TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢሰመኮ የፌዴራል መንግሥት እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች "በተቀናጀ መንገድ የሕግ በላይነትን ማስከበር" በሚል ባለፉት ጥቂት ቀናት መውሰድ በጀመሩት እርምጃ፣ ጋዜጠኞችና የማኅበረሰብ አንቂዎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን ገልጿል።

ኢሰመኮ ሁኔታዎችን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ገልጾ፤ የተወሰኑት ተጠርጣሪ ታሳሪዎች በቤተሰቦቻቸው የተጎበኙና በተለያየ የጊዜ መጠን ወደ ፍ/ቤት የቀረቡ ቢሆንም በርካታ ታሳሪዎች ከፍ/ቤት ትዕዛዝ ውጭ መታሰራቸውን፣ ፍ/ቤት ያለመቅረባቸውን፣ በቤተሰብ አለመጎብኘታቸውን አመልክቷል።

 በተለይ በአማራ ክልል በርካታ ታሳሪዎች ከመደበኛ መኖሪያ አካባቢያቸውና ከመደበኛ እስር ቦታዎች ውጭ ጭምር በመታሰራቸው ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን እንኳን ለማወቅ መቸገራቸውን አስረድቷል።

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር መንግሥት በሕጋዊ መንገድ ሊወስድ የሚችላቸውን እርምጃዎች እገበዘባለሁ ያለው ኮሚሽኑ " የዚህ አይነት የሰብአዊ መብቶች መርሆዎችን ያልተከተለና የተስፋፋ እስር ተገቢ አለመሆኑን " ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ገልጸዋል።

" በተለይ የፌደራል ሆነ የክልል የፀጥታ ኃይሎች ተጠርጣሪዎችን ከወንጀል ምርመራ በፊት ከማሰር፣ ጋዜጠኞችን በስራቸው ምክንያት ከማሰር እና ከፍ/ቤት ትዕዛዝ ውጭ ሰዎችን ከማሰር ሊታቀቡ ይገባል። በማናቸውም አይነት ሁኔታ የታሰሩ ሰዎች ሁሉ ቤተሰቦቻቸው ወዲያውኑ እንዲያውቁ እንዲደረግና ወደ ፍ/ቤትም ሊቀርቡ ይገባል” ብለዋል፡፡

አክለውም ኮሚሽኑ በማናቸውም ስፍራ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሁኔታ በድንገተኛ ጉብኝት ለመከታተል በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት፣ ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን ገልፀው ሁሉም የፌደራልና የክልል መንግሥታት አካላት ለኮሚሽኑ ሥራ የመተባበር ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

@tikvahethiopia
#ኮሮጆ
ከቦታ ወደ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የሚፈልጉትን እቃ መግዛት እጅግ አድካሚ ሆኗል። በተጨማሪም የሚፈልጉትን እቃ ማግኘት እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት እጅግ አዳጋች ነው። የግዢ ሂደትዎን በማዘመን ቤትዎ ውስጥ ሆነው ወይም ስራ ቦታ ስልክዎን ብቻ በመጠቀም Korojo መተግበሪያ ላይ የፈለጉትን ማማረጥና መሸመት ይችላሉ።

መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፤ የፈለጉትን ይሸምቱ። https://korojo.app/download
#AmharaRegion

የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ፤ በክልሉ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቋል።

ቢሮው ዛሬ ግንቦት 15/2014 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሰሞኑን መንግሥት ያካሄደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ መሆኑን አመልክቷል።

የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳሳለኝ ጣሰው የአማራ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅ ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ከ4 ሺ በላይ ሰዎች መካከል 40 የሚሆኑት ከዚህ ቀደም በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው ፍርድ የተላለፈባቸው መሆናቸው የተጠቀሰ ሲሆን 210 የሚሆኑት ደግሞ በነፍስ ግድያ የተጠረጠሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አቶ ዳሳለኝ ጣሰው በአሁኑ ወቅት መንግሥት ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ከሚደረግ ሥራ ውጭ ክልሉ አስተማማኝ ሰላም ላይ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

" ትክክለኛውን የፋኖ ስም የማይወክሉ፣ በፋኖ ስም ተደራጅተው በሕዝብ ላይ የተለያዩ ሕገ ወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ ቡድኖችን መንግሥት አይታገስም " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
በዲማ ወረዳ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ግለሰቦች በተፈፀመ ጥቃት የ6 ዜጎች ህይወት አልፏል።

ከትላትን በስቲያ ፤ በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ በሚገኘው ስደተኛ መጠለያ ጣቢያና በመርከስ ቀበሌ ለጊዜው ማንነታቸው አልታወቀም በተባሉ ግለሰቦች የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ፤ " ቅዳሜ ምሽት 3:30 አካባቢ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በፈጸሙት ጥቃት የ4 ሰው ህይወት አልፏል " ብሏል።

ግለሰቦቹ ከዲማ ከተማ 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ኡኩጎ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ በመግባት ጥቃት ማድረሳቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ ከቀኑ 10:30 አካባቢ በመርከስ ቀበሌ " ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ " ግለሰቦች በፈጸሙት ጥቃት በሞተር ሳይክል እየተንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

'አዩቴ ኢትዮጵያ ቻሌንጅ-AYuTe Ethiopia Challenge ' የተሰኘና በኢትዮጵያ ግብርናን ለማሻሻል የሚረዳ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ዕድሜያቸው ከ18-29 የሆኑ ኢትዮጵያንን የሚያሳትፍ ውድድር ይፋ ሆኗል።

ውድድሩ፥ በኢትዮጵያ ያሉ አነስተኛ አርሶ አደሮችን ተግዳሮቶች መቅረፍ ምርትን ምርታማነትን፣ ገቢን፣ የፋይናንስ አቅርቦትንና የመቋቋም አቅም ያላቸውን የግብርና ቴክኖሎጂ ሀሳቦችን አወዳድሮ ለመሸለም ያለመ ነው።

የማመልከቻ ጊዜው ከግንቦት 13 ቀን 2014 ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ አሸናፊዎች 20 ሺ ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቷል።

ለማመልከት : https://ayute-ethiopia.et/apply-here/

@tikvahethmagazine
#አቢሲንያ_ባንክ

ገንዘብ በጣም አስፈለገዎት፣ ክፍት የሆነ ባንክ የለም ? የ ኤ.ቲ.ኤም ካርድዎንም አልያዙም ? አይጨነቁ የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግን ተጠቅመው በአቅራቢያዎ ከሚገኙት የ ኤ.ቲ.ኤም ማሽኖች ያለ ካርድ ገንዘብዎን በቀላሉ ማውጣት ይችላሉ።

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
" በወረርሽኝ፣ በድርቅ፣ በረሃብ እና በጦርነት ምክንያት አስፈሪ ሁኔታን ተጋፍጠናል " - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

ዓለም የኮቪድ 19-ወረርሽኝ ወረርሽኝን፣ የዩክሬን ጦርነትን እና የዝንጀሮ ፈንጣጣ (ሞንኪፖክስ)ን ጨምሮ አስፈሪ ፈተናዎችን እየተጋፈጠች ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ይህንን ያሉት የተባበሩት መንግሥታት የጤና ባለሥልጣናት ከአፍሪካ ውጪ በ15 አገራት በተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ዙሪያ በጀኔቫ በተካሄደው ውይይት ላይ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው እስካሁን በመላው ዓለም 92 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፣ 28 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሳይያዙ እንዳልቀረ ተጠርጥሯል።

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ፤ " በዓለማችን ያለው ቀውስ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ብቻ አይደለም። በዓለም ዙሪያ ያሉ ባልደረቦቻችን በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለኢቦላ ወረርሽኝ ፣ በአፍጋኒስታን ፣ በኢትዮጵያ ፣ በሶማሊያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በሶሪያ፣ በዩክሬንና በየመን ደግሞ ውስብስብ ለሆነ ሰብዓዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት እየሰሩ ነው" ብለዋል።

" በወረርሽኝ፣ በድርቅ፣ በረሃብ እና በጦርነት ምክንያት አስፈሪ ሁኔታን ተጋፍጠናል " ሲሉ መግለፃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/WHO-05-23

@tikvahethiopia
#Update

ወደ ባህሬን ተቋርጦ የነበረው በረራ ከግንቦት 24 ጀምሮ ይጀምራል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደባህሬን አቋርጦ የነበረውን በረራ በሳምንት 3 ጊዜ ከግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን ገልጿል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
" የMokeypox በሽታ መስፋፋት ለኢትዮጵያም ስጋት ነው "

በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና መረጃ ስርዓት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዘውዱ አሰፋ ለአል ዓይን ኒውስ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

" ቫይረሱ ከዚህ በፊት ፈንጣጣ መሰሉ በሽታ ተጠቂ የሌለባቸው ሀገራት ሳይቀር እየተስፋፋ ነው፡፡

እንደማንኛውም ሀገር እኛም በቫይረሱ ስርጭት ስጋት አለን። በኢትዮጵያ የመግቢያ እና መውጫ በሮች ላይ የተለመደው ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

በሀገሪቱ የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት መግቢያ እና መውጫ ላይ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እና ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳይሄድ የተላላፊ በሽታዎች ክትትል እየተደረገ ነው።

የበሽታው ተጠቂ በኢትዮጵያ ቢገኝ ማድረግ ስለሚገባን ስራዎች፣ ለህብረተሰቡ መሰጠት ስለሚገባው የግንዛቤ ፈጠራ መልዕክት እና የህክምና ክትትል ስራዎችን ለመለየት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመሰራት ላይ ነው "

@tikvahethiopia
#ኮሮጆ
ከቦታ ወደ ቦታ እየተንቀሳቀሱ የሚፈልጉትን እቃ መግዛት እጅግ አድካሚ ሆኗል። በተጨማሪም የሚፈልጉትን እቃ ማግኘት እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት እጅግ አዳጋች ነው። የግዢ ሂደትዎን በማዘመን ቤትዎ ውስጥ ሆነው ወይም ስራ ቦታ ስልክዎን ብቻ በመጠቀም Korojo መተግበሪያ ላይ የፈለጉትን ማማረጥና መሸመት ይችላሉ።

መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፤ የፈለጉትን ይሸምቱ። https://korojo.app/download
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኮሎኔል_ገመቹ_አያና ➡️ " ኮሎኔል ገመቹ አያናን ከኦሮሚያ ፖሊስ በአደራ ከመቀበል ውጪ ምንም የወንጀል የምርመራ መዝገብ በስማቸው የለንም ፤... ኮለኔል ገመቹን ይዘን ወደ ኦሮሚያ ፖሊስ በመሔድ ተረከቡን ብለን ስንጠይቅ ኦሮሚያ ፖሊስ እኛ ጋር ጉዳይ የለውም የሚል ምላሽ ሰጥቶናል " - ኮማንደር ኤርትሮ ኦቦ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ➡️ " ኮ/ል ገመቹ መታሰራቸውን አንፈልግም ቢለቀቁ አልቃወምም "…
#Update

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር የሆነት ኮነሌል ገመቹ አያና ከስር እንዲለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ወሰነ።

ኮነሌል ገመቹ አያና በግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ/ም በተከሰሱበት በሽብር ወንጀል በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረሽብርና የህገመንግክት ጉዳዮች ወንጀል ችሎች በነጻ ከተሰናበቱ በኋላ በነጋታው ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ሲወጡ በኦሮሚያ ፖሊስ ተይዘው ለ6 ወር በገላን ፓሊስ ጣቢያና በወታደራዊ ካንፕ እንዲሁም በአዋሽ መልካሳ በአንድ ጀነራል ዶሮ እርባታ ውስጥ ታስረው እንደነበርና ከህዳር 16 ጀምሮ ደግሞ በፌደራል ፖሊስ በስር ላይ እንደነበሩ ለፍርድ ቤት አስረድተው ነበር።

ኮነሌል ገመቹ አያናን በአደራ ከመቀበል ውጪ ምንም የወንጀል የምርመራ መዝገብ እንዳልተከፈተበት የፌደራል ፖሊስ ቀርቦ ማብራሪያ መስጠቱንም ይታወሳል።

ሰበር ሰሚ ችሎቱ የኦሮሚያ ፖሊስ ቀርቦ የኮነሌል ገመቹ የእስራት ሁኔታን እንዲያስረዳ ታዞ የነበረ ሲሆን ትላንት በነበረ ቀጠሮ ችሎት አልቀረበም።

ይህን ተከትሎ መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ችሎቱ ለዛሬ በይደረሰ ቀጥሮ የነበረ ሲሆን መርምሮ ኮነሌል ገመቹ አያና ከስር እንዲፈቱ ወስኗል።

ምንጭ ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

መልቲቾይስ አፍሪካ/DSTV በየዓመቱ ለወጣት የፊልም ባለሙያዎች የአንድ ዓመት የፊልም ጥበብ ስኮላርሺፕ ይሰጣል።

የመልቲቾይስ ታለንት ፋክተሪ የስኮላርሺፕ ዕድል ወጣት ባለሙያዎችን ኬንያ በሚገኘው የመልቲቾይስ አካዳሚ የፊልም ጥበብ እውቀታቸውን የሚያጎለብቱበት ዕድል ይፈጥራል።

እድሚያችሁ ከ18-30 የሆነ ወጣቶች እስከ ግንቦት 26/2014 ዓ.ም ተከታዩን ሊንክ በመጠቀም ማመልከት ትችላላችሁ፦

www.multichoicetalentfactory.com

ለበለጠ መረጃ፦

https://cte.multichoicetalentfactory.com/Master/entrycriteria

(ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity