TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ12ኛ ክፍል ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናውን የሚወስዱበት ቀን ይፋ ተደረገ። በ2013 የጸጥታ ችግር በተከሰተባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ከጥር 24 እስከ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ፈተናው እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል። በሁለተኛ ዙር የሚሰጠውን ፈተና 58 ሺህ 936 ተማሪዎች እንደሚወስዱም የአገልግሎቱ ምክትል…
#የ12ኛ_ክፍል_ፈተና

ከመጪው ጥር 24 እስከ ጥር 27 የሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ይሰጣል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዲሁም የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያደረሰው ተፅእኖ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል።

በተለይም ወረርሽኙ ወደሀገር ከገባ በኃላ እና በትግራይ ክልል ጦርነት ከተነሳ በኃላ የዓመቱ መርሀግብር በእጅጉ ተናግቷል።

ከጥቂት ወራት በፊት ብሄራዊ ፈተና የወሰዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እስካሁን ውጤት ያልተነገራቸው ሲሆን በዚህም ያለትምህርት ወራትን ለማሳለፍ ተገደዋል።

እስካሁን የፈተናው ውጤት ይፋ የሚደረግበትም ቀን አልታወቀም።

በትግራይ ክልል ፈተና መቀመጥ የነበረባቸው ተማሪዎች በጦርነት ምክንያት ላለፉት ዓመታት በአግባቡ ለፈተና መቀመጥ አልቻሉም።

በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በፀጥታ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ከመጪው ጥር 24 እስከ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ለፈተና ይቀመጣሉ።

ይህ ፈተና ሁለተኛ ዙር ሲሆን 58 ሺ 936 ተማሪዎች ፈተናው ይወስዳሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

@tikvahethiopia
#የ12ኛ_ክፍል_ፈተና

በመጀመሪያው ዙር በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ላይ መቀመጥ ያልቻሉ ተማሪዎች ካሉባቸው አካባቢዎች አንዱ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ነው።

ወረዳው በ2ኛ ዙር ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች አስፈላጊውን ኦሬንቴሽን መስጠቱን አሳውቋል።

የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በወረዳ ደረጃ ለሚፈተኑ ተማሪዎች ህግና ስረአትን ጠብቀው በአግባቡ እንዲፈተኑ ኦሬንቴሽን መሰጠቱን የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት አሳውቋል።

የ2ኛ ዙር የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተና ከጥር 24 እስከ 27 / 2014 ዓ/ም ድረስ ይሰጠል።

ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ በወረዳና በትምህርት ቤት ደረጃ የፈተና ኮማንድ ፖስት የተቋቋመ መሆኑን የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አሳውቋል።

ከቀናት በፊት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በፀጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎችን በሙሉ እንደሚያስፈትን ማሳወቁ ይታወሳል።

ክልሉ ለ36 ሺ 800 ተማሪዎች ፈተና ለመስጠት ዝግጅት ማድረጉን መግለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia