TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ⬆️ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ሉሜ ወረዳ #የተከሰከሰው የመከላከያ ሰራዊት አውሮፕላን በፎቶው የትመለከቱትን ይመስላል። በዚህ አደጋ የ18 ዜጎቻችን ህይወት አልፏል።

ፎቶ፦ ኢቲቪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመረጃ ሳጥኑ ወደ ፈረንሳይ ተልኳል‼️

ባሳለፍነው እሁድ #የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላን የበረራ መረጃ ሳጥንና የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል መቅረፀ ድምፅ ለምርመራ ወደ ፈረንሳይ መላኩ ተገለፀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳስታወቀው፥ በአደጋ ምርመራ ቢሮ የሚመራ የኢትዮጵያ ቡድን የበረራ መረጃ ሳጥን እና የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል መቅረፀ ድምፅ በመያዝ ለቀጣይ ምርመራ ወደ ፓሪስ #ፈረንሳይ አቅንቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ተወልደ ገብረማርያም በትናንትናው እለት ከአሜሪካው ሲ.ኤን.ኤን የቴሌቪዥ ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ የአውሮፕላኑ የመረጃ ሳጥን መመርመሪያ መሳሪያ ስለሌላት ለምርመራ ወደ ውጭ ይላካል ማለታቸው ይታወሳል።

አቶ ተወልደ፥ አውሮፕላኑ የበረራ መረጃ ሳጥንና የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል መቅረፀ ድምፅ ምርመራ ከቅርበትና ከፍጥነት አኳያ  ወደ አውሮፓ ሀገራት ሊላክም ይችላልም ብለው ነበር።

በዚህም መሰረት ነው የአደጋ ምርመራ ቢሮ የሚመራ የኢትዮጵያ ቡድን የበረራ መረጃ ሳጥን እና የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል መቅረፀ ድምፅ በመያዝ ለቀጣይ ምርመራ ወደ ፈረንሳይ ያቀናው።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፓሪስ🔝ባሳለፍነው እሁድ #የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላን የበረራ መረጃ ሳጥንና የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል መቅረፀ ድምፅ ለምርመራ ፈረንሳይ ገብቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

የፈረንሳይ የበረራ ደኅንነት ምርመራ ባለሥልጣን እንዳለው ቢሾፍቱ አቅራቢያ #የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አውሮፕላን የመረጃ መመዝገቢያ ሳጥን ውስጥ የተከማቸው ሰነድ በስኬት #ተገልብጧል። መረጃው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ #ተሰጥቷል። ባለሥልጣኑ ከመረጃ ማጠራቀሚያው የነበሩ የድምጽ ሰነዶችን #አላዳመጥኩም ብሏል። ከላይ በምስሉ የሚታየው ትክክለኛው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የመረጃ ማጠራቀሚያ ነው።

Via Eshet Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ‼️

የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የማስጠንቀቂያ እና የስልጠና መስፈርቶች በቂ እንዳልነበሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማርያም ተናገሩ።

ኢንዶኔዥያ ላየን አየር መንገድ ንብረት የነበረ አውሮፕላን ባለፈው ጥቅምት ከተከሰከሰ በኋላ የአሜሪካው የበረራ አስተዳደር ባለሥልጣን እና ቦይንግ ያቀረቧቸውን ይዘቶች ተቋማቸው በሥራ መመሪያዎች ውስጥ ማካተቱን እና ለአብራሪዎቹ ማብራሪያ መሥጠቱን አቶ ተወልደ በዛሬው ዕለት ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ ተናግረዋል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው በኢንዶኔዥያ ከደረሰው አደጋ በኋላ የተወሰደው ይኸው ይኸ እርምጃ በቂ እንዳልነበር የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሾፍቱ አቅራቢያ #የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪዎች 737 ማክስ 8 የተሰኘውን ሞዴል ለማብረር የሚያስፈልጋቸውን ተገቢ ሥልጠና መውሰዳቸውን በሳምንቱ መገባደጃ ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር። ከበረራ የታገደው 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ ሥራ ከመመለሱ በፊት አምራቹ ቦይንግ ኩባንያ ይፋ አደርገዋለሁ ያለው የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር ማሻሻያ ሁሉንም ችግሮች መቶ በመቶ ሊቀርፍ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia