TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ደህንነት ያለበት፣ ሰላማዊ የሆነ፣ የሚያስተማምን ቦታ የመጣን መስሎኝ ነበር ግን ልጄ በጥይት ተመቶ መገደሉ ከማስበው በላይ ሆኖብኛል" - ወላጅ እናት

በፖሊስ እና መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች በተደጋጋሚ ሰው በሚገደልባት ሀገረ #አሜሪካ ከሰሞኑን በርካቶችን ያስቆጣ ግድያ በፖሊስ ተፈፅሞ ነበር።

ግድያው በሚቺጋን ግዛት የተፈፀመ ሲሆን በነጭ ፖሊስ የተገደለው የ26 ዓመቱ ወጣት የኮንጎ ስደተኛ ፓትሪክ ልዮያ ነው።

ፖሊስ፤ ወጣቱ ስደተኛ የሚነዳው መኪና ታርጋው ከመኪናው አይነት ጋር ባለመገናኘቱ ትራፊክ እንዳስቆመው ገልጿል፤ በኃላም በነጭ ፖሊስ ተተኩሶ ተገድሏል።

የፓትሪክ ወላጅ አባት ፒተር ልዮያ ሁኔታው እጅጉን እንዳሳዘናቸው ገልፀው ፤ " እዚህ አሜሪካ ውስጥ ሰው ባለበት የሚገደልበት አይነት ግድያ እንዳለ ፤ጥይት በያዘ ሰው እና በፖሊስ ሰው እንደሚገደል አላውቅም ነበር ፤ እኔ የማውቀው አሜሪካ ውስጥ ፖሊስ ስታገኝ ደህንነት እንደሚሰማህ ነበር " ብለዋል።

ወላጅ እናት ዶርካስ ልዮያ በመሪር ሀዘን ውስጥ ሆነው ፤ " ኮንጎን ጥለን የወጣነው የምንኖርበት አካባቢ ደህንነቱ አስተማማኝ ስላልነበረ ነው። ጦርነት ነበር ስለዚህ ደህንነት ያለበት ሰላማዊ የሆነ የሚያስተማምን ቦታ የመጣን መስሎኝ ነበር ግን ልጄ በጥይት ተመቶ መገደሉ ከማስበው በላይ ሆኖብኛል " ብለዋል።

ወጣቱን የኮንጎ ስደተኛ የገደለው ስሙና ማንነቱ ይፋ ያልተደረገው ፖሊስ ደሞዝ እየተከፈለው እረፍት እንዲወስድ ተደርጓል።

የሚቺጋን ፖሊስ ሁኔታውን "እያጣራ" ነው የተባለ ሲሆን የፓትሪክን ቤተሰቦች የወከለ ጠበቃ ፖሊሱ ላይ ክስ እንዲመሰረትና ህግ ፊት እንዲቀርብ እንደሚፈልግ ማሳወቁን ቪኦኤ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Telegram

ቴሌግራም አጫጭር የድምፅ ፋይሎችን እና የድምፅ መልዕክቶችን ለማንኛውም ቻት/መልዕክት ልውውጥ ወደ ማንቂያ ደውል መቀየር የሚቻልበትን / የራሳችንን የማሳወቂያ ድምፆችን ማዘጋጀት የምንችልበትን ገፅታ እና ሌሎችም አዳዲስ ገፅታዎች የተካከቱበት አዲስ Update ዛሬ ይፋ አድርጓል።

➡️ አዳዲስ ስለተጨመሩ ገፅታዎች ያንብቡ 👇
telegram.org/blog/notifications-bots

➡️ ዋናውን የቴሌግራም መተግበሪያችሁን #Update ለማድረግ ፦

▪️ለአንድሮይድ👉 play.google.com/store/apps/details?id=org.telegram.messenger

▪️ለIOS 👉 https://apps.apple.com/ke/app/telegram-messenger/id686449807

ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ ዋናውን የቴሌግራም መተግበሪያ (በነጭ መደብ ላይ ሰማያዊው የቴሌግራም ምልክት ያረፈበትን) እንድትተጠቀሙ እንመክራለን።

#Telegram

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በአሸባሪነት የተፈረጁ አካላትና ያልተፈረጁ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት በሀገራዊ ምክክሩ ይሳተፋሉ ?

በኢፌዴሪ ህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብለው የተፈረጁም ሆነ ያልተፈረጁም " ትጥቅ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ " ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የሀገራዊ ምክክር መድረኩ አካል ይሆናሉ ? ? የሚለው ጥያቄ የብዙሃኑ ጥያቄ ነው።

በዚህ ጉዳይ ላይ በርካቶች የገዢውን 'ብልፅግና ፓርቲ' ቁርጥ ያለ አቋም ምን እንደሆነ ለማወቅም ይፈልጋሉ።

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዜዳንት አቶ አደም ፋራህ በፋና ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው በሰጡት ቃለ ምልልስ ይህንን ጥያቄ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ አደም " ተሳታፊን መለየት እና መወሰን የብልፅግና ፓርቲ ጉዳይ አይደለም። " ብለዋል።

ይህ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተው የሀገራዊ ምክክር የኮሚሽኑ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ነገር ግን ኮሚሽኑ እነዚህ አካላት ለምክክሩ እና ለሀገር አቀፍ አካታች መድረክ እንዲቀርቡ ቢወስን ብልፅግና ይቀበላል ወይ ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ አቶ አደም ፋራህ ፦

" ብልፅግና ለአካታች ሀገር አቀፍ ምክክሩ ስኬታማነት አስተዋጽኦ የሚያበረክት ጉዳይ በሙሉ ፤ ኢትዮጵያ እንድትረጋጋ ፤ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ፤ ዴሞክራሲ እንዲዳብር ፤ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ማንኛውም ጉዳይ ኮሚሽኑ ይዞ ከመጣ ህግና ስርዓትን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ፤ አስፈላጊ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ዝግጁ ነው " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሌላው እዚህ ላይ የተነሳ ጥያቄ እንዴት ነው ኮሚሽኑ ቢፈልግ እንኳን በህግና ስርዓቱ በአሸባሪነት የተፈረጁ አካላት ተሳታፊ መሆን የሚችሉት ?

በህግ እና በስርዓቱ አሸባሪ ተብለው የተፈረጁ አካላት ትጥቃቸው እስካልፈቱ ድረስ እንዲህ ያለው ሰላማዊ መድረክ ላይ አይሳተፉም ይላል። ስለዚህ " ብልፅግና በሁለት ካርድ እየተጫወተ ነው " ፤ በሚል ለሚነሳው ክስ አቶ አደም ፋራህ ተከታዩን ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል ፦

" የህግ የበላይነት የሚባለው ለሁሉም አካል በህግ ፊት እኩል ነው። ሁሉም ከህግ በታች ነው። እንዳሻው ህግን የመጣስ መብት የሚሰጠው አካል አይደለም።

ብልፅግና ፓርቲም ህዝብ ሲመርጠው ህግና ስርዓትን አስከብር፣ በሀገሪቱ ህግ ምራኝ ፣ በህግ እና ስርዓት ምራኝ ፣ ሰላም እና ደህንነትን አስከብር፣ በማኔፌስቶው ላይ ያስቀመጥከውን በትክክል ተግብር ፣ ፈፅምልኝ ነው ያለው። ስለዚህ ብልፅግና ፓርቲ ከህግ እና ስርዓት ውጪ ወስኖ የመሄድ ስልጣን የለውም። ኮሚሽኑም በዛው ልክ ነው።

ዋናው ጉዳይ ፤ ኮሚሽኑ ለአካታች የሀገራዊ ምክክሩ ስኬትታማነት ፣ የሚለዩትን አጀንዳዎችና አጀንዳዎቹ ላይ መሳተፍ የሚገባቸው አካላት ከለየ በኃላ እነዚህ አካላት በዚህ ጉዳይ ላይ ቢሳተፉ ለአካታች ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ይጠቅማል ብሎ ካመጣው ፤ ብልፅግና ለሀገርና ለህዝብ ነው ቅድሚያ የሚሰጠውና ይቀበላል።

የቀረበው የሀገርን እና የህዝብን ጥቅም የሚያስከብር ከሆነ ሲያስፈፅምም ህግና ስርዓትን በጠበቀ አኳኃን ነው የሚያስፈፅመው።

ስለዚህም ፤ አንድ #አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ድርጅት ከአሸባሪነት የሚወጣው በምን ስርዓት ነው የሚለው ህግ እና ስርዓት ያስቀመጠው አለ ፤ ስለዚህ ህግ እና ስርዓትን በጠበቀ መልኩ ነው የምናስተናግደው።

እንደብልፅግና ፓርቲ ለአካታች ሀገራዊ ምክክሩ ስኬት በእኛ አቅም፣ በእኛ ስልጣን ማድረግ የሚገባንን ነገር በሙሉ እናደርጋለን። ይሄን ስናደርግ ህግ እየጣስን መሆን የለበትም። ስለዚህ ህግ እና ስርዓትን በጠበቀ መንገድ ሂደቱን ጠብቀን ኮሚሽኑ የሚያቀርባቸውን ነገሮች እንደመንግስት ተቀብለን የምናስተናግድበት እና ለአካታች የሀገራዊ ምክክሩ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ፤ ሁኔታዎችን የምናመቻችበት ሁኔታ ይኖራል።

ስለዚህ ሁላችንም ከህግ በታችን ነን ፤ ብልፅግናም ሲሰራ እያንዳንዱ እንቅስቃሴው ሂደቱ በህገመንግስቱ መሰረት ፣ በሀገሪቱ ህጎች መሰረት መሆን መቻል አለበት።

መሻሻል የሚገባው ህግ ካለ ፤ ለዚህ ሂደት እንቅፋት ሊሆን ይችላል ወይም ምቹ ሁኔታ አይፈጥርም ተብሎ የሚታሰብ ካለ የህግ ማሻሻያ ሂደቱን ተከትለን ነው የምናሻሽለው እንጂ ብልፅግና መሪ ፓርቲ ስለሆነ ይሄን ጥዬዋለሁ ፣ ይሄን ፈቅጃለሁ የሚልበት ሁኔታ አይኖርም።

ግን ፥ ለአካታች ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ኮሚሽኑ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ እንደ መንግስትም ፤ እንደ መሪ ፓርቲም እኛ ማድረግ የምንችለውን ሁሉ ፣ አቅማችን የሚፈቅደውን ሁሉ ፣ ህግ የሚፈቅድልንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ፤ ቁርጠኛ ነን ፤ በትክክልም እናደርገዋለን " ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ "ነሲሓ" ኢፍጣር ፕሮግራም ! «ነሲሓ» የተሰኘ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት፤ በዛሬ ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ በስድስት ጎዳናዎች ላይ 12 ኪ.ሜ የሸፈነ ጾመኞችን የማስፈጠር መርሃ ግብር አካሂዷል። የቦታዎቹ ዝርዝር እንደሚከተለው ነው። ①) ዓለም ባንክ ከሚገኘው ኢማሙ አሕመድ መስጂድ አደባባይ ጀምሮ እስከ ቤተል ባለው መንገድ፣ ②) ከቢላል ኮካ መስጂድ ወደ አብነት ባለው መንገድ በጭድ ተራ…
#Iftar

በነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት (NCDO) አስረባባሪነት ዛሬ በመዲናችን አዲስ አበባ በተመረጡ 11 ጎዳናዎች ላይ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ይካሄዳል።

«ኑ አብረን በጋራ እናፍጥር!» በሚል የሚካሄደው ይህ የኢፍጣር መርሃ ግብር 35 ኪሎ ሜትር ገደማ ይሸፍናል።

የሚያካትታቸው 11 ጎዳናዎች ዝርዝር ፦

1) ከኮካ ቢላል መስጂድ - ተክለሃይማኖት
2) ከእህል በረንዳ - ቢላል መስጂድ
3) ከቢላል መስጂድ - እፎይታ
4) ከኮልፌ ቀብር - ሎሚ ሜዳ
5) ከአስኮ አዲስ ሰፈር - በድር መስጂድ
6) ከመንዲዳ - ኢማሙ አሕመድ መስጂድ
7) ከአየር ጤና - ግራር
8) ከግራር - ስልጤ ሰፈር
9) ከጀሞ 2 አደባባይ - ኖክ
10) ከረጲ ትም/ቤት - አጃምባ ማዞሪያ
11) ከአየር ጤና እስከ አለም ባንክ
አቅሙ ያለው ሰው በዕለቱ ኢፍጣር በሚካሄድባቸው ጎፋናዎች ሲያቀና እንደ ውሃና ቴምር ያሉ ቀለል ያሉ ማስፈጠሪያቸውን ለሌሎች ቢይዝ መልካም ነው ተብሏል።

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ባለፈ አመት በ6 ጎዳናዎች ላይ ደማቅ የኢፍጣር ፕሮግራም ማካሄዱ ይታወሳል።

ተቋሙ በዚህም አመት ረመዷን ከገባ ጀምሮ በየቀኑ 250 ሰዎችን በቋሚነት እያስፈጠረ ሲሆን በክልል ከተሞች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በትጋት እየሠራ እንደሚገኝ ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ዛሬ በሚካሄደው የኢፍጣር ፕሮግራም አጋር መሆን የሚፈልጉና አቅመ ደካሞችን ማስፈጠር ለሚፈልጉ 0972747474 ላይ መደወል ይችላሉ ተብሏል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል አስወነጨፈች። ትላንትና ለሊት ሰሜን ኮሪያ የተጠረጠረ ባላስቲክ ሚሳኤል ወደ ምስራቅ ባህር ማስወንጨፏን ጎረቤቶቿ እየገለፁ ይገኛሉ። የደረሰ ጉዳት የለም። ፒዮንግያንግ ይህ የሚሳኤል ማስወንጨፍ ሙከራዋ 2022 ከገባ ጊዜ አንስቶ 9ኛው መሆኑ ነው። የአሜሪካ እና የደቡብ ኮሪያ የደህንነት ባለስልጣናት የሰሜን ኮሪያን እንቅስቃሴ በቅርበት እየተከታተሉት ነው ተብሏል። @tikvahethiopia
#NorthKorea

ሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራዋን ገፍታበታለች።

በዚህ አመት እጅግ ተደጋጋሚ የሚሳኤል ሙከራ ስታደርግ የነበረችው ሰሜን ኮሪያ በአመቱ 12ኛ ነው የተባለውን የሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታውቋል።

ሰሜን ኮሪያ ትላንት ትላንት ቅዳሜ 2 ሚሳኤሎችን በሰሜን ምስራቅ የባህር ጠረፍ ላይ ከምትገኘው ሃምሁንግ ከተማ ማስወንጨፏ እና 68 ማይል መጓዛቸው ተነግሯል።

የአሁኑ ሙከራ ከቀድሞዎቹ በኃይል ያነሰ ቢሆንም በአካባቢው ላይ ከፍተኛ ውጥረት ባለበት ሁኔታ ወቅት መፈፀሙ አሳሳቢ እንዳደረገው ተነግሯል።

በሌላ በኩል አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ዓመታዊ የጋራ ወታደራዊ ልምምዳቸውን ሰኞ ይጀምራሉ። ይህን ልምምስ ሰሜን ኮሪያ በፅኑ አውግዛዋለች። ሀገሪቱ የሁለቱን አጋሮች የጋራ ልምምዶች እንደ ወረራ ልምምድ የሚቆጠር ነው ብላዋለች።

@tikvahethiopia
" ሆሣዕና '' (የዐብይ ፆም 8ኛ ሳምንት)

እንኳን አደረሳችሁ !

ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ፆም እሁዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራው ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መግቢያ ዋዜማ ነው።

ሆሣዕና ማለት የቃሉ ትርጉም " እባክህ አሁን አድን " ማለት ነው።

ዕለቱ ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም ሽማግሌዎች እና ሕፃናት '' ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሣዕና በአርያም '' በማለት በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት ነው፡፡ 

ይህ ዕለት በቤተክርስቲያን ውስጥ ዘንባባ ተይዞ፣ እየተዘመረ እጅግ ልዩ በሆነ ሁኔታ ይታሰባል።

በዐብይ ጾም ከሰርክ ሆሣዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡

በዚህ ጊዜ በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት ካህናት መስቀል በእጃቸው አይዙም፣ አያሳልሙም ፣ ይፍቱኝ ተብሎ ወደካህን አይቀረብም፤ ይህ ሳምንት የጌታን የመጨረሻው ስቃይ የሚታሰብበት ነው።

@tikvahethiopia
" ሀገር ታማለች ፈጣሪያችንን ' አሁን አድን ' በማለት ልንማፀነው ይገባል " - ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ

የሆሣዕና በዓል በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ከ71 ሺ በላይ ወገኖችን ባስጠለለችውና በሀገራችን በተከሰተው ጦርነት የቀሞውን ድባቧን ባጣችው ሰቆጣ ከተማ ተከብሯል።

የሆሣዕና በዓል በታሪካዊው ደብረ ገነት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ነው የተከበረው።

በዓሉ ሲከበር የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርናባሰ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የጀርመን እና የአካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ካህናት እና ምዕመናን ተገኝተዋል።

ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ፥ በሀገራችን በተፈጠረው ችግር ምክንያት በርካታ ወገኖች ከቀያቸው ተፈናቅለው በማየታቸው ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው ፥ " ሀገር ታማለች ፤ ፈጣሪያችንን ' አሁን አድን ' በማለት ልንማጸነው ይገባል " ብለዋል።

አክለውም ፤ በአካባቢው ላይ በነበረው ችግር ሁሉ ከምዕመናን ልጆቻቸው ሳይለዩ የአባትነት ድርሻቸውን በሚገባ የተወጡትን ብፁዕ አቡነ በርናባስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስን አመስግነዋል።

ብፁዕ አቡነ በርናባስ በበኩላቸው ፤ የነበርንበትን ሶስት አስቸጋሪ ወራትን አልፈው ከመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ጋር ለዚህ በመድረሳቸው እግዚአብሔርን አመስግነዋል።

በበዓሉ ሊቃውንት ሕጻናት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በዓለ ሆሣዕናን የተመለከቱ የተለያዩ ጣዕመ ዝማሬዎችን በማቅረብና ፈጣሪያቸውን በማመስገን ማክበራቸውን የኢኦተቤ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ፎቶ ፦ EOTC TV

@tikvahethiopia