TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🚫STOP HATE SPEECH🚫

#TikvahEthiopia #Facebook #Telegram #Twitter ሀገራችንን እናድን! የጥላቻ ንግግሮች ሀገራችንን ወደአስፈሪ ሁኔታ ውስጥ እየከተታት ይገኛል። ሁላችም ከጥላቻ ንግግሮች ራሳችንን በማራቅ ሀገራዊ ሀላፊነታችንን እንወጣ!

#ከጥላቻ_ንግግሮች_እንቆጠብ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካምነት ይፋፋም...🔝

"ፀግሽ በፈለገ ህይወት ት/ት ቤት ምክትል ር/መር ነኘ እናም በት/ቤታችን የሚማሩ ተማሪዎች #ለተፈናቀሉ ዜጎች የድርሻቸውን በመወጣት #ከጥላቻ_ይልቅ መረዳዳትን ባህል አድርገው ግምቱ ወደ 10000 ብር የሚጠጋ ድጋፍ በማድረጋቸው አመስግንልኘ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ተስፋዎች👆

#ሰውነት ያስተሳሰራቸው፤ #ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች #የተሰባሰቡ፤ ሀገራችንን ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ለማውጣት በየዩኒቨርሲቲው እየተጓዙ የሚገኙት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት #ኑ ኢትዮጵያን #ከጥላቻ አላቀን #ታላቅ እናድርጋት የሚል #ሀገራዊ ጥሪ አቅርበዋል።

ፎቶ: የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት #ለእንግዶቹ ያደረገው #የእራት እና #የምሳ ግብዣ #WKU

Photo: @Dura_pic

ደማችን #አንድ ነው!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ዩንቨርስቲ🔝የሰላም ተምሳሌት እና የሰላም አምባሳደር በሆነው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቅዳሜው ምሽት #የStopHateSpeech የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በስኬት ተጠናቋል። በመድረኩ ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሰላም ፎረም እና የተማሪዎች ህብረት ለእንግዶቻቸው እንኳን ደህና መጣቹ በኃላ ወጣት ተማሪዎች ራሳቸውን #ከጥላቻ_ንግግሮች እንዲቆጥቡ ለሀገሪቱ ተስፋ መሆናቸውን አውቀው ለሰላም ቅድሚያ እንዲሠጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በዕለቱ ተማሪ #ሀና_ሀይሉ "Love Speech Vs Hate Speech" በሚል ልዩ ገልፃ አድርጋለች። የጥላቻን አስከፊነት የተተነተነበት፤ የፍቅርን ሀያልነት የተገለፀበት ነበር ገለፃው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FaceBook

ፌስ ቡክ #ከጥላቻ_ንግግር ፖሊሲው ጋር የሚጣረሱ መልዕክቶችን በቀጥታ በሚያሠራጩ ተጠቃሚዎች ላይ አዲስ የቁጥጥር ህግ ሊያስተዋውቅ ነው። በኒውዚላንድ ክሪስት ቸርች መስጊዶች ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ለተወሰነ ጊዜ ተጠቃሚዎችን ከፌስቡክ ማገድ እንደ አንድ የመፍትሔ ሃሳብ ቀርቧል። በፓሪስ በሚካሄደውና በፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮንና በኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን በሚመራው ጉባዔ ላይም ፅንፈኛና ተንኳሽ የሆኑ ንግግሮችን ለመቀነስ የሚረዱ ሃሳቦች ይቀርቡበታል ተብሏል። በመስጊዶቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በስፋት ከተሠራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል በኋለ ፌስቡክ ትችት አጋጥሞታል። በኒውዚላንድ ክሪስትቸርች ከተማ ሁለት መስኪዶች ላይ በተከፈተ ተኩስ 49 ሰዎች ሲገደሉ ብዙዎች መጎዳታቸው ይታወሳል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech
#ከጥላቻ_ንግግር_እንቆጠብ!!
የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የውይይት መድረክ ከልዩ ልዩ ጥበባዊ ዝግጅቶች ጋር በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ነገ #ቅዳሜ እና #እሁድ በቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አማካኝነት በግቢያችን ይካሄዳል።

#ፕሮግራሞች

#ቅዳሜ

☞ ብዙ ኪ.ሜ አቆራርጠው ለፍቅር እና ለሰላም ለሚመጡት የTIKVAH-ETH
ቤተሰብ አባላት ደማቅ አቀባበል ይደረጋል፣ ጥበባዊ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ።

#እሁድ

√የደም ልገሳ ፕሮግራም
√በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት ስለጥላቻ ንግግር ፅሁፎችን ይቀርባሉ ፤ ልዩ ልዩ
ኪነ ጥበባዊ ስራዎች ይቀርባሉ፡፡
√በግቢያችን የፅዳት ዘመቻ ይካሄዳል

#ዋቸሞ_ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia