#ትምህርት_ሚኒስቴር
" በሁሉም ክልሎች በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው 50 ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም ክልሎች በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው 50 ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡ አሳወቀ።
ትምህርት ቤቶቹ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱና በችሎታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው ናቸው ተብሏል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሁሉም ክልሎች በዓይነታቸው ልዩ የሆኑና የልህቀት ማዕከል የሚሆኑ 50 ትምህርት ቤቶች ይገነባሉ ብለዋል።
ት/ ቤቶቹ ቀጣይ የአገር መሪ የሚሆኑ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎች የሚፈልቁበት በችሎታቸው ብቻ የሚመረጡ ተማሪዎች የሚማሩባቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።
በትምህርት ቤቶቹ የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መሠረት ባደረገና የትምህርት ሚኒስቴር በሚያወጣውን መመዘኛ የሚያሟሉ ተማሪዎች የሚማሩባቸው መሆናቸው ተገልጿል።
በሁሉም ክልሎች በሚገነቡት እነዚህ የልህቀት ማዕከላት ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የሚመለመሉ ተማሪዎችን ተቀብለው የሚያስተምሩ ይሆናሉ።
ይህንን መረጃ ያጋራው የትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገፅ ሚኒስትሩ የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ መቼ ተጀምሮ መቼ ለማጠናቀቅ እቅድ እንደተያዘ የተናገሩት ነገር ስለመኖሩ ያለው ነገር የለም።
@tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶ/ር ደብረፅዮን በቢቢሲ ኒውስ ሀወር ላይ ቀርበው ምን አሉ ?
የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ዛሬ ከቢቢሲ ኒውስ ሀወር ጋር በነበራቸው ቆይታ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር በሌሎች አካላት አማካኝነት (ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ) ንግግርና ውይይት መደረግ መጀመሩን ገልፀዋል።
በዚህም ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል።
ከፌዴራል መንግስት ጋር በሌሎች አካላት አማካኝነት (በUN ፣AU እና ኬንያ) የተጀመረው ውይይት ግጭቱ እንዲቆም ተስፋ የሚሰጥ ምልክት መሆኑን ነገር ግን የዲፕሎማሲ ውጤቱ በመጠበቅ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ዶ/ር ደብረጽዮን አሁንም ለችግሮች ሰላማዊ መፍትሔዎችን እንፈልጋለን ሲሉ ተደምጠዋል።
ቢቢሲ ኒውስ ሀወር በዚህ ዘገባው ከፌዴራል መንግስት በኩል ሰዎችን አላነጋገረም።
ዶ/ር ደብረፅዮን ቃላቸውን የሰጡበት የቢቢሲ ኒውስ ሀወር ፕሮግራም: www.bbc.co.uk/sounds/play/w172xv5kpz8pyk8?s=09
ከሰሞኑን ጠ/ሚ ዶክተር ዐብይ አህመድ ከዳያስፖራዎች ጋር በነበራቸው ዝግ ውይይት የሀገሪቱን ጥቅም የሚያስቀድም ምክንያታዊ ድርድር ይካሄዳል ስለማለታቸው አንድ የዳይስፖራ ተወካይ መናገሩን ኤፒ ዘግቦ ነበር።
ይህንንም ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፤ ይህ እንዳልተባለ፤ ህወሓት አሁንም በህግ ሽብርተኛ ድርጅት በመሆኑ ሽብርተኛ ከሆነ ድርጅት ጋር እንነጋገራለን የሚል አቋም የተገለፀበት አጋጣሚ እንደሌለ አሳውቀው ነበር።
አሁንም ትግራይ ክልልን ከአፋር እንዲሁም ከአማራ በሚያዋስኑ አካባቢዎች ባለው ግጭት ሰዎች እየተፈናቀሉ መሆኑ ሪፖርት እየተደረገ ነው። በተለይ በአፋር ክልል ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕከተኛ ፅ/ቤት ሪፖርት ማደረጉ አይዘነጋም።

TIKVAH-ETHIOPIA
#UAE የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዩኤኢ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ አቡ ዳቢ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር የጋራ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት @tikvahethiopia
#UAE #ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ጦር ምክትል አዛዥ ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ በኡቡ ዳቢ ውይይት አድርገው ነበር።
ውይይቱ በትብብር በጋራ ስለሚሰሯቸው ስራዎች እንዲሁም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር ላይ ያተኮረ እንደነበር ዋም ዘግቧል።
መሪዎቹ በምሥራቅ አፍሪካ ሰላም ለማውረድ የሚደረገውን ጥረት ጨምሮ በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተወይይተዋል።
ዶክተር ዐቢይ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም፣ መረጋጋት እና አንድነትን ተመኝተዋል።
ልማትን ለማሳካት ፣ የህዝቦችን መልካም የወደፊት ተስፋ ለመገንባት የመረጋጋት ፣ የሰላም ፣ የአብሮ መኖር እና የመተሳሰብ ምሰሶዎች ላይ ጠንካራ መሰረት መገንባት እንደሚያስፈልግ ሀገራቸው ያላትን ጽኑ እምነት ገልፀዋል።
ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ ፤ የኢትዮጵያ መንግስት የ " ሁቲ አማፅያን " በሀገራቸው ላይ የፈፀሙትን ጥቃት በማውገዝ ላሳየው አቋምና ከዩኤኢ ጎን በመሆን አጋርነቱን በመግለፁ አመስግነዋል።
በሌላ በኩል እኤአ በየካቲት ወር በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ስኬትን እና መልካም እድልን ተመኝተዋል።
ዶ/ር ዐቢይ በበኩላቸው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ላላት አቋም እና ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ስለምታደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውንና አድናቆታቸውን ገልጸው ለተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቀጣይ እድገትና ልማት ተመኝተዋል።
በተጨማሪም የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት በጥበብ እና ሚዛናዊ በሆነ ዲፕሎማሲ ላይ የተመሰረተ እና በተለያዩ የዓለም ሀገራት መረጋጋትንና በተለይ በቀውስ ወቅት ሰላምን ለማስፈን ጥረት እያደረገች ያለውን ግንኙነት እና የጋራ ችግሮችን ለመፍታት ከአገራት ጋር ያላትን ትብብር አድንቀዋል።
ዶ/ር ዐቢይ ፥ የተባበሩት አረብ ኤምሬት የጸጥታ እና የግዛት አንድነቷን ለማስጠበቅ በምትወስዳቸው እርምጃዎች ሁሉ ኢትዮጵያ አጋርነቷን እንደምትገልፅ አረጋገጠዋል።
የሽብር ጥቃቱ ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር፣ በቀጠናው ሚካሄደውን የሰላም ጥረት የሚያዳክም እና ሁሉንም ዓለም አቀፍ እና ሰብአዊ ደንቦችን እና ህጎችን የሚጥስ መሆኑንም ገልፀዋል።
ዛሬ ወደ ዩ.ኤ.ኢ ያቀናው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የመሩት የልዑካን ቡድን የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ ፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ፣ የሰለም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱአለም ፣ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፣ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የተካተቱበት ነው።
ይህን ዝርዝር መረጃ ያገኘውነው የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ መንግስት ከሚቆጣጣረው ከዋም ነው።

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ጠርቷል ?
ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፏል።
በሀገራችን በተከሰተ ሰላም እጦት ምክኒያት የዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደት መቋረጡን አስታውሷል።
ነገር ግን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ተማሪዎች ጥሪ እንዳስተላለፈ ተደርጎ እየተወራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው እስከ አሁን ምንም አይነት የጥሪ ማስታወቂያ #እንዳላስተላለፈ አስገንዝቧል።
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ይህን አውቀው አዲስ ማስታወቂያ ሲኖር #በተረጋገጡ የዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ እንደሚያሳራጭ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

#ZHAddis
እጆላይ ያለው ካሜራ ጊዜ በሄደ ቁጥር የሚሰጠው ጥቅም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ዝቅ እንደሚል ያቃሉ ከማይፈለግ እቃጋ ሳይመደብ አሁኑኑ እኛ ዘንድ ይዘው ይምጡ እንዳይቆጩ አርገን በጥሩ ዋጋ እንገዞታለን።
ይደውሉልን : 0911156257 ከታች ያለውንlink በመጫን የቴሌግራም አባል ይሁኑhttps://t.iss.one/joinchat/AAAAAEUTeB3LSYVFukiuQw
ቦሌ ወሎሰፈር HMM ህንፃ 2ኛ ፍቅ205

Photo
ፎቶ : የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ የማስታወሻ ሐውልት ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ተመርቋል።
ሀውልቱ በሀዲያ ልማት ማህበር (ሀልማ) የተሰራ ሲሆን 17.5 ሜትር ቁመት ያለው ሲሆን በ5 መቶ 30 ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈ ነው።
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ቤተሰቦች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ከፍተኛ የክልልና የዞን ባለስጣናት ፣ የቀድሞ የአየር ኃይል ባልደረቦችና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተው ነበር።
በሆሳዕና ከተማ የተገነባው የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ማስታወሻ ሀውልት ለሀገራቸው ላደረጉት ውለታና ለፈፀሙት ጀብድ ክብር የቆመ ነው።
Photo Credit : ኤፍቢሲ

#ColonelBezabihPetros
ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ በኢትዮጲያ አየር ኃይል ታሪክ ውስጥ በብዙዎች ዘንድ የብሔራዊ ጀግና ተምሳሌት ተደርገው ይቆጠራሉ።
በተለይም በ1969 ዓ.ም በተካሄደው የኢትዮ ሶማሊያ ጦርነት /ሚግ 23 ጀት በማብረርና ሞቃዲሾ ድረስ በመዝለቅ / በሰይድ ባሬ ወታደራዊ ጦር ሰፈር ላይ ያደረሱት ተደጋጋሚ ጥቃት ዛሬም ድረስ ይነገርላቸዋል።
በ1977 ከኤርትራ ሻዕቢያ ኃይሎች ጋር በነበረ ውጊያ በናቅፋ ግንባር አውሮፕላኑ ተመቶ ወደቀ በኃላም በሻዕቢያ እጅ ገቡ ታስረውም ቆዩ በ1983 (ከ7 ዓመት በኃላ) ግን ከእስር ተፈቱ።
በኃላም ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በባድመ ድንበር ውዝግብ ምክንያት ወደ ጦርነት በገቡበት ወቅት ኮሎኔሉ ለሀገር ክብር በድጋሚ ሻዕቢያን ለመደምሰስ ዘመቱ።
የኤርትራ አየር ኃይል የኢትዮጵያን አየር ጥሶ ትግራይ ግብቶ በአይደር ትምህርት ቤት ላይ ያደረሰውን ድብደባ ለመበቀል የኤርትራን የአየር ክልል ጥሰው ገቡ።
ግን ኮሎኔሉ ሲያበሩት የነበረው ጀት ተመቶ መውደቁን ተከትሎ / በምርኮ በኤርትራ ወታደሮች እጅ ከገቡ በኋላ / እስከዛሬ ከምናልባት በስተቀር ስለአሳቸው አውነተኛ መረጃዎችን ማግኘት አልተቻለም።
ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ለሀገራቸው በኢትዮ ሶማሊ ጦርነት ሆነ ከሻዕቢያ ጋር በተደረገው ጦርነት የሰሯቸው የጀብድ ታሪኮች በርካታ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል።
ይበልጥ በእሳቸው ዙሪያ የተፃፉ ፅሁፎችን መፅሀፍትን አግኝታችሁ ብታነቡ ለሀገራቸው ስለሰሯቸው ስራዎች ብዙ ታውቃላችሁ።

#Save_the_Children
በኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች የህፃናት አድን ድርጅት (Save the Children) በ136 ትምህርት ቤቶች ላይ የምገባ ፕሮግራም እየሰጠ መሆኑን ለኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን አሳውቋል።
ለ90 ሺህ ተማሪዎች በ136 ትምህርት ቤቶች ላይ በኦሮሚያ ፣ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች በ4 ወረዳዎች GPE ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በተገኘ ድጋፍ የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን የኢትየጵያ ደቡባዊ አካባቢ ማናጀር የሆኑት ዶክተር ሀይሉ ተስፋዬ ገልፀዋል።
በዚህ የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ማድረጉንና በተማሪዎች ትምህርት ውጤት እና የትምህርት ጥራት ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዲመጣ ማድርጉን ማናጀሩ ጨምረው ገልፀዋል።
ዶክተር ሀይሉ ተስፋዬ በቀጣይ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር Save the Children ዋነኛ አላማ ያደረገው የህፃናትን ትምህርትንና የምገባ ፕሮግራም የሚደረስና ጥራቱን የመጠበቅ ተግባር እንቀጥላለን ብለዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ስራው እንዲሳካ ለሚያደርገው ደግፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ማስጠንቀቂያ !
የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ የግንባታ ሳይቶች ከሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል ግንባታቸው ተጠናቆ ቁልፍ እንዲወሰዱ የተነገራቸው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕድለኞች ባለመምጣታቸው፣ በቀናት ውስጥ ቁልፍ እንዲወስዱ ማስጠንቀቂያ ሰጠ፡፡
ኮርፖሬሽኑ ቁልፍ ላልተወሰደባቸው ቤቶች የሚያደርገውን ጥበቃ እንደሚያነሳ አስታውቋል፡፡
የጋራ መኖሪያ ቤቶች በሚገኙባቸው ፕሮጀክት ሳይቶች በሙሉ የተለጠፈው የኮርፖሬሽኑ ማስጠንቀቂያ፣ የሕንፃና የቤት ቁልፍ ርክክብ ከተጀመረ ብዙ ወራት ቢቆጠሩም ነዋሪው ቤቱን ተረክቦ እያደሰና እየገባ አለመሆኑን ይገልፃል።
በዚህም ምክንያት የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቶች ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ በመሆናቸው፣ ነዋሪዎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስከ የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ መጥተው ቁልፍ እንዲረከቡ ያሳስባል፡፡
ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-01-30
ምንጭ፦ ሪፖርተር

Telegraph
Reporter
#ADDISABABA የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ የግንባታ ሳይቶች ከሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል ግንባታቸው ተጠናቆ ቁልፍ እንዲወሰዱ የተነገራቸው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕድለኞች ባለመምጣታቸው፣ በቀናት ውስጥ ቁልፍ እንዲወስዱ ማስጠንቀቂያ ሰጠ፡፡ ኮርፖሬሽኑ ቁልፍ ላልተወሰደባቸው ቤቶች የሚያደርገውን ጥበቃ እንደሚያነሳ አስታውቋል፡፡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች…
#ShabelleBank
የሸቤሌ ባንክ ምስረታ ስነ- ስርአት ተካሔደ።
የሸቤሌ ባንክ መመስረቻ ስነ ስርአት ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ተካሒዷል።
በ2011 የሶማሊ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም " ሄሎው ካሽ " በሚል የገንዘብ ግብይትና ዝውውር አገልግሎት መስጠት የጀመረው ተቋሙ ለመቶ ሺህ ለሚሆኑ የአካባቢው ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሮ እያገለገለ ይገኛል።
በማይክሮ ፋይናንስነት አገልግሎቱ እስከ አሁን 1 ሚሊየን 3 መቶ ሺህ በላይ የሚደርሱ ደንበኞችን እንዳሉት ይገለፃል።
ተቋሙ በእስከ አሁን ሒደቱ በ43 የተለያዩ የአገልግሎት ማዕከላት ሲኖረው 500 ቋሚ ሰራተኞችን ይዞ በ 3.7 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር ጠቅላላ የሐብት መጠን በማስመዝገብ በ2013 አመተ ምህረት ከብሔራዊ ባንክ ባገኘው እውቅና ወደ እስላሚክ ሸቤሌ ባንክነት ማደግ ችሏል።
በዛሬው የባንክ በምስረታ የሐገር ሽማግሌዎች ፣ የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፣ አምባሳደር ዶ/ር መሐሙድ ድሪር ፣ የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሐሰን መሐመድ፣ የተለያዪ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
#SRTV

ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ህዳር 21 ቀን 1972 ዓ/ም ለንባብ ለበቃው “ታጠቅ” ለተሰኘ የሰራዊቱ ጋዜጣ በሰጡት ቃለምልልስ የተናገሩት ፦
“… እኛ ብንሞት ሌላ ሰው ይተካናል ፤ መተኪያ የሌላት ኢትዮጵያ ከሞተች ግን ተተኪው ትውልድ ስለሚሞት ዋጋ አይኖረውም፡፡
የሀገርን ሉአላዊነት በአስተማማኝነት መጠበቅ ቆራጥነት እና ልበ ሙሉነት ይጠይቃል፡፡
እኛ በሕይወት ቆመን እያየን ጠላት አንዲት ስንዝር መሬት ቆርሶ መሄድ ቀርቶ በአንድ እግሩ እንኳ ሊቆምባት አይችልም፡፡
ከሀገር ወዲያ ሌላ መኖሪያ ዋሻ ስለሌለ በሃገርና በነፃነት ጉዳይ ምንም ቀልድ ሊኖር አይችልም፡፡ ”