TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#IFTAR በደሴ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሄደ። በደሴ ከተማ ዛሬ ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት " ኑ በጋራ እናፍጥር" በሚል ተካሂዷል። የኢፍጣር ስነስርዓቱ ከ " ፒያሳ እስከ መናኸሪያ " ባለው ጎዳና ላይ የተካሄደ ሲሆን እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የደሴ ከተማ ነዋሪ ታድሟል። በሌላ በኩል ደሴ የረመዳንን በዓል አስመልክቶ " ከኢድ እስከ ኢድ " በተሰኘው መርሃ ግብር ደሴ የሚገቡ…
#Iftar

የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው።

አርብ በደሴ ለሁለተኛ ጊዜ ታላቅ የሆነ የጎዳና ላይ ኢፍጧር መካሄዱ ይታወሳል።

ትላንት ደግሞ በቡታጅራ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ ኢፍጧር ከማርስ ታወር ህንፃ - መናኸሪያ ድረስ ተካሂዷል (ፎቶው ከላይ ተያይዟል) ። ዝግጅቱን ያዘጋጀው ኢኽላስ በጎ አድራጎት ማህበር መሆኑን አዘጋጆቹ ገልፀውልናል።

በአሁን ሰዓት ደግሞ በኮምቦልቻ እና ሀረር ከተማ የኢፍጣር ስነ ስርዓት ለማካሄድ ዝግጅት እየተካሄደ ነው የሚገኘው።

(በሌሎች አካባቢዎች ላይ ያለውን ተከታትለን እናሳውቃለን)

ፎቶ ፦ ከቡታጅራ (ሚያዚያ 8)

@tikvahethiopia
@TikvahGift

ውድ ቤተሰቦቻችን የትንሳኤ በዓል መዳሻ አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በበዓላት ወቅት ከምናደርገው በተለየ የ " እንኳን አደረሳችሁ " የሞባይል ካርድ ስጦታዎች ተዘጋጅተዋል።

ለ10 ቀናት በተከታታይ በሚቆየው በዚሁ መርሃግብር በየዙሩ ለበርካታ የቤተሰባችን አባላቶች የሞባይል ካርድ እና ፓኬጅ ሽልማቶች ተዘጋጅተዋል።

Tikvah Gift https://t.iss.one/+SnnnagG5QdRvkFPX

@tikvahgift
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት📣 የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎና ከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ፤ " የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወደ ቅዱስ ላልይበላ ዓለም አቀፍ ቅርስ ሊመለከት ይገባል " ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። ብፁዕነታቸው ቅዱስ ላልይበላን በማስመልከት ዛሬ በተሰጠ መግለጫ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በነበረው ጦርነት የቅዱስ ላልይበላ ቅርስ የቱሪዝም እና የከተማው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጫና ውስጥ መውደቁን…
#HappeningNow

" ወደ ቅዱስ ላልይበላ ተመልከቱ ! "

ለታሪካዊው እና ዓለማቀፋዊው የላልይበላ ቅርስ በሸራተን አዲስ ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

የቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስቲያናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሃይማኖቶች እና ብሔረሰቦች ከዚያም አልፎ የዓለም ሁሉ ቅርስ በመሆናቸው ቅርሱን በመጠበቅ ላይ ያሉ ወገኖችን መርዳትና መደገፍ የዓለም ሁሉ ትኩረት ሊሆን እንደሚገባ ተገልጿል።

" ወደ ቅዱስ ላልይበላ ተመልከቱ!" በሚል ጥሪ ዛሬ በሸራተን አዲስ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በዚህም ለጥንታዊው እና ታሪካዊው ላልይበላ ካህናት፣ ገዳማውያን፣ ቅርስ ጠባቂዎች ፣ የአብነት ተማሪዎች ፣ አረጋውያን እና ህጻናትን ለመርዳት ብሎም የቅርሱን ልማት ለማፋጠን ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ መቅረቡን የኢኦተቤ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ማስታወሻ፦ ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አቢሲኒያ እና ዳሽን ባንኮች በ 👉 0712 የባንክ የሒሳብ ቁጥር ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia
#ረመዳን

የታላቁ የረመዳን ፆም በትግራይ ክልል መቐለ ምን ይመስላል ?

የእልምና እምነት ተከታዮች ለቪኦኤ ሬድዮ የሠጡት ቃል ፦

አቶ አደም ያሲን ሐሰን ፦

" ሀብታሞቹ በተቻለ መጠን ይተባበራሉ ፤ እንደ ድሮ ሳይሆን ችግር በጣም ችግር አለ።

ድሮ ሃብታሞች ይሰጡ ነበር 30 ሰው ፣ 10 ሰው ብለው ይወስኑ ነበር አፍጥር ላይ ፤ አብልተው አጠጥተው ፣ ልብስ ሰጥተው ይሰዱ ነበር አሁን እንደሱ አልተቻለም።

ኢኮኖሚያቸው፤ ከኪሳቸውም ብዙ ወጪ የሚያደርጉት ስለሌለ ፤ ገንዘብም ስላጠራቸው ብዙ ለመስራት አልተቻለም። ባንክ ስለሌለ፣ ስራ ስለሌለ ሊረዱና ሊንቀሳቀሱ አልቻሉም። "

አቶ አህመድ አወል ፦

" መሰረታዊ ነገሮች እንደ ቴምር ፣ እንደ ሩዝ ፣ ዘይት ለማግኘት በጣም ከባድ ነው። ህብረተሰቡ ካለችው ትንሽ ከሚያፈጥራት ነገር እያካፈለ ነው እያሳለፈ ያለው።

የአፍጥር ፕሮግራም ድሮ ጥሩ ነበር፤ ያለውን አዘጋጅቶ አሰባስቦ ብርም፣ ቴምርም፣ ምግብም ይሁን አዘጋጅቶ ምስኪኖችን ጠርቶ ያበላ ነበር አሁን ግን ከብዷል።

ለራሱ ስለከበደው ለራሱ ማፍጠሪያ ያደረጋት ትንሽ በሰሃን አድርጎ ለጎረቤትም ያለችውን ነው እንጂ እንደድሮ አይደለም ከበድ ይላል።

ይህ ለረመዳን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ህብረተሰቡ በጣም ተቸግሯል። በተለይ በረመዳን ፆመ ውለህ የሚበላ ስታጣ በጣም ይሳዝናልም።

የመተጋገዝ ባህልን ለማስቀጠል ተቸግረናል ሃብታም ይሁን ድሃ አሁን ላይ ባንክ በመዘጋቱ፣ ስራም ስለሌለ እኩል ሆኗል።

እኔ በህይወቴ ብዙ ረመዳን አሳልፊያለሁ ፤ እንደአሁኑ አይቼም አላውቅም፤ ከባድ ነው የዓለም ማህበረሰብ አንዳች መፍትሄ ካላመጣ በጣም የሚከብድ ነው። "

ወ/ሮ ስትሆነ መሐመድ ብርሃን ፦

" ... ረመዳን በጣም ያሳዝናል ፤ የነበረው እና አሁን ያለው በጣም ይለያያል፤ ግን ምን ማድረግ አይቻልም ወቅቱ ያመጣው ስለሆነ ለአላህ ጥለን ዱአ ማድረግ ብቻ ነው። ፍጡር በልቶ ለሊት የማይበላ ሰው ነው የሚበዛው ከዚህ የሚያሳዝን ነገር የለም ሰው ለመኖር መብላት አለበት ካልበላ በጣም ያሳዝናል።

የሚኖር ሰው ለደስታ፣ ለሳቅ ፣ ለጫወታ ነው ከዚህ ሁሉ የወጣን ነን እኛ ፤ የትግራይ ሰው እጅግ በጣም ያሳዝናል በዚህ በዚህ ሲታይ፤ ባንክ የለም፣ ማውጣት የለም፤ ያለውም ብር አጥቷል የሌለውም አጥቷል ሁሉም አንድ ነው። ያለው በጣም በብዙ ችግር ነው ዱአ አድርጉልን ፤ በዓለም ላይ ያላችሁ በሙሉ ዱአ አድርጉልን። "

አቶ አብዱራህማን መሀመድ ሳላህ፦

" በዚህ ረመዳን ላይ የኑሮው ጉዳይ በጣም እየወረደ ነው ያለው። እንቅስቃሴ የለም፤ ሌላው ግን በሰላም ሰግደን እወጣለን ፣ መስጂጋችን በሰላም እንገባለን፣ እንደድሮው ነው ሰላም ያለነው አልሃምዱሊላህ ፤ ሰላም ስላልነበር አምና ቤታችን ነበር የምንሰግደው አሁን አልሃምዱሊላህ ሰላም ነው። ቤት ባፈራው ነው እንጂ ፤ እንደድሮ አፍጥር በወዙም የለም፤ እንቅስቃሴ የለም ገቢ የለም "

የቀጣዩ ዓመት ረመዳን ፤ አሁን ያለው ችግር ተወግዶ ሰላም የሰፈነበት እንዲሆን ያላቸውን ምኞት ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Iftar የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው። አርብ በደሴ ለሁለተኛ ጊዜ ታላቅ የሆነ የጎዳና ላይ ኢፍጧር መካሄዱ ይታወሳል። ትላንት ደግሞ በቡታጅራ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ ኢፍጧር ከማርስ ታወር ህንፃ - መናኸሪያ ድረስ ተካሂዷል (ፎቶው ከላይ ተያይዟል) ። ዝግጅቱን ያዘጋጀው ኢኽላስ በጎ አድራጎት ማህበር መሆኑን አዘጋጆቹ ገልፀውልናል። በአሁን ሰዓት ደግሞ በኮምቦልቻ…
#Iftar

#Assosa #Kombolcha #AA #Harar #Metu #Tullubolo

ዛሬ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ላይ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት ተካሂዷል።

በተለይም በታሪካዊቷ እና ጥንታዊቷ ሀረር ከተማ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን በተገኘበት ነው የአፍጥር ስነ ስርኣቱ የተካሄደው።

በኮምቦልቻ ከተማ ፥ ዛሬ ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጣር " ኑ አብረን እናፍጥር " በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል። በስነስርዓቱ ላይ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ባለፈ የሌሎች እምነት ተከታዮች የተገኙ ሲሆን ስነስርኣቱ እጅግ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።

በመዲናችን አዲስ አበባ ደግሞ በነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት አስተባባሪነት ዛሬ በ11 ጎዳናዎች ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዶ በሰላም መጠናቀቁን አዘጋጆች አሳውቀውናል።

በተጨማሪ ዛሬ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ከተካሄደባቸው ከተሞች መካከል አሶሳ አንዷ ስትሆን ፤ ስነ ስርዓቱ በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች አስተባባሪነት ነው የተካሄደው። በመርሃ ግብሩ ላይ ወላጅ አልባ እና አቅመ ደካሞች፣ አረጋዊያን እና ደጋፊ የሌላቸው ወገኖች ከከተማው ሙስሊም ህብረተሰብ ጋር በጋራ አፍጥረዋል።

በአፋር ክልል ዱብቲ ከተማም ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል ፤ " አንድነታችንን እያጠናከርን ኑ በጋራ እናፍጥር " በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተካሄደው።

በመቱ እና በቱሉቦሎም ዛሬ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተካሂዷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow " ወደ ቅዱስ ላልይበላ ተመልከቱ ! " ለታሪካዊው እና ዓለማቀፋዊው የላልይበላ ቅርስ በሸራተን አዲስ ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው። የቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስቲያናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሃይማኖቶች እና ብሔረሰቦች ከዚያም አልፎ የዓለም ሁሉ ቅርስ በመሆናቸው ቅርሱን በመጠበቅ ላይ ያሉ ወገኖችን መርዳትና…
" ወደ ቅዱስ ላልይበላ ተመልክቱ "

ትላንት ምሽት በሸራተን አዲስ የቅዱስ ላልይበላ ገዳም ካህናትና አገልጋዮችን ለመደገፍ " ወደ ቅዱስ ላልይበላ ተመልክቱ ! " በሚል የገቢ ማሰባሰቢያ ስነስርዓት ሲካሄድ እንደነበር መልዕክት ልከንላችሁ ነበር።

በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር 8 ሚሊዮን ብር ያህል መሰብሰቡ ይፋ ተደርጓል።

ማስታወሻ ፦ ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አቢሲኒያ እና ዳሽን ባንኮች በ 👉 0712 የባንክ የሒሳብ ቁጥር ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia
#ATTENTION📣

በአማራ ክልል ፤ በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ ቦታዎች ከትላንት ጀምሮ የፀጥታ ችግር መፈጠሩን ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።

ግጭት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች በርካቶች ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ሲሆኑ በዙሪያቸው የሚገኙ ቦታዎች ላይም ጭንቀት እና ውጥረት ፈጥሯል።

በተለይ ደግሞ አጣዬ እና በዙሪያዋ ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ ችግር ስለደረሰባት የአካባቢው ነዋሪ በከፍተኛ ፍረሀት ላይ እንደሚገኝ ቤተሰቦቻችን አመልክተዋል።

ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ ባሶች ፣ አነስተኛ የህዝብ ማመላላሻ መኪኖች መንገድ በመዘጋቱ በመቆማቸውም መንገደኞች በከፍተኛ እንግልት ላይ ናቸው።

ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ከተማ እየመጡ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ቆመው ከሚገኙባቸው ቦታዎች አንዷ አጣዬ ስትሆን ፤ አጠቃላይ የትራንስፖርት አገልግሎት በፀጥታ ችግር ተስተጓጉሏል።

ይህ ቀጣና ከዚህ በፊትም እጅግ ከፍተኛ የዜጎች ስቃይ የደረሰበት ፣ ሰው የቀጠፈበት፣ ንብረት የወደመበት በመሆኑን አሁን እየታየ ያለው ምልክት በእጭሩ እንዲቀጭ ማድረግ እንደሚገባ እና ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ የአካባቢው ቤተሰቦች አሳስበዋል።

ፎቶ ፦ ELA (Tikvah Family)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሂደት ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን እንዲያጣራ ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላከው ኮሚቴ ምንድነው ያለው ? የ2013 የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት አስመልክቶ የአማራ ክልል ትምህርት ባቀረባቸው ቅሬታዎች ላይ የተደረሰበት ሂደት ኮሚቴው ለህዝብ አሳውቋል። በዚህም መሰረት ፤ በጦርነት አውድ ውስጥ ቆይተው ፈተና እንዲወስዱ የተደረጉ በክልሉ የሁሉም…
#NewsAlert

ትምህርት ሚኒስቴር በጦርነት እና ግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ እና የ12ኛ ክፍል " የማለፊያ ውጤት ያላመጡ " ተማሪዎች በዚህ ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ ሆነው መፈተን እንደሚችሉ አስታወቀ፡፡

ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ተጨማሪ የቅበላ አቅም እንዲኖር ከስምምነት ላይ መደረሱን እና ተጨማሪ የቅበላ አቅም በፍትሀዊነት በጦርነቱ ምክኒያት ለተጎዱ ክልሎች እንዲከፋፋል ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ፣ የሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች በጋራ መግለጫ እየሰጡ እንደሚገኙ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia