TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ትምህርት ሚኒስቴር በጦርነት እና ግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ እና የ12ኛ ክፍል " የማለፊያ ውጤት ያላመጡ " ተማሪዎች በዚህ ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ ሆነው መፈተን እንደሚችሉ አስታወቀ፡፡ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ተጨማሪ የቅበላ አቅም እንዲኖር ከስምምነት ላይ መደረሱን እና ተጨማሪ የቅበላ አቅም በፍትሀዊነት በጦርነቱ…
#ውሳኔ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎችን አስመልክቶ ውሳኔ መተላለፉን አሳውቋል።

ከውሳኔዎቹ አንደኛው ከዚህ በፊት በተላለፈው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች መግባት ከቻሉት የክልሉ ተማሪዎች በተጨማሪ 4339 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ቅበላ እንዲያገኙ ተወስኗል ብሏል።

እነዚህ 4339 ተማሪዎች እንዴት እና በምን አግባብ ቅበላ ሊያገኙ እንደቻሉ (የተበላሸ ውጤታቸው ተስተካክሎ ወይስ ሌላ ስለሚለው) ቢሮው ዝርዝር ማብራሪያ አልስጠም።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሌላ ተላልፏል ያለው ውስኔ ፥ በ2013 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመግቢያ ነጥብ ያላሟሉ የክልሉ #ሁሉም_ዞኖች ተማሪዎች በ2014 ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በመደበኛ ተማሪነት (as regular students) መፈተን እንደሚችሉ ነው።

ቢሮው ፤ ትምህርት ሚኒስቴር የውጤት መቁረጫ ነጥብ ተወስኖ እና ያለፉት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫ ፎርም የሚሞላበት የመጨረሻው ቀን ከተወሰነ በኋላ ከአማራ ክልል በተነሳ ቅሬታ መነሻነት ቅሬታውን አዳምጦ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ማድረጉ ትልቅ መደማመጥ የተስተዋለበት ነበር ሲል ገልጿል።

" ይህም ለቀጣይ በመደማመጥ ላይ የተመሰረተ የሀገር ግንባታ ጉዟችን አንድ ማሳያ ነው ብለን እናስባለን " ሲል አክሏል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከተፈጠረው ችግር አኳያ ውሳኔው ያላረካቸው አካላት ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገመታል ያለ ሲሆን የክልሉ ተማሪዎች በመደበኛ ተማሪነት የመፈተን እድሉን በድጋሜ ማግኘታቸውን እንደ ትልቅ አጋጣሚ አድርገው ለውጤታማነት እንዲጠቀሙበት አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ስርቆትን ለመከላከል ፈተና በኦንላይን የማስፈተን ፤ ይህ ባይሆን እንኳን ተማሪዎችን ወደ ማዕከል ዩኒቨርሲቲዎች በማስመጣት ፈተና ለመስጠት እያሰበ ነው። የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ለህ/ተ/ም/ቤት በሰጡት ማብራሪያ ባለፈው ዓመት ተጀምሮ የነበረውን የ12ኛ ክፍል ፈተናን በታብሌት ለመስጠት የተጀመረውን ስራ በከፍተኛ ደረጃ እየገፋንበት ነው ብለዋል። ሂደቱ…
#NewsAlert

ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በፌደራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንዲሰጡ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

መኮራረጅ፣ የፈተና ስርቆትና ሌሎች ችግሮችን ለማስቀረት ከዚህ በኋላ ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በትምህርር ቤቶች ሳይሆን በፌደራል ተቋማት ውስጥ ብቻ የሚሰጡ ይሆናል ሲሉ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል።

ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት የትምህርት ጥራት ላይ እንሰራለን ያሉት ሚኒስትሩ አንዱ ችግር ከሀገር አቀፍ ፈተና ጋር ተያይዞ የሚነሳ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ እየሰራን ነው ብለዋል።

ሚኒስቴሩ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ለመስጠት የሚያስችሉ አንድ ሚሊዮን ታብሌቶችን በማስመጣት ላይ መሆኑን ፕሮፌሰር ብርሀኑ መግለፃቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#US_VISA

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በስቴት ዲፓርትመንት በተቀመጡና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች መሰረት Diversity Visa (ዲቪ) ን ጨምሮ ሁሉንም የስደተኛ እና ስደተኛ ያልሆኑ የቪዛ ሂደት ማስቀጠል መጀመሩ ዛሬ አሳውቋል።

እስካሁን በትዕግሥት ለጠበቁም " ትዕግስታችሁን እናደንቃለን " ብሏል።

የአሜሪካ ኤምባሲ ፤ ቀጠሮ ለመያዝ ጊዜው ሲደርስ አመልካቾች መረጃ በኢሜል ይላክላቸዋል ያለ ሲሆን ጥያቄ ካላችሁ ይህንን ድረገፅ ጎብኙ ብሏል ፦ https://et.usembassy.gov/visas/

የአገልግሎቱ ፈላጊዎች " የግል ጉዳዮቻቸውን " በተመለከተ ጥያቄያቸውን በፌስቡክ ወይም በሜሴንጀር በኩል ቢያነሱ ለጥያቄያቸው መልስ መስጠት እንደማይችል የገለፀው የአሜሪካ ኤምባሲ " የግል መረጃችሁን በፌስቡክ ገፁ ላይ አታጋሩ " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከፍተኛ ጫና እያሳደረብን ነው " የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ምደባ የሚጠባበቁ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ምደባው እንዲፋጠንለቸው በድጋሚ ጠይቀዋል። የመጀመሪያውን ዙር ፈተና ተፈትነው እና ውጤታቸውን አውቀው ቤታቸው የተቀመጡ ተማሪዎች 6ኛ ወራቸውን ሊደፍኑ እየተቃረቡ ይገኛሉ። እስካሁን ምደባ ይፋ የሚሆንበት ቀን ይፋ ያልተደረገ ሲሆን ይህ ሁኔታ ተማሪዎችና ወላጆችን ጫና ውስጥ…
#የዩኒቨርሲቲ_ምደባ

የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ፤ ከተያዘው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ የ2013 ዓ.ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች የዩኒቨርሲቲ ምደባቸውን ማወቅ ይችላሉ ሲል አሳውቋል።

መቼ ? በየትኛው ቀን ? ስለሚለው ጉዳይ አንድ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ቁርጥ ያለውን ቀን ለማሳወቅ እየተሰራ መሆኑን እና ሚኒስቴሩ ቀኑን እንደሚያሳውቁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#አቢሲንያ_ባንክ

የባንካችን የስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ሳያሳስብዎት 24 ሰዓት ከ እሁድ እስከ እሁድ በመረጡት የቨርቹዋል ባንኪንግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመገኘት ገንዘብዎን ተቀማጭ ወይም ወጪ ማድረግ ይችላሉ።

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
#Russia #Ukraine

ሰሞኑን አዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በር ላይ በርካታ " ኢትዮጵያዊያን ሩሲያን ወግነው ዩክሬንን ለመውጋት " ለመመዝገብ ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው የሚል ምስል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ ነው።

ኢትዮጵያውያኑ በእጃቸው ላይ ዶክመት ይዘው ተሰልፈው ይታያል።

የሩስያ ኤምባሲ ፕረስ አታቼ የሆኑት ማሪያ ቸርኑኪና ለአል ዐይን በሰጡት ቃል ፤ " ሩሲያ ለዩክሬን ጦርነት ኢትዮጵያዊያንን ለመቅጠር ማስታወቂያ አላወጣችም፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መረጃም ሀሰተኛ ነው " ሲሉ መልሰዋል።

ነገር ግን ኢትዮጵያውን ወደ ኢምባሲው መሄዳቸው እውነት መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያውያን ወደ ሩሲያ ኢምባሲ የሄዱት ለምልመላ ሳይሆን ለሩሲያ ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት መሆኑን ነው የገለፁት።

ይሁንና ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት " በርካታ ኢትዮጵያዊያን በኢሜይል እና በአካል ከሩሲያ ጎን መሆናቸውን እያሳወቁን ነው ለዚህ እናመሰግናለን " ሲሉም አክለዋል።

ኢትዮጵያዊያን ይሄንን እያደረጉ ያለው ረጅም እና ታሪካዊ በሆነው የኢትዮጵያ እና ሩሲያ ወዳጅነት ላይ ስለሚተማመኑ እንደሆነ ኤምባሲው ተገልጿል።

የዩክሬን ኤምባሲ ደግሞ ሩስያ ምልመላ እያደረገች ነው በሚል የተሰራጨውን መረጃ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ ማጣሪያ ድረገፅ በሰጠው ቃል ፤ "ይህ አሳዛኝ ድርጊት ነው። አንድ ኢትዮጵያዊ በዚህ ጦርነት ህይወቱ ቢያልፍ ለዩክሬንም ሆነ ለኢትዮጵያ አሳዛኝ ክስተት ይሆናል። " ብሏል።

መረጃው የአል ዓይን ኒውስ እና የኢትዮጵያ ቼክ የመረጀ ማጣሪያ ድረገፅ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የዋጋ ግሽበት📈

መቆሚያ ያልተገኘለት የዋጋ ግሽበት አሁንም ማሻቀቡን እንደቀጠለ ነው።

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ እንደሚያሳየው የመጋቢት ወር 2014 ዓ/ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ34.7 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የምግብ ዋጋ ግሽበት የመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ43.4 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ከየካቲት ወር 2014 ጋር ሲነጻጸር በ1.5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

በያዝነውም ወር በአብዛኛው በእህሎች የዋጋ ጭማሪ የታየ ሲሆን የአትክልት ዋጋም ላይ መጠነኛ ጭማሪ ታይቷል፡፡

ሩዝ፣ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽንቡራና ምሥር በአብዛኛው የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡

በተጨማሪም ወተት፣ አይብና ዕንቁላል፣ ቅመማ ቅመም (በዋናነት ጨውና በርበሬ) ጭማሪ አሳይተዋል፡፡

የምግብ ዘይትና ቅቤ ዋጋ በፍጥነት የጨመረ ሲሆን ቡናና ለስለሳ መጠጦች ተከታታይ የዋጋ ጭማሪ ማሳየታቸውን ኤጀንሲውን ዋቢ አድርጎ ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... እንዲህ ብሎ መናገር ከባድ ነው ግን ዓለም መባላትን መርጧል። " - ፖፕ ፍራንሲስ በጎርጎራውያኑ ዘመን አቆጣጠር የክርስትና እምነት ተከታዮች የእየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓልን አከብረዋል። በዓሉ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ የተከበረ ሲሆን በአውሮፓ ሀገራት፤ በዩክሬንና ሩስያ ጦርነት ሳቢያ በዓሉ ተቀዛቅዞ ነው የተከበረው። በዓሉን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን…
" ሰው እየተሰቃየ ጡንቻን ማሳየት ይብቃ " - ፖፕ ፍራንሲስ

በዓለም ዙሪያ ያሉ ጦርነቶች እና ግጭቶች እንዲያበቁ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ሊቀ ጳጳሳ ፖፕ ፍራንሲስ አሳስበዋል።

ይህን ያሳሰቡት ትላንትና የትንሳኤን በዓል አስመልክቶ ባሰሙት ቡራኬ ነው። ዕለቱን " በጦርነት የተወረሰ የትንሳኤ በዓል " ያሉት ሲሆን ዐለም ለክፋት እና ለብጥብጥ እንዳይንበረከክ ተማጽኖ አቅርበዋል።

100,000 የሚጠጉ ምእመናን ፊት በሮም የጴጥሮስ አደባባይ ቆመው " ብዙ ደም መፋሰስ፣ ብዙ ዓመፅ አይተናል " ያሉት ፖፕ ፍራንሲስ " ብዙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ራሳቸውን ከቦምብ ለመከላከል ሲሉ በአሁኑ ሰዓት ተሸሽገው ይገኛሉ " ሲሉ ስለ ዩክሬን ጦርነትና ለጦርነቱ ሰለባዎች አፅኖት ሰጥተው አሳስበዋል።

በሌሎች አካባቢዎች እንደ መካከለኛው ምስራቅ ፣ ሊባኖስ ፣ ሶሪያ ፣ የመን ፣ ኢራቅ ፣ አፍጋኒስታን፣ ሊቢያ እና አንዳንድ የአፍሪካ ክፍሎች ባሉ ግጭቶች ብዙ ሰዎች ስቃይ ላይ እንደሆኑም በማስታወስ ፤ ሰላም ማስፈን ይቻላል፣ ሰላም ግዴታ ነው፣ ​​ሰላም ቀዳሚ እና የሁሉም ሰው ሀላፊነት " ነው ብለዋል።

" ዐለም ጦርነትን መላመድ የለበትም፥ አዲስ የተስፋ ቀን ይምጣ፥ ለሰላም በቁርጠኝነት እንቁም ፥ ሰው እየተሰቃየ ጡንቻን ማሳየት ይብቃ " ያሉት የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ " የዐለም መሪዎች የህዝቡን ተማጽኖ ይሰማሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

መረጃው ከቪኦኤ እና ዶቼ ቨለ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION📣 በአማራ ክልል ፤ በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ ቦታዎች ከትላንት ጀምሮ የፀጥታ ችግር መፈጠሩን ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል። ግጭት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች በርካቶች ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ሲሆኑ በዙሪያቸው የሚገኙ ቦታዎች ላይም ጭንቀት እና ውጥረት ፈጥሯል። በተለይ ደግሞ አጣዬ እና በዙሪያዋ ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ ችግር ስለደረሰባት የአካባቢው ነዋሪ በከፍተኛ…
#ትኩረት📣

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞንና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ አካባቢዎች ያገረሸው የፀጥታ ችግር ነዋሪዎች ላይ የከፋ የደህንነት ስጋት ደቅኗል።

ከትላንት አንስቶ ባለው ሁኔታ የጉዳት ሪፖርቶች ያሉ ሲሆን የተሟላ መረጃ ለማግኘት ግን ለጊዜው አልቻልም።

" በአካባቢው ላይ ከዚህ በፊት በተከሰቱ ችግሮች እጅግ ከፍተኛ ስቃይ አይተናል ፤ ሴቶች ፣ ህፃናት፣ አረጋዊያን ያሳለፉትን መከራ በቃላት ለመግለፅ የማይቻል ነው " ያሉት በአዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ችግሩ ሳይስፋፋ በፍጥነት እልባት እንዲሰጠው ተማፅነዋል።

እስካሁን በክልል መንግስት ሆነ በዞንም ደረጃ ስላለው ሁኔታ የተባለ ነገር የለም።

በአዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ባለው ችግር ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መስመር ለደህንነት ስጋት በመደቀኑ በርካታ የህዝብ ተሽከርካሪዎች ለመቆም መገደዳቸውን እና በዚህም ከፍተኛ መጉላላት እየተፈጠረ መሆኑ ጥዋት ማሳወቃችን ይታወሳል።

ዛሬ ማምሻውን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ፤ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው ለዝርፊያ እና ለወንበዴ እንዳይጋለጡ ወጣቶች፣ የፀጥታ መዋቅሮች ሌሎችም አካላት ተደራጅተው አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።

#TikvahFamily

@tikvahethopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ትምህርት ሚኒስቴር በጦርነት እና ግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ እና የ12ኛ ክፍል " የማለፊያ ውጤት ያላመጡ " ተማሪዎች በዚህ ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ ሆነው መፈተን እንደሚችሉ አስታወቀ፡፡ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ተጨማሪ የቅበላ አቅም እንዲኖር ከስምምነት ላይ መደረሱን እና ተጨማሪ የቅበላ አቅም በፍትሀዊነት በጦርነቱ…
የትምህርት ሚኒስቴርና የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች !

ከብሄራዊ ፈተና አስተዳደር ጋር በተያያዘ ባለፉት አመታት የታዩ ችግሮች ለመቅረፍ ከፈተና ዝግጅት ጀምሮ እስከ ውጤት ማሳወቅ ያሉትን ተግባራት በጥቃቄ እንዲከናወኑ ፦

1ኛ. ፈተናዎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደግፎ መስጠት የሚቻልበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ፤ ይህ እውን እስኪሆን ድረስ የሚሰጡ ፈተናዎች በየክልል ትምህርት ቤቶች መሆኑ ቀርቶ የፈተና ጣቢያዎች በፌዴራን ተቋማት ውስጥ ብቻ ሊሆኑ የሚችሉበትን መንገድ ከአሁኑ እንዲመቻች፤

2ኛ. ማህበረሰቡ ለረጅም ጊዜያት ሲጠይቅ የነበረውን እና መንግስት ግልፅ አቋም የያዘበትን የትምህርት ስርዓቱን የጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ማሳኪያ መሳሪያ አድርጎ መጠቀም፣ ማንንም የማይጠቅም በተለይ የልጆቻችን ትምህርት የሚጎዳ መሆኑ ታውቆ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከእንዲህ አይነት ጎጂ አሉታዊ እንቅስቃሴ እራሱን እንዲያቅብ፤

3ኛ. በየደረጃው ያለው የፖለቲካ እና ከመንግስት አመራር ፤ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ፤መላው ህብረተሰብን ጨምሮ በጉዳዩ ዙሪያ ማነጋገርና ለመፍትሄው በከፍተኛ ደረጃ ተሳትፎ እንዲደረግ ለማስቻል ርብርብ እንዲደረግ ከወዲሁ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

(ተጨማሪ ከላይ ያንብቡ)

#ትምህርት_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia