TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እገታ

ከኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ወደ አዲስ አበባ እየመጡ የነበሩ 4 የሕዝብ ማመላለሻና 1 የጭነት ተሸከርካሪዎች መታገታቸው ተሰምቷል።

ተሳፋሪዎቹ ከደራ ወረዳ ጉንዶ መስቀል ከተማ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ሳሉ መታገታቸው የተገለፀ ሲሆን እገታው የተፈፀመው በሂደቡአቦቴ ወረዳ ወዘሚ በሚባል መንደር ነው።

የደራ ወረዳ አስተዳዳሪ ውብሸት አበራ 4 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችና 1 የጭነት መኪና መታገታቸውን አረጋግጠዋል።

የመንግስት የጸጥታ ኃይል ወደስፍራው መሄዱን ያነሱት አቶ ውብሸት እስካሁን 230 ሰዎች ከእገታው መለቀቃቸውን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በተሸከርካሪዎቹ ውስጥ ምን ይህል ሰዎች እንደተሳፈሩ ከጉንዶ መስቀል መረጃ እየሰበሰቡ እንደሆነ ያነሱት ገልፀው፤ የተለቀቁ ቢኖሩም አሁንም የታገቱ እንዳሉ ማወቃቸውን ተናግረዋል።

እገታው የተፈጸመው መንግስት ሸኔ እራሱን ደግሞ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ በሚጠራው ቡድን እንደሆነም ነው የገለፁት። ተሸከርካሪቹ የታገቱበት አካባቢ በብዛት ቡድኑ የሚንቀሳቀስበት ነው ብለዋል።

አሁን በእገታ ላይ ያሉ ሰዎችን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን ገልፀዋል።

የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የታገቱት ሰዎች ጨለንቆ እንደተወሰዱ ገልጸው በስፍራው መንግስት " ሸኔ " እራሱን ደግሞ " የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት " ብሎ የሚጠራው ቡድን #ማሰልጠኛ እንዳለው ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ይህንን ጉዳይ እንዳልሰሙና በአካባቢው ”ሽፍታ ይንቀሳቀስ ይሆናል” እንጅ ሌላ ችግር የለም ሲሉ ተናግረዋል።

የደራ ፍቼ አዲስ አበባ መንገድ ለ8 ወራት ያህል ተዘግቶ የነበረ ሲሆን አገልግሎት መስጠት የጀመረው በቅርቡ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
#እገታ

ከሰሞኑን ጎንደር ላይ አንድ እስራኤላዊ ዜጋ ታግቷል ተብሎ መረጃ ሲሰራጭ ነበር።

ይህን ተከትሎ የሀገሪቱ መንግሥት ዜጋውን ለማስለቀቅ ፍለጋ ጀምሮ ነበር።

ነገር ግን ጎንደር ላይ ታግቷል ተብሎ የተነገረው ኤስራኤላዊ ጉዳይ ውሸት ሆኖ በመገኘቱ የእስራኤል ባለስልጣናት ፍለጋቸውን እንዳቋረጡ የእስራኤል ጋዜጦች ዘግበዋል።

ጋዜጦቹ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳምንታት በፊት ወደ ትውልድ ሀገራቸው ያመሩት የ79 ዓመቱ ፍራንሲስ አደባባዪ በውሸት " ታግቻለው " በማለት የማስለቀቂያውን ገንዘብ በመፈለግ ድርጊቱን እንደፈፀሙ #እንደሚያምን ፅፈዋል።

ባለፈው ሳምንት የፍረንሲስ አደባባዪ ዘመዶች እንዳስታወቁት ከሆነ ፍረንሲስ እጅ እና እግራቸውን ታስረው በታጠቀ ሰው ሲጠበቁ የሚያሳይ የተቀዳ መልእክት፣ ምስሎች እና አጭር ቪዲዮ ክሊፕ አጋቾቹ ልከውላቸዋል።

ታጋቾቹ ከእስር እንዲፈቱ 2.5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ወይም 45,000 ዶላር እየጠየቁ ነበር ተብሏል።

በተቀዳው መልዕክት ላይ ፍራንሲስ " እርዱኝ ወንድም እና እህቶቼ ፤ በጫካ ውስጥ ነኝ፤ ታግቻለሁ ፤ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ነው ... ይህንን ችግር በጠላቶቼም ላይ እንዲሆን አልመኝም " ሲሉ ተደምጠዋል።

የእስራኤል ባለስልጣናትም ከ #ኢንተርፖል ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ እየሰሩበት ነበር።

ነገር ግን ፍራንሲስ አደባባዪ ከእስራኤል የሚደወሉ የስልክ ጥሪዎችን እመለሱ መሆኑን ካወቁ በኋላ ባለስልጣናት ፍለጋውን ማቋረጣቸውን ጋዜጦቹ ዘግበዋል።

ዘመዶቻቸው ግን አሁንም ድረስ ፍራንሲስ አደባባዪ መታገታቸውን እና ለደህንነታቸው  አጥብቀው እንደሚሰጉ ተናግረዋል። ለእስራኤል መንግሥት አቤት እንደሚሉም አሳውቀዋል።

ፍራንሲስ የ79 አመት የእድሜ ባለፀጋና ባለትዳር እንዲሁም የ8 ልጆች አባት መሆናቸውን የገለፁት ቤተሰቦቻቸው እገታውን ያቀነባበረ አካል ስለመኖሩ ምልክት እንዳላገኙ  በእርግጠንኘት ደግሞ እገታውን እሳቸው (ፍራንሲስ) እንዳላቀነባበሩ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#እገታ

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈፀመው እገታ መባባሱን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በቅርብ ጊዜ እገታ ተፈፅሞባቸዋል ከተባሉ አካባቢዎች አንዱ የምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ነው።

በዋናው የፌዴራል መንገድ ላይ ወረዳውን አቋርጠው በተሽከርካሪ ሲሄዱ የነበሩ 10 የግንባታ ባለሞያዎች በታጣቂዎች ታግተው 20 ቀናት ያህል ከቆዩ በኃላ የተጠየቁትን የማስለቀቂያ ገንዘብ ከፍለው ከእገታ ነፃ ወጥተዋል።

ከታጋቾቹ አንዱ እገታውን የፈፀሙት የ #ሸኔ / የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች ናቸው ያሉ ሲሆን አጋቾቹ " ለመገናኛ ብዙሃን መረጃ ከሰጠን እንደሚገድሉን አስጠንቅቀውናል " ብለዋል።

በወቅቱ የግንባታ ባለሞያዎቹን ጨምሮ 30 የሚደርሱ የአንድ ድርጅት ሰራተኞች በአንድ ተሽከርካሪ ሆነው ሲጓዙ የነበረ ሲሆን 20 የሚደርሱት ሴቶች እንደነበሩ አስታውሰዋል።

ሴቶቹን ለአንድ ቀን ካሳደሯቸው በኃላ በነፃ ሲለቋቸው ሌሎች ታጋቾች ግን አጠቃላይ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ከፍለው ከ20 ቀን በኃላ መለቀቃቸውን ገልጸዋል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳንዲ ወረዳ በፊንጫ ጎደቲ ከ10 ቀናት በፊት 8 አርሶ አደሮች ታግተው እያንዳንዳቸው ከ250 እስከ 300 ሺህ ብር ከፍለው ተለቀዋል።

አንድ የአካባቢው ተወላጅ ፤ ታጣቂዎቹ በቀጥታ ወደ ሰዎች ቤት በመሄድ፣ ስልካቸውንም በመቀማት ነው አግተው የሚወስዱት ብለዋል።

በኃላም ታጋቾች በጎረቤትና በቤተሰብ ስልክ ደውለው አጋቾች የጠየቁት ብር እንዲከፈላቸው ተደርጎ እንደሚለቀቁ አስረድተዋል።

ስምንቱ አርሶ አደሮች ከ 250 ሺህ እስከ 300 ሺህ ብር ተጠይቀው ከብት ያለው ሽጦ ፤ ዘመድ ያላቸውም ተበድረው ከእገታው ወጥተዋል ብለዋል።

ታግተው የተለቀቁት ሰዎች እንደሚናገሩት ፤ እገታውን የሚፈፅሙት መንግስት " ሸኔ " የሚላቸው ኃይሎች እንደሆነ የገለፁት ተወላጁ ከታጋቾች ባገኙት ቃል አጋቾቹ " ታጋዮች ነን ለህዝብ ነው የምንዋጋው ለመኖር የሚያስፈልገንን ገንዘብ ማግኘት አለብን " በሚል ሰዎችን ይዘው እንደሚሄዱ ነው የገለጹት።

" እነሱ ይሁኑ ፤ በእነሱ ስም የተደራጁ ይሁኑ በግልፅ ባይታወቅም አንድ መረጃ ከተናገራችሁ ' በህይወት አትኖሩም ' የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነው የሚለቁት " ያሉት የአካባቢው ተወላጅ " በዚህም የተለቀቁ ሰዎች ምንም ነገር መናገር ይፈራሉ። " ብለዋል።

የሰሞኑን እገታ ብቻ ሳይሆን በ2 ወራት በፊት 3 ሰዎች ታግተው ከ300 ሺህ እስከ 350 ሺህ ብር ከፍለው መውጣታቸውን አመልክተዋል።

በአካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ እየተፈፀመ ባለው እገታ ምክንያት ነዋሪው በስጋት ቄዬውን እየለቀቀ እየሸሸ ነው ሲሉ አሳውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ ከሳምንታት በፊት የ " አሉቶ ላንጋኖ ጂኦተርማል ፕሮጀክት " ሰራተኞች በታጣቂዎች ታግተዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም ምን ያህል ሰራተኞች እንደሆኑ ባይገልጽም " ሰራተኞቹ ባልታወቁ ኃይሎች መታጋታቸውን አመልክቷል።

የስራ ባልደረቦቻቸው የታገቱት 6 ሰራተኞች እንደሆኑ ገልጸዋል።

እነዚህ ሰራተኞች አሁን ምን ላይ እንዳሉ አይታወቅም። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ባልደረቦቻቸው ለታጋቾች ደህንነት በመስጋት መረጃ ለመስጠት እንደማይፈልጉ ተነግሯል።

ጥቅምት 9 / 2015 ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ዞን፣ የኢስት ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች የሆኑ " የቻይና ዜጎች ታግተው " መወሰዳቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ " አዲስ ስታንዳርድ " ዘግቧል።

ነዋሪዎች እንዳሉት የሸኔ ታጣቂዎች ከሀምቢሶ ከተማ በአምስት ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘውን ኢስት ሲሚንቶ ፉብሪካ በመቆጣጠር በቁጥር ያልታወቁ የቻይና ዜጎችን አግተው ወስደዋል።

ታጣቂዎቹ " ፊቼ " ን ለመቆጣጠር በማሰብ ጋረ ሹሂ በሚባል ቦታ ላይ ከመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ጋር ረዘም ያለ እና ከፍተኛ ውጊያ ማድረጋቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸው ታጣቂዎቹ ወደ ጫካ ሲያፈገፍጉ የቻይና ዜጎች አግተው ነው ብለዋል።

በኦሮሚያ ፤ ስለተባባሰው እገታ የክልሉ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል ድርጊቱን የሚፈፅሙት የሽብርተኛ ቡድኑ " ሸኔ ነው " ብሏል።

ይህን የሚፈፀመው የፀጥታ ኃይል ስምሪትን እያየ ነው ሲል ገልጿል።

" ቡድኑ አለሁ ለማለት እና ኪሱን ለማደለብ በንፁሃን ላይ እገታ ይፈፅማል ፣ ያፍናል ፣ ይገድላል " ያለው ክልሉ ፤ " መንግሥት ዜጎች ወጥተው እንዲገቡ ሰላም እንዲረጋገጥ የተቻለውን እየሰራ ነው " ብሏል።

" ሰላም የመላ ህዝብ ነው " ክልሉ " ህዝቡ ተደራጅቶ ሰላሙን ማስጠበቅ ፣ ልማቱን ማስቀጠል አለበት። እኛ እያንዳንዱ ቀበሌ እና ቤተሰብ ላይ የፀጥታ ኃይል ስምሪት መስጠት አንችልም። ስለዚህ ህብረተሰቡ ከመንግሥት የፀጥታ ጋር አብሮ በመስራት ፣ መረጃ በመስጠት ፤ ተደራጅቶ አካባቢውንም መጠበቅ አለበት " ሲል ገልጿል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት / ኦነሰ በበኩሉ መሰል ድርጊት እንደማይፈፅም እና እጁ እንደሌለበት ገልጾ " ይህ የሽፍቶች ስራ ነው " ብሏል ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል።

" ሁኔታው በስልጣን ላይ ካለው አካል አቅም በላይ እየሆነነው " ያለው ታጣቂ ቡድኑ " ይህ የሆነው ደግሞ በየቦታው ሽፍታ በመብዛቱ ነው " ሲል ገልጿል።

የታጣቂው ቡድን ፤ " የእገታ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙት ኃይሎች ከመንግስት ኃይል ጋር ግንኙነት ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም ይችላል " ብሏል።

" ነፍጥ ይዘው መሰል ድርጊት (እገታ) የሚፈፅሙ ተበራክተዋል ፤ በዚህ ምክንያት በስልጣን ላይ ያለው አካል የህዝብን ደህንነት ማስጠበቅ አቅቶታል " ያለው ቡድኑ " ሰላም እና ዴሞክራሲ በሰፈነበት ሀገር መንግት ነኝ የሚል አካል ነበር ተጠያቂነት ወስዶ ማስተካከል የነበረበት ይህን ግን እያየን አይደለም ስለዚህ ወንጀለኞች ነፍጥ አግኝተው መሰል ወንጀል ፈፅመው ራሳቸውን እያበለፀጉ ናቸው " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እገታ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈፀመው እገታ መባባሱን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል። በቅርብ ጊዜ እገታ ተፈፅሞባቸዋል ከተባሉ አካባቢዎች አንዱ የምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ነው። በዋናው የፌዴራል መንገድ ላይ ወረዳውን አቋርጠው በተሽከርካሪ ሲሄዱ የነበሩ 10 የግንባታ ባለሞያዎች በታጣቂዎች ታግተው 20 ቀናት ያህል ከቆዩ በኃላ የተጠየቁትን…
#እገታ

ከ3 ሳምንት በፊት መስከረም 20/2016 ዓ/ም ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ከባቱ ከተማ ወጣ ብሎ ወደሚገኘው የአሉቶ ጂኦተርማል ፕሮጀክት ሲጓዙ በታጣቂዎች ከታገቱት 6 ሰዎች ውስጥ 3ቱ ቢለቀቁም ሌሎች 3 ሰዎች ደግሞ እስካሁን እንደታገቱ ናቸው።

ከዚህ ቀደም ስማቸው ይፋ እድንዳይሆን ጠይቀው መረጃ የሰጡ የፕሮጀክቱ ሰራተኛ ታጋቾቹ እያንዳንዳቸው በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ እንደተጠየቀባቸው / በድምሩ የተጠየቀው 60 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተናግረው ነበር።

ከታጋቾቹ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትላንት ቃላቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን ፤ ታጋቾቹን የማስለቀቅ ጥረት መቀጠሉን በማስረዳት እስካሁን 3ቱን ማስለቀቅ መቻሉን ተናግረዋል።

" ግማሾቹ ተለቀዋል፡፡ የተቀሩትንም ለማስለቀቅ ጥረቶች ቀጥለዋል " ያሉት አቶ ሞገስ ተለቀዋል የተባሉ 3ቱ ሰራተኞች በምን አይነት መንገድ እንደተለቀቁና የተቀሩት 3ቱ ደግሞ ለምን ሳይለቀቁ ቀሩ የሚለውን ጥያቄ ለታጋቾቹ ደህንነት በሚል ሳያብራሩት ቀርተዋል፡፡

ከእገታ ነፃ ከወጡት ውስጥ አንደኛው #ኬንያዊ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የፕሮጀክቱ ሰራተኞች እንዲሁም የታጋች ቤተሰቦች እገታውንና የተለቀቁትን ታጋቾች በተመለከተ " ለደህንነታችን መልካም አይደለም " በማለት ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት አልፈለጉም።

ፌዴራል ፖሊስ ስለ ተስፋፋው የ #እገታ ተግባር ምን ይላል ? እገታን ለማስቀረት መንግሥት ምን እየሰራ ነው ?

የፌዴራል ፖሊስ ቃል አቀባይ አቶ ጄኢላን አብዲ ችግሩን ከመሰረቱ ለመከላከል ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ ያሻዋል ብለዋል።

" እገታን ሰራዊት በማዘዝና ኮማንድ በመስጠት ሙሉ በሙሉ የምንከላከለው አይደለም፡፡ የሆነ ቦታ ላይ ተደብቀው እንደዚህ አይነት ድርጊት ሚፈጽሙ አካላት አሉ፡፡ " ሲሉ ገልጸዋል።

" ህዝብ ጋር ተባብረን መረጃ ስንቀበል አስቀድመን ያስቀረነውም ሆነ ያስለቀቅናቸው እገታዎች አሉ፡፡ " ያለቱ አቶ ጄይላን " ህብረተሰቡ ነው መጠቆም ያለበት እደዚህ አይነት ነገሮችን፡፡ " ብለዋል።

° ህብረተሰቡ ጥቆማዎችን በሚሰጥበት ወቅት ከአጋቾች ለሚደርስበት ጥቃት ምን ያህል የማምለጥ ዋስትና ይኖረዋል ? የጸጥታ ኃይሉ በፍጥነት የመድረስ ሁኔታ ላይ ጥያቄ አይነሳም ወይ ? የተባሉት የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ፦

" ከህብረተሰቡ ራሱ ጥንቃቄ የጎደሉ አካሄዶች ይስተዋላሉ፡፡

ለምሳሌ መሬት ትገዛለህ ይህን ያህል ብር ይዘህ ና ተብለው የታገቱ አሉ፡፡ እገታ ድንገት በአጋቾች የሚፈጸም እንደመሆኑም እያንዳንዱን ነገር መከላከል አዳጋች ነው፡፡

እገታ ደግሞ ሳይጠበቅ ቶሎ የሚፈጸም ተግባር ስለሆነ ቶሎ ለመቆጣጠር አመቺ አይደለም፡፡ " ሲሉ መልሰዋል።

አቶ ጀኢላን ፤ ፖሊስ ጥቆማ ከደረሰው ቶሎ ወንጀሉ የተፈጸመበት ስፍራ በመድረስ እርምጃ ለመውሰድ ሚያስችል የተሸለ ቴክኖሎጂ አለው ያሉ ሲሆን በየስፍራው ፖሊሶችም እንዲኖሩ የሚያስችል የቁጥጥር ስርኣት መዘርጋቱን ገልጸዋል፡፡

አሁን አሁን በአደንዳዥ እፆች የሚደገፍ የእገታ ወንጀል በተለይ #በከተሞች መበራከታቸውንም ያስገነዘቡት አቶ ጀኢላን " ወንጀሉ ከተፈጸመም በኋላ በርካታ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

እገታ በሚፈጸምበት ጊዜ ፖሊስ የራሱ ወታደራዊ ስልት የሚጠቀም ይሆናል እንጂ ከአጋጆች ጋር በምንም አይደራደርም ያሉ ሲሆን ይህን በሚያደርጉ ተቋማት ተግባር ላይ ማብራሪያ እንደማይሰጡ ገልጸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ / ዶቼ ቨለ ነው።

@tikvahethiopia
#እገታ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በተለይም አሰላ ከተማ ዙሪያ ላይ ያሉ ነዋሪዎች እየተባባሰ የመጣዉ የእገታ ወንጀል እንዳማረራቸው ተናግረዋል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

-  ሰዎችን አግቶ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብን የመጠየቅ ተግባር ህብረተሰቡን አማሯል።

- ከአሰላ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኙ ገጠራማ ቀበሌያት፤ በተለይም ሄጦሳ ወረዳ፤ #ቂሊሳ በሚባል አከባቢ በሌሊት ሰዎችን በማገት ገንዘብ መጠየቅ እየተለመደ የመጣ ተግባር ሆኗል። ይህ ቦታ ቁሉምሳ ከሚባለው የአሰላ ከተማ መግቢያ አከባቢ እጅግ ቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው።

- በዶዶታም ተመሳሳይ የእገታ ተግባር በሌሊት ይፈፅማል።

- ከከተማ ውጪ ያለው የትኛውም አከባቢ መሰል ስጋት አለ፡፡

-  ሰዎች ሲታገቱ ባላቸው የኢኮኖሚ አቅም የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲከፍሉ በአጋቾቻው ይወሰንባቸዋል።

- የታገቱት ሰዎች የተጠየቁትን ተደራድረው ከፍለው ከመውጣት ውጪ ህይወታቸውን የማቆያ ሌላ ስልት የለም።

- አጋቾቹ እነማን እንደሆኑ አይታወቅም እሱ ነው ትልቁ ችግር።

- ከፍተኛ የአርሶ አደር የኢኮኖሚ አቅም የሚስተዋልበት አከባቢ ነው በቀጣይም ለመሰል ዘረፋ ተጋላጭ እንዳኆን ስጋት አለን።

- ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው አርሶ አደሮች አከባቢውን ለቀው ወደ ከተማ በመሸሽ ላይ ሲሆኑ አቅም የሌለው ግን አከባቢው ላይ ተቀምጦ የሰቀቀን ህይወት ይመራል።

ፖሊስ ምን ይላል ?

የአርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር አህመድ ከድር ፦

▸ ችግሩ ጎልቶ የሚስተዋለው ከከተማ ራቅ ባሉ ደናማ አከባቢዎች ነው፡፡ እንደሚባለው ሳይሆንም አልፎ አልፎ በአንዳንድ አከባቢዎች በደን በተሸፈኑ ገጠራማ አከባቢዎች በተለይ ወደ አኖሌ ባሉ ደናማ የዝዋይ ዱግዳ ወረዳ አዋሳኝ ነው።

▸ በተለያዩ ጊዜያት ተግባሩን ለማስቆም የሚወሰዱ ኦፕሬሽኖች በመኖራቸው እንዲህ ጎልቶ በከተማ ዙሪያ የሚፈጸም ነገር የለም፡፡

▸ በተለይ በአሰላ ከተማ ዙሪያም ሆነ በአስፓልት መንገዶች ላይ እንዲህ ያለ ነገር የለም፡፡ ወንጀሉ አልፎ አልፎ የሚስተዋለው በዶዶታ እና ሁሩታ ወረዳዎች ዳገታማ አከባቢዎች እና ከምስራቅ ሸዋ ዝዋይ ዱግዳ ጋር ከሚያዋስኑን አከባቢ ነው፡፡

▸ መሰል ተግባርን የሚፈጽሙ በውንብድና ስራ የተሰማሩ አሉ፡፡ አንዳዴ ኦነግ ሸኔ በሚል ትጥቅ አንግቦ በጫካ የሚንቀሳቀሰውን ሃይል እንደ ሽፋን በመጠቀም በዝርፊያው የተሰማሩ መኖራቸውን አረጋግጠናል፤ በዝርፊያ ላይ እያሉም ጭምር ተቆጣጥረን ለህግ ያቀረብናቸው አሉ።

• ምን ያህል ሰዎች ተያዙ ? የሚለውም ጥያቄ ላይ ዝርዝር ምላሽ ሳይሰጡ አልፈዋል።

▸ በተለያየ ጊዜ ኦፕሬሽኖችን እያካሄድን ነው ፤ ከታጣቂዎች በተጨማሪ በታጣቂዎች ስም የተደራጁ መኖራቸውን ህዝቡን እናስገነዝባለን፡፡ እነዚህ ማህበረሰቡን በስልክ ጭምር እየደወሉ የሚያስፈራሩትን ተከታትለን እየያዝን ነው፡፡

(ከዶቼቨለ ሬድዮ ጣቢያ ቃለምልልስ የተወሰደ)

@tikvahethiopia