TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ህንድ

በሰሜን ህንድ በቡድን ጾታዊ ጥቃት ተፈጽሞብኛል ብላ ለመክሰስ ፖሊስ ጣቢያ የሄደችው የ13 ዓመት ታዳጊ በፖሊስ መደፈሯ ቁጣን ቀስቅሷል።

አሁን ላይ ታዳጊዋን የደፈረው ፖሊስ ከስራው የተገደ ሲሆን ፤ በቁጥጥር ስርም ውሏል።

ታዳጊዋ ባለፈው ወር በ4 ወንዶች መደፈሯን ተናግራለች፡፡ የታዳጊዋ የመደፈር ዜና በመላ ህንድ ትልቅ ቁጣ ቀስቅሶ ነበር።

የታዳጊዋ ወላጅ ባቀረቡት ክስ፤ አራቱ ወንዶች ሴት ልጃቸውን የደፈሯት ለአራት ቀናት ያክል ማደያ ወደ ተባለ ግዛት ወስደው እቤት ውስጥ በመዝጋት ነበር ብሏል፡፡

አራቱም ወንዶች ለአራት ቀናት ከደፈሯት በኋላ ወደ መኖሪያ አከባቢዋ መልሰው ጥለዋት መሰወራቸውንም ነው ወላጅ አባቷ የገለጹት፡፡

በሚቀጠለው ቀን ታዳጊዋ ከአክስቷ ጋር በመሆን ክስ ለመመስረት ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄደች ቢሆንም፤ በፖሊስ ጣቢያው ኃላፊ እንደተደፈረች ኤን-ዲቲ-ቪ የተባለ የህንድ ቻናል ዘግቧል፡፡

ዜናውን ተከትሎ በግዛቱ ያሉትን ህጎች ጥያቄ ውስጥ መግባታቸው በመነገር ላይ ያለው፡፡

የህንድ ኮንግረስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ፕሪያንካ ጋንዲ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ‘‘ ፖሊስ ጣቢያዎች ለሴቶች ደህንነት አስተማማኝ ካልሆኑ ፤ ሴቶች ታዲያ የት ሄደው ይከሳሉ? ’’ የሚል ትችት አዘል መልእክት አጋርቷል፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ /ND TV

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ነገ ሚያዚያ 27/2014 ዓ.ም የሚከበረውን የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በዓልን በማስመልከት ከንጋቱ 12:00 ሰዓት 21 ጊዜ መድፍ የሚተኮስ መሆኑን መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ 81ኛው የድል በዓል 4 ኪሎ በሚገኘው የድል ሐውልት አባት አርበኞች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ወጣቶች፣ ታዳጊዎች፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች በተገኙበት ተከብሯል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Djibouti

በጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደተገኘው መረጃ ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል በጋራ ለማልማት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የነዳጅ ማከማቻው በጂቡቲ ነጻ ወደቦች ቀጠና የሚካሄድ ነው።

የመግባቢያ ስምምነቱ ሃገራቱ ወደፊት በዘርፉ ለሚያካሂዱት ልማት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርና ተጨማሪ እድሎችን ለማየት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

የአሳማ መኖን ከሌሎች በዓድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል የምግብ ዘይት ሲያመርቱ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የሰሜን ምዕራብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከአማራ ጤና ቢሮ እና ከደቡብ ጎንደር ዞን መስተዳደር ጋር በመሆን በማህበረሰቡ ጥቆማ መሰረት በተደረገው ክትትልና ፍተሻ ነው።

ለምግብነት ሊውል የማይችል ህገ-ወጥ የዘይት ምርቱ የተያዘው በደቡብ ጎንደር ዞን በወረታ ከተማ ሲሆን በጥሬ ግብዓትነት የሚጠቀሙት የአሳማ መኖ፣ የዘይት ተረፈ ምርትን (ፋጉሎን)፣ ሱፍን እና ሌሎች ለጊዜው ምንነታቸው ያልተለዩ በማዳበሪያ ታስረው የተቀመጡ ነገሮችን በመቀላቀልና በማፍላት በሰው እግር በመርገጥ ህገ-ወጥ የዘይት ምርቱን እንደሚያመርቱ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የሰሜን ምዕራብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ቆየ እንደገለጹት የምርቱ ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ የተመረመረና ሦሰቱም ፓራሜትር የወደቀና ከፍተኛ የአሲድ ክምችት በውሰጡ መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡

አክለው ምርቱ በምንም መመዘኛ ለምግብነት ሊውል የማይችል፣ለተለያዩ በሸታዎች የሚያጋልጥ እንደሆነ ህዝባችን እንዲገነዘብልን እንፈልጋለን ሲሉ ገልፃዋል፡፡

ህገ-ወጥ ምርቱ ምንም አይነት የብቃት ማረጋገጫ ያልተሰጠውና ምርቱን ለህብረተሰቡ የሚያከፋፍሉት ሳይታሸግ፣ ምንም የምርት መለያ ሳይለጥፉ ከበርሜል በመቅዳት እንደሚያሰራጩ ተደርሶባቸዋል ብለዋል።

በሀገርቱ የተከሰተውን የምግብ ምርቶች ዋጋ መናርን ተከትሎ ጥራትና ደህንነታቸው ያልተጠበቁ ምርቶች የጤና ጉዳት እንዳያደርሱ ህብረተሰቡ በየአካባቢውና በግብይት ወቅት ተገቢው ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስገንዝበዋል።

ጥቆማ መስጫ፦ 8482

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

የባንካችን የስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ሳያሳስብዎት 24 ሰዓት ከ እሁድ እስከ እሁድ በመረጡት የቨርቹዋል ባንኪንግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመገኘት ገንዘብዎን ተቀማጭ ወይም ወጪ ማድረግ ይችላሉ።

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
" በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኬንያ ውስጥ እንደአገራቸው በነፃነት እንዲኖሩ እፈልጋለሁ " - ኡሁሩ ኬንያታ

የኬንያ ፕሬዚዳንት የሆኑት ኡሁሩ ኬንያታ በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለምን በጽ/ቤታቸው ዛሬ ተቀብለው አነጋገሩ።

በዚህም ወቅት ፤ ፕሬዜዳንቱ " ኢትዮጵያ የኬንያ የቁርጥ ቀን ወዳጅ ናት " ያሉ ሲሆን " ኢትዮጵያ ችግር ባጋጠማት ጊዜ ሁሉ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ከጎኗ እንደምንቆም እናረጋግጣለን " ብለዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል በኢኮኖሚው መስክ በመሠረተ-ልማት ትስስር፣ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት ዘርፎች የተጀመሩ ትብብሮች ተጠናከረው እንደሚቀጥሉ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ኡሁሩ በኬንያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ኬንያ ውስጥ እንደአገራቸው በነፃነት እንዲኖሩም እፈልጋለሁ ብለዋል።

https://telegra.ph/Ethiopia-Kenya-05-05

Via Ethiopian Embassy in Kenya

@tikvahethiopia
" ጋዜጠኛን ከሕግ ውጭ ሰውሮ ማቆየት ይቁም " - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከቀናት በፊት ማንነታቸውን ባልገለጹ የመንግስት ሰዎች ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ ተይዞ መወሰዱንና የት እንዳለ አለመታወቁን ከሰማበት ጊዜ ጀምሮ መልስ የሚሰጥ አካል ባለመኖሩ በእጅጉ እንዳሳሰበው ገልጿል።

ማህበሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፤ ጋዜጠኛው በምን ጥፋት ተጠርጥሮ እንደተያዘና ምክንያቱ ምን እንደሆነ በግልጽ ካለመነገሩ በላይ የት እንደሚገኝ አለመታወቁ ከዚህ ቀደምም ማሕበሩ ሲቃወመው የቆየው በሌሎች ጋዜጠኞችም ላይ የደረሰው መሰል ድርጊት አካል ሆኖ እንዳገኘው አሳውቋል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ የማህበሩ መስራች አባል መሆኑን በማሳት ታፍኖ ተወስዶ እንዲሰወር የተደረገው የዓለማችን የፕሬስ ነጻነት ሳምንት በሚከበርበት ወቅት መሆኑ መንግስት በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በመገናኛ ብዙኃን ላይ ጥቃት እንደከፈተ ያስቆጥረዋል ሲል ገልጿል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ያጠፋው ጥፋት ቢኖር እንኳን የፍትህ አካላት እንደማንኛውም ተጠርጣሪ በህግ ቁጥጥር ስር ሊውልና ዳኝነት ሊሰጠው ሲገባ ከተያዘበት ቀን አንስቶ የት እንደሚገኝ ሳይገለፅ መቆየቱ የመብት ጥሰት ብቻ ሳይሆን መንግስት ይህን ያልተገባ አደገኛ አዝማሚያ በጋዜጠኞች ላይ ማድረስ እንደመብት የቆጠረው አስመስሎታል ሲል ኮንኗል።

ማህበሩ ፤ ጋዜጠኛ ጎበዜ ለምን እንደታሰረ፣ የት እንደሚገኝ እና የተያዘበት ምክንያት በግልጽ እንዲነገር በጽኑ ጠይቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia