TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE መንግስት ከ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ስርጭት ጋር በተያያዘ ከባድ ፈተናዎች ገጥሞት እንደነበር እና የፀጥታ ኃይሎችም ተሰውተው እንደነበረ ገለፀ። ይህ የተሰማው ትምህርት ሚኒስቴር የ9ወር የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለህ/ተ/ም/ቤት ካቀረበ በኃላ ከምክር ቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ነው። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማብራሪያ በፈተና ስርጭት ወቅት እጅግ ከባድ…
የመምህራን ጥራት ጉዳይ !

" ... በመምህራን ጥራት ላይ ያለውን ችግር ታውቁታላችሁ። #በሚያስተምሩበት ትምህርት ፈተና ተሰጥቷቸው ምዘናውን ያለፉ ከ50% በላይ ያገኙ መምህሮቻችን ከ30% በታች ናቸው፤ በሚያስተምሩት ትምህርት ነው የምላችሁ። አስቡት ባዛ እውቀት ላይ ያለ ልጆች አስተምሮ ምን ያህል ያበቃል ?

አስተማሪዎች ጥራት ላይ በከፍተኛ ደረጃ ለመስራት አሁን የኮተቤን መምህራን ትምህርት ቤት ካሪኩለሙን በሙሉ ፤ ሌላ ትምህርት የሚያስተምረውን አቁሞ የዚህ ሀገር ጥሩ መምህራን የሚወጡበት ቦታ እንዲሆን በከፍተኛ ደረጃ እየሰራን ነው ፤ ኳሊቲውን እና የቅበላ አቅሙን ለማሻገር " - የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ
ረመዷን ከሪም ! አዲስ አበባን ጨምሮ በተመረጡ 25 የአገራችን ከተሞች ላይ ለፆም መያዣ (ሱሁር) እና ማፍጠሪያ የሚያገለግል የ 2014 ዓ.ም. የጊዜ ሰሌዳ ከታች የሚገኘውን የቴሌግራም ቻነል ሊንክ በመጠቀም ያግኙ!

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል መቀላቀልዎንም አይርሱ ! https://t.iss.one/BoAEth
አቢሲንያ አሚን! ዕሴትዎን ያከበረ!
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ " ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት " ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የአየር ጉዞ ትኬት ዋጋ ላይ 20 % ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።

ወደ ሀገር ቤት ተጓዦች ትኬታቸውን እኤአ ሚያዝያ 6 እስከ ሚያዝያ 21 ቀን 2022 በመቁረጥ እና ጉዟቸውን ከሚያዝያ 25 እስከ ግንቦት 15 ቀን 2022 ድረስ በማመቻቸት የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#USA #ETHIOPIA #EHRC

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እና ከምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ጋር ውይይት አደረጉ።

ውይይቱ ፥ በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰቱት ግጭቶች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን በተመለከተ መሆኑን በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
#ኬላ

የጉምሩክ ኬላ ካልሆነ በስተቀር አሁንም ገመድ አስሮ መኪና የሚያስቆሙ ህገ ወጥ ናቸው ተብሏል።

ከትላንት በስቲያ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ለህ/ተ/ም/ቤት የሚኒስቴሩን የ8 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት አንድ ጥያቄ ተጠይቆ ነበር።

ይኸውም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የተከፈቱት የቁጥጥር ኬላዎች አሁንም አዋጅ ከተነሳ በኃላ ገመድ በመዘርጋት እያስቆሙ የትራንስፖርት ሁኔታውን እያጓተቱ ነው በእዚህ ላይ ምን እየተሰራ ነው ? የሚል ነበር።

ይህንን በተመለከተ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገ/መስቀል ጫላ የጉምሩክ ኬላ ካልሆነ በስተቀር አሁንም ገመድ አስሮ መኪና የሚያስቆሙ ህገ ወጥ ናቸው ብለዋል።

አቶ ገ/መስቀል ጫላ ፦

" ከስምንት ወራት በኃላ በሁሉም ክልሎች በሚባልበት ደረጃ ጉሙሩክ የሚያውቃቸው ኬላዎች ካልሆኑ በስተቀር ኬላዎች እንዲነሱ ተደርጓል።

የጉሙሩክ ኬላ ካልሆነ በስተቀር አሁንም ኬላ ገመድ አስሮ መኪና የሚያስቆሙ ካሉ ህገወጥ ናቸው። ይሄ በግልፅ መታወቅ አለበት። ህገወጥ ናቸው ግን እኛ ባለን መረጃ አብዛኛዎቹ ክልሎች ይሄንን ኬላ አንስተው የጉሙሩክ ኬላዎች ብቻ ገቢ እና ወጪ እቃዎችን የሚቆጣጠሩበት ሁኔታ አለ " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመምህራን ጥራት ጉዳይ ! " ... በመምህራን ጥራት ላይ ያለውን ችግር ታውቁታላችሁ። #በሚያስተምሩበት ትምህርት ፈተና ተሰጥቷቸው ምዘናውን ያለፉ ከ50% በላይ ያገኙ መምህሮቻችን ከ30% በታች ናቸው፤ በሚያስተምሩት ትምህርት ነው የምላችሁ። አስቡት ባዛ እውቀት ላይ ያለ ልጆች አስተምሮ ምን ያህል ያበቃል ? አስተማሪዎች ጥራት ላይ በከፍተኛ ደረጃ ለመስራት አሁን የኮተቤን መምህራን ትምህርት ቤት…
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ስርቆትን ለመከላከል ፈተና በኦንላይን የማስፈተን ፤ ይህ ባይሆን እንኳን ተማሪዎችን ወደ ማዕከል ዩኒቨርሲቲዎች በማስመጣት ፈተና ለመስጠት እያሰበ ነው።

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ለህ/ተ/ም/ቤት በሰጡት ማብራሪያ ባለፈው ዓመት ተጀምሮ የነበረውን የ12ኛ ክፍል ፈተናን በታብሌት ለመስጠት የተጀመረውን ስራ በከፍተኛ ደረጃ እየገፋንበት ነው ብለዋል።

ሂደቱ አሁን ላይ በአቅም ጉዳይ መቆሙን የገለፁት ሚኒስትሩ " ሁሉንም ሂደት ከጨረስን በኃላ ይሄ የሚጠይቀውን ወደ 1 ሚሊዮን ታብሌት ሃገር ውስጥ ለማስገባት ወደ 460 ሚሊዮን ዶላር ይጠይቃል፤ ይሄን ከቻይና መንግስት ጋር በሚደረግ ንግግር በእርዳታ ሊመጣ የሚችልበትን መንገድ በብዙ መንገድ ጠ/ሚኒስትሩም ገብተውበት እየገፋን ነው " ብለዋል።

" እሱ እንኳን ቢያቅተን በዚህ ዓመት የምንችለውን ሁሉ ሞክረን የምንወስደው እርምጃ ግን አንዱ በየትምህርት ቤቶቹ ፈተናን መፈት ትተን የሚያስወጣንን ወጪ አውጥተን ተማሪዎቹን ከየትምህርት ቤታቸው አምጥተን በየዩኒቨርሲቲ ማዕከላት ውስጥ ፈተናዎቹን እንዲወስዱ ማድረግ ነው ፤ ይሄን ነው አንዱ ልንሄድበት እያሰብን ያለነው " ብለዋል።

ሚኒስትሩ በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የፈተና ስርቆት መቆም አለበት ያሉ ሲሆን " ስርቆት መቆም ያለበት ሰነፍ ተማሪን እና ጎበዝ ተማሪን ለመለየት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የሞራል መሰረታችንን እየበላው በመሆኑ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

አክለውም ፤ በቀጣይ አመት የሚጀመረው የመውጫ ፈተና የተገባበት አንድ ተማሪ ከታችን ያለውን አጭበርብሮ አልፎ ቢመጣ ኮሌጅም ከገባ በኃላ እንደገና ፈተና እንደሚጠብቀው አውቆ ቢያንስ ኮሌጅ ከገባ በኃላ በደንብ ተምሮ እንዲያውቅ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
#UNGA

በአሜሪካ አነሳሽነት 193 አባል ሀገራት ላሉት የተመድ ጠቅላለ ጉባኤ የቀረበው ሩስያን ከተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት የማገድ የውሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምፅ ዛሬ ፀድቋል።

የውሳኔ ሃሳቡን ከ193 አባልት 93 ሀገራት የደገፉት ሲሆን 58 ሀገራት ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል፤ 24 ሀገራት ደግሞ ተቃውመዋል።

በዚህም በአብላጫ ድምጽ ሩሲያን ከሰብአዊ መብቶች ም/ቤት ታግዳለች።

የውሳኔ ሃሳቡ ለጉባኤው የቀረበው ሩሲያ ጦሯ ዩክሬን ውስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ግፍ ፈጽሟል በሚል ነው።

የውሳኔ ሃሳቡን አሜሪካ፣ ዩኬ፣ ፈረንሳይ፣ ካናዳ፣ ዴንማርክ ፣ጀርመን፣ ፖላንድ ፣ ጃፓን፣ ጣልያን፣ ፖርቹጋል፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ...ሌሎችም በርካታ ሀገራት ደግፈዋል።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ሴኔጋል፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ደ/አፍሪካ፣ ፓኪስታን፣ ኩዌት፣ ኳታር፣ ኡጋንዳን ጨምሮ 58 ሀገራት በድምፀ ተአቅቦ አልፈዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ፣ ጎረቤታችን ኤርትራ፣ አልጄሪያ ፣ ቡሩንዲ፣ ቻይና፣ ጋቦን፣ ኢራን፣ ሶሪያ ዝምባብዌ...ሌሎችም ሀገራት ተቃውመዋል።

እንደ ጎረቤታችን ሱማሊያ፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ፣ ሞሪታኒያ፣ የመሳሰሉ ሀገራት ጭራሽ ድምፅ አልሰጡም።

ዛሬ ሩስያ ከተመድ ሰብዓዊ መብት ም/ቤት ትታገድ ተብሎ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ተቃውማ ድምፅ የሰጠችው ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት ዙሪያ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ " ሩስያ ዩክሬንን ወራለች ወታደሮቿንም ታስወጣ " በሚል በቀረበ የውሣኔ ሃሳብ ላይ ሙሉ በሙሉ ድምፅ ሳትሰጥ ወንበሯን ባዶ አድርጋ መውጣቷ ይታወሳል። በወቅቱ ውሳኔው " በበሳል ዲፕሎማሲ የተደረገ ውሳኔ ነው " መባሉ አይዘነጋም።

ሩስያ የዛሬውን የተመድ ጉባኤ ውሳኔ " ህገወጥ " ብላዋለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ስርቆትን ለመከላከል ፈተና በኦንላይን የማስፈተን ፤ ይህ ባይሆን እንኳን ተማሪዎችን ወደ ማዕከል ዩኒቨርሲቲዎች በማስመጣት ፈተና ለመስጠት እያሰበ ነው። የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ለህ/ተ/ም/ቤት በሰጡት ማብራሪያ ባለፈው ዓመት ተጀምሮ የነበረውን የ12ኛ ክፍል ፈተናን በታብሌት ለመስጠት የተጀመረውን ስራ በከፍተኛ ደረጃ እየገፋንበት ነው ብለዋል። ሂደቱ…
ሀገርና ትውልድ እየገደለ ያለው የፈተና ስርቆት !

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" ... ፈተናዎች ይሰረቃሉ። ቢያብስ እኔ እስከናውቀው ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ያልተሰረቀበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም፤ ደረጃው ይለያይ እንጂ።

አንዱ መሰረታዊ ጥያቄ መጠየቅ ያለብን እንዴት ነው የሚሰረቀው ? ማነው የሚሰርቀው ? ለምድነው የሚሰርቀው ? የሚለው ነው።

አንደኛው በአጠቃላይ ፈተናውን አውጥቶ ሶሻል ሚዲያ ላይ ለቆ ሁሉም እንዲያገኘው ማድረግ ነው። ይሄ የተወሰነ ግሩፕን ለመጥቀም የታለመ እንቅስቃሴ አይደለም። በአጠቃላይ የትምህርትሩትን Integrity ለማናጋት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው። ምክንያቱም አንድ ፈተና አውጥቶ ለሁሉም በሶሻል ሚዲያ ሲለቀቀ አንድ የተወሰነ ግሩፕ የሚጠቀምበት ሁኔታ የለም ሁሉም ነው የሚያገኘውና፤ እሱ በአጠቃላይ እንደማህበረሰብ ሁሉን ነገር ፖለቲካ እና የፖለቲካ ትርፍ ማግኛ እየተደረገ የሚኬድበት አካሄድ ያመጣው ጣጣ ነው። በስፋት እና በስነስርዓት መታለፍ ያለበት ሂደት ነው።

ፈተና ሚሰረቀው ግን በዛ መልክ ብቻ አይደለም፤ በተለያየ መልክ ፈተና ይሰረቃል። ከየት በኩል ነው ስርቆቱ ሊመጣ የሚችለው ብለን ለማየት ሞክረን ነበር።

ፈተና አውጭዎቹ ፣ ፈተና የሚያዘጋጁ ሰዎች አካባቢ ስርቆት ሊፈፀም ይችላል። ፈተና አውጭዎችን የምንከታተልበት መንገድ በጥንቃቄ ለመመለከት ሞክረናል እዛ አካባቢ ትልቅ አደጋ አላየንም።

ፈተና ሲታተም ፤ አታሚ መስሪያ ቤት ውስጥ የሚደረገው ጥንቃቄ እና ጥበቃ አለ። ፈተና የሚያትመው 4 ኪሎ ያለው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ነው። ፈተና ማተመ ከተጀመረ ጀምሮ በፌዴራል ፖሊስ ዕዝ ስር ነው። በሙሉ ካሜራ እየታየ ነው የሚታተመው ያ ፈተና እዛ ይሰረቃል የሚለው እድል አነስተኛ ነው።

በአብዛኛው ፈተና ከስርጭት ጋር በተያያዘ ፈተናው ተይዞ በየክልሎች በሚሰራጭበት ጊዜ ካለው ጀምሮ ነው ችግሩ ያለው።

አንዳንዱ ሆን ተብሎ ነው፤ አንዳንዱ በየክልሉ ያሉ የመንግስት በዞን ይሁን በወረዳ በተለያየ ደረጃ ያሉ የመንግስት ባለሟሎች የሚሳተፉበት ነው። ይሄ መነሻው ይሄን ፈተና ሰርቆ ለአካባቢው ተወላጆች / ተፈታኞች በመስጠት አካባቢዬን እጠቅማለሁ ተብሎ የሚታሰብ የትምህርት ስርዓቱን ከፖለቲካ እና ከክልላዊነት ጋር ያጣበቀው አካሄዳችን ያመጣው በጣም ትልቅ ችግር ነው።

... ፈተና ሰርቀን የአካባቢያችንን ሰው እንጠቅማለን ፤ የአካባቢያችንን ተማሪ እንጠቅማለን ብሎ የሚያስብ ሰው የሚያስበው ምንድነው ? ያ በስርቆት አልፎ የመጣ ተማሪ ኮሌጅ ገብቶ በስርቆት እና በማጭበርበር ድግሪ ያገኛል ፤ በስርቆት እና በማጭበርበር የያዘውን ድግሪ ይዞ እዛው ክልል መንግስት ውስጥ ነው ስራ የሚቀጠረው እና በትክክል እንዲሰራ ነው የሚጠበቀው ? ክልል መንግስት ውስጥ ገብቶ መስረቅ ነው የሚጀምረው / የትም ቦታ ቢገባ።

የስርቆት ስርዓቱ አንዴ ከታች ማበላሸት ከጀምርን በፍፁም መቆሚያ የሌለው ማንንም በተለየ የማይጠቅም ህብረተሰብን ግን በጋራ ይዞ ገደል የሚገባ ስራ ነው።

ፈተናዎች የሚሰረቁት ፤ ፈተናው ከመሰረቁ ባሻገር ተማሪዎች ሊፈተኑ ከገቡ በኃላ ያለአግባብ በኩረጃ ወይም በፈታኞች እርዳታ ያለ አግባብ ውጤት እንዲያመጡ በተቀናበረ እና በተደራጀ መንገድ እንቅስቃሴ ይካሄዳል።

... የምናውቃቸው ነገሮች አሉ። አንዳንድ ክልል ፈታኞች ሲሄዱ ገንዘብ ተዋጥቶ፣ በሬ ታርዶ ፣ ድግስ ተደርጎ ፣ እንደውም ከገንዘቡ ተጨማሪ ለፈታኞቹ ጉቦ ተሰጥቶ ወይ ፈተናውን አይቶ እዛው እራሳቸው አርመው ለተማሪዎቹ እንዲሰጡ ወይም እርስ በእርስ ሲኮራረጁ ዝም ብሎ እንዲያዩ የሚደረግበት ጉደኛ ሀገር እኮ ነው ያለነው።

የግል ትምህርት ቤቶች ባለቤቶች የነሱ ትምህርት ቤቶች የሚፈተኑባቸውን ትምህርት ቤቶች / ቦታዎች እየፈለጉ ፈታኞቹን ለማማለል ጉቦ ለመስጠት የሚወጣው ወጪ በሚሊዮን ነው የሚቆጠረው።

እንዴት አድርገን ነው እንደሀገር በዚህ ሁኔታ ይሄ 12ኛ ክፍል ፈተና ላይ የጀመረ ነገር አይደለም የምናወራው ፤ ከስር ጀምሮ የመጣ ነው ኮሌጅ ሲደርስ ደግሞ የሚያቆም አይደለም። ኮሌጅ ውስጥ ያለውን የፈተና ስርቆት እና ማጭበርበር እና ኩረጃ ሁላችንም የምናውቀው ነው።

ወረቀት ለአንድ ትምህርት ስርዓት ለአንድ ሰው ዲፕሎማ / ዲግሪ ሲሰጥ ለህብረተሰቡ እየነገር ያለው ይህ ሰው በተማረበት ትምህርት መስክ ይሄን ያህል ውጤት አለው ተቀበል ነው ህብረተሰብን የሚለው። ያ ወረቀት በስርቆት ከመጣ፣ ያ ወረቀት በኩረጃ ከመጣ ያ ወረቀት ትርጉም የለውም።

... ብዙ የግል ኮሌጆች የዲግሪ ወፍጮ ቤቶች ናቸው ። ዲግሪ ነው እየሸጡ ያሉት ልጆችን አስተምረው ፣ አብቅተው አይደለም። ያ ማለት ጥሩ ጥሩ ትምህርት ቤቶች ፣ ጥሩ የሚያስተምሩ የሉም ማለት አይደለም።

ነገር ግን አንዴ የትምህርት ስርዓቱ ከታች እስከ ላይ መሰረታዊ Integrity ከተበላሸ ፤ ለምን ይገርመናል አሁን ያለንበት መከራ ውስጥ መሆናችን እንደ ሀገር ። የሚያበላሸው ሁሉን ነገር ነው። ሲቪል ሰርቪሳችን ፣ ፖለቲካችንን ያበላሸዋል።

በትንሽ በትልቁ የምንባለው እና የምንጋደለው እኮ ከትምህርት ስርዓትም ጋር የተያያዘ ነው። ለዚህ ነው ይሄን ነገር እንደቀላል ነገር አይደለም ማለት ያለብን ፤ ... በመሰረታዊ መንገድ ይሄን ካልቀየርነው የትም አንሄድም። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የነዳጅ ትራንስፖርት ባለንብረቶች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ የጊዜ ገደብ ማስቀመጡ ተሰማ። የማህበሩ አባላት ዛሬ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ባደረጉት ጠቅላላ ስብሰባ በተደጋጋሚ መንግስት ቸልተኛ በመሆኑ የነዳጅ አመላላሽ ቦቴ ቁጥር ከ3500 በ20 እጅ ቀንሷል ብለዋል። ጅቡቲ ደርሶ መልስ 25,000 ብር እየከሰሩ መሆኑንና ይኸም የሆነውም የብር ዋጋ በመውረዱና መለዋወጫ በመወደዱ…
" የአድማ እቅዱን ትተነዋል "

ከቀናት በፊት የነዳጅ ትራንስፖርት ባለንብረቶች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ የጊዜ ገደብ አስቀምጦ እንደነበር ይታወሳል።

ማህበሩ ፤ መንግስት ዝቅተኛ የትርፍ ህዳግን ካልከለሰ እና ለሚነሳው ጥያቄ ምላሽ ካልተሰጠው በ10 ቀናት ውስጥ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚያደርግ ገልጾ ነበር።

ትላንት አዲስ በወጣው መግለጫ ማህበሩ አድማ ለማድረግ ያሰበውን እቅድ ትቶታል።

ይህም የሆነው ከትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚንስቴር ጋር ገንቢ ውይይት በመጀመሩ መሆኑን ገልጿል።

" የነዳጅ ታሽከርካሪዎች መደበኛ ሥራቸውን ይቀጥላሉ " ያለው ማህበሩ " መንግሥት በስምምነቱ መሠረት መፍትሔ ይሰጠናል ብለን እናምናለን " ብሏል።

Credit : The Reporter

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የአድማ እቅዱን ትተነዋል " ከቀናት በፊት የነዳጅ ትራንስፖርት ባለንብረቶች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ የጊዜ ገደብ አስቀምጦ እንደነበር ይታወሳል። ማህበሩ ፤ መንግስት ዝቅተኛ የትርፍ ህዳግን ካልከለሰ እና ለሚነሳው ጥያቄ ምላሽ ካልተሰጠው በ10 ቀናት ውስጥ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚያደርግ ገልጾ ነበር። ትላንት አዲስ በወጣው መግለጫ ማህበሩ አድማ ለማድረግ ያሰበውን እቅድ ትቶታል። …
#Update

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፥ ከፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር ተወካዮች ጋር ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ መደረሱን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ፥ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር ከአገልግሎት ታሪፍ ጋር በተያያዘ አገልግሎትን ስለማቋረጥ በተመለከተ መግለጫ አውጥቶ እንደነበር አስታውሷል።

ይህንን ተከትሎ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተሽከርካሪ ባለንብረት ተወካዮች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጿል።

በዚህም የፈሳሽ ጭነት የማጓጓዝ አገልግሎት እንደከዚህ ቀደሙ ያለምንም መስተጓጎል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ ኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ተቀራራቢ ለማድረግ እና ከጎረቤት ሀገራት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የዋጋ ተመን ለማውጣት መታቀዱ ታውቋል። የመንግስት ድጎማም ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ብቻ እንዲሆን ታስቧል። አቶ ገብረመስቀል ጫላ (የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር) ለህ/ተ/ም/ቤት የሚኒስቴሩን የ8 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የተናገሩት ፦…
#ነዳጅ

መንግስት ከተመረጡ የብዙሃን አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ውጭ የነዳጅ ድጎማን በሂደት እንደሚነሳ ታውቋል። ይህ ድጎማ ሲነሳ የተሽከርካሪ ባለቤቶች ጫና ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ይታመናል።

አቶ ገብረመስቀል ጫላ (የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር) ፦

" ነዳጅ በጣም ውድ ምርት ነው ። እኛ ሀገር ግን እንደ ውድ ምርት አንጠቀምም። ስለዚህ እያንዳንዱ ተሽከርካሪ ያለው ዜጋ ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም አለበት።

ትንሽ ሲቆይ ነዳጅ እንደሬሽን በኮታ ሊሰጥም ይችላል። ስለዚህ ያ ከመምጣቱ በፊት እያንዳንዱ ዜጋ ይሄ ገንዘብ የኔ ገንዘብ ነው የሀገሬ ነው ማለት አለበት።

እኛ አሁን እንደመንግስት 4 ቢሊዮን ዶላር ለመድረስ እንደወላድ ሴት ቀን እንደምትቆጥር ነው በየአንዳንዷ ቀን ስንት ዶላር እንደገባች የምንቆጥረው በዛ ልክ ተሰርቶ የሚመጣውን ዶላር ውስጥ ፤ ከዛ ዶላር ሶስት አራተኛውን ለነዳጅ ነው የምንከፍለው።

ስለዚህ ይሄ የሁላችንም ገንዘብ ስለሆነ ነዳጅን መቆጠብ የሁላችንም ኃላፊነት ነው የሚሆነው። አለፍ ሲልም የዛ አካል የሚሆነው ቅዳሜ እና እሁድ በህዝብ ትራንስፖርት መጠቀም ፤ እንደዚሁም የእግር ጉዞ መለማመድም በጣም ወሳኝ ሆኖ ነው የሚገኘው። "

@tikvahethiopia
#TikvahFamily

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ከሙስሊም ተማሪዎች ጋር በተያያዘ በርካታ ጉዳዮች እየተነሱ እንደሆነ ይታወቃል።

የቲክቫህ - ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላትም ጉዳዩ በዛው ዕለት አልያም በቀጣዩ ቀን የሚመለከታቸው አካላት በመነጋገር #በፍጥነት_ይፈቱታል በሚል በትኩረት ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ቀናት አልፎ አሁን ላይ ምዕመኑ ሰልፍ እስኪወጣ አስገድዶታል።

ዛሬ ምዕመኑ በአንዳንድ መስጂዶች በሰልፍ ድምፁን አሰምቷል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት " ሆን ተብሎ በሚመስልና በዘመቻ መልኩ የረመዳን ፆም ወቅትን ጠብቆና አንዳንድ ትምህርት ቤቶች፤ ተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ ጭምር ትምህርት ቤት ውስጥም አትሰግዱም ፤ ወጥታችሁም (ከግቢ) አትሰግዱም ብለዋቸዋል " ሲል ይገልጻል።

አንዳንድ የትምህርት ቤት አስተዳደሮችም ተማሪዎቹን ኢ-ህገመንግስታዊ የሆነ " ተንኳሽ ንግግር " ተናግረዋቸዋል ብሏል።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምንም እንኳን ስለጉዳዩ በግልፅ ያለው ነገር ባይኖርም ትምህርት ከማንኛውም ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴ ነጻ በሆነ ሁኔታ መካሄድ አለበት ሲል አሳውቋል።

ዛሬ የነበረውን የተቃውሞ ሰልፍ እንዲሁም አጠቃላይ ከሰሞኑ የነበሩትን ሁኔታዎች በሚመለከት ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በዝርዝር ቀርቧል ፤ ያንብቡ 👇https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-04-08

@tikvahethiopia
#PressRelease

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ጠቅላይ ምክር ቤት መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. 48ተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

በዚህ ስብሰባ ማጠናቀቂያ ም/ቤቱ ባለአስር ነጥብ የአቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia