TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ውጤቶች : ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስገብቶ ባስፈተነው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የተመዘገቡ ውጤቶች በጥቂቱ ከላይ ተያይዘዋል። More : @tikvahuniversity #TikvahFamily @tikvahethiopia
ውጤቶች : ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት / ዩኒቨርሲቲ አስገብቶ ባስፈተነው የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና የተመዘገቡ ውጤቶች በጥቂቱ ከላይ ተያይዘዋል።

እስካሁን ድረስ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በኩል በታየው የጥቂት ተማሪዎች ውጤት ብቻ ዝቅተኛው ውጤት 120 ሲሆን ከፍተኛው ደግሞ 666 ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር በአጠቃላይ ከውጤት ጋር በተያያዘ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

More : @tikvahuniversity

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ረመዷን

የረመዷን ወር መግቢያ ጨረቃ ዛሬ ባለመታየቷ ምክንያት ታላቁ የረመዷን ጾም ሀሙስ መጋቢት 14 ይጀምራል።

እንኳን ለታላቁ የረመዷን ጾም በሰላም አድረሳችሁ።

ረመዷን የፍቅር፣ የአንድነት፣ የሰላም፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት ወር እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ረመዷን

በመላው ዓለም ላይ የሚታወቁት የዝምባብዌ ዜግነት ያላቸው የእስልምና መሁር ሙፍቲ  ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ስለ ቅዱሱ የረመዷን ወር እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ፦

ሙፍቲ  ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) ፦

" ረመዷን ምንድን ነው ? ሰዎች እየፆምን ነው ይላሉ ይህ ግን የረመዷን አንዱ ክፍል ብቻ ነው።

ረመዷን ፦
🤲 #የሰላም ወር ነው፤
🤲 #የመረጋጋት ወር ነው፤
🤲 #የመፈወሻ ወር ነው፤
🤲 #የቸርነት ወር ነው፤
🤲 #የምህረት ወር ነው፤
🤲 #የይቅርታ ወር ነው፤
🤲 #ጀነትን የምናገኝበት ወር ነው፤
🤲 ይህ ወር #ሙስሊም መሆናችንን የምናከብረበት ነው ፤ ሙስሊም በመሆናችን #ራስን_መግዛትን የምንለማመድበት የፈለግነውን ብቻ ሳይሆን ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ የወሰነውን የምናደርግበት ወር ነው ፤  ሱብሃንአላህ ! ስለዚህ ለአላህ ቃል ጥረት ማድረግ ግዴታችን ነው። "

መልካም #የረመዷን_ጾም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲሆን እንመኛለን።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ትንሳኤ

እንኳን አደረሳችሁ !

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።

በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።

በተጨማሪም ፤ በዓሉን በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በጥቃት፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን ፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን።

የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን !

መልካም በዓል !
#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopia
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መልዕክት መለዋወጫ !

ከዚህ ቀደም ተከፍተው አገልግሎት ላይ የነበሩት የመልዕክት መቀበያዎች በተደጋጋሚ በቴሌግራም ቴክኒንክ ችግር አገልግሎታቸው እየተደነቃቀፈ ነው።

በዚህም ምክንያት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የሚመጡትን መልዕክቶች ለማግኘት ችግር ሆኗል ፤ ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን።

ችግሩን ለመቅረፍ እና በየትኛውም መልኩ ነፃነቱ የተጠበቀ ለቲክቫህ አባላት ብቻ የሚያገለግል የሀሳብ መለዋወጫ በቅርቡ ይፋ የምናደርግ ሲሆን እስከዛው ድረስ ግን በዚህ አዲስ መልዕክት መቀበያ ላይ ብቻ መልዕክት ማጋራት ይቻላል  👉@tikvah_eth_BOT

በተጨማሪ @tikvah_Ethiopia_Fam ወይም ደግሞ 0703313630 መደወል ይቻላል።

በቲክቫህ ቤተሰብ ውስጥ ማስተላለፍ የሚቻሉ መልዕክቶች ምን አይነት ናቸው ?

- የፀጥታ ችግሮች፣ የደህንነት ስጋቶች፣ የወንጀል ድርጊቶች በመንግስት አካላት / ተቋማት የሚፈፀሙ ማንኛውም አይነት አስተዳዳራዊ በደሎች፤
- የየመንገድ ፣ የውሃ፣ እንዲሁም የኑሮ ውድነት፣ የኢኮኖሚና የሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎች፤
- በግልም ሆነ በጋር የማያጋጥሙ ችግሮች፣ ሊበረታቱ የሚግባቸው ተግባራት፣
- ለሀገር እና ለትውልድ ጠቃሚ ናቸው የሚባሉ ሃሳቦችን፣
- የእርስ በእርስ እገዛዎች ፣ የበጎ አድራጎት ስራዎች፣
- ጥቆማዎችን ፣ ጥያቄዎችን ፣ ይሄ ነገር ለቤተሰቡ ቢጋራ መልካም ነው የምትሉትን (ዜና ፣ መረጃ) ሁሉ ማቅረብ ትችላላችሁ።

ምን መላክ አይቻልም ?

ስድብ፣ የጥላቻ ንግግር ፣ የማንኛውም የግለሰብ ማንነትን በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የሚነካ ፣ ህዝብን በጅምላ የሚፈርጅ፣ ፣ ህዝብ ላይ ጥላቻን የሚያሰርፅ፣ ሀገር ሊያስጣ የእርስ በእርስ ግጭት የሚያባብስ፣ ሀሰተኛ መረጃ ፅሁፍ / መልዕክት መላክ በፍፁም አይቻልም። በየትኛውም አካል ላይ ትችትም ይሁን ቅሬታ ለመግለፅ የሚፈልግ የቤተሰቡ አባል የሚጠቀማቸውን ቃላት የመምረጥ ግዴታ አለበት።

ውድ ቤተሰቦቻችን ማንኛውም መልዕክት ስትልኩ የራሳችሁ የግላችሁ መልዕክት መሆኑን በማስረጃ አስደግፋችሁ ላኩልን። እናተ ያላረጋገጣችሁትንና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስላያችሁት የራሳችሁ በማስመሰል ማንኛውም መልዕልት መላክ ፍፁም አይቻልም።

ማስታወሻ ፦ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት #በፌስቡክ#ዩትዩብ#ቲክቶክ ላይ ምንም አይነት የመሰባሰቢያ መድረክ (ገፅ) የላቸውም።

ትዊተር ፦ https://twitter.com/tikvahethiopia?t=jZrpieALuIGzw6OM-HWgEw&s=09

ሀሳባችን ስንገልፅ ቃላትን እንምረጥ !!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ!!
#TikvahFamily

@tikvah_eth_BOT
#ዒድ_አልፈጥር

ውድ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ዒድ ሙባረክ !

በዓሉ የሰላም ፣ የአንድነት ፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

በዓሉን ስታከብሩ የተቸገሩት ፣ ያጡትን ፣ በችግር ላይ የወደቁትን ፤ በሰላም እጦት የሚሰቃዩትን ፣ በጦርነት እና በግጭት ወገን ዘመዶቻቸውን ከጎናቸው የተነጠቁትን ፣ ከሞቀው ቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የቀሩ ወገኖቻችን በማሰብ ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።

ሀገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን!!
መልካም በዓል !

ፎቶ፦ አቤል ጋሻው (ፋይል)

#TikvahFamily ❤️

@tikvahethiopia
#ትዊተር

ለጥንቃቄ ...

የትዊተርን አዲስ አሰራር ተከትሎ የበርካታ ታዋቂ ሰዎች እና ተቋማት #የማረጋገጫ_ምልክት ከትላንት ጀምሮ ተነስቷል።

ታዋቂው ቱጃር ኤሎን መስክ በ44 ቢሊዮን ዶላር ትዊተርን ከገዛው በኋላ በመተግሪያው ላይ የመጡ ለውጦች በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ እየሆኑ ይገኛል።

ከዚህም ውስጥ አንዱ ትዊተር ታዋቂ ግለሰቦች የሚሰጠውን የማረጋገጫ መልክት (Twitter verification) በክፍያ መጀመሩ ዋነኛው ነው።

ለግለሰብ በወር 8 ዶላር ለድርጅት ደግሞ 1000 ዶላር ማስከፈል የጀመረው መተግበሪያው ከትላንት ጀምሮ ክፍያ ያልፈጸሙ ያላቸውን አካውንቶች የማረጋገጫ ምልክታቸውን አንስቷል።

የማረጋገጫ ምልክታቸው የተነሳው በሀገራችን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ ታዋቂ ሰዎች ፣ የሚዲያ ተቋማት ፣ ትልልቅ የመንግስት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ መስሪያ ቤቶች ነው።

በርካቶች ይሄንን ውሳኔ  በተመሳሳይ ስም የሚከፈቱ " የማረጋገጫ ምልክት " የሚኖራቸው አካውንቶች እንዲኖሩ እድሉን ይከፍታል በሚል የተቃወሙት ቢሆንም ውሳኔው ግን ተግባራዊ ተደርጓል።

ይህም ሀሰተኛ መረጃን ያባብሳል ተብሎ ተሰግቷል።

በተለይ አሁን ላይ የማረጋገጫ ምልክቱን በቀላሉ ማግኘት መቻሉ ለአጭበርባሪዎች (Scammers) በር በመክፈት በርካቶችን ሊጎዳ ይችላል።

የገጾችን ትክክለኛነት ለማሳየት የምንጠቀምበት ይህ የማረጋገጫ ምልክት ከዚህ በኋላ ለማረጋገጫነት ብዙም ጥቅም የሚኖረው አይመስልም።

የገጹ ተከታይ ብዛት እንደ ማረጋገጫ መውሰድ ብንችልም እንደ ሀገራችን የሀሰተኛው ገጽ ተከታይ ቁጥር ከትክክለኛው በሚበልጥበት ሁኔታ የገጹን ትክክለኛነት ለማረጋገጥም አዳጋች ያደርገዋል።

ከዚሁ ከትዊተር ማረጋገጫ ምልክት መነሳት ጋር በተያያዘ ጦርነት ውስጥ ባለችው ሱዳን የሆነ አንድ ጉዳይን እናጋራችሁ።

በጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ (RSF) የትዊተር አካውንት ያለው ሲሆን አካውንቱም 82.7K ተከታይ እና የሰማያዊ ማረጋገጫ ምልክት ነበረው።

ትዊተር ትላንት ይህንን የማረጋገጫ ምልክት ባነሳበት ሰዓታት ውስጥ የሰማያዊ ምልክት #የገዛ በተመሳሳይ በRSF ስም የተከፈተ 26 ሺ ተከታዮች ያሉት ገፅ ጄነራል መሀመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) በጦርነቱ ላይ #እንደተሞቱ አድርጎ አንድ ፅሁፍ አስራጭቷል።

የዚህን የማረጋገጫ ምልክት ከትዊተር የገዛ ገፅ ያወጣውን ሀሰተኛ ፅሁፍ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች አይተውታል ፤ ይህን ሀሰተኛ ፅሁፍ ያመኑም አልጠፉም።

ውድ ቤተሰቦቻችን በትዊተር አዲስ አሰራር ሁሉም ሰው ሰማያዊ የማረጋገጫ ምልክት እየገዛ በመሆኑ የሰማያዊ ምልክት ያላቸው አካላት ናቸው የሚያሰራጩት በማለት ሁሉንም የምታዩትን መረጃዎች አትመኑ፤ መረጃዎችን መርምሩ፣ አጣሩ። እናመሰግናለን !!

#TikvahFamily

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine
ሃሳብን መግለፅ ... በጥሩ ቃላት !

ሁሉም ሰዎች ከእኔ / እኛ ጋር አንድአይነት ወጥ የሆነ አመለካከት፣ አስተሳሰብ ይኖራቸዋል ብሎ መጠበቅ ፈፅሞ ሊሆን የማይችል ነው።

ነገር ግን ከእኛ ጋር የሚቃረን ሃሳብ በተመለከትን ወቅት ለዛ ግብረመልስ የምንሰጥበት መንገድ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።

ይህን ለማለት መነሻ የሆነን የኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፍፁም ከመስመር የለቀቀ መሆኑን በመገንዘብ ነው።

እኛ ያልደገፍነው ወይም ከእኛ ጋር የማይስማማ / ያላሳመነን ሀሳብ ስንመለከተ ከሰዎች ጋር እልህ እና ንትርክ፣ ጥላቻ ውስጥ በማያስገባ ቃላት በመጠቀም ሀሳባችንን ብንገልፅ የተሻለ ነው።

ለምሳሌ ፦

አንድ የግለሠብ ሃሳብ / ማንኛውም አይነት ዜና / መረጃ / ንግግር በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ብንመለከት እና ያን ነገር ፍፁም በእኛ ዘንድ ተቀባይነት ባይኖረው እንዲህ በሚል ሃሳባችንን ብንገልፅስ ...

• ንግግሩ / መረጃው ሀሰት ከሆነ ፤ " ይህ ፍፁም ሀሰት ነው ፤ እኔ ይህ ሀሰት ስለመሆኑ በቂ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ እችላለሁ " በሚል የኛን ማስረጃና ሃሳብ ማቅረብ።

• ሃሳቡን ካልደገፍነው / ካልወደድነው ፤ " እኔ ይህንን ሀሳብ በፍፁም አልደግፈውም / አልወደድኩትም ምክንያቱም ... ይህ ይህ ስለሆነ " ብንል።

• ጥላቻን የሚሰብክ መልዕክት ከሆነ ፤ " ይህ በእኔ አመለካከት ጥላቻን የሚሰብክ ስለሆነ አመለካከትህን ብታርም እና ቀና አመለካከት ብትይዝ " በሚል ወንድማዊ ምክር ብንለግስ።

በእርግጥ ያለንበት ሁኔታ በብዙ የሚያበሳጭ ፣ የሚያቆስል ፣ የሚያናድድ ጉዳዮች የተሞላ ቢሆንም በሌሎችም ጉዳዮች ሃሳብ ስንገልፅ እርስ በእርስ ለመግባባት ፣ ለመተራረም እና አብሮነትን ለማጠናከር በሚያግዙ ቃላት ብንመላለስ በትንሹም ቢሆን ሰላማዊ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን መፍጠር ይቻላል።

ማንም ሰው እራሱንም ሆነ ሰውን እንዲሁም የገዛ ሀገሩን እስካልጎዳ፣ ሌላውን እስካልበደለ ድረስ የፈለገውን ሀሳብ የማራመድ መብት ቢኖረውም ያንን የሚገልፅበት መንገድ ነገ የተሻለ ለውጥን ሊያመጣ በሚችል መልኩ መሆን አለበት።

ተቃራኒ ሃሳብ ስንመለከተ ዘለን የገለሰቡን ብሄርን ፣ ማንነትን በመተንኮስ፣ በጥላቻ እንዲሁም በእልህ በፍረጃ የምንሰጠው ሃሳብ ችግር ከመፍጠር እና ከማባባስ ውጭ የሚፈይደው ነገር አይኖርም።

ሃሳብ እና አስተያየት የምንሰጥባቸው ቦታዎችን መምረጥ ተገቢ ነው ፤ የሃይማኖት ጉዳይ ላይ ፣ በፖለቲካውም ላይ ፣በትምህርቱም ላይ ... እየገቡ ከሰዎች ተቃራኒ ሃሳብ ጋር መጋጨት እና መነታረክ ከምንም በላይ ለራስ ጤና ጎጂ ነው።

በጅምላ / ሌሎች ሰዎች ስለፃፉ ብቻ ሳይሆን ስለምናውቀው ጉዳይ በተሻለ ቃላት ሃሳባችንን የሚገባው ቦታ ላይ ብናስቀምጥ በተሳሳተ መንገድ እየሄዱ ያሉ በርካቶችን መለወጥ ይቻላል።

እዚህ ጋር ልብ ማለት የሚገባው ፦ በማህበራዊ ሚዲያው ሆን ተብለው ለጥላቻ ፣ ለግጭት ፣ ሰዎችን ለማበሳጨት እና ስሜታዊ ለማደርግ የሚከፈቱና ሁሉም ገፆች ላይ እየገቡ የሚፅፉ በርካታ ሀሰተኛ አካውንቶች መኖራቸውን ነው።

#tikvahfamily

@tikvahethiopia @tikvah_eth_BOT
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ #ኔትዎርክ ተቋርጧል። በትግራይ ክልል ከምሽት 12 ሰዓት አንስቶ የኔትዎርክ አገልግሎት መቋረጡን በዚህም ምክንያት " ምን ተፈጥሮ ነው ? " በሚል ጭንቀት እንደገባቸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰቡን አባላት መልዕክት ይዞ ኢትዮ ቴሌኮምን አነጋግሯል። ኢትዮ ቴሌኮም ፤ እውነት ነው ኔትዎርክ ተቋርጧል ሲል አረጋግጦልናል። " ኔትዎርክ የተቋረጠው ፋይበር ተቆርጦ…
#Update

ኢትዮ ቴሌኮም በ " ፋይበር መቆረጥ " ምክንያት በትግራይ ተቋርጦ የነበረውን የኔትዎርክ አገልግሎት ለማስቀጠል ሲያከናውን የነበረውን የጥገና ስራ ማጠናቀቁንና አገልግሎት መመለሱን አሳውቆናል።

ኢትዮ ቴሌኮም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መረጃ ፤ ሰራተኞቹ ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ በሁለት ቦታዎች ላይ የነበረውን የፋይበር መቆረጥ በመጠገን ወደነበረበት መመለስ ችለዋል።

የፋይበር መቆረጥ ያጋጠመው በ " አላማጣ " እና በ " ሰመራ " በኩል ሲሆን በምን ምክንያት ሊቆረጥ እንደቻለ የማጣራት ስራ ለመስራት እየተሞከረ ነው ተብለናል።

" የፋይበር መቆረጥ በተለያዩ ቦታዎች አልፎ አልፎ ያጋጥማል " ያለን ኢትዮ ቴሌኮም በሁለቱ ቦታዎች ያጋጠመውን የፋይበር መቆረጥ ምክንያት ለማወቅና " በዚህ ነው ሊቆረጥ የቻለው " የሚለውን ለመለየት እየተሰራ ነው ሲል አስረድቶናል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia