TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MekelleUniversity

" ዛሬ ሰላም ስለሆነ ወደምትወዱት ዩኒቨርሲቲያችሁ ተመልሳችኃል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ግዙፍ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ የሆነው መቐለ ዩኒቨርሲቲ ትላንት ለተማሪዎቹ ይፋዊ የአቀባበል መርሀ ግብር አካሂዷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ከትምህርታቸው ርቀው የቆዩ ተማሪዎች፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣ የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኣል ክፍሌ ፤ በርካታ ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው መምህራን በሌለ ግብዓት እና መሰረተ ልማት ዝግጅት አድረግው ተማሪዎችን በመቀበላቸው አድንቀዋል።

" ከትምህርት የተለያችሁበት ወቅት ፈታኝ እንደነበር እናውቃለን " ያሉት ዶ/ር ሳሙኤል " ዛሬ ሰላም ስለሆነ ወደምትወዱት ዩኒቨርሲቲያችሁ ተመልሳችኃል " ብለዋል።

" ወደፊት መልሰን ሰላምን እንዳናጣ እናተ አለኝታ እንድትሆኑን እንፈልጋለን፣ ሀገራችን በሰላም እንድትቆይ ልማቷም እንዲሰፋ ፤ ከድህነት እንድትወጣ ፤ ችግርም ካለ ቁጭ ብሎ የሚነጋገር ትውልድ ከእናተ ጀምረን ማግኘት እንሻለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" የሰላም መታጣት ባዶ የሆኑ ቄዬዎችን ሰፈሮችን ፤ የፈረሱ መሰረተ ልማቶችን እንጂ የተሻለ ሀገር አስረክቦ አያውቅም " ያሉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው " ወደፊት በሚኖራችሁ የህይወት ምዕራፍ የኢትዮጵያ ኩሩ ልጆች ሆናችሁ ኢትዮጵያን ስታገለግሉ ለንግግር እና ሀሳብ ቦታ እንድትሰጡ ፣ ምትማሩት ትምህርት እንዲቀይራችሁ ፣ ሃሳብን ንግግርን እንድታስቀድሙ፣ ከጦርነት ሰላምን እንድታስቀድሙ አደራ እላለሁ " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የመቐለ ከተማ ከንቲባ አማካሪ አቶ ነጋሽ ኣርዓያ ትምህርት ሚኒስቴር የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

" እዚህ ያሉት ተማሪዎች የተወሰኑ ተማሪዎች ናቸው ፣ የራያ ተማሪዎች አልመጡም፣ የወልቃይት ተማሪዎች ተከዜን ተሻግረው እዚህ መድረስ አልቻሉም ፤ የኢሮብ፣ ባድመ ተማሪዎች ታግተዋል፤ በጣም የተወሰኑ ተማሪዎችን ይዘን ነው እየቀጠልን ያለነው " ብለዋል።

" የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባልሆነበት ጊዜ ትምህርት መቀጠል አስፈላጊ ቢሆንም ከፊል ነው ፤ ስለዚህ የትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች ባላቸው ኃላፊነት የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበርና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አደራ እላለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

ጦርነት #ክፉኛ_ያወደማትን ትግራይን መልሶ በመገንባት ሂደት የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ተማሪዎች ድርሻ ትልቅ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia