TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የ12ኛ_ክፍል_ፈተና

በመጀመሪያው ዙር በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ላይ መቀመጥ ያልቻሉ ተማሪዎች ካሉባቸው አካባቢዎች አንዱ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ነው።

ወረዳው በ2ኛ ዙር ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች አስፈላጊውን ኦሬንቴሽን መስጠቱን አሳውቋል።

የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በወረዳ ደረጃ ለሚፈተኑ ተማሪዎች ህግና ስረአትን ጠብቀው በአግባቡ እንዲፈተኑ ኦሬንቴሽን መሰጠቱን የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት አሳውቋል።

የ2ኛ ዙር የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተና ከጥር 24 እስከ 27 / 2014 ዓ/ም ድረስ ይሰጠል።

ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ በወረዳና በትምህርት ቤት ደረጃ የፈተና ኮማንድ ፖስት የተቋቋመ መሆኑን የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አሳውቋል።

ከቀናት በፊት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በፀጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎችን በሙሉ እንደሚያስፈትን ማሳወቁ ይታወሳል።

ክልሉ ለ36 ሺ 800 ተማሪዎች ፈተና ለመስጠት ዝግጅት ማድረጉን መግለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#UAE

ታሪካዊ ነው የተባለው ጉብኝት ዩኤኢ ውስጥ እየተካሄደ ነው።

ዛሬ የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ገብተዋል። ዩኤኢ ሲድርሱም እጅግ የሞቀ አቀባበል እንደተሰረገላቸው ነው ለማወቅ የተቻለው።

ታሪካዊ ነው የተባለ የሰላም ጉብኝት እያካሄዱ ነው ተብሏል።

ፕሬዜዳንቱ በሼክ መሀመድ ቢንዛይድ የተጋበዙ የመጀመሪያው የእስራኤል ፕሬዝዳንት መሆናቸው ተገልጿል።

የእስራኤሉ ፕሬዜዳንት ፤ ሼክ መሀመድ ቢንዛይድ በቤተ መንግስታቸው ላደረጉላቸው አቀባበል እና መስተንግዶ አመስግነው ፤ መካከለኛው ምስራቅ አዲስ ዘመን ውስጥ ገብቷል ብለዋል። ለዚህም ልዑሉና ሌሎች መሪዎች ግንኙነታቸውን መደበኛ ለማድረግ ላደረጉት ጥበባዊ እና ደፋር ውሳኔ አመስግነዋል።

በሼክ መሀመድ ቢንዛይድ እና አይዛክ ሄርዞግ መካከል የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር ላይ ባተኮሩ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክክር መደረጉ ተሰምቷል።

በእስራኤል የአሜሪካው አምባሳደር ቶም ኒድስ ጉብኝቱን በተመለከተ " ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ ላደረጉት ታሪካዊ ጉብኝት እንኳን ደስ አሎት ! ዲፕሎማሲ ይህንን ይመስላል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#UAE 👉 #EGYPT #ETHIOPIA #ISRAEL

ባለፉት ቀናት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከፍተኛ ባለልስጣናት፣ የግብፅ ፕሬዜዳንትን እንዲሁም የእስራኤል ፕሬዜዳንትን በሀገሯ ተቀብላ አድተናግዳለች።

ሀገሪቱ በቅድሚያ ያስተናገደችው የግብፁን ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲን ሲሆን በመቀጠል ደግሞ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ዛሬ ደግሞ የእስራኤል ፕሬዜዳንት አይዛክ ሄርዞግን ነው።

ከሁሉም መሪዎች እና ባለስልጣናት ጋር ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል። የዛሬው የእስራኤሉ ፕሬዜዳንት ጉብኝት ግን ታሪካዊ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#ATTENTION

" ... በዓሉ ለመታደም የምትመጡ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ እና ስለታማ ነገሮችን መያዝ ይቻልም " - የአዊ ፖሊስ

የ82ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዊ ዞን ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ ክብረ በዓሉ በዓለም የሳይንስ፣ የባህልና የትምህርት ተቋም (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ በሚደረገውን እንቅስቃሴ በርካታ እንግዶች የሚታደሙበት ስለሆነ ይሄን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የፀጥታ ስጋቶችን በመለየትና ከአጋር የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የቋሚ እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ጥበቃን በማጠናከር እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

የትራፊክ እንቅስቃሴ የተመቻቸ እንዲሆን በርካታ የትራፊክ ፖሊሶችን መሰማራታቸው ተገልጿል።

ፖሊስ የአካባቢው ወጣቶች እንግዶች በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች ሁሉ እገዛ እንዲያደርጉላቸው ለማደርግ በማደራጀት ወደ ስራ አስገብቻለሁ ብሏል።

በፀጥታ ስራው የመስተዳድር አካላትን ጨምሮ የአማራ ልዩ ኀይል፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የመደበኛና የአድማ መከላከል ፖሊስ እና የሚሊሻ ኀይል በፀጥታ ስምሪቱ መሳተፋቸው ተገልጿል።

በክብረ በዓሉ ለመታደም የሚመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ምንም አይነት የጦር መሳሪያ እና ስለታማ ነገሮችን መያዝ እንደማይቻል ተገንዝበው ለፀጥታ ኀይሎች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"ኢመደበኛ አደረጃጀት" የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ስለ " ኢ-መደበኛ አደረጃጀት " ምንድነው ያሉት ? አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፦ " ... ኢመደበኛ አደረጃጀት ያልናቸው አንዳንዶች በጦርነቱ ወቅት በጣም ከፍተኛ የሆነ ድርሻ የነበራቸው አሉ። አንዳንዶች ግን ጦርነቱን የሆነ ከተማ ውስጥ ሆነው በፌስቡክ፣ በዩትዩብ፣ ልክ እዛ ሆነው ምሽግ እንደሰበሩ የሚያሳዩ።…
#ETHIOPIA

" ሀገራዊ ውይይት "

የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከቀናት በፊት ከተደረገው የፌደራል የፀጥታ ም/ቤት እና የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች ውይይት በኃላ ለሚዲያዎች በሰጡት ቃል ስለሀገር አቀፍ ውይይት ምን አሉ ?

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፦

" ... አጠቃላይ በሀገራችን በአሁኑ ሰዓት ብዙ የማያግባባ ነገር አለ ወደሚያግባባ ነገር ለመምጣት Inclusive Peace Dialogue የሚባለው ወይም ይሄ በጋራ በጠረጴዛ ዙሪያ የማያግባቡ ጉዳዮችን ወደማየት ጉዳይ የምንገባበት ምዕራፍ ያው ኮሚሽንም እየተዘጋጀ ስለሆነ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው አፈጉባኤው እንደተናገሩት የጥቆማ እና ሌላው ስራ አልቆ ወደመምረጥ ሂደት እየገቡ ነው።

እነዚህ የማያግባቡ ጉዳዮች ላይ መግባባት ምንችል በጋራ መነጋገራችን ስለሆነ .. በባንዲራ ጉዳይ ልዩነት አለ፣ በህገመንግስት ጉዳይ ልዩነት አለ ... ብዙ የማያግባቡ ጉዳዮች አሉ ስለዚህ የማያግባቡትን ቁጭ ብሎ ስንነጋገር ስለሆነ መግባባት የምንችለው ለዛ ሰፊ ቦታ መስጠት ያስፈልጋል።

በዚህ የተነሳ እዚህም እዚያ መንግስት ለዚህ ተግባር በጣም አስፈላጊ የሆኑ አካላትን ከእስር እየለቀቀ መሆኑ ይታወቃል ፤ እንደገና በዚህ ጉዳይ ላይ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተባባሪ መሆን አለበት ህዝቡም ተባባሪ መሆን አለበት።

የታጠቀውም ፤ ያልታጠቀውም ኃይል ለውይይትና ለድርድር፣ ለንግግር እራሱን ማዘጋጀት አለበት።

የግድ ካልታሰርኩ በሚል ዝም ብሎ እዚህም እዚያም ነገሮችን የሚያባብሱ ሰዎች አሁንም ቢሆን መንግስት ህግና ስርዓት ለማስከበር ዝግጁ ነው ፤ በእነዚህ አካላት ላይ ወደፊት እርምጃ መወሰዱ አይቀርም። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሳውዲ ታሳሪዎች ጉዳይ ከንጉሥ ሰልማን ጋር ለመወያየት ለፊታችን ቅዳሜ ቀጠሮ መያዙ ተሰምቷል። የኢትዮጵያንና የሳውዲ ዐረቢያን ግንኙነት ለማሻሻልና በሳውዲ ታስረው የሚገኙና ወደ ሀገራቸው መመለስ በሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግስት የላካቸው ከፍተኛ የልዑክ ቡድን የፊታችን ቅዳሜ ከንጉስ ሰልማን ኢብኑ አብዱልአዚዝ ጋር ዉይይት ያደርጋሉ። በተጨማሪ ልዑኩ…
" ከሳኡዲ መልካም ዜና እየሰማን ነው " - ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

በሳኡዲ እስር ቤቶች በሚገኙ ዜጎቻችን ዙሪያ ለመነጋገር ወደ ሳኡዲ አረቢያ ከተጓዙት ልዑክ መልካም የሆነ ዜና እየሰማን እንገኛለን ሲል ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

በደማም ከሳዑዲ አረቢያ የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ወደ ሳዑዲ ያቀናው ልዑክ ያደረገው ውይይት #ፍሬያማ እንደነበር ገልፀዋል።

ኡስታዝ አቡበከር ፤ በቅርቡ በእስር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችን ጉዳይ እልባት እንደሚያገኝ መልካም ነገር ሰምተናል ብለዋል።

" ይህ ትልቅ እፎይታ የሚሰጥ መልካም ዜና ወደ ተግባር ወርዶ የወገኖቻችን ጭንቀት እና ስቃይ ያበቃ ዘንድ የሁላችንም እገዛ እና ዱዓ ያስፈልገዋል። ሁላችንም በዱዓ ልናግዛቸው እና ልናስታውሳቸው ይገባል " ሲሉም ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በሳዑዲ አረቢያ ስላሉ ዜጎቻችን ምን ተሰማ ?

(ከኡስታዝ አህመዲን ጀበል - ያገኘነው መረጃ)

• እስር ላይ ከሚገኙ ዜጎች ጋር በተያያዘ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ያመራው የኢትዮጵያ ልዑክ በደማም ከሳዑዲ አረቢያ የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወይይቷል።

• የመጀመሪያው ውይይት የተደረገው በአቶ አህመድ ሽዴ እና በሳዑዲ አረቢያው የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር መካከል ረጅን ሰዓት የወሰደ በዝግ ነበር ፤ በኃላም ሌሎች ልዑካን ተቀላቅለዋል።

• ከመንግስት የተላከ ደብዳቤ ለሳዑዲው ባለስልጣን እንዲደርስ ተደርጓል።

• የእስረኞች ችግር እና የተፈጠረ ያለው ነገር በአጠቃላይ የሻከረ ግንኙነት ስለሆነ ከተሳካ እንደበፊቱ ምንም እንኳን ህገወጥ ቢሆኑም የመታገስ እና የመጠበቅ ፤ የማንገላታት ነገር ስላለነበር ይሄን ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ በጉዳዩ ዙሪያ በአረብኛ ቋንቋ ዶ/ር ጄይላን ማብራሪያ ጠይቀዋል።

• የሳዑዲው ባለስልጣን በመንግስት በኩል የቀረበውን ብቻቸውን በአጭር ጊዜ መመለስ እንደማይችሉና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር በመነጋገር መጋፍትሄ እንሰጣለን ብለዋል።

• በሌላ በኩል ለሳዑዲ መንግስት በየትኛውም እስር ቤቶች ያሉ ሴቶች እና ህፃናት ከልዑካን ቡድኑ ከመጡት ጋር እንዲሄዱ እንዲደረግም ጥያቄ ቀርቦ ነበር፤ በዚህም ሀሙስ ዕለት ልኡከን ቡድኖቹ ሲመለሱ አበረው እንዲሄዱ ሊሲፓሴ የማዘጋጀት ሀሳብ ነው ያለው።

• አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና አቶ አህመድ ሽዴ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ይጠበቃል።

• አሁን በሳዑዲ የቀረ የልዑካን ቡድን ያለ ሲሆን በእስር ቤቶች ውስጥ ካሉ ሴቶች እና ህፃናት፣ ልጆች የታቀፉ እናቶች ጋር በመጪው ሀሙስ ወደ ሀገር እንዲመለሱ ለማድረግ ነው ያለው እንቅስቃሴ። (ይሄን በተስፋ መጠበቅ ነው)

• ሌላው ትኬት ቆርጠው መመለስ ለሚችሉ በየትኛውም እስር ቤት ላሉ ወገኖች እድል እንዲሰጣቸው ተጠይቆ ነበር ይህን በተመለከተ የሳዐዲ ባለስልጣናት ተነጋግረው ውሳኔ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

• በአጠቃላይ አሁን እየተፈጠረ ያለው ሁኔታ በግንኙነት መሻከር በመሆኑ እንደከዚህ በፊቱ በትዕግስትና በመልካም እይታ እንዲመለከቱ እና ሁኔታዎች በፈቀዱ ጊዜ በዘመቻ ለማውጣት ሙከራ እንደሚደረግ ነው የተነሳው። አሁን ያሉትን 100 ሺዎችን ማውጣት ቢቻል እንኳ ከስር ከስር ሌሎችም ውጭ ያሉትን ማሰሩ ከቀጠለ 800 ሺ የሚጠጉ ዜጎችን በአንድ ጊዜ ካለውም የሀገሪቱ ሁኔታ ፣ የኢኮኖሚው ሁኔታ አንፃር ፈታኝ ስለሚሆን እንደከዚህ ቀደሙ በትዕግስት እና በመልካም እይታ እንዲታይ ነው የተጠየቀው።

በሳዑዲ አረቢያ ከ100 ሺህ በላይ ታሳሪዎች በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ?

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ "የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት ጀመረ" የሚሉ በርካታ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ ይገኛሉ።

መንግስት በዚህ ጉዳይ በይፋ ያሳወቀው ነገር ባይኖርም ከዚህ ቀደም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ለማመንጨት መቃረቡ በተደጋጋሚ ተገልጿል።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጩ ለነበሩት የግድቡ መረጃዎች ምንጫቸውን ለማወቅ ብናስስም ልንደርስበት አልቻልንም።

በይፋ በመንግስት ይሁን በግል ሚዲያ ላይ ቀርቦ ይህንን ትልቅ ታሪካዊ ክስተት ለህዝብ ያሳወቀ አካል የለም፤ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ተቋማት በኩልም በፅሁፍ የወጣም ነገር የለም።

የግድቡ ሂደት በኃይል ማመንጨቱ በኩል አሁን ስላለበት ሁኔታ የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

ነገር ግን በዚህ ሂደት ማህበራዊ ሚዲያውን ስንዳስስ የኢትዮጵያ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ በተረጋገጠ የትዊተር ገፃቸው ላይ ፦

" የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) ኤሌክትሪክ ለማመንጨት እየተሞከረ ነው።

ይህ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨትም በላይ ነው።

ከNoMore ጉዟችን ብዙ እንደሚመጣ ግልፅ ነው። " የሚል ፅሁፍ ከላይ ከምትመለከቱት ፎቶ ጋር አስፍረው ተመልክተናል።

የህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት በቅርብ ጊዜ እውን እንደሚሆን በመንግስት በኩል ከሳምንታት በፊት መገለፁ መላው ሀገር ወዳድ ህዝብ ጉዳዩን በንቃት እንዲከታተለው ሆኗል።

ከዛሬ ነገ የላቡን ውጤት ለማየት ፣ ታሪካዊውን ሂደትም ለመመዝገብ በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል፤ በሚመለከታቸው ተቋማት በኩል መረጃ ባለመኖሩ ግን ለማህበራዊ ሚዲያ ይፋዊ ላልሆኑ መረጃዎች ተጋላጭ ሆኗል።

@tikvahethiopia
#AU2021

ኢትዮጵያ እንግዶቿን መቀበል ጀመረች።

የዝምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስት ፍሬድሪክ ሻቫ እና የሳዖቶሜና ፒሪንሲፔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤዲቴ ራሞስ ቴንዡዋ በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና በ40ኛው የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።

የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች የሚሳተፉበት የህብረቱ የስራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ ጥር 25 እና ጥር 26 ቀን 2014 ዓ/ም ይካሄዳል።

ፎቶ : ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#CHINA

ቻይና በኢትዮጵያ 🇪🇹 እየተሻሻለ መጥቷል ያለችውን የሀገር ውስጥ ሁኔታና መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀነ ገደብ ከመድረሱ በፊት እንዲያበቃ ያሳለፈው ውሳኔ ደስ እንዳሰኛት ገልፃለች።

የኢትዮጵያ ህዝብ የውስጥ ጉዳዩን በአግባቡ የመቆጣጠር ጥበብና ብቃት እንዳለውም አምናለሁ ስትል አስታውቃለች።

@tikvahethiopia
ዩኤኢ የሚሳኤል ጥቃት ተሰነዘረባት።

የእስራኤል ፕሬዜዳንት አይዛክ ሄርዞግ ' ታሪካዊ ' ለተባለው ጉብኝታቸው የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) በገቡበት በትላንትናው ዕለት የተባባሩት አረብ ኤሜሬትስ 2 የባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት በአቡ ዳቢ ተሰንዝሮባታል።

የሀገሪቱ ጦር የተፈፀመውን ጥቃት ማክሸፉንና የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ገልጿል።

የሚሳኤል ጥቃት ፈፃሚው የየመን ሀውቲ እንደሆነም ጦሩ አሳውቋል።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬት የአየር ኃይል በየመን ህጋዊነትን ለመመለስ ከተመሰረተው ጥምረት ጋር በመሆን በየመን አል-ጃውፍ ግዛት የሚገኘውን የሚሳኤል ማስወንጨፊያ ቦታ ማውደሙን ገልጿል።

የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ፤ ማንኛውም አይነት ስጋት ለመመከት እንዲሁም ሀገሪቱን ከማንኛውም አይነት ጥቃት ለመከላከል አስፈላጊ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑ አረጋግጧል።

የእስራኤል ፕሬዜዳንት ቢሮ ባወጣው መግለጫ ፕሬዜዳንቱ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የስራ ጉብኝታቸውን አቋርጠው እንደማይመለሱና በጉብኝታቸው እንደሚቀጥሉ አሳውቋል።

ሀውቲዎች ስለትላንቱ ጥቃት እስካሁን ያሉት ነገር ባይኖርም በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ላይ እያካሄድን ነው ስላሉት ኦፕሬሽን በቀጣይ ሰዓት መግለጫ እንደሚያወጡ ገልጸዋል።

የተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ ከሀውቲ ኃይሎች የትላንቱ መሰል ጥቃት ሲፈፀምባት በዚህ ወር ለ3ኛ ጊዜ ነው።

ከጥቂት ቀናቶች በፊት የ ሀውቲ ኃይሎች በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ላይ በፈፀሙት ጥቃት የሰዎች ህይወት ማለፉ እና ጉዳት መድረሱ ይህንንም ጥቃት ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ ሀገራትና ተቋማት ማውገዛቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቪድዮ - የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ አየር ኃይል ከጥምር ጦሩ ጋር በመሆን በየመን " አል-ጃውፍ " ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የሚሳኤል ማስወንጨፊያ ቦታ በተሳካ ሁኔታ ማውደሙን በመግለፅ ከላይ የተያያዘውን ቪድዮ አጋርቷል።

@tikvahethiopia
አሜሪካ የሀውቲን ጥቃት አወገዘች።

አሜሪካ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ አቡ ዳቢ የተፈፀመውን የሃውቲ ሚሳኤል ጥቃት እንደምታወግዝ አሳውቃለች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቃል አቅባይ የሆኑት ኔድ ፕራስ ፥ " የእስራኤል ፕሬዝዳንት በአካባቢው መረጋጋትን ለማስፈን እና ድልድይ ለመገንባት የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ባሉበት በአሁን ወቅት ሀውቲዎች ሰላማዊ ሰዎችን የሚያሰጉ ጥቃቶችን መሰንዘር ቀጥለዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

በነገራችን ላይ አሜሪካ ከሁለት ቀናት በፊት ለዜጎቿ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያስቡበት ማሳሰቢያ ሰጥታ ነበር።

አሜሪካ ከኮቪድ19 ምክንያት በተጨማሪ በሚሳኤል ወይም የድሮን ጥቃቶች ስጋት የተነሳ እና ሁኔታው አሳሳቢ በመሆኑ ዜጎቿ ወደ ሀገሪቱ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲያስቡበት ነበር ያሳሰበችው።

አሜሪካ ለዜጎቿ ባሰራጨችው የጥንቃቄ መልዕክት የቅርብ ጊዜ ጥቃቶች ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች እና በሲቪል መሠረተ ልማት ላይ ያነጣጠሩ እንደነበረ አሳውቃ ነበር።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ ቁልፍ አጋር ከሆኑት መካከል አንዷ እንደሆነች ይታወቃል።

@tikvahethiopia