TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዱላ አታቀብሉ፤ አታጋግሉ!⬇️

የኦነግ አመራሮች አቀባበል #ያማረ እንዲሆን እና የኦነግ ደጋፊ የሆኑ ወንድሞች ደሥ እንዲላቸው ማገዝ #ተገቢ ነው። ከፀቡ በፊትም በሰከነ
መንገድ #ተነጋግሮ መግባባት መልመድ አለብን። አላሥፈላጊ የሆነ #ፉክክር እና #ብሽሽቅ አያሥፈልገንም።

ለወጣቱ ለባለፉት 27 ዓመታት ሲሰበክለት የኖረው #ልዩነት እንጅ ወንድማማችነት እና መተባበር አይደለም። ሥለዚህ በትንሽ ነገር ወደፀብ ለማምራት ቀላል ሆኗል። ጦር ለማወጅም ማሰላሰል አያሥፈልግም። #ሞባይልን ወጣ አድርጎ መተኮሥ ነው። ሃላፊነት የማይሰማው እና #ቢራ እየጠጣ "አትነሳም ወይ" የሚል ብዙ ነው። የእብድ ገላጋዩ እና ዱላ አቀባዩ የትየለሌ ነው። የሚመክር እና አንተም ተው፣ አንተም ተው የሚል ነው የሚያሥፈልገን። በዚህ የተነሳም ሰፊው መንገድ ይጠበናል። #የምንፈልገውን ባንዲራ ለመሥቀል ሌላውን ማውረድ ተገቢ አይደለም።

ሌሎችም የሚፈልጉትን እና #አርማየ ነው የሚሉትን ቢሰቅሉ የሌላውን #መብት እሥካልነኩ ድረሥ #መብታቸው ነው። ሥንተባበር ሁሉም #ቀላል ይሆናል። ሆደ ሰፊነት ያሥፈልጋል።

ፌሥቡክ ላይ የምታጋግሉ ሰከን በሉ!
.
.
ከዳንኤል ተፈራ (የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፌደራል ፖሊስ-አልታገስም አለ⬆️

ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል እየተፈጠረ ያለውን ግጭትና ህገወጥ ተግባር ከዚህ በኋላ #እንደማይትገስ የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ኢብሳ ነገዎ ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ላይም ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል፥ በትናንትናው እለት እና ዛሬ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል ግጭት መፈጠሩን አስታውቀዋል።

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን #የኦነግ ቡድን ለመቀበል እየተደረገ ባለ ቅድመ ዝግጅት ወቅት ወጣቶች የድርጅቱን አርማ ለመስቀል ዝግጅት እያደረጉ ነበር፤ ይህንን የከለከላቸው አካል የለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ሆኖም ግን አስፋልትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን እንዳያቀልሙ ተከልክው፤ ይህንንም ተወያይተን እሺ ብለው ተቀብለው ትተው ነበር ብለዋል።

ሆኖም ግን ማንም ያልፈቀደላቸው አካላት የእነሱን ባንዲራ አውርደው የሌላ ለመስቀል ሲሉ ግጭት ተፈጥሯል ሲሉም ገልፀዋል።

ግጭቱ ለማንም ጠቃሚ አይደለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ችግሩን #በውይይት መፍታት ሲቻል ወደ አላስፈላጊ ግጭት መግባት ተገቢ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።

ፖሊስ የህግ የበላይነትን የማስከበር ሀላፊነት ስላለበት ከዚህ በኋ እንዲህ አይነት #ግጭቶችን በትእግስት እንደማያልፍም ኮሚሽነር ዘይኑ አሳስበዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር #ብርሃኑ_ነጋ፥ የዴሞክራሲ ስርዓትን እንገንባ ብለን ስንሰና ስርዓቱን ለመገንባት የሚያስፈልግ እነዚህን ባህሪያትን ተቀብለን ካልተነሳን ግን ስርዓቱን መገንባት እንችልም ብለዋል።

የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ልዩነቶችን መቀበል የግድ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ልዩነቶቹ ደግሞ ሀሳቦችን፣ አርማዎችን እና ባንዲራዎችን ሊያጠቃልል ይችላል ብለዋል።

ትናንትና እና ዛሬ በአዲስ አበባ የተስተዋሉ ችግሮች ደግሞ ከዚህ ጋር የሚፃረሩ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ማንኛውም አካል ስሜቴን ይገልፅልኛል ያለውን አርማ የመያዝ እና የማውለብለብ #መብት አለው ሲሉም ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ #ኢብሳ_ነገዎ በበኩላቸው፥ ሰሞኑን በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የተስተዋለው ችግር #ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አንስተዋል።

ወጣቱም ከዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች ሊቆጠብ እንደሚገባም አቶ ኢብሳ ጥሪ አስተላልፈዋል።

አሁን ላይ እየታየ ያለው ግጭት እና ያልተገባ #ፉክክር ድርጅታቸውን የማይወክል መሆኑንም ነው አቶ ኢንብሳ ተናግረዋል።

©Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ አህመድ ሽዴ⬇️

በአዲስ አበባ ከተማ ሰዎች ታፍሰው ተወሰዱ ተብሎ የሚሰራጨው ወሬ የተሳሳተ መሆኑንና ህብረተሰቡን ለማደናገር የሚሰራ ስራ እንደሆነ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትሩ አቶ #አህመድ_ሽዴ
አስታወቁ።

ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳይ በሰጡት መግለጫ፥ በተለያዩ አካባቢዎች ህይወት እንዲጠፋና ንብረት እንዲወድም በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች በህጋዊ መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

መንግስት በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ከመስከረም 2 ጀምሮ የፖለቲካ ኃይሎችን ለመቀበል በደጋፊዎቹ መካከል በተፈጠረው ያልተገባ #ፉክክር ግጭቶች መፈጠራቸውን አስታውሰዋል።

እየሰፋ ቤደው ግጭትም በቡራዩ 27 ሰዎች በአዲስ አበባ 28 በጥቅሉ 55 ሰዎች #ህይወታቸው እንዳለፈ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በቡራዩ ከተማ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት እንዳጋጠመና 3 ሺህ 50 ሰዎችም መፈናቀላቸውን ገልፀዋል።

እነዚህን ግጭቶች የብሄር ማስመሰልና በማህበራዊና በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የተዛቡ መረጃዎችን በማቅረብ ግጭቱን ለማባባስ እንቅስቃሴ ተደርጓል ብለዋል።

በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ ከግጭቱ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸው 170 ሰዎችና በቡራዩ ከተማ ደግሞ 390 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተናግረዋል።

እንዲሁም በአዲስ አበባ ሁከቱና ብጥብጡን ለማማባባስ ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ 1200 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ችግሩን ለመቆጣጠር የፍትህና የፀጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ ችግሩ በቁጥጥር ስር እንደዋለ አስታውቀዋል።

#መንግስት በደረሰው የህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት የተሰማውን #ሀዘን ሚኒስትሩ ገለፀዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia