TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MekelleUniversity

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ህዳር 06/2012 ዓ/ም የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ከንድያ ገ/ህይወት፣ ወ/ሮ ሊያ ካሳ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ወንድወስን አንዱሃለም የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ አካላት በተገኙበት ተመርቆ መደበኛ ስርጭቱን ጀምሯል።

(ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 - ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

2 ኛው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን መድረክ "የአልሙናይ ተሳትፎ ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ውጤት" በሚል መሪ ቃል ቅዳሜ ታህሳስ 4፣ 2012ዓ.ም በአዲስ አበባ ሃርመኒ ሆቴል ይካሄዳል። በመድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና የክብር እንግዶችን ጨምሮ ከ200 በላይ ታዳሚያን እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekelleUniversity #AddisAbeba

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን የምክክር መድረክ በሀርሞኒ ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል። መድረኩ "የAlmuni ተሳትፎ ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ውጤት" በሚል ርእስ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።ከ200 በላይ የቀድሞ ምሩቃን፣ መምህራን እንዲሁም የአሁን ተማሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

(ኤልያስ መሰረት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዩኒቨርስቲዎችን ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ተጠርጣሪዎች ለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መቐለ ዩኒቨርስቲ አዲሱን የኲሓ መለስ ዜናዊ ቴክኖሎጂ ካምፓስ ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሰቲው የዶርሚተሪ አቀማመጥ የመቀየር ፤ ሰፋፊ ወርክሾፖችን የማዘጋጅት፣ መፀዳጃ እና መታጠቢያ ቤቶችን በበቂ ሁኔታ የማዘጋጀት፣ የምግብ አቅርቦት እና አሰፈላጊ የሆኑ ግብሃቶችን የማሟላት ስራ በማከናዎን ላይ ይገኛል። ዩኒቨርስቲ ተጨማሪ ካምፓሶችን ለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ የማዘገጃጀት ሂደት ላይ ይገኛል።

ምንጭ:- መቐለ ዩኒቨርስቲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

ዛሬ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በመቐለ ከተማ በሚገኙ የበግ ገበያዎች በመገኘት የግንዛቤ መፍጠር ስራ ሰርተዋል።

በቦታዉ ተገኝተው የነበሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሂወት እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አግልግሎት ሃላፊነቱን እየተወጣ ሲሆን አሁንም በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው ምላሽ ግን አጥጋቢ አለመሆኑን ጠቅሰዋል። እንደዚህ አይነት ስራዎችን በቀጣይነት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

አሁንም ድረስ ሰው በባለሙያ ለሚሰጡ ምክሮች ቦታ እንዳልሰጠ ነው። በተፋፈነ ቦታ ሁነው ከሚገበያዩት ውስጥ የፊት መሸፈኛ ማስክ ያደረጉት በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው። አካላዊ መራራቅ የሚባለውም ምንም ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም።

የከተማ አስተዳደሩ ይህን ችግር ለመቅረፍ በከተማው ከ20 በላይ የበግ መገበያያ ቦታዎችን ያዘጋጀ ሲሆን እስካሁን ግን አይደር እና ሽላናት አካባቢ ያሉት ብቻ ናቸው በሰው ተጨናንቀው ያሉት።

በተጨማሪ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ለፋሲካ በዓል ያስተላልፉትን መልዕክት በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ : https://t.co/VyAlYvQ1o1

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዓይደር ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ምርመራ ትላንት በይፋ ጀምሯል።

ምርመራው የትግራይ ክልል የጤና ምርምር ኢንስቲትዩት የሚላክን ሳምፕል ብቻ ስለሚሰራ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ በአካል ወደ ዓይደር መምጣት እንደማይችል ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ ! መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው 3290 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ፤ 1 ደግሞ በሶስተኛ ዲግሪ መሆኑ ታውቋል። ከጠቅላላው ተመራቂዎች መካከል 30% እንዲሁም በጤና መስክ ከተመረቁት መካከል ደግሞ 38% ሴቶች መሆናቸው ከኢፕድ የተገኘው መረጃ ያሳያል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

ዛሬ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመርቋል።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ዶ/ር ሙሉ ነጋ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ፕሮፌሰር ፈትየን ኣባይን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት ተገኝተው ነበር።

የዛሬውን የምርቃት ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎች ከላይ ተያይዘዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

የመቐሌ ዩኒቨርስቲ በተለያየ ምክንያት ወደየ ቀያቸው መሄድ ላልቻሉ ተማሪዎች የሽኝት ኣገልግሎት ለመስጠት ባሶችን ማመቻቸቱን ገልጿል።

በመሆኑም ባሶቹ MoSHE ከ ትራንስፖርት ሚንስተር ጋር በመተባበር ኣስር (10) ባሶችን የሚያቀርብ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት መንገድ ላይ እንደሆኑ እና እሁድ ገብተው እንደሚያድሩ ማወቅ ተችሏል።

አገልግሎቱ የሚሰጣቸው ተማሪዎች :-

1. መደረሻቸውን ደቡባዊ ትግራይ የሆኑ፤
2. ከክልል ውጪ ላሉት ተማሪዎችን ደግሞ እስከ አዲስ አበባ ለሆኑ፤
3. የትግራይ ተማሪዎች ሆነው ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የሚሄዱ ካሉ፤

በዚህ መሰረት ያልተመዛገቡ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የተማሪ ህብረት ቢሮዎች እንዲመዘገቡ መልዕክት ተላልፏል።

ማሳሰቢያ:-

- ባሶቹ ልክ #ሰኞ ጠዋት 12፡00 ሰዓት ከየ #ጊቢው እንደሚነሱ አውቃችሁ ተማሪዎች አስፈላጊዉን የሆነውን ዝግጅት ሁሉ እንድታደረጉ፤

- እንዲሁም ጊቢው ውስጥ ላሉ ተመራቂ ተማሪዎች ጓደኛ እና ወላጅ የሆናችሁ ይህን ተገንዝባችው ተማሪዎችን እንድታሳውቁ ሲል የመቐሌ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ገልጾልናል።

Via Abrhaley Arefaine - ETH/HI/EDU/IN/SU V/president and Mekelle University SU President.

@tikvahethmagazine
#MekelleUniversity

ዛሬ ከሰዓት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በወቅታዊ የተማሪዎች ጉዳይ መግለጫ አውጥቷል።

ይህ መግለጫ በዩኒቨርሲቲው ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ በኩል ነው የተሰራጨው።

ዩኒቨርሲቲው ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ፣ መቐለ እና አዲስ አበባ ከሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤቶች እና "ከትግራይ ክልል መንግስት" ጋር በመነጋገር 4 ሺህ 896 ከትግራይ ክልል ውጭ የመጡ ተማሪዎችን በአብዓላ (አፋር ክልል) በኩል እሁድ ሐምሌ11/2013 ዓ.ም ለመሸኘት ዝግጅት አድርጎ መንቀሳቀሱን ገልጿል።

ይህን እንቅስቃሴ ሲያደርግም ምንም አይነት ገንዘብ ማንቀሳቀስ በማይችልበት፣ ስልክም ሆነ ሌላ ምንም የግንኙነት መንገድ በሌለበት እና በከተማው ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ባለበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነበር ብሏል።

እሁድ ጥዋት ተማሪዎችን የያዙ የመጀመሪያ 10 አውቶብሶች አባዓላ ከደረሱ በኋላ የአፋር ክልል ልዩ ኃይል ወደኋላ እንዲመለሱ ትዕዛዝ እንዳስተላለፉ፤ ተማሪዎቹን አጅበው የሄዱት የተባበሩት መንግስታት ወኪሎችም ሁኔታውን ለማስረዳት ቢሞክሩም እንዳልተሳካ አሳውቋል።

አብዓላ ድረስ ተማሪዎቹን ርክክብ ይፈፅማሉ የተባሉ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተወካይም በሰዓቱ ስልክ ሲደወልላቸው "አሁን ሰመራ ነው የምገኘው" የሚል ምላሽ እንደሰጡ እና ተማሪዎቹን ተቀብለው ወደመሃል ሀገር የሚያጓጉዙት አውቶብሶችም በቦታው እንደሌሉ ተወካዩ ማሳወቃቸውን ዩኒቨርሲቲው በመግለጫው ጠቅሷል።

በዚህ ምክንያት ጉዞው አጅበው የተንቀሳቀሱ የድርጅቱ ሰዎች ባላሰቡት መልኩ አውቶብሶቹ እንዲመለሱ እና መርሃግብሩ እንዲሰረዝ ተደርጓል ሲል አሳውቋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Mekelle-University-07-21

@tikvahethiopia
#MekelleUniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ሀገር ሰራተኞቹን እየሸኘ ነው።

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከላፈው እሁድ ዕለት አንስቶ ከትግራይ ክልል ውጭ የመጡ ከ4,800 በላይ ተማሪዎችን በአፋር አድርጎ ወደቤተሰቦቻቸው እየሸኘ ነው ፤ ዩኒቨርሲቲው ከተማሪዎች በተጨማሪም የውጭ ሀገር ዜጋ ሰራተኞቹንም እየሸኛቸው ይገኛል።

ዩኒቨርስቲው ከሃምሌ 20 ቀን 2013 በኃላ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎቹን የሚቀልብበት እና የሚያስተዳድርበት በጀት እንደሌለው አሳውቆ ነበር።

በሌላ በኩል የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የሆኑ ከ7 ሺህ 500 በላይ ዜጎች እስካሁ ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የዩኒቨርሲቲው የባንክ አካውንት በመታገዱ ያለፈው በጀት ዓመት የሰኔ ወር እና የአዲሱ በጀት ዓመት የሃምሌ ወር በጀት ባለመለቀቁ ፣ በትግራይ ክልል አጠቃላይ ባንክ ባለመኖሩም ሰራተኞቹ ከሰኔ ወር ጀምሮ ደሞዝ አላገኙም።

የዩኒቨርሲቲው ኮርፖሬት #ለጀርመን_ድምፅ በሰጠው ቃል መሰረት ከ7,500 በላይ ሰራተኞቹ መካከል ከ5,500 በላይ ሰራተኞች የሰኔ ወር ደሞዝ ያላገኙ ናቸው።

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ደሞዝ ስላልተከፈላቸው እራሳቸውን ጨምሮ በነሱ ስር ያለው ቤተሰብም ጭምር ችግር ላይ መሆኑን በኮርፖሬት ኮሚኒኬሽኑ በኩል ገልጿል።

@tikvahethiopia
#MekelleUniversity

ትግራይ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ቀደመው የመማር ማስተማር ስራቸው ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

ከነዚህም ውስጥ የኣክሱምና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው መማር ያልቻሉ ተማሪዎች በአጭር ቀናት ውስጥ በስልክ እየደወሉ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለማስታወሻ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/77964

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ በተመሳሳይ ለሁሉም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ላልተመደቡ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጥሪ አቅርቧል።

ዩኒቨርስቲው በጦርነቱ ምክንያት ትምህርት ያቋረጡ የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች ቀጥሎ የተቀመጡትን መረጃዎች ከሚያዝያ 16-20/2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ሰዓታት ብቻ ከታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመጠቀም መረጃዎች እንዲያቀብሉ ጠይቋል።

ተፈላጊ መረጃዎቹ ምንድናቸው ?

👉 ሙሉ ስም
👉 የመታወቅያ ቁጥር
👉 ትምህርት ክፍል
👉 የስንተኛ ኣመት ተማሪ መሆንዎ

እነዚህን መረጃዎች የመላኪያ ስልክ ቁጥሮች ፦

1. EiTM - 0984026089 / 0984026059
2. MIT - 0984026727
3. CHS - 0984023986
4. CVS - 0984024072
5. CLG - 0984023987
6. CSSL - 0984023985
7. CBE - 0984024069
8. IPHC - 0984025512
9. CDAaNR - 0984025593
10. CNCS - 0984025582
11. Other Universities - 0984025589

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፅሁፍ መልእክቱን ሲልኩ #በእንግሊዘኛ እንዲልኩ አሳስቧል።

ዩኒቨርሲቲው በሌሎች የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩና በጦርነቱ ምክንያት ያቋረጡ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ከላት የተጠየቁትን መረጃዎች ፤ከዛ በተጨማሪ ሲማሩበት የነበረውን የዩኒቨርሲቲ ስም በማከል መረጃ እንዲያሳውቁ ጥሪውን አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፥ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎቹን በቅርብ ጊዜ እንደሚጠራ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MekelleUniversity

" ዛሬ ሰላም ስለሆነ ወደምትወዱት ዩኒቨርሲቲያችሁ ተመልሳችኃል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ግዙፍ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ የሆነው መቐለ ዩኒቨርሲቲ ትላንት ለተማሪዎቹ ይፋዊ የአቀባበል መርሀ ግብር አካሂዷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ከትምህርታቸው ርቀው የቆዩ ተማሪዎች፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣ የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኣል ክፍሌ ፤ በርካታ ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው መምህራን በሌለ ግብዓት እና መሰረተ ልማት ዝግጅት አድረግው ተማሪዎችን በመቀበላቸው አድንቀዋል።

" ከትምህርት የተለያችሁበት ወቅት ፈታኝ እንደነበር እናውቃለን " ያሉት ዶ/ር ሳሙኤል " ዛሬ ሰላም ስለሆነ ወደምትወዱት ዩኒቨርሲቲያችሁ ተመልሳችኃል " ብለዋል።

" ወደፊት መልሰን ሰላምን እንዳናጣ እናተ አለኝታ እንድትሆኑን እንፈልጋለን፣ ሀገራችን በሰላም እንድትቆይ ልማቷም እንዲሰፋ ፤ ከድህነት እንድትወጣ ፤ ችግርም ካለ ቁጭ ብሎ የሚነጋገር ትውልድ ከእናተ ጀምረን ማግኘት እንሻለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" የሰላም መታጣት ባዶ የሆኑ ቄዬዎችን ሰፈሮችን ፤ የፈረሱ መሰረተ ልማቶችን እንጂ የተሻለ ሀገር አስረክቦ አያውቅም " ያሉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው " ወደፊት በሚኖራችሁ የህይወት ምዕራፍ የኢትዮጵያ ኩሩ ልጆች ሆናችሁ ኢትዮጵያን ስታገለግሉ ለንግግር እና ሀሳብ ቦታ እንድትሰጡ ፣ ምትማሩት ትምህርት እንዲቀይራችሁ ፣ ሃሳብን ንግግርን እንድታስቀድሙ፣ ከጦርነት ሰላምን እንድታስቀድሙ አደራ እላለሁ " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የመቐለ ከተማ ከንቲባ አማካሪ አቶ ነጋሽ ኣርዓያ ትምህርት ሚኒስቴር የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

" እዚህ ያሉት ተማሪዎች የተወሰኑ ተማሪዎች ናቸው ፣ የራያ ተማሪዎች አልመጡም፣ የወልቃይት ተማሪዎች ተከዜን ተሻግረው እዚህ መድረስ አልቻሉም ፤ የኢሮብ፣ ባድመ ተማሪዎች ታግተዋል፤ በጣም የተወሰኑ ተማሪዎችን ይዘን ነው እየቀጠልን ያለነው " ብለዋል።

" የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባልሆነበት ጊዜ ትምህርት መቀጠል አስፈላጊ ቢሆንም ከፊል ነው ፤ ስለዚህ የትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች ባላቸው ኃላፊነት የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበርና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አደራ እላለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

ጦርነት #ክፉኛ_ያወደማትን ትግራይን መልሶ በመገንባት ሂደት የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ተማሪዎች ድርሻ ትልቅ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
#MekelleUniversity

የመቐለ ዩኒቨርስቲ በ29ኛ ዙር ከ2000 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ። ከተመራቂ ተማሪዎች 40 በመቶ ሴቶች ናቸው።

ዩኒቨርስቲው ከተማሪዎች ምረቃ ጎን ለጎን 29ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉም አክብረዋል። 

በምረቓው ስነ-ሰርአት የዩኒቨርስቲው ፕረዚደንት ተወካይ ዶ/ር ዓብደልቃድር ከድር  ንግግር አድርገው ነበር።

ባለፉት 3 አመታት በትግራይ በተካሄደው ጦርነት የደረሰው ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት እጅግ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አስታውሰዋል።

ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በተገኘው አንፃራዊ እርጋታ ዪኒቨስቲው ተስተጓጉሎ የነበረውን የመማር ማስተማር ስራ ፈጥኖ መጀመሩን ገልጸዋል።

የ17 ወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው የነገ ተስፋ አንግበው ወደ ስራ በመመለስ ተማሪዎችን ለዛሬ ምረቃ ላበቁ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት ምስጋና አቅርበዋል።

ዩኒቨርስቲው የድህረ ጦርነት እቅድ በማዘጋጀት ፤ ከፌደራልና በአገሪቱ ክልሎች እንዲሁም በውጭ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲ በመነጋገርና በመፃፃፍ ያለፉት 3 የጦርነት አመታት የሚያካክስ ስራ ለመስራት በከፍተኛ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

ዩቨርሲቲው በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን በመረዳት የፌደራል መንግስት የመደበለት አነስተኛ በጀትና የሰራተኞች ውዙፍ ደመወዝ በአፋጣኝ በመመለስ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ ስራውና ተልእኮው እንዲመለስ እንዲያደርግ አደራ ብለዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር  የማህበራዊ ዘርፍ  ክላስተር ሰክሬተሰሪያት ሃላፊና የመቐለ የኒቨርስቲ ቦርድ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት በበኩላቸው ፤ መቐለ ዩንቨርስቲ በጦርነቱ ምክንያት የደረሰበትን ጉዳት ተቋቆቁሞና ወደ ስራ ተመልሶ በአጭር ጊዜ ይህን የመሰለ ድንቅ የምረቃ ስነ-ሰርአት ማዘጋጀቱ ነገ ለመድረስ ያቀደውን እንደሚያሳካ እንደ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል።

ይህንን የሆነው ለሰላም በተከፈለው እጅግ ወድ ዋጋ በመሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች ሆኑ ሌላው የማህበረሰብ ክፍል የተጀመረው ሰላም ስር እንዲሰድ በተሰማሩበት ሁሉ ሰላምና ልማት መስበክ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ዩኒቨርስቲው በ29 አመታት ጉዞው የዛሬ ጨምሮ ከ100 ሺህ በላይ ተማሪዎች ማስመረቁ ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያስረዳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።                              
 
@tikvahethiopia