TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Abyei #UNISFA

ተመድ ሜ/ጄነራል ቤንጃሚን ኦሉፊሚ ሳውየርን የአብዬ ጊዜያዊ የፀጥታ ሃይል አዛዥ አድርጎ ሾሟል።

ሜ/ጄነራል ቤንጃሚን ኦሉፊሚ ዜግነታቸው ናይጄሪያዊ ሲሆኑ በኢትዮጵያዊው ሜጀር ጀነራል ከፍያለው አምዴ ተሰማ ምትክ ነው በቦታ የተሾሙት።

ሜ/ጀነራል ከፍያለው አምዴ በአብዬ ግዛት የነበረውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ሲመሩ እንደነበር ይታወቃል።

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሜ/ጄነራል ከፍያለው አምዴ የአብዬ ጊዜያዊ የፀጥታ ኃይል አዘዥ ሆነው ከተሸሙበት ጊዜ አንስቶ ላሳዩት ትጋት፣ የሰጡት አግልግሎትና ውጤታማ አመራር ምስጋና አቅርበዋል።

ሱዳን በአብየ ግዛት ያለው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ከስፍራው እንዲወጣ ጥያቄ ማቅረቧ ይታወሳል።

ከሳምንታት በፊት ተመድ በአብዬ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የመተካቱ ሂደት በየካቲት ወር እንደሚጀመር መግለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia