሰላም እና የፍቅር አምባሳደር ወጣቶች ነጩን አርማ ከፍ አድርገው ዛሬ #ሀዋሳ_ዩኒስቨርሲቲ ይገባሉ። #WSU #WKU #AMU #StopHateSpeech

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተጓዙ የሚገኙት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት/የሰላም እና የፍቅር አምባሳደሮች/፦

#WKU

√እሱባለው ኑጉሴ (ሳሪሳዊ)
√አዳነ ለገሰ
√ጃቤዝ ብራሀኑ
√መሀመድ ያሲን
√ማህሌት ተረፈ
√ጀማል ሁሴን
√ኪሩቤል ኪዳኔ
√ፍሬው ጌታቸው
√ያብስራ ለገሰ
√ዳግም ዳንኤል
√ሳምራዊት
√ያብስራ
√ጌታቸው ታያቸው
√ጌታሰው ሙሉዬ
√አቤል ወርቁ
√ኑሩሴን ከማል
√መዝግቡ ተስፋኤ
√ሄኖክ ጰጥሮስ
√ቤተልሄም አሰፋ
√ትግስት መኮንን
√ኪያ
√ኤፍም ስዩም
√ልዕልት ተፈራ
√ሰላም በላይ
√ኬሮድ
√ናትናኤል መርከቡ
√ተምኪን ኑረዲን
√ምረት ዳንኤል
√አብዱረዛቅ ታለገን
√ሶሪ

#WU

√መልካሙ እንደርሪያስ
√ሰሎሞን ወንድሙ
√ደሳለኛ ኦሌ
√አንጮቴ አዲሴ

#WSU

√ጉተማ ለታ
√አቅለሲያ ሲሳይ
√ሙሉጌታ አደሩ
^ቤቴልሔም ቱሉ
√ወንድማገኝ ብርሃኔ
√ቤቴልሔም አዱኛ
√ዳንኤል ተሾመ
√ጊዜው ጌትነት
√ነጻነት ቹቹ
√ጌታሰው ምህረት
√ፍላጎት ጥላሁን
√ዮርዳኖስ ግርማ
√በረከት ጉዲሳ
√ወንድማገኝ
√ትግስት ተስፋዬ
√ቃልኪዳን አክሊሉ
√ዱሬሳ በዳሶ
√ገመቺስ ፈቃዱ
√እዮብ ተስፋዬ
√መሐመድ አህመድ
√ሚኪያስ ሙሉ
√ቢኒያም ይርጋ
√ፍሬዘር ገዛኻኝ
√ብርሃኑ
√በፀሎት
√ዳንኤል ጋምቤሮ
√በረከት ቶማስ

#AMU

√ያቤፅ ደጀኔ
√መልካሙ ማቴዎስ
√ቅድስት ይልማ
√ሀብታሙ ይልማ
√አሳየኝ ወ/ሚካኤል
√የምስራች የቆየ
√ሐይማኖት ሹሜ
√አዱኛ ሶሪ
√ተመስገን ደሞዜ
√ስራነሽ ዘለቀ
√ኤልሻዳይ
√ሸምሱ ረታ
√ሀብታሙ አጌና
√ምስራቅ በዛብህ
√ቃለአብ አየለ
√ማስተዋል ኃ/ኢየሱስ
√ናትናዔል ሲሳይ
√ሐይማኖት እንዳላማው
√ምህረት መውጫ
√ሚፍታህ እንድሪስ
√አሸናፊ ታሪኩ
√ተመስገን ኑሪ
√ኢየሩስ አለሙ
√ዘለዓለም አያና
√አበበ ደባልቄ
√ምስጋናው አላምራው
√ገበየሁ ሀላዩ
√ናትናኤል ደሳለኝ
√ሙሐመድ አብዱልመናን
√ታረቀኝ ጳውሎስ
√ቴዎድሮስ መኮንን
√ጌትነት ለይላ
√ፎዝያ ሰይድ
√ንጉሴ ሮባ
√እሱባለው አድጎ

#HU

√በረከት

#MKU

√አማኑኤል ደመቀ
√መልካም ኣንጋው
√ገዳምብርሃኑ ወ/ገብርኤል
√ትንሳኤ አለማየሁ
√በረከት ተፈራ ዋዶ
√አብሃለይ አረፋይኔ
√ሰዓረ ገ/ዋህድ

ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፦ 5 ተወካዮች
ከሚዛን ቴፒ፦ 5 ተወካዮች

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Imala gaarii nagayaan galaa
መልካም መንገድ - ሠላም ግቡ!!


#JU/Jimma University/

/STOP HATE SPEECH/

√Jaraso Haile
√Daniel Tadesse
√Sinishawu Kedir
√Semira Jemal
√Ayanalem Kasa
√Desta Mohhamed
√Bereket Lera (Beki)
√Mesay Galana (Messi)
√Mohhamed Degesiso
√Mohhamed Baker
√Sultan Ahamed
√Makades zawude
√Lemlem Beyene
√Beruk Marakos
√Yadani Endale
√Tehitina Demisse
√Betelehem Lama
√Mulatu Abate
√Kasahun Tesfaye
√Jabesa Obesa
√Moges Hamaro
√Dese Alamayo
√Wondosen Negese
√Surafel Bedru
√Murutessa Kamal

#AMU

√Bikela Mekonnen
√Aschalw Dechassa
√Tigest Kassu
√Melkamu Matiyas
√Liuel Shimels

#WSU

√Duresa Bedaso
√Gudisa Robe
√Hayleyesus Esubalw
√Womdemenh Asheber
√Daniel Gambero
√Fereweyn Negatu
√Lidya Gezahgn
√Chala Awel

#WKU

√Mahelet Tefera
√Yonatan Abebe
√Ikrem Nuredin
√Hayat Hasen
√Asresash Assefa
√Solomon Hailu

Imala gaarii nagayaan galaa
መልካም መንገድ - ሠላም ግቡ!!


#Haramaya_University

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WKU ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንትነት ያመለከቱ ተወዳዳሪዎች የመጀመሪያ ዙር የውጤት መግለጫ፦

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WKU

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባውን ዘመናዊ የመምህራን መኖሪያ እያስመረቀ ይገኛል።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከ464,000,000 ብር (አራት መቶ ስልሳ አራት ሚሊዮን ብር) በላይ ወጪ በማድረግ ያስገነባው የመምህራን መኖሪያ አፓርታማ በዛሬው ዕለት በመመረቅ ላይ ይገኛል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር በከፊልም ቢሆን ለማቃለልና በተለይም መምህራን በዩኒቨርስቲው አቅራቢያ ሆነው በተረጋጋ ሁኔታ መደበኛ ስራቸውን ለማከናወን እንዲያግዛቸው ታስቦ በዩኒቨርሲቲው አቅራቢያ በጉብሬ ክፍለ ከተማ የተገነባ ነው።

ግንባታው በ1719 ካሬ ላይ ያረፈ ሲሆን አራት ብሎኮች አሉት። ባለ ሁለት መኝታ ያላቸው 72 ቤቶችን፤ ባለ አንድ መኝታ ቤት ያላቸው 120 ቤቶችን እና 60 እስቱዲዮዎች ሲሆኑ በድምሩ 252 አባወራዎችን የሚያስተናግድ የመኖሪያ ክፍሎች ያሉት ነው።

በተጨማሪ ደግሞ ደረጃውን የጠበቀ የኪችን ካቢኔት የተገጠመለት ፤ ነዋሪዎችን የዋይፋይ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የመስመር ዝርጋታ የተደረገለት፤ የራሱ የሆነ ትራንስፎርመር ተገጥሞለት የተሟላ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል ሆኖ የተገነባ ፤የውሃ እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ የራሱ የሆነ ጥልቅ የመጠጥ ጉድጓድ ውሃ የተቆፈረለት ጭምር ነው።

ለህንጻው ነዋሪዎች አገልግሎትን የሚሰጡ 24 ሱቆች (በእያንዳንዱ ብሎክ ላይ 6 ሱቆች) ፤ 4 ካፍቴሪያዎች (በእያንዳንዱ ብሎክ ላይ 1 ሱቅ) ፤ 4 ሱፐር ማርኬት (በየብሎኩ 1 ሱፐርማርኬት)፤ አንድ ፋርማሲ ያለው ሆኖ ለዘመናዊ የአኗኗር ዘዴ አመቺ ሆኖ መገንባቱ ተገልጿል።

#WKU

@tikvahethiopia
#WKU

" አንድ ተመራቂ ተማሪ እና አንድ  መምህር ጉዳት ካስተናገዱ በኋላ ሁኔታዉ በቁጥጥር ስር ውሏል " - የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አመራር

ከሰሞኑ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አንድ ሽጉጥ የታጠቀ ወጣት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ተኩስ በመክፈቱ አንዲት ተመራቂ ወጣት እና አንድ መምህር ተጎድተዋል።

የግቢዉ ተማሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት በወቅቱ የተፈጠረው የተኩስ ድምጽ እና ሁኔታ እጅግ ረብሿቸው ነበር።

ይሁንና " ታጥቆ ወደ ግቢው የገባው አካል በቁጥጥር ስር መዋሉና ሰላም መሆኑ " ተነግሯቸው ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ መደረጉን አስረድተዋል።

ሁኔታውን በተመለከተ አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የዩኒቨርሲቲው ኃላፊ " ጉዳዩ ድንገት በመፈጠሩ ለጥቂት ሰአታት ግርግር ቢፈጥርም በግቢዉ የጸጥታ ሀይል በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል " ብለዋል።

በወቅቱ " የመመረቂያ ጽሁፍን በዲስፕሊን ምክኒያት እንዳያቀርብ የተከለከለ የነርሲንግ ተማሪ  ሽጉጥ ታጥቆ በመምጣት ጉዳት አድርሷል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የመመረቂያ ወረቀቷን ታቀርብ የነበረዉንና ጓደኛዬ የሚላትን ' እኔ ካላቀረብኩ አንችም አታቀርቢም ' በማለት ሽጉጥ ተኩሶ በማቁሰል በዛ የነበሩትን መምህራን አባሯል " ሲሉ አስረድቷል።

ከዚህ በኋላ ሰዎችን ባይጎዳም ደጋግሞ መተኮሱ በግቢው ውስጥ ችግር መፍጠሩን የሚገልጹት ሀላፊዉ ይህም ተማሪዎችን መረበሹን ገልጸዋል።

በዚህ ወቅት የተሰማዉን የተኩስ ድምጽ የሰማዉ የግቢዉ የጸጥታ ሀይል ወጣቱን በፍጥነት በመቆጣጠር ሁለቱን ተጎጅዎች ወደህክምና ሊወስዳቸዉ እንደቻለና ገልጸዋል።

በወቅቱ ከተከሰተዉ ችግር ለመሸሽ መምህራኑ ባደረጉት ጥረት አንዱ በመስኮት ሲዘል ከፍተኛ አደጋ እንደደረሰበትና የሁለት እግሮቹ አጥንቶች ተሰብረዉ ከፍተኛ የአጥንት ህክምና በማስፈለጉ የግቢዉ ማህበረሰብ ገንዘብ እያወጣለት መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለማወቅ ችሏል።

አንድ ጉዳዩን የምታውቅ ተማሪ ፤ " 1 ወር ከ15 ቀን ልጅ በፊት ደብድቧት ሆስፒታል ገብታ ፤  እሱም 2 ዓመት ተቀጥቶ ነበር። ከዛም በፊት መትቷት ያቃል። ባለፈው ደግሞ ዲፌንስ አቀርባለው ብሎ ሲከለከል ሽጉጥ ይዞ መተኮስ ጀመረ ልጅቷን ተኩሶ ስቷቷል ፤ ከዛ ይዞ ደብድቧታል። ጭንቅላቷ ተፈንክቷል። አንድ መምህርም ከፎቅ ዘሎ ተሰብሯል። አንድ ተማሪም ወድቃ ጭንቅላቷ ውስጥ ደም ፈሶ ሰርጀሪ ተሰርቶላታል " ብላለች።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
#WKU

" አሳይመንቱን ቤት ድረስ አምጥተሽ ስጪን " በማለት ተማሪውን ደፍሯል የተባለው የዩኒቨርሲቲ መምህር ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰሞኑን ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ #ሴት ተማሪዎች መልዕክቶችን ተቀብሏል።

ይህም " የሴቶች ጥቃት አሳስቦናል " የሚል ነው።

ተማሪዎቹ የመደፈር እና የጥቃት ወንጀል በመምህር ሳይቀር መፈጸሙን በመግለጽ ስጋታቸውን ገልጻዋል።

በየጊዜው እንዲህ ያለ ነገርም እንሰማለን ነው ያሉት።

ከጠቆሙት አንዱ ጉዳይ በመምህሯ የተደፈረችን ተማሪ የሚመለከት ነው።

በተማሪዎች ስለሚነሳው ጉዳይ ተቋሙ ምን ይላል ? በማለት ጥያቄ አቅርበናል።

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የዩኒቨርሲቲው አመራር የመምህሩ ጉዳይ #ከ2_ወራት_በፊት መከሰቱን እና ከአስገድዶ መድፈር ጋር በተያያዘ በቅርብ የተፈጸመ ጥቃት አለመኖሩን ገልጸዋል።

" ወንጀሉን ከ2 ወራት በፊት እንደፈጸሙ የተጠረጠሩት መምህር በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ ነው " ብለዋል።

ድርጊቱ እንዴት ተፈጸመ ?

በወቅቱ አንድ የሂሳብ መምህር በክፍል ውስጥ ሆነው ከተማሪዎቻቸው አሳይንመንት በመቀበል ላይ ነበሩ። የአንደኛዋን ተማሪያቸውን ወረቀት ግን ሳይቀበሉ ነበር የወጡት።

ይሁንና " #አልቀበልሽም " የተባለችው ተማሪም ምን አድርጌ / ምንስ አጥፍቼ ነው ? ብላ በምትጨነቅበት ሰአት ከክፍሉ ተጠሪ ያገኙትን ስልክ ተጠቅመው የደወሉላት መምህር  " አሳይመንትሽን ቤቴ መጥተሽ ማስረከብ ትችያለሽ " ይሏታል።

ተማሪዋም በተሰጣት አድራሻ ተመርታ ወደተባለችው ቦታ ትሄዳለች። የጠበቃት ግን አሳይመንቱን መቀበል ሳይሆን ሌላ ነበር።

ተማሪዋ እያነባች ጓደኛዋን ይዛ ወደሆስፒታል ካመራች በኃላ በሆስፒታል ህክምና አግኝታለች።

የሆስፒታል ማስረጃዋን ይዛም ወደ ዩኒቨርሲቲዉ ሂዳ አመልክታቸለች።

በወቅቱ ዩኒቨርሲቲው በተማሪዋ አቤቱታና በቀረበዉ የህክምና ማስረጃ  መሰረት ጉዳዩን ወደ #ዲስፕሊን በመዉሰድ በፍጥነት መምህሩን ከስራ ሊያግድ ችሏል።

መምህሩ ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ #ራሱን_ደብቆ እና ስልኩን አጥፍቶ ቆይቷል ተብሏል።

የዩኒቨርስቲው አስተዳደር #የስራ_እግድ ማሳለፉንም ተከትሎ ከተደበቀበት በመዉጣት ሲመለስ ጉዳዩን ከዩኒቨርስቲው በመረከብ ይዞ መምህሩን ሲያፈላልግ የነበረው ፖሊስ #በቁጥጥር_ስር ሊያውለው ችሏል።

አሁን ላይ የምርመራ ሂደቱ አልቆ ፍርዱን እየተጠባበቀ ሲሆን ወደፊት የፍርድ ሂደቱ የሚገለጽ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ከሰሞኑ በዚሁ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አንድ ሽጉጥ የታጠቀ ወጣት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ተኩስ በመክፈቱ አንዲት ተመራቂ ወጣት ተማሪና አንድ መምህር መጉዳቱን መረጃ መለዋወጣችን ይታወሳል👉 https://t.iss.one/tikvahethiopia/88025

@tikvahethiopia