TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ፌደራል ፖሊስ-አልታገስም አለ⬆️

ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል እየተፈጠረ ያለውን ግጭትና ህገወጥ ተግባር ከዚህ በኋላ #እንደማይትገስ የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ኢብሳ ነገዎ ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ላይም ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል፥ በትናንትናው እለት እና ዛሬ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል ግጭት መፈጠሩን አስታውቀዋል።

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን #የኦነግ ቡድን ለመቀበል እየተደረገ ባለ ቅድመ ዝግጅት ወቅት ወጣቶች የድርጅቱን አርማ ለመስቀል ዝግጅት እያደረጉ ነበር፤ ይህንን የከለከላቸው አካል የለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ሆኖም ግን አስፋልትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን እንዳያቀልሙ ተከልክው፤ ይህንንም ተወያይተን እሺ ብለው ተቀብለው ትተው ነበር ብለዋል።

ሆኖም ግን ማንም ያልፈቀደላቸው አካላት የእነሱን ባንዲራ አውርደው የሌላ ለመስቀል ሲሉ ግጭት ተፈጥሯል ሲሉም ገልፀዋል።

ግጭቱ ለማንም ጠቃሚ አይደለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ችግሩን #በውይይት መፍታት ሲቻል ወደ አላስፈላጊ ግጭት መግባት ተገቢ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።

ፖሊስ የህግ የበላይነትን የማስከበር ሀላፊነት ስላለበት ከዚህ በኋ እንዲህ አይነት #ግጭቶችን በትእግስት እንደማያልፍም ኮሚሽነር ዘይኑ አሳስበዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር #ብርሃኑ_ነጋ፥ የዴሞክራሲ ስርዓትን እንገንባ ብለን ስንሰና ስርዓቱን ለመገንባት የሚያስፈልግ እነዚህን ባህሪያትን ተቀብለን ካልተነሳን ግን ስርዓቱን መገንባት እንችልም ብለዋል።

የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ልዩነቶችን መቀበል የግድ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ልዩነቶቹ ደግሞ ሀሳቦችን፣ አርማዎችን እና ባንዲራዎችን ሊያጠቃልል ይችላል ብለዋል።

ትናንትና እና ዛሬ በአዲስ አበባ የተስተዋሉ ችግሮች ደግሞ ከዚህ ጋር የሚፃረሩ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ማንኛውም አካል ስሜቴን ይገልፅልኛል ያለውን አርማ የመያዝ እና የማውለብለብ #መብት አለው ሲሉም ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ #ኢብሳ_ነገዎ በበኩላቸው፥ ሰሞኑን በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የተስተዋለው ችግር #ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አንስተዋል።

ወጣቱም ከዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች ሊቆጠብ እንደሚገባም አቶ ኢብሳ ጥሪ አስተላልፈዋል።

አሁን ላይ እየታየ ያለው ግጭት እና ያልተገባ #ፉክክር ድርጅታቸውን የማይወክል መሆኑንም ነው አቶ ኢንብሳ ተናግረዋል።

©Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Amhara

" የተከሰተው ችግር #በውይይት_ተፈቷል ፤... የሰላም #ስምምነትም ተደርጓል " - የሰ/ ወሎ ዞን አስተዳደር

የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ፤ ከሰሞኑን ከክልል ልዩ ሀይል መልሶ ማደራጀት ጋር ተያይዞ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በውይይት መፈታቱን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

የፀጥታ ችግሩን ለመፍታት በሐይማኖት አባቶች፣ በአገር ሽማግሌዎችና በዘወልድ ሽምግልና ስርዓት የሠላም ስምምነት ተደረጓል ብሏል።

በሰላም ስምምነት ስነስርዓቱ ላይ ፦
- የአገር መከላከያ ሠራዊት ፣
- የክልል ፣ የዞን ፣ አመራሮች
- የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮች
- የአገር ሽማግሌዎች የሰላም ስምምነቱን አስመልክተው መግለጫ መስጠታቸውንም የዞን አስተዳደሩ አመልክቷል።

ስምምነቱን በተመለከተ የሰ/ወሎ ዞን አስተዳደር ለህዝብ ያሰራጨው መረጃ #ከላይ ተያይዟል።

NB. ውድ ቤተሰቦቻችን በዚህ የሰ/ወሎ ዞን አስተዳደር መግለጫ ዙሪያና ስምምነቱ ዙሪያ ከፋኖ አደረጃጀት አመራሮች ዘንድ የሚሰጥ አስተያየት ካለ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #US

አሜሪካ ከ #አማራ_ፋኖ ታጣቂዎች ጋር የሰላም ንግግር እንዲጀመር የኢትዮጵያ መንግሥትን እንደጠየቀች አሳውቃለች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እንዲሁም የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሃመር በኦንላይን መግለጫ ሰጥተው ነበር።

መግለጫቸው ባለፉት ቀናት በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ቆይታ የተመለከተ ነበር። 

በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ጨምሮ ከተለያዩ ባለስልጣናትና የተቋማት መሪዎች ጋር በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች #በውይይት እንዲፈቱ መነጋገራቸውን አሳውቀዋል።

አሜሪካ በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለው ግጭት እልባት እንዲያገኝ የበኩሏን ሚና እየተጫወተች መሆኑን ገልጸው በአማራ ክልልም ግጭቶች በሰላም እንዲቋጩ ከፋኖ ጋር ንግግር እንዲጀመር ጥሪ መቅርቡን ተናግረዋል።

አምባሳደር ማይክ ሃመር ምን አሉ ?

" ባለፈው ሕዳር ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር በዳሬሰላም በተደረገው ውይይት ላይ በቀጥታ ተሳትፈናል። አሁን ይህን ለመቀጠል ዝግጁ ነን። ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ እንዴት መመቻቸት እንደሚቻል ለሁለቱም አካላት ሃሳብ አቅርበናል።

ከፋኖ ጋር ንግግር እንዲደረግ አምባሳደር ማሲንጋ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን እናውቃለን።

ሰላምን ለማረጋገጥ ያሉትን እድሎች በመጠቀም ጥረታችንን ለመቀጠል ዝግጁ ነን። በተደጋጋሚ እንዳልነው ለነዚህ ግጭቶች ወታደራዊ መፍትሄ አማራጭ አይሆንም አሁንም ትኩረት መደረግ ያለበት ውይይት ላይ ነው። " ብለዋል።

ሞሊ ፊ ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያ በአሁን ወቅት በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያጋጠሟትን ፈተናዎች በሰላም ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ቁርጠንኝነታቸው እንዲቀጥሉ እናበረታታለን።

በታጣቂዎች ለሚፈፀሙት ጥቃቶች የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ስለሚወስዱት እርምጃ አሳሳቢነት ገልጸናል። የጸጥታው ሁኔታን አሳሳቢነት ብንረዳም የሲቪሎችን መብት ለመጠበቅ ተጨማሪ ጥሪ ያስፈልጋል " ብለዋል።

አምባሳደር ማይክ ሃመር ፤ " ከተለያዩ ባለስልጣናት ጋር በተደረገው ስብሰባ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ውይይት ለማመቻቸት እንዲሁም የቀጠሉትን ግጭቶች በሰላም ለመፍታት ከአማራ ፋኖ ጋር ሊደረግ የሚችል ንግግር ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለን ገልጸናል " ብለዋል።

ሃመር በኢትዮጵያ ላለው ግጭት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለ ገልጸው የኢትዮጵያ መንግሥትም ለሰላማዊ መፍትሄ ዝግጁነት እንዳለው መግለፁን እናደንቃለን ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ቀደም ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ ፅኑ አቋም እንዳለው መግለፁ ይታወቃል። ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋርም በይፋ ሁለት ጊዜ ድርድር ቢቀመጥም መጨረሻ ላይ መሳካት አልቻለም። በአማራ በኩል ከፋኖ ጋር ለድርድር ስለመቀመጥ እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም።

አሜሪካውያኑ ባለስልጣናት በሰጡት መግለጫ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ሳይሳካ ቀርቶ የተቋረጠው ድርድር መቼ እንደሚቀጥል እንዲሁም መንግሥት ከፋኖ ጋር ለድርድር ይቀመጥ እንደሆነ በግልፅ ባይናገሩም የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰላማዊ መፍትሄ ዝግጁ እንደሆነ እንዳሳወቃቸው ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ / ጋዜጠና ኬኔዲ አባተ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia