TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሳይንስ እና ቴክኖ. ዩኒቨርሲቲ⬇️

አዳማና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ሊሰጥ ነው።

በ2011 #የአዳማና #የአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ፈተና ለ3ኛ ጊዜ ‘#በቀጥታ’ በበይነ መረብ ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል።

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስር የሚገኙት የአዳማና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች ለ2011 የትምህርት ዘመን የመሰናዶ ትምህርት ጨርሰው #ከፍተኛ ውጤት ያመጡትና ለፈተና ከቀረቡት 4 ሺህ 700 ተማሪዎች መካከል በፈተና በማወዳደር 3ሺህ ተማሪዎች ሊቀበል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፈተናው #ረቡዕ ነሃሴ 30፣ 2010 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ እስከ 11፡00 ድረስ በተለያዩ ክልሎች ባሉ 37 ዩኒቨርስቲዎች በቀጥታ በበይነ መረብ የሚሰጥ ሲሆን፥ የመግቢያ ውጤቱ ለታዳጊ ክልሎች፣ ለሴቶችና አካል ጉዳተኞች ዝቅ እንዲል ተደርጓል ተብሏል፡፡

ፈተናው ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ሂሳብና ኢንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶቸን የሚያካትት ሲሆን፥ ዝቅተኛው የማለፊያ ውጤት ከ50 በላይ ሁኗል ተብሏል፡፡

ፈተናው በበይነ መረብ ከአንድ ማዕከል የሚተላለፍ ሲሆን፥ የወረቀት ብክነትንና የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደረግ ነው የተገለጸው፡፡

ታላላቅ ድርጅቶች ብዛት ያለው የሰው ሀይል ለመቅጠር በፈተና ማወዳደር በሚፈልጉበት ጊዜ ይህንን ስርዓት በመጠቀም ፈትነው ለቃለመጠይቅ ብቻ የሚፈልጉትን ሰው በመጥራት መቅጠር እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም ይህንን የፈተና ስርዓት መጠቀም ለሚፈልግ ማንኛውንም አካል ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አርበኞች ግንቦት 7⬇️

የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ከመስከረም 5/2011 ጀምሮ #መቀሌ#አዳማና #አዲስ አበባን ጨምሮ በ32 ከተማዎች ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚያካሂዱ ተገለጸ፡፡

ከአቀባበል ኮሚቴ በተገኘው መረጃ እሁድ ጳጉሜ 4/2010 ብርሀኑ ነጋን (ፕ/ር) ጨምሮ አመራሮቹ ኢትዮጵያ እንደገቡ በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሕዝቡ ንግግር ያደርጋሉ፤ የስታዲየሙ ንግግር በኢሳትና ሌሎች ቴሌቪዥን ጣቢያዎች #በቀጥታ ይተላለፋል ተብሏል፡፡ በስታዲየሙ የሚገኘውን የሕዝብ መጨናነቅ ለመቀነስ በመስቀል አደባባይ በስክሪን ንግግሩ ይተላለፋል፡፡

መስከረም 6 እና 7 በባሕርዳር እና ጎንደር፣ መስከረም 12 በአዳማ አመራሮቹ የሚገኙበት ሕዝባዊ ትዕይንት ከተካሄደ በኋላ በተከታታይ ቀናት #በመቀሌ#ወልዲያ#ደሴ እና #አምቦ ተመሳሳይ ፕሮግራም ይኖራል፡፡

ንቅናቄው አቀባበሉን በተመለከተ ትናንት በሰጠው መግለጫ “በዕለቱ ሥነ ሥርዓት ለማስከበርና የሕዝብን ደሕንነት ለመጠበቅ ከተሰማሩ የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ታሪካዊ የአቀባበል በዓሉ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲካሄድ” ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፓሪሱ ጥቃት⬇️

ፈረንሳይ በመዲናዋ በሰኔ ወር የፈነዳውን ቦምብ #ያቀነባበረው የኢራን የደህንነት
መስሪያ ቤት መሆኑን አረጋግጫለው አለች፡፡

በወቅቱ በፓሪስ ጎዳና ላይ ከኢራን የተሰደዱ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንደነበሩ ተነግሯል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ፈረንሳይ የሁለት #ኢራናውያንን እና ከሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት ጋር የተያያዙ የባንክ አካውንቶችን አግዳለች፡፡

ከፍንዳታው ጋር በተያያዘም ረዥም ጊዜ የፈጀ ምርመራ ካካሄደች በኋላ ነው ይፋ ማድረጓን ያስታወቀችው፡፡

የኢራን የደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ የሆኑት ሰይድ ሐሺም #በቀጥታ ትዕዛዙን እንደሰጡ ተገልጿል፡፡

የደህንነት መስሪያ ቤቱ ቃልአቀባይ ፓሪስ የደረሰችበትን ምርመራ ተቀባይነት የለውም ያሉ ሲሆን በጀርመን ተያዙ ተያዙ የተባሉ ዲፕሎማታቸውንም እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም ጥቃቱ የተፈጸመው የሁለቱ ሀገራትን የረዥም ጊዜ ወዳጅነት በማይፈልጉ ሴረኞች የተቀነባበረ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ሲጂቲኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Adwa123 #አድዋ123

"አድዋ የሙዚቃ ፌስቲቫል"-በመስቀል አደባባይ የተዘጋጀውን ይህን #የሙዚቃ_ፌስቲቫል በOBN ቴሌቪዥን #በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለዶ/ር አብይ አህመድ አቀባበል አድርገዋል። ጋዜጣዊ መገለጫም ሰጥተዋል። ይህም በቀጥታ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ፌስቡክ ገፅ #በቀጥታ ሲሰራጭ ነበር" The Prime Minister of Israel"

WATCH LIVE! Prime Minister Benjamin Netanyahu welcomes Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed, at the Prime Minister's Office in Jerusalem🇮🇱https://www.facebook.com/IsraeliPM/
#ምርጫ2013 #በምርጫብቻ

ውድ የቲክቫህ አባላት የፊታችን ሰኞ ከሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች፣ ማብራሪያ የምትፈልጉበት ጉዳይ ይኖር ይሆን ?

የምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ በቀጥታ ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ።

ወ/ሪት ሶሊያና ምላሽ የሚሰጡት #በቀጥታ በ Voice Chat ላይ ነው።

ጥያቄዎቻችሁን ከታች በአስተያየት መስጫው ላይ አስቀምጡ ፤ አንድ አባል ለሚያቀርበው ጥያቄ ሌላ አባል #Reply መስጠት የማችል ሲሆን Reply የሚሰጣጡ አባላትን ከአስተያየት መስጫው ተሳትፏቸውን የምንገድበው ይሆናል።

(ይህ ጥያቄ መቀበያ ነገ ጥዋት 3:00 ይዘጋል)

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
በቀጣይ ...

ምርጫ ቦርድ የዛሬውን ማጠቃለያ መግለጫ ከደቂቃዎች በኃላ ከስካይ ላይት ሆቴል ይሰጣል።

የቤተሰባችን አባላት በስፍራው ይገኛሉ።

የቦርዱን መግለጫ #በቀጥታ በቴሌግራም Voice Chat ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሰንገን ኦባሳንጆ የሚመራው በኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን የምርጫ ትዝብቱን #የመጀመሪያ ሪፖርት ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ያቀርባል።

ሪፖርቱን #በቀጥታ በቴሌግራም Voice Chat መከታተል የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
#UNSC

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ሁኔታ ላይ እየመከረ ነው።

ይህ ስብሰባ ምክር ቤቱ በስምንት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ጉዳይ #በግልጽ የመከረበት ነው።

ስብሰበውን #በቀጥታ በUN የYoutube ገፅ መከታተል ይቻላል።

@tikvahethiopia
" እጅግ ነውር ተግባር ነው "

ከ2 ዓመት በፊት የቀረበን ሪፖርት በቀጥታ ገልብጦ ያቀረበው የዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር” እጅግ ነውር ተግባር” ፈጽሟል ሲል የዉሃ ፣ መስኖ ፣ ቆላማ አከባቢ እና አከባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ።

ቋሚ ኮሚቴው የዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ9 ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት እንዲያቀርብ በተገኘበት መድረክ ምንም ዓይነት የሪፖርት ማሻሻያ ሳያደርግ በቀጥታ #እየገለበጠ እንደሚያስተላልፍ ደርሼበታለዉ ብሏል።

ዛሬ ቋሚ ኮሚቴው የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል።

በዚህም ወቅት ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፖርቶችን በቀጥታ ገልብጦ ከማምጣቱም ባሻገር የተቋሙ የበላይ ሃላፊዎች #የማያዉቁት እና #ያልተገመገመ ሪፖርት ለምክርቤት መላኩ " እጅግ ነዉር ነዉ " ሲል ወቅሷል፡፡

ሪፖርቱ ከ2012 ጀምሮ እስካለንበት 2014 የግማሽ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርቶች #በቀጥታ ተገልብጠዉ የተላለፉ ናቸዉ።

ለማሳያነትም ፤ በስነምግባር እና በጸረ ሙስና ብልሹ አሰራሮች ናቸዉ ተብለዉ ከቀረቡት 16 ጥቆማዎች መሀል 13ቱ ተጣርተዉ መልስ የተሰጣቸዉ ሲሆኑ 3 ጥቆማዎች በሂደት ላይ የሚገኙ ናቸዉ " የሚለዉ አፈጻጸም ከ2012 የ9 ወር ሪፖርት ቃል በቃል ምንም ለዉጥ ሳይደረግበት ተገልብጦ የመጣ መሆኑን በግልጽ ያሳያል ሲሉ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት ፈትያ አህመድ ገልፀዋል።

ሰብሳቢዋ ይህንን ሀሰት ነዉ የሚል አካል ካለ በርካታ ተጨባጭ የሰነድ ማሳያዎች ማቅረብ እንችላለን ሲሉ ተናግዋል።

በሚኒስቴር ዲዔታ ማዕረግ የሚኒስቴሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ በሪፖርቱ ላይ የቀረበዉ ትችት ትክክል እንደሆነ አምነዋል።

የሪፖርት ጥራትና ወቅታዊነት ጉዳይ ፍጹም ለጥያቄም ቢሆን የሚቀርብ ጉዳይ እንዳልሆነ አንስተዋል። ይህም መስተካከል እንዳለበት እንደሚያምኑ እና የተለያዩ መ/ቤቶች አንድ ላይ መዋሃድ ይህንን ክፍተት መፍጠሩን እንደምክንያት አንስተዋል።

በቀጣይ ይህንን አስተካክለዉ እንደሚቀርቡ ገልጸዉ ቋሚ ኮሚቴዉን ይቅርታ መጠየቃቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
የእርዳታ ምግብ ጉዳይ !

" ህወሓት ለትግራይ ህዝብ የቀረበውን እርዳታ ለጦርነት እያዋለው ነው " - ኢትዮጵያ

" ከሰብዓዊ እርዳታ ስርቆት ጋር በተያያዘ ማንኛውም ክሶች እመረምራለሁ " - USAID

ዳግም ያገረሸው የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በቀጠለበት በአሁን ወቅት በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት " ህወሓት " ለትግራይ ህዝብ የገባውን ሰብዓዊ እርዳታ ለጦርነት እያዋለው መሆኑን በተደጋጋሚ አንፅንኦት ሰጥቶ እየገለፀ ነው።

ግጭቱ የተጀመረ ሰሞን ምንም እንኳን ህወሓት ያበደርኩትን ነዳጅ መልሼ ወስጃለሁ የሚል ማስተባበያ ቢሰጥም 500 ሺህ ሊተር ነዳጅ ከመቐለ WFP መጋዘን መዘረፉን የዓለም አቀፍ ተቋማት መግለፃቸውን የኢትዮጵያ መንግስትም ይህን መሰል ድርጊት እንደሚያወግዝና ነዳጁ እንዲመለስ ጠይቆ ነበር።

በአሁን ወቅት ደግሞ ውጊያ በሚደረግባቸው አካባቢዎች ህወሓት ለህዝብ የቀረቡ ምግቦችን ለውጊያ እየተጠቀመበት መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ይገልፃል። ለአብነት ኮርን ሶያ ብሌንድ (USAID ምልክት ያለበት) የተሰኘውን አጣዳፊ የምግብ እጥረትን ለማከም የሚውል አልሚ ምግብ በውጊያ ስፍራ መገኘቱን አሳውቋል።

በተጨማሪ መከላከያው በሚሰብራቸው ምሽጎችን ለእርዳታ የተላኩ የስንዴ ክምችቶች (USAID - የአሜሪካ ምልክት ያለባቸው) መገኘታቸውን ተገልጿል።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እስካሁን #በቀጥታ ምላሽ የሰጠ ዓለም አቀፍ ተቋም ባይኖርም ትላንት የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ከእርዳታ ምግብ ጋር በተያያዘ በትዊተር ገፁ አንድ ፅሁፍ አውጥቷል።

በችግር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሲቪሎች ህይወታቸው ጥገኛ የሆነበትን ምግብ ከአፋቸው ተነጥቆ በታጠቁ አካላት ጥቅም ላይ ማዋል እንዲሁም በታጠቁ አካላት የሰብዓዊ እርዳታ መውሰድና ጥቅም ላይ የማዋል ድርጊትን አወግዛለሁ ብሏል።

@tikvahethiopia
G4 U1-3.pdf
65.4 MB
መነጋገሪያ የሆነው የ4ኛ ክፍል መፅሀፍ ምንድነው ?

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጀው የ4ኛ ክፍል የሒሳብ መፅሀፍ መነጋገሪያ ሆኗል።

ይህ መፅሐፍ መነጋገሪያ ሊሆን የቻለው በውስጡ #ገፅ_18 ላይ " የግዕዝ ቁጥሮች ምልክቶች #በቀጥታ ከግሪክ ቁጥሮች የተወሰዱ ናቸው" የሚል ሀሳብ ይዟል በመባሉ ነው።

ይህም ጉዳይ በርካታ ዜጎችን አስቆጥቷል።

መፅሀፉ ውስጥ ገብቷል የተባለው ሀሳብ የታየው በሶፍት ኮፒ በተሰራጨው የመፅሀፉ ቅጂ ላይ መሆኑን በርካታ ወላጆች ልከውልን ተመልክተነዋል።

መምህራንም በተመሳሳይ ደርሷቸው እንደነበር ገልፀውልናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ት/ት ቢሮ የተገለፀው ሃሳብ "በመጽሐፉ ውስጥ የማይገኝና ሆነ ተብሎ የተሰራጨ የሀሰት መረጃ" ነው ብሎታል።

ይህም የተደረገው ሆን ብለው ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ውዥንበር ለመፍጠር በሚፈልጉ አካላት ነው ሲል ገልጿል።

አዲሱ መፅሀፍ ህትመቱ ተጠናቆ በሁሉም ት/ቤቶች እየተሰራጨ መሆኑን አሳውቋል።

ቢሮው በPDF ስለተሰራጨው መፅሀፍ ያለው ነገር/የሰጠው ማብራሪያ የለም።

በዚህ ጉዳይ ላይ ግልፅ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጉዳዮች፦

1ኛ. የሶፍት ኮፒ መፅሀፉ በማን፣ እንዴት፣ መቼ ተዘጋጀ ? ስህተት መሆኑ ከታወቀ እንዴት ተሰራጨ ?

2ኛ. ለት/ቤቶች #ታትሞ የተሰራጨው መፅሀፍ ዝግጅቱ መቼ ተጀመረ፣ መቼ ታተመ፣ መቼ ተጠናቀቀ ?

ሶፍት ኮፒው በትክክል ከሚመለከተው አካላት ተልኮ ከሆነ እና ስህተት ካለው "ሀሰተኛ / ህዝብ ውዥንብር ውስጥ ለመክተት የፈለጉ አካላት" ከማለት ስህተት መሆኑን በመግለፅ ማረም አይቻልም ነበር ወይ ?

ይህ ጉዳይ በዚህ ደረጃ መነጋገሪያ የሆነው ሀገር የሚረከቡ ትንንሽ ልጆች ስለሚማሩበትና ነገ ስለ ሀገራቸው ምን እያወቁ ነው የሚያድጉት የሚለው ስለሚያሳስብ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #EU #UNICEF የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ። ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ የተቋረጡ የጤና አገልግሎቶች እንደገና እንዲጀምሩ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት (EU) የ31.5 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉን ያደረገው የማስጀመር እና የአቅም ግንባታ ስራ እንዲሰራ ለማስቻል ለተመድ የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) መሆኑን ኤፍ ቢ ሲ…
" የሰላም ስምምነቱን መደገፋችንን እንቀጥላለን " - አውሮፓ ህብረት

የአውሮፓ ህብረት የሰላም ስምምነቱን መደገፉን እንደሚቀጥል ዛሬ ባሰራጨው ፅሁፍ አረጋግጧል።

" ከሰላም ውጭ አማራጭ የለም " ያለው ህብረቱ አጋሮቹ UNICEF እና PLAN የህብረቱን የገንዘብ ድጋፍ በተግባር ላይ ማዋል ይጀምራሉ ሲል አመላክቷል።

የአውሮፓ ህብረት ፤ ለሕዝብ አፋጣኝ ቀጥተኛ ድጋፍ ለማረጋገጥ ሥራችንን እንቀጥላለን ብሏል። ህዝቡም የህብረቱን እንቅስቃሴ ይከታተል ዘንድ ጥሪ አቅርቧል።

ትላንት ህብረቱ የኢትዮጵያን ህዝብ #በቀጥታ እንደሚረዳ ገልጾ የትምህርት እና ጤና ዘርፉን ለመደገፍ 38 ሚሊዮን ዩሮ ( 2.1 ቢሊዮን ብር) ለግሷል።

" ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ይመለሳሉ " ኢትዮጵያውያን የጤና አገልግሎት ያገኛሉ። " ያለው ህብረቱ የአውሮፓ ዜጎች ከፕላን ኢንተርናሽናል (PLAN) ኢትዮጵያ እና ዩኒሴፍ (UNICE) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያውያንን ይረዳሉ ሲል አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba • ከወራት በፊት "በቅርብ ቀናት በድጋሚ ይወጣል። " ሲባል የነበረውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ለማውጣት ሂደቶች እየተጠናቀቁ ነው ተብሏል። • ትክክለኛው የዕጣ መውጫው ቀን እስካሁን አይታወቅም። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰረዘውን የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ዕጣ ለማውጣት ሂደቶች እየተጠናቀቁ ሲል አሳውቋል። የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤…
#Update

የተሰረዘው የአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ነገ ይወጣል።

በቅርቡ በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ምክንያት ተሰርዞ የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ በነገው ዕለት እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

በጉዳዩ ላይ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ ያስሚን ወሀቢረቢ እና የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሽመልስ ታምራት ዛሬ በሰጡት መግለጫ የተናገሩት ፦

- ነገ 25 ሺህ 791 የ40/60 እና 20/80 ቤቶች ዕጣ ይወጣባቸዋል።

- በነገው እጣ 146 ሺህ 892 እስከ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በቂ ቁጠባ ያላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ይሳተፋሉ።

- በነገው እጣ አወጣጥ ነባርና በ2005 ዓ.ም በባለሶስት መኝታ ቤት የተሰሩ 300 ቤቶችም ይተላለፋሉ።

- በእጣ አወጣጡ ላይ ከዚህ ቀደም የገጠሙ ችግሮች እንዳይደገሙ አዲስ የእጣ አወጣጥ ስርዓት ተዘርግቷታ።

- የመረጃ ማጥራት እና ማደራጀት ስርዓቱ ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ተከናውኗል።

- የእጣ ማውጫ መተግበሪያውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ያለማው ሲሆን ከፌደራል ተቋማት እና ከከተማ አስተዳደሩ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

- የእጣ አወጣጡ በቆጣቢዎች የቅድመ ግምገማ ወይም የእጣ አወጣጥ ሙከራ የተካሄደበት ነው።

- ነገ ከሰዓት ላይ የሚካሄደው የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓቱም በቴሌቪዠን #በቀጥታ_ስርጭት ይተላለፋል።

Credit : ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
" የምግብ ችግሩ የከፋ ነው "

ከትግራይ አዋሳኝ በሆኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች " አበርገሌ " እና " ፃግብጅ " ተፈናቅለው በዋግኽምራ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች በምግብ እጦት ምክንያት በተለያዩ በሽታዎች እየተጠቁ መሆኑ ተገልጿል።

በተለይ ነፍሰጡር እናቶች እንዲሁም እናቶች በምግብ እጦት ለበሽታ እየተጋለጡ ሲሆን ለሁለት ዓመታት በዋግኽምራ ዞን ሲቆዩ ከተለያዩ የመንግስት እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እርዳታ እያገኙ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ከመንግስትም ሆነ ከረጂ ድርጅቶች እርዳታ እየመጣ አይደለም ተብሏል።

ነፍሠጡር እናቶች ፣ የሚያጠቡ እናቶች እና ህፃናት በሳምባ ምች እና በተቅማጥ በሽታ እየተያዙ መሆኑ ተመላክቷል።

የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ ለተፈናቃዮች የሚቀርብ የምግብ ድጋፍ፣ የንፅህና መጠበቂያ፣ የውሃ አቅርቦት፣ መድሃኒት በመቋረጡ / እንደ በፊት ባለመሆኑ ዜጎች ችግር ላይ ናቸው ብሏል።

" ዜጎች በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ " ያለው መምሪያው በተለይም የምግብ ችግሩ የከፋ ነው " ሲል አሳውቋል። በምግብ እጥረቱ ሳቢያ እንዲሁም በውሃ አቅርቦት አለመኖር ዜጎች ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጡ መሆናቸውን ገልጿል።

ጤና መምሪያው መሰረታዊ የህክምና አገልግሎቶች እየሰጠ የተፈናቃዮችን ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን ጠቁሞ በህፃናት ላይ የሚታየው የሳንባ ምች እና የተቅማጥ በሽታ ለመከላከል የሚያስፈልጉ መድሃኒቶች ከፍተኛ እጥረት መኖሩን ጠቁሟል።

ከምንም በላይ ግን የምግብ አቅርቦቱን ማስተካከል ካልተቻለ ያለውም ችግር መቅረፍ እንደሚያጋግት ጠቁሟል።

#ምግብ_እጦት ጋር በተያያዘ ህይወቱ ያለፈ ሰው ስለመኖሩ የተጠየቀው የጤና መምሪያው ፤ #በቀጥታ በረሃብ የሞተ ሰው #እንደሌለ ነገር ግን #ረሃብ ለሌሎች በሽታዎች ስለሚያጋልጥ በሌሎች ህመሞች የመሞት እንድል እንዳላቸው አመልክቷል።

የጤና መምሪያው መንግስት በዋግኽምራ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች ትኩረት እንዲሰጥ ፣ አጋር ድርጅቶችም ከዚህ በፊት ሲያደርጉ የነበረውን የመድሃኒት ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና ሌሎች ድጋፎች እንዲቀጥሉና ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቋል።

በተጨማሪ የሰላም ስምምነት ከተፈጠረ አካባቢው ነፃ መሆን አለበት ነዋሪዎችም ወደ ቀደመው ቄያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ እና እንዲደገፉ የማድረግ ስራ መንግስት ሊሰራ ይገባ ተብሏል።

መረጃ ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ እና መጠነ ሰፊ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ዛሬ ይፋ እንደሚያደርጉ ተነግሯል። ውሳኔው የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት በየዕለቱ ከሚመለከቱት በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ተጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በላይ አመልካቾች የሚቀርቡ ከሆነ ጥያቄያቸውን ሳይመለከቱ በቀጥታ ከአገር እንዲባረሩ ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን…
#Update

የአሜሪካ ፕረዚደንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አገሪቱ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ሲባል የሀገሪቱን ፍልሰተኞች ሕግ አጥብቀዋል።

ይህ የጆ ባይደን ውሳኔ ባለሥልጣናት በሜክሲኮ በኩል ድንበር አቋርጠው የገቡ ስደተኞችን / ጥገኝነት ጠያቂዎችን በቀጥታ በኃይል ወይም በግዳጅ  እንዲመልሷቸው ሥልጣን የሚሰጥ ነው።

ጉዳያቸው የሚመዘገቡ ሰዎች ዕለታዊ ኮታ ከተሟላ የተቀሩት ከአሜሪካ በኃይል እንዲወጡ ይደረጋሉ።

ከዚህ ባለፈ ለአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የውጪ ዜጋ ወደ አገር እንዳይገባ " #እንዲታገድ " የሚል ትዕዛዝ ፕሬዜዳንቱ አስተላልፈዋል።

#ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ አፍሪቃውያን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ እንደሚሻገሩ ይታወቃል።

አሜሪካ የፍልሰተኞችን ፍሰት ለመግታት በሚል ከሜክሲኮ የሚያዋስናትን ድንበር ከማጠር ጀምሮ በርካታ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።

ይህ የአሁኑ የፕሬዜዳንት ባይደን ውሳኔ ስደተኞች የጥገኝነት ጥያቄያቸው ለሚመለከተው የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ቀርቦ ሳይታይ #በቀጥታ እንዲባረሩ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፤ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ግን ሕጉ የስደተኞችን መሰረታዊ መብት ይጥሳል ሲል ተቃውሟል።

መረጃው የጀርመን ዜና አገልግሎት፣ የዶቼ ቨለ እና ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል። በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል። በመንግስት…
የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችለው የመቁረጫ ነጥብ ስንት ነው ?

በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን የመቁረጫ ነጥብ ፦

➡️ በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ የወንድ ተማሪዎች የሬሜዲያል የመግቢያ ውጤት ከ600ው 204 ነው።

➡️ በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ የሴት ተማሪዎች የሬሜዲያል የመግቢያ ውጤት ከ600ው 192 ሆኖ ተቆርጧል።

(ተጨማሪ የመቁረጫ ነጥብ ከላይ ተያይዟል)

ከዚህ ባለፈ ግን እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግልና በመንግስት ተቋማት) በራሳቸው ክፍያ የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ።

ይህ ማለት ፦

➡️ ከ600ው የትምህርት ብዛት ፈተናቸውን ተፈትነው 31% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡ (186 እና በላይ) ፤

ከ500 የትምህርት ብዛት የተፈተኑ (ዓይነስውራን ተማሪዎች) 31% እና በላይ ውጤት ያመጡ (155 እና በላይ) ፤

ከ700ው የትምህርት ብዛት የተፈተኑ 31% እና ከዛ በላይ ውጤት ያመጡ (217 እና በላይ) ... በፈለጉት አማራጭ ማለትም በግል ሆነ በመንግሥት ተቋማት ከፍለው የሬሜዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ።

በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና #በቀጥታ የሚያሳልፈው ውጤት 50% እና በላይ መሆኑ ይታወቃል።

የሬሜዲያል ፕሮግራም መቁረጫ ነጥብ (በመንግሥት ስፖንሰርሺፕ / ተመድቦ ለመማር) ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

በግል ከፍለው በመንግሥትም ይሁን በግል ተቋም ለመማር የሚፈልጉ ከተፈተኑት ፈተና ውጤት 31% እና በላይ ውጤት ማምጣት አለባቸው።

@tikvahethiopia