TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የነዳጅ_ዋጋ !

አሁን በዓለም ገበያ 1 በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ 106.6 ዶላር እየተሸጠ የሚገኝ ሲሆን በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት አንድ በርሜል ነዳጅ 104.3 ዶላር በሆነ ዋጋ እየተሸጠ ይገኛል።

#OilPrice

@tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ያለበት ቦታ ሳይታወቅ ቀናት መቆጠራቸው እንዳሳሰባቸው ጠበቃው ተናገሩ።

እሁድ ሚያዚያ 23/2014 ዓ.ም. በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎ በቁጥጥር ሥር ውሏል የተባለውን የጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ አድራሻን ማወቅ እንዳልተቻላቸው ጠበቃው አዲሱ አልጋው ተናግረዋል።

ጠበቃው እንዳሉት እሁድ ረፋድ ላይ የታጠቁ እና ሲቪል የለበሱ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ጋዜጠኛው ተከራይቶ ወደ ሚኖርበት ጊቢ በአጥር ዘለው ከገቡ በኋላ 'ለጥያቄ ትፈለጋለህ' ብለው ደንበኛቸውን ይዘው መሄዳቸውን ተናግረዋል።

ጋዜጠኛው በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ከዋለ 48 ሰዓታት ቢያልፉም እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረቡ እና ታስሮ የሚገኝበትን ቦታ ለማወቅ ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#GONDAR

የአማራ ክልል ሰላም እና ህዝብ ደህንነት ቢሮ በጎንደር ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉ 6 የፖለቲካ እና የፀጥታ መዋቅር አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ ነው ብሏል።

እነዚህ ስድስት የፖለቲካና የፀጥታ መዋቅር አመራሮች ስማቸው በይፋ ያልተገለፀ ሲሆን በምን አይነት የአመራርነት ቦታ ላይ ያሉ እንደሆኑ አልተብራራም።

ቢሮው ፤ ከህዝቡ ፣ ከፖለቲካ አመራሩ እና ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ውይይት እና ግምገማ ከተደረገ በኃላ የማስተካከያ እና የእርምት እርምጃዎች እንደሚወሰዱ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሁለተኛውን ብሔራዊ የሥራ ጉባኤ አስመልክቶ ንግድ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር አዘጋጅቷል፡፡

ውድድሩ በ2 ዙር የሚደረግ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር ምርጥ አስር የንግድ ሥራ ሀሳቦች የሚለዩ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ምርጥ ሦስቱ ተለይተው የሥራ ማስኬጃ ካፒታል የሚሰጣቸው ይሆናል ተብሏል።

መስፈርቶች፦

- የሥራ ፈጠራው ኦርጂናል እና ፈጽሞ ያልተተገበረ መሆን አለበት፤

- የንግድ ሀሳቡ ባለቤት/ቶች ኢትዮጵያዊ/ያን መሆን አለባቸው፤

- የንግድ ሀሳቡ ኢትዮጵያ ውስጥ መተግበር አለበት

- ሴቶች፤ አካል ጉዳተኞች፤ ተፈናቃዮች እና ቤት አልባ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ይበረታታሉ።

የማመልከቻ ጊዜው ግንቦት 02 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 12 ሰዓት የሚያበቃ ይሆናል።

ሙሉ መረጃውን በማግኘት ለመወዳደር ተከታዩን አድራሻ ይክፈቱ https://forms.gle/c1kNcPAKQUMA459J7

@tikvahethmagazine
" ሀገር ፈርሳ ተቅበዝባዥ ከመሆናችን በፊት ሁሉም ለሀልዎቷ ዘብ ይቁም " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ልኮልናል።

ፓርቲው ፤ በመግለጫው ከሰሞኑን በጎንደር ከተማ የተፈጠረውን ክስተት ይህን ተከትሎም በስልጤ ዞን የተፈጠረውን ክስተት ዳሷል።

በተጨማሪ ሰሞኑን በደራሼ ስለተፈጠረው ችግር አንስቷል።

እናት ፓርቲ ፤ ከሰሞኑን ከሃይማኖት ጋር የተፈጠሩ ክስተቶችን በቅርበት ሲከታተል መቆየቱን አመልክቶ አሰባሰብኩኝ ባለው መረጃና ማስረጃም ጉዳዩ ለሀገር አንድነት የሚቆሙ የሃይማኖት ተቋማትን በማፍረስ ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ እንጂ ሃይማኖታዊ ግጭት አይደለም ብሏል።

ፓርቲው በጎንደር ከተማ እና በስልጤ ዞን ወራቤ በደረሰው ነገር ሁሉ ማዘኑን ገልጾ ፤ ጥቃት የተሰነዘረባቸው ወገኖች ሲሳደዱ በየቤታቸው አስገብተው ከጥቃት የመታደግ ሥራ በመሥራት ኢትዮጵያዊ ከፍታቸውን በመከራ ወቅት ላሳዩ ወገኖች ምስጋና አቅርቧል።

በሌላ በኩል በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልል፣ በደራሼ ልዩ ወረዳ፣ ጊዶሌ ከተማና አካባቢው ላይ በዚሁ ሰሞን " የጠየቅነውና ቃል የተገባልን ለምን አይፈጸምም ? " በሚል መነሻ እንዲሁም በአስተዳደሩ እንዝህላልነት ችግር ተከስቶ ቀላል የማይባል የሰው ሕይወት እንደጠፋ፣ ንብረት እንደወደመ አመልክቶ ይህም ሀዘኑን እጥፍ ድርብ እንዳደረገበት ገልጿል።

(ሙሉ መገለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#መግቢያ_ቀናት

የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አዲስ የተመደቡላቸውን ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን እና ሪፖርት የሚያደርጉበትን ቀን እያሳወቁ ይገኛሉ።

እስካሁን ባለው የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ያሳወቁ ተቋማት እና የአዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መግቢያ/ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ፦

👉 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ሚያዚያ 24 እና 25/2014 ዓ/ም ፤ በረመዷን በዓል ምክንያት መድረስ ለማይችሉ እስከ አርብ ሚያዚያ 28 /2014 ዓ/ም ድረስ

👉 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኦንላይን ምዝገባ ግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ/ም ፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ግንቦት 8 እና 9/2014 ዓ/ም

👉 ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም

👉 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 27 እና 28/2014 ዓ/ም

👉 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2 /2014 ዓ/ም

👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ/ም

👉 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 29 እና 30 /2014 ዓ/ም

👉 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እስከ 30 /2014 ዓ/ም

👉 ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እና 29/2014 ዓ/ም

👉 ASTU / AASTU ሚያዚያ 28 እና 29 /2014 ዓ/ም በቅጣት ግንቦት 1 /2014 ዓ/ም

👉 ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ፤ ምዝገባ ግንቦት 10 እና 11

👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 01 እና 02 /2014 ዓ/ም

👉 ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግንቦት 12፣ 13 እና 14

ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎች ጥሪ ሲያቀርቡ ተከታትለን የምናሳውቅ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጉዳይ ብቻ በ @tikvahuniversity መከታተል ይቻላል።

@tikvahethiopia
" የኢትዮጵያ እና አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ እንዲሻሻል በትኩረት ይሰራል " - አምባሳደር ስለሺ በቀለ

በአሜሪካ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ስለሺ በቀለ የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ እንዲሻሻል በትኩረት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

አምባሳደሩ ይህን ያሉት ዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች እና ሰራተኞች ጋር ትውውቅ ባደረጉበት ወቅት ነው።

አምባሳደር ስለሺ እንደገለጹት የሚሲዮኑ ባልደረቦች ዋና ትኩረት ዘመናትን ያስቆጠረው የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲሻሻል ሁሉን አቀፍ ጥረት ማድረግ ላይ ይሆናል።

በዳያስፖራ ተሳትፎ፣ ህዝብ ለህዝብ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ንግድና ኢንቨስትመንት፣ ገጽታ ግንባታ፣ ቱሪዝምና በሌሎች ዘርፎች ያለውን ትብብር ማጎልበት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የሚሲዮኑ ባልደረቦች የአገራቱ ግንኙነት ዘመናትን ያስቆጠረውን ዲፕሎማሲያዊ መስተጋብር የሚመጥን እንዲሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ በሙሉ አቅም እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

መረጃው የኤምባሲው ነው።

@tikvahethiopia
#Hawassa

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ለኢንቨስትመንት የተሰጡ እና እስካሁን ያልለሙ መሬቶች ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ ወስኛለሁ አለ።

በከተማው ውስጥ ለኢንቨስትመንትና ለተለያዩ አገልግሎቶች መሬት ወስደው ካላለሙና ከአቅም በታች ካለሙ ግለሰቦችና ተቋማት እጅ መሬት ለመንጠቅ መወሰኑን አስተዳደሩ አሳውቋል።

የከተማው ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በተለያዩ ጊዜያት ለኢንቨስትመንት ከተሰጡ በርካታ መሬቶች ውስጥ 17ቱን ከዛሬ ጀምሮ የመንጠቅና ወደ መሬት ባንክ የማስገባት ስራ ይሰራል ብሏል።

ዛሬ የሚጀመረው የመጀመሪያ ዙር ሲሆን በቀጣይ ጊዜያት ያልለሙ መሬቶች ላይም እርምጃው ይቀጥላል ብሏል፤ ስራው ጥንቃቄ ሚፈልግና በባለሀብቱ ዘንድ ቅሬታ በማይፈጥር መልኩ ስለሚሰራ በዙር ማከናወን አስፈላጊ ይሆናል ሲል መምሪያው ገልጿል።

ዛሬ እርምጃው ተግባራዊ የሚሆንባቸው 10ሩ በአገልግሎት ዘርፍ ፣ 6ቱ በኢንደስትሪው ዘርፍና 1ዱ በግብርና ዘርፍ ለመሰማራት የተሰጡ መሬቶች ሲሆኑ በጥቅሉ ከ321 ሄክታር በላይ መሬት ወደ መሬት ባንክ ይገባል መባሉን የከተማው ኮሚኒኬሽን መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#ችሎት

በአዲስ አበባ ከተማ በተከበረው በዒድ አል ፈጥር በዓል ላይ በመስቀል አደባባይ አካባቢ የአድማ ብተና የጭስ ቦንብ በማፈንዳት ወንጀል የተጠረጠረ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ፍርድ ቤት ቀረበ።

የፌደራል ፖሊስ የ 'አድማ ብተና ዘርፍ አባል' የሆነው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ከትናንት በስቲያ ሰኞ በአ/አ በተከበረው የዒድ አል ፈጥር በዓል ላይ በመስቀል አደባባይ የሰማዓታት መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ ከፈነዳው የአድማ በታኝ የጭስ ቦንብ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውሎ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ዛሬ ረፋድ ላይ ቀርቧል።

መርማሪ ፖሊስ ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በዓሉ ዕለት በተመደበበት ወንጀል የመከላከል ምደባ ላይ እያለ የታጠቀውን አድማ በታኝ የጭስ ቦንብ በአግባቡ መታጠቅ ሲገባው በአግባቡ ባለመታጠቅ የጭስ ቦንቡ እንዲፈነዳና ሁከት እና ብጥብጥ እንዲፈጠር አድርጓል ያለው መርማሪ በዚህ በተፈጠረ ሁከትና ብጥብጥ የመንግስትና የግለሰብ ንብረት ጉዳት መድረሱን አብራርቷል።

በተጠረጠረበት ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት ወንጀል ለተጨማሪ ማስረጃ አሰባስቦ ለመቅረብ 14 ቀን እንዲሰጠው መርማሪው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ በበኩሉ በዕለቱ አስቀድሞ በተመደበበት ቦታ ከለሊቱ ሰባት ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ እንደነበር እና በሰዓቱ በቦታው ላይ የነበሩ ሰዎች ቁጥር መጨመርና መጨናነቁን ተከትሎ ከታጠቀው ሶስት አድማ በታኝ የጭስ ቦንብ ውስጥ አንደኛው በማያውቀው ሁኔታ መሬት ላይ ወድቆበት በድንገት መፈንዳቱን ገልጿል።

ሆኖም ምንም አይነት ተንኮልም ሆነ ክፋት በውስጤ አልነበረም ወድቆ ሲፈነዳ እኔ እራሴ ደንግጬ ነበር ሲል እያለቀሰ ሁኔታውን ለችሎቱ አስረድቷል።

በተጨማሪም ተጠርጣሪው ወላጆቹን በሞት ማጣቱን ገልጾ እህትና ወንድሙን በሱ እርዳታ እያስተማራቸው እንደሆነ እና ከለሊት 7:00 ጀምሮ ለጥበቃ ስራ ከመሰማራቴ ውጪ ሌላ ክፋት በውስጤ የለም ሲል ለችሎቱ አብራርቷል።

ጉዳዩን የተከታለው ፍርድ ቤቱ ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ 14 ቀን ፈቅዷል። ለግንቦት 10 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
የአለም ዋንጫ ወደ ሀገራችን ይመጣል !

የ ኳታሩ የአለም ዋንጫ ከመጀመሩ አስቀድሞ የ አለም ዋንጫ ለእይታ ከሚቀርቡባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ሀገራችን ቀዳሚዋ ነች ።

የአለም ዋንጫው በዚህ ዓመት በቀዳሚነት ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ የሁለት ቀን ቆይታ እንደሚኖረው ተገልጿል ።

የአለም ዋንጫው ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ሀገራችን ሲመጣ በዘንድሮው አመት ግንቦት 16 እና 17 በሀገራችን ቆይታን ያደርጋል ።

ከአለም ዋንጫው ጋር የ 1998ቱ የአለም ዋንጫ አሸናፊ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን አጥቂ ዴቪድ ትሪዝጌት እንደሚመጣ ተነግሯል ።

https://t.iss.one/tikvahethsport

@tikvahethsport
#Kenya

ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በርካታ የፀጥታ ኃይሎችን አሰማርታለች።

በሀገሪቱ የማርሳቢት ግዛት ውስጥ በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት ምክንያት በርካታ ሰዎች መገዳላቸውን ተከትሎ ነው በሺዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶችና የፀጥታ ኃይሎች የተሰማሩት።

የሀገሪቱ መንግስት ለተፈጠረው የፀጥታ ችግር ድርቅ፣ ፖለቲካዊ ቅስቀሳ እና ከኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ በቀላሉ መገኘቱ ነው ብሏል።

የኬንያ የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር ፖሊስ ከደቡብ ኢትዮጵያ በሕገወጥ መንገድ የገቡ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን እና ጥይቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተናግረዋል።

የኬንያ መንግሥት በማርሳቢት የፀጥታ ኃይል ከማሰማራት በተጨማሪ ለአንድ ወር የሚቆይ የሰዓት እላፊ አዋጅ እንዲሁም ትጥቅ እንደሚያስፈታም ገልጿል።

በማርሳቢት ከተማ በቅርቡ የተፈጸመውን ግድያ አረመኔያዊ ሲል የኬንያ መንግሥት ያወገዘው ሲሆን በዚህም የአካባቢው አስተዳዳሪም መገደላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል የቀጠሮ እስረኛ የነበሩት ሜ/ጄነራል ገ/መድህን ፍቃዱ (ወዲ ነጮ) በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል። በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ይፋ በተደረገው መረጃ ሜ/ጄነራል ገ/መድህን ከረፋዱ 3፡30 አካባቢ በቤተሰብ ጥየቃ ሠዓት ባለቤታቸው እና ልጃቸው አስጠርተዋቸው እያወሩ እያለ በድንገት ይወድቃሉ። ወዲያውኑ ከቤተሰቦቻቸው…
ፎቶ : የቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል የቀጠሮ እስረኛ የነበሩት ሜጀር ጄነራል ገ/መድህን ፍቃዱ (ወዲ ነጮ) ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው መገለፁ ይታወሳል።

የሜ/ጄነራል ገ/መድህን ስርዓተ ቀብር ዛሬ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።

የኢትዮጵያ መንግስት ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፈቃዱን (ወዲ ነጮ) ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዘ በአገር ክህደት ወንጀል ነበር በቁጥጥር ስር ያዋላቸው።

ጥቅምት 24/2013 ዓ/ም ላይ የሰሜን ዕዝ ከማዕከል ጋር የሚኖረው የመገናኛ ሥርዓት እንዲቋረጥ በማድረግ የህወሃት ቡድን ጥቃት እንዲፈፅም አመቻችተዋል ተብለው ነበር ከነጓዶቻቸው በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት።

ሜ/ጄነራሉ ከቀናት በፊት ታስረውበት በሚገኘው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በቤተሰብ ጥየቃ ሠዓት ባለቤታቸው እና ልጃቸው አስጠርተዋቸው እያወሩ እያለ በድንገት እንደወደቁ በኃላም ወደ ህክምና ቦታ ቢወሰዱም ህይታቸው ማለፉ መግለፁ አይዘነጋም።

ይህን ተከትሎ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፈቃዱ (ወዲ ነጮ) አስክሬን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ህክምና ተቋም መላኩን እና ውጤቱ እንደታወቀ እንደሚገለፅ ገልጾ የነበር ሲሆን እስካሁን በይፋ የተሰጠ መረጃ የለም።

@tikvahethiopia