TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አገር መከላከያ ሰራዊት‼️

#በዳውድ_ኢብሳ የሚመራው #ሸኔ የተሰኘው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ክንፍ በምእራብ ኦሮሚያ አካባቢዎች እየፈጸመ ያለው ፀረ-ህዝብና ፀረ ሰላም ተግባር ህዝቡ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን #ማስወገዱን የጦር ኃይሎች ምክትል ኢታማዦር ሹም ጀነራል #ብርሃኑ_ጁላ አስታወቁ።

ቡድኑን #ትጥቅ_የማስፈታት ስራም አጠናክሮ እያከናወነ መሆኑንም ጀነራሉ ተናገረዋል። ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለማካሄድ ከመንግስት ጋር #ተስማምቶ ወደ አገር የተመለሰው የዳውድ ኢብሳው ኦነግ የገባውን ቃል ኪዳን #በማፍረስ ህዝብና አገርን በሚጎዳ ተግባር በመሰማራቱ እርምጃው እየተወሰደበት መሆኑን ነው ጀነራሉ በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት።

በአሁኑ ወቅት ቡድኑ አፈግፍጎ ወደ ጫካ #እየሸሸ ቢሆንም ሰራዊቱ ህግ የማስከበር ስራውን ከአካባቢው ህዝብና የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አክለው ገልጸዋል።

እርምጃው የሚወሰደው በኦነግ ታጣቂዎች የተለያየ ህገ ወጥ አርምጃና ግፍ የተማረረው ህዝብ #ባቀረበው_ጥያቄ መሰረት መሆኑንም ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እገታ

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈፀመው እገታ መባባሱን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በቅርብ ጊዜ እገታ ተፈፅሞባቸዋል ከተባሉ አካባቢዎች አንዱ የምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ነው።

በዋናው የፌዴራል መንገድ ላይ ወረዳውን አቋርጠው በተሽከርካሪ ሲሄዱ የነበሩ 10 የግንባታ ባለሞያዎች በታጣቂዎች ታግተው 20 ቀናት ያህል ከቆዩ በኃላ የተጠየቁትን የማስለቀቂያ ገንዘብ ከፍለው ከእገታ ነፃ ወጥተዋል።

ከታጋቾቹ አንዱ እገታውን የፈፀሙት የ #ሸኔ / የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች ናቸው ያሉ ሲሆን አጋቾቹ " ለመገናኛ ብዙሃን መረጃ ከሰጠን እንደሚገድሉን አስጠንቅቀውናል " ብለዋል።

በወቅቱ የግንባታ ባለሞያዎቹን ጨምሮ 30 የሚደርሱ የአንድ ድርጅት ሰራተኞች በአንድ ተሽከርካሪ ሆነው ሲጓዙ የነበረ ሲሆን 20 የሚደርሱት ሴቶች እንደነበሩ አስታውሰዋል።

ሴቶቹን ለአንድ ቀን ካሳደሯቸው በኃላ በነፃ ሲለቋቸው ሌሎች ታጋቾች ግን አጠቃላይ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ከፍለው ከ20 ቀን በኃላ መለቀቃቸውን ገልጸዋል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳንዲ ወረዳ በፊንጫ ጎደቲ ከ10 ቀናት በፊት 8 አርሶ አደሮች ታግተው እያንዳንዳቸው ከ250 እስከ 300 ሺህ ብር ከፍለው ተለቀዋል።

አንድ የአካባቢው ተወላጅ ፤ ታጣቂዎቹ በቀጥታ ወደ ሰዎች ቤት በመሄድ፣ ስልካቸውንም በመቀማት ነው አግተው የሚወስዱት ብለዋል።

በኃላም ታጋቾች በጎረቤትና በቤተሰብ ስልክ ደውለው አጋቾች የጠየቁት ብር እንዲከፈላቸው ተደርጎ እንደሚለቀቁ አስረድተዋል።

ስምንቱ አርሶ አደሮች ከ 250 ሺህ እስከ 300 ሺህ ብር ተጠይቀው ከብት ያለው ሽጦ ፤ ዘመድ ያላቸውም ተበድረው ከእገታው ወጥተዋል ብለዋል።

ታግተው የተለቀቁት ሰዎች እንደሚናገሩት ፤ እገታውን የሚፈፅሙት መንግስት " ሸኔ " የሚላቸው ኃይሎች እንደሆነ የገለፁት ተወላጁ ከታጋቾች ባገኙት ቃል አጋቾቹ " ታጋዮች ነን ለህዝብ ነው የምንዋጋው ለመኖር የሚያስፈልገንን ገንዘብ ማግኘት አለብን " በሚል ሰዎችን ይዘው እንደሚሄዱ ነው የገለጹት።

" እነሱ ይሁኑ ፤ በእነሱ ስም የተደራጁ ይሁኑ በግልፅ ባይታወቅም አንድ መረጃ ከተናገራችሁ ' በህይወት አትኖሩም ' የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነው የሚለቁት " ያሉት የአካባቢው ተወላጅ " በዚህም የተለቀቁ ሰዎች ምንም ነገር መናገር ይፈራሉ። " ብለዋል።

የሰሞኑን እገታ ብቻ ሳይሆን በ2 ወራት በፊት 3 ሰዎች ታግተው ከ300 ሺህ እስከ 350 ሺህ ብር ከፍለው መውጣታቸውን አመልክተዋል።

በአካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ እየተፈፀመ ባለው እገታ ምክንያት ነዋሪው በስጋት ቄዬውን እየለቀቀ እየሸሸ ነው ሲሉ አሳውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ ከሳምንታት በፊት የ " አሉቶ ላንጋኖ ጂኦተርማል ፕሮጀክት " ሰራተኞች በታጣቂዎች ታግተዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም ምን ያህል ሰራተኞች እንደሆኑ ባይገልጽም " ሰራተኞቹ ባልታወቁ ኃይሎች መታጋታቸውን አመልክቷል።

የስራ ባልደረቦቻቸው የታገቱት 6 ሰራተኞች እንደሆኑ ገልጸዋል።

እነዚህ ሰራተኞች አሁን ምን ላይ እንዳሉ አይታወቅም። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ባልደረቦቻቸው ለታጋቾች ደህንነት በመስጋት መረጃ ለመስጠት እንደማይፈልጉ ተነግሯል።

ጥቅምት 9 / 2015 ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ዞን፣ የኢስት ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች የሆኑ " የቻይና ዜጎች ታግተው " መወሰዳቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ " አዲስ ስታንዳርድ " ዘግቧል።

ነዋሪዎች እንዳሉት የሸኔ ታጣቂዎች ከሀምቢሶ ከተማ በአምስት ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘውን ኢስት ሲሚንቶ ፉብሪካ በመቆጣጠር በቁጥር ያልታወቁ የቻይና ዜጎችን አግተው ወስደዋል።

ታጣቂዎቹ " ፊቼ " ን ለመቆጣጠር በማሰብ ጋረ ሹሂ በሚባል ቦታ ላይ ከመንግስት ጸጥታ ኃይሎች ጋር ረዘም ያለ እና ከፍተኛ ውጊያ ማድረጋቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸው ታጣቂዎቹ ወደ ጫካ ሲያፈገፍጉ የቻይና ዜጎች አግተው ነው ብለዋል።

በኦሮሚያ ፤ ስለተባባሰው እገታ የክልሉ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል ድርጊቱን የሚፈፅሙት የሽብርተኛ ቡድኑ " ሸኔ ነው " ብሏል።

ይህን የሚፈፀመው የፀጥታ ኃይል ስምሪትን እያየ ነው ሲል ገልጿል።

" ቡድኑ አለሁ ለማለት እና ኪሱን ለማደለብ በንፁሃን ላይ እገታ ይፈፅማል ፣ ያፍናል ፣ ይገድላል " ያለው ክልሉ ፤ " መንግሥት ዜጎች ወጥተው እንዲገቡ ሰላም እንዲረጋገጥ የተቻለውን እየሰራ ነው " ብሏል።

" ሰላም የመላ ህዝብ ነው " ክልሉ " ህዝቡ ተደራጅቶ ሰላሙን ማስጠበቅ ፣ ልማቱን ማስቀጠል አለበት። እኛ እያንዳንዱ ቀበሌ እና ቤተሰብ ላይ የፀጥታ ኃይል ስምሪት መስጠት አንችልም። ስለዚህ ህብረተሰቡ ከመንግሥት የፀጥታ ጋር አብሮ በመስራት ፣ መረጃ በመስጠት ፤ ተደራጅቶ አካባቢውንም መጠበቅ አለበት " ሲል ገልጿል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት / ኦነሰ በበኩሉ መሰል ድርጊት እንደማይፈፅም እና እጁ እንደሌለበት ገልጾ " ይህ የሽፍቶች ስራ ነው " ብሏል ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል።

" ሁኔታው በስልጣን ላይ ካለው አካል አቅም በላይ እየሆነነው " ያለው ታጣቂ ቡድኑ " ይህ የሆነው ደግሞ በየቦታው ሽፍታ በመብዛቱ ነው " ሲል ገልጿል።

የታጣቂው ቡድን ፤ " የእገታ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙት ኃይሎች ከመንግስት ኃይል ጋር ግንኙነት ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም ይችላል " ብሏል።

" ነፍጥ ይዘው መሰል ድርጊት (እገታ) የሚፈፅሙ ተበራክተዋል ፤ በዚህ ምክንያት በስልጣን ላይ ያለው አካል የህዝብን ደህንነት ማስጠበቅ አቅቶታል " ያለው ቡድኑ " ሰላም እና ዴሞክራሲ በሰፈነበት ሀገር መንግት ነኝ የሚል አካል ነበር ተጠያቂነት ወስዶ ማስተካከል የነበረበት ይህን ግን እያየን አይደለም ስለዚህ ወንጀለኞች ነፍጥ አግኝተው መሰል ወንጀል ፈፅመው ራሳቸውን እያበለፀጉ ናቸው " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው የታጠቀ ኃይል) በታንዛኒያ የሰላም ድርድር እየተደረገ ነው ሲል መግለጫ አወጣ። ምንም እንኳን ከቀናት በፊት የዲፕሎማቲክ ምንጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በወታደራዊ አዛዦች አማካኝነት ለሰላም ድርድር መቀመጣቸውን ቢያሳውቁም እስከዛሬ ደረስ ከሁለቱም በኩል ምንም ነገር ሳይባል ቆይቷል። በዛሬው…
#Update

" ከ #ሸኔ ጋር ሁለተኛው ዙር ውይይት አሁንም ቀጥሏል፤ እየተካሄደ ነው የሚገኘው። ... በእኛ በኩል ድርድሩ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንዲሆን ፍቃደኛ አይደለንም " - አምባሳደር መለስ ዓለም

መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ጋር ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጥቷል።

የሰላም ድርድሩ እየተካሄደ መሆኑን ማረጋገጫ የሰጠው ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በሰጠው መግለጫ ነው።

ባለፉት ቀናት የዲፕሎማቲክ ምንጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ላይ እንደተቀመጡ ፣ በዚሁ የሰላም ድርድር ላይ የታጣቂው ቡድን አመራሮች ጃል መሮ ድሪባ እና ጃል ገመቹ አቦዬ ወደ ዳሬሰላም እንዲሄዱ ተደርገው ድርድሩን እየተካፈሉ እንደሆነ መነገሩ አይዘነጋም።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትም ፤ በይፋዊ መግለጫ ድርድሩን በተመለከተ ምንም ሳይባል የቆየው ጃል መሮ ድሪባ እና ጃል ገመቹ አቦዬ ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ድርድሩ ስፍራ እንዲደርሱ በማሰብ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

ታጣቂ ቡድኑ በኦሮሚያ ክልል ላለው ግጭት  ሰላማዊ የፖለቲካ እልባት ለማግኘት ቁርጠኛ መሆኑንም አሳውቆ የሰላም ድርድሩ ሲጠናቀቅ ተጨማሪ መረጃዎችን እንደሚሰጥ ይፋ አድርጓል።

እስከ ዛሬ ድረስ በመንግስት በኩል የሚወጡትን የድርድር መረጃዎች በተመለከተ ምንም ሳይባል ቆይቷል።

በዛሬው ዕለት ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ምንም እንኴን የተብራራ ነገር ባይገልጹም በታንዛኒያ ሁለተኛው ዙር ድርድር ከ " ሸኔ " ጋር እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ " የመጀመሪያው ዙር ከሸኔ ጋር የተደረገ ውይይት ነበር ሁለተኛ ዙር አሁንም ቀጥሏል። እየተካሄደ ነው የሚገኘው " ብለዋል።

" በእኛ በኩል ድርድሩ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንዲደረግ/እንዲሆን ፍቃደኛ አይደለንም። ስለዚህ ጊዜው ሲደርስና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ይፋ የሚሆን ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ " የዲፕሎማሲ አንደኛው ባህሪ በግልፅም በይፋም የሚደረጉ ነገሮች እንዳሉ ሆነው ሌሎች ነገሮች ግን ጊዜያቸውን የሚጠብቁ እንደሆኑ መረዳት ያስፈልጋል። ግን እየተከናወነ እንደሆነ እገልፃለሁ። " ብለዋል።

እንደ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ከሆነ የሰላም ድርድሩ እየተመራ ያለው በጦር አዛዦች ሲሆን ኃላ ላይ የመንግሥት የፖለቲካ ሰዎች (የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የፍትህ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮ) ወደ ታንዛኒያ አምርተው ድርድሩን ተቀላቅለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ትላንት በተጠናቀቀው የካቲት ወር በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካቶች ተገድለዋል። ጉዳትም ደርሷል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወሩ ስለነበሩት ሁኔታዎች ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት እጅግ በርካታ ቀናትን የወሰደ ሙከራ ቢያደርግም ምንም ምላሽ የሚሰጠ አካል አላገኘም። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ግን ስለነበሩት ሁኔታዎች…
#AmharaRegion

° " ህዝቡ በታጠቁ ቡድኖች ነው ለጥቃት የተዳረገው በገዛ ከተማው ነው መአት ያወረደበት ... ጥቃት ፈፃሚዎቹ ከአጎራባች ' ሸኔ ' ናቸው " - የአጣዬ ከተማ ከንቲባ

° " #ሀሰት_ነው የኦሮሞ አርሶ አደሮች እንጂ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት አይደሉም " " - አባገዳ አህመድ ማህመድ

በአማራ ክልል ፤ የሰሜን ሸዋን እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደርን በሚያጎራብቱ አካባቢዎች ላይ ግጭት ከጀመረ ከሳምንት በላይ ሆኖታል።

በተደጋጋሚ ፦
- የሰዎች ደም በሚፈስበት፣
- ንብረት በሚወድምበት ፣
- ሰዎች ቄያቸውን ለቀው በሚፈናቀሉበት በዚህ ቀጠና ባለፈው የካቲት ወር ውስጥም በርካቶች መገደላቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ #ከ8_ቀናት በፊት የተቀሰቀሰው ግጭት እጅግ መባባሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በመነሻው ላይ በሁለቱም በኩል እርስ በእርስ መወነጃጀል ያለ ሲሆን በኤፍራታ ግድምና ቀወት ውስጥ ግጭቱ ከፍቶ መዋሉ ነው የተሰማው።

በሁለቱም በኩል ያሉት ነዋሪዎች ፣ የአጣዬ ከንቲባ ፣ የአካባቢው አባገዳ ምን አሉ ?

በኤፍራታ ግድም ወረዳ የአላላ ከተማ ነዋሪ ፤ ጦርነት ከተጀመረ 8 ቀን መያዙን ፣  ብዙ ቤቶች መቃጠላቸውን ገልጸዋል።

ነዋሪው " የአርሶ አደሮች ዱቄት ሳይቀር ፣ በግ ፣ ፍየል ፣ ግመል ፣ አህያ፣ ከብት በሙሉ ሙልጭ አድርገው ወስደውብናል። ኃላሸት የሚባል ሰውም ገድለውብናል እኛው ክልል ላይ ገብተው " ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ካደረጉ በኃላ ህዝቡ ተሬ እና ዘንቦ ወደሚባለው አካባቢ በለበሰው ልብስ ሸሽቶ ተጠልሎ እንደሚገኝ ገልጸዋል። " በተከታታይ 18 ሰዎችን ገድለውብናል "ም ብለዋል።

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰንበቴ ነዋሪ ፤ " እስከ ጅሌ ጥሙጋ ባርሲሳ ፣ ካራ ሌንጫ ፣ መከና ወይም አጣዬ ከተማ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ከትላንትና ጀምሮ ተኩስ ነበር። ትላንት አንዲት ሴት እንዲሁም ግመልና ከብቶችም ተመተው ነበር ግጭቱ የቀጠለው በዚህ ነው፤ አንድ ሰው ሲሞት ሁለት ሰው ቆስለዋል፤ አንዱ ወደ አዳማ ተልኳል። ዛሬ ደግሞ 4 ሰው ሲሞት 3 ሰው ቆስሏል " ብለዋል።

ዋነኛው እቅዳቸው የጅሌ ጥሙጋ ከተማ #ሰንበቴን " እንይዛለን ፣ እናጠፋለን " የሚል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አንድ የአጣዬ ነዋሪ ደግሞ ፤ ሰሞኑን ግጭት ተባብሶ ዛሬ አጣዬን በተኩስ ልውውጥ ሲያናውጥ መዋሉን ፣ 5 ሰው መገደሉም. ጥቃት ፈፃሚዎቹ የታጠቁ አካላት " ሸኔ " ናቸው ብለዋል።

ሌላው የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ፣ የሰንበቴ ነዋሪ " ግጭቱ የጀመረው #መጋቢት_አንድ ላይ ነው። ይህም በጅሌጥሙጋ ኮላሽ የሚባል ስፍራ 1 ሰው ገድለው 2 ሰው አቁስለው ከብቶችንም ነድተው ከሄዱ በኃላ ነው ግጭቱን የተስፋፋው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ከባልች ቀበሌ እስከ ሰንበቴ እና መከና አጣዬ ድረስ ጦርነት ነው። የዛሬውን ለየት ያደረገው ታጣቂዎቹ #ከሰሜን_ሸዋ ተሰባስበው ፤ እራሳቸውን አደራጀትው ሌሊቱን በተሽከርካሪዎች ተጉዘው መጥተው ውጊያ መክፈታቸው ነው " ሲሉ አክለዋል።

ባለፉት 10 ቀናት 29 ሰዎች መገደላቸውን ተናግረው የተወሰዱት ከብቶችና የወደመው ንብረትም ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ አስተያየት #አልቀበልም ያሉት የአላላ ነዋሪው ፤ " አማራው ሲያጠፋ በአማራው አጥፊውን መዞ ለህግ ማቅረብ፤ ከኦሮሞውም ሲያጠፋ አጥፊውን መዞ ለህግ ማቅረብ ሰላም የሚያሰፍነው ይሄ ብቻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" በህግ እና በሽምግልና  ነገሩ መክሰም አለበት እነሱ የሚሉት ከጨፋ ጀምሮ እስከ ሸዋሮቢት ድረስ የኦሮሞ ቦታ ነው። አጣዬም #የኛ_ነች ፤ አላላም ፣ ሞላሌም ፣ ማጀቴም ... ሁሉም የኛ ነው የሚሉት። መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ችግሩን ሊፈታው ይገባል " ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን #አባገዳ አህመድ ማህመድ " መንገድ የለም። ከጅሌ ጥሙጋ እና አርጡማ ፋርሲ ወረዳዎች እንዲሁም ከዞን መገናኘት አልቻልንም " ብለዋል።

" በዚህ ምክንያት የሃይማኖት አባቶች እና አባ ገዳዎች ተሰባስበው መፍትሄው ምንድነው ? ለማለት መንገዱ ተከፍቶ ለህዝቡ ምግብ ለማድረስ ፣ የቆሰሉትንም ወደ ህክምና ቦታ ለመውሰድ ጥረት ላይ ነን። መንገድ ከተዘጋ 1 ወር ሊሆነው ነው። እኛም ሆነ መንግሥታዊ አመራሩ ሄደን ማየት አልቻልንም። የአማራ ክልልም #ታጣቂዎቹን_ስለሚፈሯቸው ቀርበው ለማነጋገር አልተቻለም። እኛ ጋር ያሉትን #ወሰናችሁን አልፋችሁ አትሂዱ እያልን እየመከርናቸው ነው ። " ገልጸዋል።

ነዋሪዎችና የአካባቢው አስተዳደሮች ጥቃቱን የከፈቱት " ሸኔ (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) " ናቸው ቢሉም አባገዳ አህመድ " ሀሰት ነው " ብለዋል።

" ሀሰት ነው የኦሮሞ አርሶ አደሮች እንጂ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት አይደሉም። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እዚህ አልገባም። እየተዋጋ ያለው እራሱ ነዋሪው ነው " ብለዋል።

የአጣዬ ከተማ ከንቲባው ተመስገን ተስፋ ፤ ከተማዋና ህዝቡ በታጠቁ ቡድኖች ነው ለጥቃት የተዳረጉት ብለዋል።

አጣዬ ላይ ' #ወረራ ' መፈፀሙን ገልጸው " ሰውም አልቋል፤ ሚሊሻውም የሚችለውን ያህል ሞከረ አለቀ " ብለዋል።

ይህን የሚፈፅሙት ከአጎራባች  " #ሸኔ በሏቸው " ሲሉ የጠሯቸውን የታጠቁ ኃይሎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

" ዋናው መፍትሄ መንግሥት ጠንከር ብሎ #እርምጃ መውሰድ ያለበት ላይ እርምጃ መውሰድ ፤ ይሄ ነበረ መፍትሄው  አሁን ባለው መንገድ ፣ #በእሹሩሩ ሰውም አለቀ " ብለዋል።

#የአጣዬ_ህዝብ የገዛ ከተማው ላይ እንዳለ መአት እንደወረደበት የገለጹት ከንቲባው " እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፤ መንግስት ቢደርስልን ጥሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በኩል ለጥፋቱ ለችገሩ " የፋኖ ታጣቂዎችን " ተጠያቂ ሲያደርጉ ከሰሜን ሸዋ ዞን በኩል ደግሞ " ሸኔን (የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) " ተጠያቂ ያደርጋሉ።

NB. ባለፉት አምስት ዓመታት አጣዬ ከ10 ጊዜ በላይ የመቃጠል አደጋ አስተናግዳለች።

እስካሁን የአማራ ክልል መንግሥት ስለ ጉዳዩ ያለው ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ #ባለቤትነቱ የቪ.ኦ.ኤ. ራድዮ (ጋዜጠኛ መስፍን አራጌ) መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia