TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር የሆነት ኮነሌል ገመቹ አያና ከስር እንዲለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ወሰነ። ኮነሌል ገመቹ አያና በግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ/ም በተከሰሱበት በሽብር ወንጀል በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረሽብርና የህገመንግክት ጉዳዮች ወንጀል ችሎች በነጻ ከተሰናበቱ በኋላ በነጋታው ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ሲወጡ በኦሮሚያ…
ኮለኔል ገመቹ አያና ዛሬ ከታሰሩበት ተፈተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸው ታውቋል።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር ኮነሌል ገመቹ አያና በስር ፍርድ ቤት ነጻ ከተባሉበት ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ለ 6 ወራት በኦሮሚያ ፖሊስ ቀሪውን ከህዳር 16 ጀምሮ ደግሞ በፌደራል ፖሊስ በአጠቃላይ ለአንድ አመት ካለፍርድ ቤት ትዛዝ በእስር ላይ እንደነበሩ መግለጻቸውን ተከትሎ የዓቃቤ ህግን የይግባኝ መዝገብን ሲመለከት የነበረው የጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት የኦሮማያ ፖሊስ በእስራት ሁኔታቸው ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ታዞ ባለመቅረቡ ካለምክንያት መታሰር የለባቸውም ዜጎች ሰብዓዊ መብት መጣስ የለበትም ሲል ከእስር እንዲፈቱ አዟል።
በትዛዙ መሰረት ኮለኔል ገመቹ ዛሬ ከታሰሩበት ከፌደራል ፖሊስ ተፈተው ቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
(ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ)
@tikvahethiopia

#የመኪና_ስርቆት
አዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው ኦፕሬሽን በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ 22 ተሽከርካሪዎችን እና 33 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ይስተዋል የነበረውን የተሽከርካሪ ስርቆት ለመከላከል እና ወንጀል ፈፃሚዎችን ህግ ፊት ለማቅረብ የአዲስ አበባ ፖሊስ በጥናት ላይ በመመስረት የምርመራ እና የክትትል ቡድን አቋቁሞ ባካሄደው ኦፕሬሽን በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ 22 ተሽከርካሪዎችን ማስመለሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።
ተሽከርካሪዎቹ እየተሰረቁ አብዛኞቹ ወደ #ሃዋሳ ከተማ እንደሚወሰዱ በምርመራ ማረጋገጥ እንደተቻለ የገለፀው ፖሊስ ከተሰረቁት ተሽከርካሪዎች መካከል ሰባቱ በአዲስ አበባ የተገኙ ሲሆን የተቀሩት 15 ተሽከርካሪዎች ደግሞ በሀዋሳ ከተማ እና ከሀዋሳ ከተማ 100 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኝ አነስተኛ ከተማ ተይዘው ዛሬ ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ/ም ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መደረጉን አሳውቋል።
ተሽከርካሪ በመስረቅ፣ የተሰረቀውን ተሽከርካሪ በመግዛት እና በመደለል ተሳትፎ ያደረጉ ከአዲስ አበባ 19 ከሃዋሳ ደግሞ 14 በአጠቃላይ 33 ግለሰቦች ተይዘው ምርመራው በስፋት መቀጠሉን ፖሊስ አክሎ አመልክቷል።
ተሽከርካሪዎቹን ለጥበቃ ምቹ በሆነ ቦታ ባለማቆም በሚፈጠር ክፍተት እና አሽከርካሪዎች ለልዩ ልዩ ጉዳይ የመኪናቸውን ቁልፍ ተሽከርካሪ ላይ ጥለው ሲወርዱ እና የተሽከርካሪውን ቁልፍ በልዩ ልዩ አጋጣሚ በማስቀረፅ ወንጀል ፈፃሚዎቹ የስርቆት ወንጀሉን ሲፈፅሙ እንደነበር በምርመራ ተረጋግጧል።
አዲስ አበባ ፖሊስ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ አስገንዝቦ ለስራው ስኬታማነት ድጋፍ ላደረጉት የፌዴራል ፖሊስና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋና አቅርቧል።
Via - AA POLICE

ከዓለም ዙሪያ #1 ፦
➡️ #ሴኔጋል ፦ በምዕራብ ሴኔጋል ፤ ቲቫዋን በምትሰኝ ከተማ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰ ቃጠሎ 11 አዲስ የተወለዱ ህጻናት መሞታቸውን ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ተናግረዋል።
➡️ #አፍጋኒስታን ፦ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል እና ሰሜናዊ ከተማ ማዛር ኢ ሻሪፍ ከተከታታይ በደረሱ ፍንዳታዎች ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። ዳኢሽ ለጥቃቱ ኃላፊነት መውሰዱን ሮይተርስ ዘግቧል።
➡️ #ሩስያ ፦ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ ለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ወታደሮቻቸውን ወደ ሀገሪቱ ከላኩ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩክሬን ውስጥ በወታደራዊ ዘመቻው ከቆሰሉ ወታደሮች ጋር ተገናኝተዋል። በሌላ የሩስያ ጉዳይ ፤ ሀገሪቱ ያለባትን የውጭ ሀገራት እዳ በራሷ መገበያያ ገንዘብ “ሩብል” ለመክፈል ወስናለች ፤ እዚ ውሳኔ ላይ የደረሰችው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ከቀናት በፊት በሩሲያ በአሜሪካ ባንኮች በኩል የምትፈጽመውን የውጭ ዕዳ ክፍያ ፍቃድ መሰረዙን ተከትሎ ነው።
➡️ #ዩክሬን ፦ ወደ ሰቨሮዶንስክ ከተማ የሚወስደውን አውራ ጎዳና ለመቆጣጠር በሩስያ እና ዩክሬን ኃያሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተደረገ ነው። ሩሲያ ይህን ከተማ ለመቆጣጠር ተቃርቢያለሁ ብትልም አንድ ከፍተኛ የዩክሬን ባለሥልጣን ነገሩን አስተባብለዋል። ይህ ጎዳና ዩክሬን የምትቆጣጠራቸውን ከተሞች ሩሲያ ከያዘቻቸው ከተሞች ጋር የሚያገናኝ ከፍ ያለ ወታደራዊ ዋጋ ያለው ነው።
➡️ #ጋምቢያ ፦ የጋምቢያ መንግስት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ከ20 አመታት በላይ በዘለቀው የስልጣን ዘመናቸው ተፈጽመዋል በተባሉ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ማሰቃየት እና ሌሎች ወንጀሎች ላይ ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል።
#አልጀዚራ #ቲአርቲወርልድ #ስፑትኪን #ሮይተርስ

#Motta 📍
የሞጣ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ኮማንድ ፖስት ፤ በህግ የሚፈለጉ ግለሰቦች በሁለት ቀን ለመንግስት እጅ እንዲሰጡት አሳሰበ።
ኮማንድ ፖስቱ ይህን ያሳሰበው ትላንት ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ/ም በወቅታዊ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ ነው።
በህግ የሚፈለጉ ግለሰቦች ከሁለት ቀን ሞጣ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት በመቅረብ ለመንግስት እጅ እንዲሰጡ ያሳሰበው ኮማንድፖስቱ ግለሰቦቹ በተሰጣቸው እድል ባለመጠቀም ለሚወሰደው ርምጃ ሁሉ ሀላፊነት አልወስድም ብሏል።
በሌላ በኩል ፤ ኮማንድ ፖስቱ ፦
➡️ ማንኛውንም ህ/ሠብ በቡድን መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን ገልጿል።
➡️ ማንኛውም ማህበረሰብ በህግ የሚፈለጉ አካላትን ደብቆ ወይም አከራይቶ ቢገኝ ተጠያቂ መሆኑን አውቆ ችግር ፈጣሪዎችንና ተፈላጊዎችን አጋልጦ እንዲሰጥ አሳስቧል።
➡️ ከጠዋቱ 12:30 በፊትና ከምሽቱ 1: 30 በኋላ ስምሪት ከተሰጣቸው የጸጥታ ሀይሎች ውጭ የእንቅስቃሴ ገደብ ተቀምጧል። ይህ ሳይሆን ቢቀር የጸጥታ ሀይሉ እርምጃ ይወስዳል ተብሏል።
➡️ ስምሪት ከተሰጠው የጸጥታ ሀይል ውጭ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈጽሞ ተከልክሏል።
(ተጨማሪ ክልከላዎችን ከላይ ያንብቡ)

🫂 ከጭልጋና አካባቢው ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖች ወደ ቦታቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።
በጭልጋና አካባቢዋ ተፈናቅለው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሠራ እንደሚገኝ ተነግሯል።
ከትላንት አንስቶ ከአይከል እና በዙሪያዋ ተፈናቅለው የነበሩ 11 ሺህ 938 የህበረተሰብ ክፍሎች ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ሲሆን ወደ አይከል ከተማ ሲገቡ ማህበረሰቡ በነቂስ ወጥቶ ተቀብሏቸዋል።
ተፈናቃዮቹ ከዚህ በፊት በአይከል ከተማና በአካባቢዋ ይኖሩ የነበረ ሲሆን ከማንነት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከቦታቸው ተፈናቅለው በተለያዬ ቦታ ነበሩ። አሁን ላይ በተፈጠረው አንፃራዊ ሰላም ከትላንት አንስቶ ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል።
ፎቶ ፦ የጭልጋ ኮሚኒኬሽን