TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ለኢትዮጵያዉያን ማረጋገጥ የምፈልገው፤ የኢትዮጵያ አንድ አካል፤ የአንድ ዛፍ አንድ ቅጠል አይደለም! እንደው ዝም ብሎ የሚረግፍ ሀገር አይደለም፡፡ እኛ ስለፈለግን የምንጠብቀው፤ ሰላልፈለግን የሚፈርስ ሀገር አይደለም፡፡ እንደው በዋዛ እንበተናለን ብሎ መጠበቅ ከንቱ ህልም ነው፡፡ #ጥላቻ እና #ክፉ ስራ ከሚሰሩ ሰዎች ኢትዮጵያን በመጠበቅ ሀገራችንን ማስፋት፣ ማሳደግ የሁሉም ዜጎች ሃላፊነት ነው፡፡"

◾️ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ◾️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጥር 1 እስከ ጥር 21...

የምንሰራቸው ስራዎች፦

1. በየዕለቱ ሰላምን ፍቅርን እና አድነትን የሚመለከቱ በቻናላችን የሚተላለፉ መልዕክቶችን ሁላችንም በፌስቡክ ገፃችን ላይ መለጠፍ።

2. ስለሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት የሚገልፁ መልዕክቶችን ለወዳጆቻችሁ መላክ።

3. #ጥላቻ እና #ዘረኝነትን የሚሰብኩ የፌስቡክ ጓደኞችን #ብሎክ ማድረግ።

4. የተለያዩ የሀሰተኛ መረጃዎች የሚሰራጩባቸውን የፌስቡክ ገፆች አለመከተል።

5. ስድብ፣ ሰዎችን ማንቋሸሽ፣ ብሄር ተኮር ጥላቻዎችን የምትሰሙባቸውን ሚዲያዎች ማግለል።

የቻናላችን አባላት በሚገኙበት ቦታ ሁሉ ከጥር 1 እስከ ጥር 21 የሰላም፣ የፍቅር እና አንድነት ሳምንታት ታውጇል!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech

ደካማ አመራሮች...

"የኢትዮጵያ ህዝብ እርስ በእርሱ እንዳይተማመን ያደረጉት ደካማ አመራሮች ነበሩ። አንዱ ሌላውን #እንዲገድል ጎራዴ በመኪና ተጭኖ እንዲጓዝ ሲያደርጉ የነበሩት አመራሮች ናቸው። ... በሙሉ ሲሰበክ የነበረው #ጥላቻ፤ አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ ነው። አማራው ኦሮሞው ላይ፤ አማራው ትግሬው ላይ እንዲነሳ፤ ወላይታ ሲዳማ ላይ፤ ሲዳማ ወላይታ ላይ እንዲነሳ ሲሰራ ከርሟል ይሄ ድምር ውጤት ደግሞ #የመንግስት ነው።" አዲሱ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር #ታከለ_ታደሰ በTIKVAH-ETH የStopHateSpeech 3ኛው መድረክ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስለ #ጥላቻ

ጥላቻ ክፉ ደዌ ነው። የአስተሳሰብ ሚዛንህን ያዛባዋል። ሁሌም ግራና ቀኙን ከማየት ይልቅ በአንድ አቅጣጫ እንድትተም ያስገድድሃል። ጥላቻ የምክንያታዊነት ባላንጣ የስሜታዊነት ደግሞ የቅርብ አጋር ነው። ትናንት ሸጋ ያልከውን ዛሬ አፈር ከድሜ እንድታስገባው፤ ዛሬ ቀሽም ያልከውን ደግሞ ነገ ከነገ ወዲያ እንድታሞካሸው ያደርግሃል። ነጩን ጥቁር፣ ጥቁሩን ደግሞ ነጭ አድርጎ ያሳይሃል። ይህን ክፉ አባዜ በግዜ ወግድ ካላልከው ቤቱን እላይህ ላይ ሰርቶ ተደላድሎ ይኖራል። ጥላቻን ፊት ከሰጠከው የልብ ልብ ተሰምቶት እላይህ ላይ ወጥቶ ይጋልብብሃል። እንደ ኮሶ ተጣብቶህ እድሜ ልክህን የእኩይ ተግባሩ ተጋሪ ያደርግሃል።

“ሳይኮሎጂ ቱዴይ” ስለ ጥላቻ በአንድ መጣጥፉ ከጠቀሰው ጥቂት በመቀንጨብ ይህችን አጭር ሃሳቤን ልቋጭ፦

“Hate masks personal insecurities. Not all insecure people are haters, but all haters are insecure people…Haters cannot stop hating without exposing their personal insecurities. Haters can only stop hating when they face their insecurities.”

የሃሳብ ብዝሃነት፣ የሰለጠነ፣ ከጥላቻና ከመዘላለፍ የፀዳ ውይይት ለዘላለም ይኑር!!!

Via Sileshi Yilma Reta(SYR)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"#ጥላቻ መሃይምነት ነው..." ዶክተር ፀደይ(መቐለ ዩኒቨርሲቲ) ከተናገሩት የተወሰደ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦

#ጥላቻ_በሽታ_ነው!

"...የአለሙ ሰላምም ይቅር፤ የአገሩም አንድነት ይቆይ፤ ሰው ለገዛ ሰላሙ ካሰበ ጥላቻን ማስወገድ ግድ ይለዋል፤ አሲድ በአንድ እቃ ውስጥ ብዙ ሲቆይ መዝምዞ የሚጨርሰው የተቀመጠበትን እቃ ነው፤ ጥላቻም እንደዚሁ፤ የተቀመጠበትን ልብ ገዝግዞ ይጨርሳል እንጂ፤ የምንጠላው ሰውማ ምን ይሆናል? የሚጠላ ልብ ፈጽሞ ደስታን ሊያስተናግድ አይቻለውም፤ ምናልባት ለገዛ እራሳችን ሰላም ስንል ፍቅርን ብንለምድ ይበጀናል እንጂ፤ አገርማ የሰው ድምር ብቻ እኮ ናት። ጥላቻ ሰው መግደሉ አይቀርም፤ ቀድሞ የሚሞተው ግን የጠላው እንጂ የተጠላው አይደለም።"

Via ሚስጥረ አደራው

#ሼር #share

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥላቻ_ቦታ_የለውም!

#ዶናልድ_ትራምፕ በአሜሪካ የደረሰውን የጅምላ ግድያ አወገዙ።/የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ጥላቻ ቦታ የለውም ሲሉ ነው ያወገዙት፡፡ በአሜሪካ በቴክሳስና ሃዋይ በደረሰ ጥቃት ሃያ ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል፡፡ በቴክሳስ በገበያ ማእከል በተከፈተ የተኩስ እሩምታ ቢያንስ ሃያ ሰዎች ሲሞቱ በሃዋይ ዳዮታን ደግሞ አንድ ግለሰብ እህቱን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች መግደሉ ይታወቃል፡፡ ዶናልድ ትራምፕ በሁለቱ የአገሪቱ ግዛቶች የተከሰተው ጅምላ ጭፍጨፋ በጣም እንዳሳዘናቸው ተናግረው አሜሪካ ለእንደዚህ አይነት ጥላቻ ቦታ የላትም ሲሉ አውግዘውታል፡፡ ከዚህ በኋላ አሜሪካ እንደዚህ አይነት ጥቃቶችን ለመከላከል ጠንካራ ስራዎች መስራት ይገባታል ሲሉ ዶናልድ ትራምፕ አስታውቀዋል፡፡

ትራምፕ ይህን ይበሉ እንጂ ለሟቾቹ ምክንያት ናቸው እየተባሉ በአሜሪካውያን እየተወቀሱ ይገኛሉ፡፡ የዶናልድ ትራምፕ ጸረ ስደተኛ ፖሊሲያቸው እንዲሁም የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን መቃወማቸው ለችግሩ ምክንያት እንደሆነ በመጥቀስ፡፡ በቴክሳሱ ጅምላ ግድያ ተጠርጣሪ የሆነው የ21 አመት ወጣት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በሃዋይ እህቱን ጨምሮ ሌሎችን ለሞት የዳረገው ከፖሊስ ጋር ሲታኮስ መገደሉ ታውቋል፡፡ በጥቃቱ ከሟቾቹ በተጨማሪ በርካቶች መቁሰላቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

Via #bbc/ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያውያኑ ከከፋፋይ ሀሳቦች ይልቅ በአንድነት ላይ እንዲያተኩሩ ተጠየቁ!

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ #በዴንቨር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ትናንት አወያይተዋል። በውይይቱም በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በመተባበር ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ አምባሳደሩ ጠይቀዋል።

#ጥላቻ እና #ከፋፋይ ሀሳቦችን በመተው ወደ አንድነትና የሚያስማሙ ሀሳቦች ላይ እንዲያተኩሩም ነው መልዕክት የተላለፈው። ለዚህም በአንድነት መሥራት እንደሚገባቸው አምባሳደር ፍፁም ጠይቀዋል። #በዴንቨር የሚኖሩ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላትም ኢትዮጵያዊነትን መሠረት ያደረገ ውይይት መዘጋጀቱ ተገቢ መሆኑን መናገራቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያሳያል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሩዋንዳው #ጄኖሳይድ ወቅት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምን አደረገ ? ከ800 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ባለቁበት የሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ወቅት የዓለም መሪዎች ምንም እንኳን ስለ ዘር ጭፍጨፋው (ጄኖሳይድ) ቢያውቁም ጣልቃ አልገቡም ነበር። ለረጅም ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ' ጄኖሳይድ ' የሚለውን ቃል ከመጠቀም ተቆጥቦ ነበር ፤ ይህም #በአሜሪካ ጫና እንደሆነ ይነገራል። አሜሪካም…
ሚዲያ የሩዋንዳውን የዘር ጭፍጨፋ (ጄኖሳይድ) እንዴት አቀጣጠለ ?

በ100 ቀናት ከ800,000 እስከ 1,000,000 ቱትሲዎችና ለዘብተኛ የሚባሉ ሁቱዎች ባለቁበት የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ/ጄኖሳይድ ሚዲያዎች ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው።

እንዴት ?

- ራዲዮ-ቴሌቭዥን ሊብሬስ ዴስ ሚልስ ኮሊንስ (RTML) እንዲሁም መንግታዊው ' ሬድዮ ሩዋንዳ ' በቱትሲዎች ላይ በመላ ሀገሪቱ ጥላቻ እንዲፈጠርና የሩዋንዳ ጄኖሳይድ እንዲፈፀም ዋና አቀጣጣይ ነበሩ።

- RTML ሚዲያ በወቅቱ በብዙ ወጣቶች ዘንድ ተደማጭነት የነበረው ነው። ጣቢያው በወጣቶች ዘንድ እጅግ የሚወደዱ ሙዚቃዎችን እያስተላለፈ #በመሃል ያቋርጠውና ቱትሲዎችን በመጥቀስ " እነዚያ ሰዎች እጅግ ቆሻሻ ቡድን ናቸው " የሚሉ አዋራጅና ቀስቃሽ መልዕክቶችን ያስተላልፋል። በስርጭቶቹ ውስጥ "#በረሮዎች" እና "#እባቦች" የሚሉ ቃላት በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ ያውላል።

- RTML ሚያዚያ 6 /1994 ፕሬዜዳንት ጁቬናል ሃብያሪማና የነበሩበት አውሮፕላን ተመቶ ሲወድቅ በቅድሚያ ድርጊቱን የፈፀመው RPF ነው ብሎ የፈረጀ እና ንፁሃንን ለጭፍጨፋ ያመቻቸ ሚዲያ ነው።

- በጭፍጨፋው ወቅት ጨፍጫፊዎቹ በአንድ እጃቸው ሬድዮ በአንድ እጃቸው ደግሞ #ቆንጨራ ይዘው ነበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩት። በዚህም ወቅት RTML እና ሬድዮ ሩዋንዳ ቱትሲዎች እና እነሱን የሚሸሽጉ ሁቱዎች እንዲገደሉ ያሉበትን አድራሻ ጭምር ሲገልጹ ነበር።

- ሚዲያዎቹ ጎረቤት በጎረቤቱ ላይ እንዲነሳ እና ቱትሲ የሚባሉትን በጠቅላላ እንዲያጠፏቸው ሲሰብኩ ነበር። በዚህም ብዙዎቹ ሁቱዎች የገዛ ጎረቤታቸውን አንዳንዶቹ ከቱትሲ ጋር የተዛመዱ #ዘመዶቻቸውን ጭምር ጨፍጭፈዋል።

- ሚዲያዎቹ የተለያዩ አነሳሽ ቃላቶች በመጠቀም ቱትሲዎች #እንዲጠሉ#እንዲገደሉ ሰዎችን ሲያበረታቱ ነበር። ትንንሽ ልጆች ፣ ታዳጊዎች ሳይቀሩ በራሳቸው ወገን #ጥላቻ እንዲሞሉ አድርገዋል።

- የሁቱ ሚዲያዎች በቀደመው ጊዜ #ቱትሲዎች ሀገሪቱ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ይዘው በነበረበት ወቅት " በደል ፈፅመዋል " በማለትና " የሀገሪቱ ችግሮች እነሱናቸው እስከመጨረሻ ካልጠፉ በቀር ምንም መፍትሄ የለም " በማለት ሁቱዎችን ይቀሰቅሱ ነበር።

በነገራችን ላይ ከጭፍጨፋው ጅማሮ #በፊትም የሀገሪቱ መንግሥት ሚዲያዎችን በመጠቀም ሰፊ የሆነ የጥላቻ ፕሮፖጋዳንዳ ሲሰራ ቆይቷል።

በተለይ ቱትሲዎችን ከRPF ኃይል ጋር በማገናኘት ሁቱዎች ውስጣቸው በከፍተኛ ጥላቻ ታውሮ የገዛ ወገናቸውን እንዲጨፈጭፉ ሰርቷል።

አጠቃላይ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የታየ እጅግ  አስከፊው የዘር ጭፍጨፋ የአንድ ሌሊት ውጤት አልነበረም፤ በሂደት የመጣ እንጂ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Rwandan genocide
Apr 7, 1994 – Jul 15, 1994

@tikvahethiopia