#ሀሰት_ነው !
" ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ " በሚል የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።
በ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ማጠቃለያ ላይ ተማሪዎች ማጠቃለያ ፈተናዎችን ለመውስድ እየተዘጋጁ ይገኛሉ።
ነገር ግን ማህበራዊ ኃላፊነት በጎደላቸው አካላት ሆን ተብሎ ተማሪዎችን ለማዘናጋት በዘንድሮ ዓመት ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወር የለም ተብሎ በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች የሚናፈሰው ወሬ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የወረደ አቅጣጫ የለም ያለው የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች " ተማሪዎች ዘንድሮ በያላችሁበት ትደግማላቸሁ" በሚል አሉባልታ ሳይምታቱ ለትምህርታቸው ትኩረት ስጥተዉ ለተሻለ ውጤት እንዲተጉ መልዕክት አስተላልፏል።
በተጨማሪ ⬇️
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚኒስቴሩን ስም እና አርማ በመጠቀም የተሳሳቱ እና የተዛቡ መረጃዎች እየተለቀቁ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች እና ወላጆች የሚሰረጩት መረጃዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን በማወቅ በትኩረት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አሳስቧል።
@tikvahethiopia @tikvahuniversity

#WorldCup
የኳታሩ አለም ዋንጫ ሊጀምር የወራቶች እድሜ ብቻ ሲቀሩት የአለም ዋንጫው በዛሬው ዕለት አስቀድሞ በተያዘለት ቀን #ኢትዮጵያ 🇪🇹 ደርሷል።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሸራተን ሆቴል በተደረገ ጋዜጣዊ መግለጫ የቀድሞ የባርሴሎና እና የቼልሲ የመስመር ተጫዋች ብራዚላዊው ጁሊያኖ ቤሌቲ እና የ ኮካ ኮላ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የአለም ዋንጫው በሀገራችን የሁለት ቀናት ቆይታ ሲኖረው በነገው ዕለት ከ ረፋዱ 4:30 ጀምሮ በመስቀል አደባባይ በመገኘት የስፖርት አፍቃሪው አብሮ ፎቶ መንሳት እንደሚችል ተገልጿል።
አስቀድሞ ዴቪድ ትሪዝጌት እንደሚመጣ ተገልፆ የነበረ ቢሆንም ተጫዋቹ ባጋጠመው ከአቅም በላይ የሆነ የግል ጉዳይ ሊገኝ አለመቻሉ ታውቋል።
Via @tikvahethsport (ቲክቫህ ስፖርት)

#NewsAlert
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለማችንን ትልቁን የጤና ተቋም የዓለም የጤና ድርጅትን ለሁለተኛ ዙር እንዲመሩ ዳግም ተመረጡ።
የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ብቸኛ ዕጩ ሆነው ዳግም መመረጣቸው የተረጋገጠው በጄኔቫ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉብዔ ላይ ነው።
ዶክተር ቴድሮስ ያለተፎካካሪ በብቸኛ ዕጩነት በቀረቡበት መድረክ ላይ ከተለያዩ የድርጅቱ አባል አገራት ለዕጩነት ለተሰጣቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ተቋሙን በይፋ ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ለሁለተኛ ዙር መምራት ይጀምራሉ መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
@tikvahethiopia

" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመኪና ስርቆት እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዳይለየው " - የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት
የሰረቀውን መኪና ይዞ ለማምለጥ የሞከረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር መዋሉን በአዲስ አበባ ከተማ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት አስታወቀ።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ሰርቆት የነበረውን መኪና እያሽከረከረ በመሸሽ ላይ የነበረ ተጠርጣሪ ግለሰብ ሲደረግበት ከነበረው ክትትል ለማምለጥ መኪናውን ከመብራት ፖል ጋር አጋጭቶ በግለሰቦች መኖሪያ ቤት ጣሪያ በመዝለል ለማምለጥ ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ በአካባቢው ወጣቶችና ነዋሪዎች ርብርብ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሎ በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን የገለፀድ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከቅርብ ጊዜ ውዲህ የመኪና ስርቆት እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዳይለየው አሳስቧል።
Via Mayor Office of AA

#AGMAS
አግማስ የህክምና መገልገያ መሳርያዎች አስመጪ በእጆ ላይ ይገኛል፡፡ ቻናላችንን በመቀላቀል ስለእቃዎቻችን የዋጋ ቅናሾች ፡ የማጣርያ ሽያጮች እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ያግኙ፡፡
የምናስመጣቸው ምረቶች ፤ የተላዩ የኬምስትሪ ማሽኖች እና ሪኤጀንቶች፤ የራጅ እና የአልትራሳዉንድ ማሽኖች እንዲሁም ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በ +251-929 5003 77/ 78 +251-911 95 6626 ይደዉሉ
https://t.iss.one/agmasmedical

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ትላንት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ መግለጫ አውጥቶ ነበር።
ፓርቲው በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ ፤ " የሕግ የበላይነትን እና ሥርአትን ሕግን እየሸራረፉ እና መብቶችን እየጣሱ ማረገገጥ አይቻልም " ያለ ሲሆን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እያከናወነ ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ በሕግ አግባብ ብቻ እንዲያከናውን አሳስቧል።
ክልሉ እያከናወናቸው ያሉት የጅምላ እስር ለብልሹ አሰራር እና ለዘፈቀደ ውሳኔ ተጋላጭ በመሆናቸው በአስቸኳይ እንዲቆሙ ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
በሌላ በኩል ፤ የክልሉ መንግሥት እየወሰደ ባለው እርምጃ አብን አመራሮቹ እና አባላቱን ጨምሮ ባላቸው የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ምክንያት በግለሰቦች ላይ እየተፈጸመ ያለው እስር እንዲቆም እና በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት የታሰሩ ሰዎች ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠይቋል።
በተጨማሪ አብን የክልሉ መንግስት እየወሰደው ባለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ሂደት እየታዩ ያሉ ግልፅ ችግሮችን ሰበብ በማድረግ የአማራን ክልል የግጭት ማዕከል ለማድረግ እየሰሩ ያሉ ግለሰቦች እና ቡድኖችን በጽኑ አወግዛለሁ ያለ ሲሆን " ጠላት ጦርነት ለመክፈት በተዘጋጀበት ወቅት የአመጽ ጥሪ ማድረግ ያለንበትን አጠቃላይ የጸጥታ ከባቢያዊ ሁኔታ የዘነጋ እና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ከመሆኑም በላይ ለጠላት የሚደረግ ስልታዊ ድጋፍ በመሆኑ የአመጽ ጥሪ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ " ሲል በመግለጫው አሳስቧል።
(አብን ትላንት ያወጣው መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፤ ከአብን ስራ አስፈፃሚ አባልነት በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አሳውቀዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአብን አባሉ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፤ " አብን ባለፈው የካቲት አካሂዶት በነበረው ጊዜያዊ የአስፈፃሚ ሪፎርም ላይ ንቅናቄው በቀጣይ 3 ወር ውስጥ የሚያካሂደው ሪፎርም ተከናውኖ አዳዲስ አመራሮች እስኪመረጡ ድረስ ከ2 እስከ 3 ወር ላልበለጠ ጊዜ ወደ ስራ አስፈፃሚ እንድመለስ የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ ወስኖ ነበር። " ብለዋል።
አክለውም ፤ " ወደ አመራርነት የመመለስ ፍላጎት ባይኖረኝም የድርጅቴ ውሳኔ ስለነበር ውሳኔውን ተቀብየው ቆይቻለሁ " ሲሉ ገልፀዋል።
ዶ/ር ደሳለኝ ፤ " ለአጭር ጊዜ ብዬ የተመለስኩበት ጊዜ ስለተጠናቀቀ እንዲሁም ወደፊት ጊዜው ሲደርስ በምገልፃቸው ምክንያቶች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከአብን ስራ አስፈፃሚ አባልነቴ በፈቃዴ ለቅቂያለሁ " ያሉ ሲሆን በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ግን የአብን ሪፎርም በስኬት እስኪጠናቀቅ እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
" የንቅናቄው ሪፎርም በአጭር ጊዜ ተጠናቆ አብን ተጠናክሮ ሲቆም ደግሞ ልክ ከአብን ሊቀ መንበርነቴ በገንዛ ፈቃዴ እንደለቀቅሁት ሁሉ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነቴንም በገዛ ፈቃዴ በመልቀቅ አዳዲስ መሪዎች በማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ እድል እንዲያገኙ ለማድረግ መወሰኔን እገልፃለሁ " ሲሉም አክለዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#USA መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች በርካቶች በሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ከሰሞኑን ተፈፅመው በነበሩ ጥቃቶች ሰዎች ተገድለዋል ፤ ቆስለዋል። ሰሞኑን በኒው ዮርክ ግዛት በፋሎ ከተማ አንድ ነጭ ታጣቂ ጥቁሮች የሚበረክቱበት መገበያያ ሥፍራ ገብቶ ጥቃት ፈፅሞ 10 ሰዎችን ገድሏል። ይኸው ተጠርጣሪ 18 ዓመቱ ሱሆን ፔይተን ጌንድሮን ይባላል ጥቃቱን 320 ኪሎ ሜትር ተጉዞ መጥቶ መፈፀሙን ፖሊስ ገልጿል። አሜሪካዊው…
#US
በየጊዜው በርካቶች በታጣቁ ሰዎች በሚከፈት ተኩስ የሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ትላንትም እጅግ በጣም ዘግናኝ የሚባል ጥቃት ተፈፅሞ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት ተገድለዋል።
በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት አንድ የ18 ዓመት ወጣት በከፈተው የተኩስ እሩምታ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት መገደላቸውን ተዘግቧል።
ድርጊቱ የተፈፀመው በደቡብ ቴክሳስ ግዛት፣ ዩቫልዲ ከተማ ሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው አንድ ወጣት ድንገተኛ ተኩስ ከፍቶ ነው 19 ህፃናትን ጨምሮ 2 አዋቂዎችን የገደለው።
ከተገደሉት ሁለት አዋቂዎች አንዷ በዚያው ትምህርት ቤት የምታስተምር መምህርት ነበረች።
ፖሊስ እንዳለው ድርጊቱ የፈፀመው ወጣት የታጠቀው ኤአር-15 ከፊል አውቶማቲክ ጠመንጃ ነበር።
ወጣቱ መጀመርያ ሴት አያቱን ከገደለ በኋላ ነው ሕጻናቱን በግፍ የገደላቸው ተብሏል።
አንዳንድ መገናኛ ብዙኃን ወጣቱ በዚያው አካባቢ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት የ2ኛ ደረጃ ተማሪ እንደሆነ እየዘገቡ ይገኛሉ።
የቴክሳስ ግዛት ገዥ ግሬግ አቦት ወጣቱ " ሳልቫዶር ራሞስ " እንደሚባልና መኪናውን ደጅ አቁሞ ወደ ትምህርት ቅጥር ግቢው ከገባ በኋላ አሰቃቂው ድርጊት እንደፈጸመ ተናግረዋል።
አሶሲየትድ ፕሬስ እንደዘገበው ከትምህርት ቤቱ በቅርብ የነበረ አንድ የድንበር ጠባቂ ፖሊስ የተኩስ ድምጽ ሰምቶ ወደ ትምህርት ቤቱ በመግባት ይህን ወጣት ታጣቂ ተኩሶ ባይገድለው ኖሮ የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊሆን ይችል ነበር።
እንደ Gun Violence Archive ድረገፅ መረጃ በአሜሪካ ሀገር ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ (በመሳሪያ እራሳቸውን የሚያጠፉትን ጨምሮ) በየዓመቱ #አርባ_ሺህ (40,000) ይሞታሉ።
(ኤፒ/ቢቢሲ - ፎቶ - ሶሻል ሚዲያ)