TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Syria : በርካታ የውጭ ኃይሎች እጃቸውን በከተቱበትና 10 ዓመታትን በዘለቀው የሶሪያ እርስ በእርስ ጦርነት ቢያንስ 350,209 ሰዎች እንደተገደሉ UN እአአ ከ2014 ወዲህ ባደረገው የመጀመሪያ ይፋዊ የሞት ቁጥር አስታውቋል።

ይህ ቁጥር ግን ድርጀቱ ማንነታቸው የለያቸው ሰዎች እንጂ በጦርነቱ የተገደሉ ሰዎችን ቁጥር በትክክል አያሳይም ተብሏል።

UN ከ2014 በኋላ የሟቾችን ቁጥር መመዝገብ በይፋ አቁሞ ነበር። ምክንያቱም ድርጅቱ መረጃው የተመሰረተው በሶሪያ ይንቀሳቀሱ የነበሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የነበሩ ሲሆን ከጦርነቱ መፋፋም ጋር ተያያዞ የድርጅቶቹ ቁጥር በመመናመኑ የተነሳ መሬት ላይ ያለውን የሟቾቹን ቁጥር በትክክለኛው የሚያሳይ መረጃም ለማግኘት ተቸግሮ ነበር።

ነገር ግን ጦርነቱ በዚህ አመት 10 አመት ማስቆጠሩን ተከትሎ UN የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት ለሰብዓዊ መብቶች ፅ/ቤት በአገሪቱ ውስጥ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ ለማወቅ እንዲሞክር ተጠይቋል።

ባለፈው ዓርብ ለም/ቤቱ ሪፖርት ያደረጉት የተመድ የሰብዓዊ መብት ኃላፊ ሚሸል ባችሌት "ውስብስብና አድካሚ ስራ" ያሉት ሲሆን ተለይተው የታወቁ ሟቾች ቁጥር 350,209 ነው ብለዋል።

ሟቾቹ የሲቪልና ተዋጊዎችን ቁጥር ያካተተ ሲሆን ጊዜው ከአውሮፓውያኑ 2011-2021 ነው።

የሰብዓዊ መብት ኃላፊዋ ከሟቾች ውስጥ እንደ የሴቶች ሟቾች አኃዝ ሁሉ የህፃናት ሟቾች ቁጥር 8 በመቶ ገደማ ነው።

በሶሪያ ጦርነት ከሀገሪቱ መንግስት እና ተቃዋሚዎች ውጪ የሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ቱርክ፣ ኢራን ሌሎችም ኃይሎች እጅ ያለበት ሲሆን የውጭ ኃይሎቹ እንደግፈዋለን ለሚሉት አካል መሳሪያ በማቅረብ፣ ቢሊዮን ዶላሮችን በማፍሰስ፣ ወታደር በመላክ ፣ በማሰልጠን፣ የአየር ድብደባ በመፈፀም ተሳትፈዋል በሲቪሎች ግድያ ውስጥም እጃቸው አለበት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING🚨 የበሽር አላሳድ አገዛዝ ተገረሰሰ። የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ወደቀ። እሳቸውም ሀገር ለቀው ጠፍተዋል። የታጠቁ የሶሪያ ተዋጊዎች የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄዱ ነበር። በተለይም በሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ የታጣቁ ተቃዋሚዎች ከረዥም ዓመታት በኋላ የአገሪቱ ጦር ላይ ድንገታዊ ጥቃት…
#Syria : የ24 ዓመታት የፕሬዜዳንት በሽር አልአሳድን አገዛዝ ያስወገዱት የታጠቁት ተቃዋሚዎች አልአሳድ ሀገር ጥለው መጥፋታቸውን ገልጸዋል።

የሶሪያ ተዋጊዎች በደማስቆ የሚገኘውን የአውሮፕላን ማረፊያን ከመቆጣጠራቸው ጥቂት ጊዜ በፊት በሶሪያ አየር ክልል ውስጥ የአንድ አውሮፕላን እንቅስቃሴ ተመዝግቧል።

የIL76 አውሮፕላን የበረራ ቁጥሩ ' የሶሪያ አየር 9218 ' ከደማስቆ የተነሳ የመጨረሻ በረራ ነበር።

ይኸው አውሮፕላን መጀመሪያ ላይ ወደ ምሥራቅ በረረ፣ ከዚያም ወደ ሰሜን ዞሮ ሲበር ነበር።

ለደቂቃዎች ሆምስን ከዞረ በኃላ ከራዳር እይታ ውጭ ሆኗል። አውሮፕላኑ የት ይገባ የት ምንም አልታወቀም።

በሽር አልአሳድ ከሀገር መውጣታቸው ይነገር እንጂ የት እንዳሉ እስካሁን አይታወቅም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Syria : የ24 ዓመታት የፕሬዜዳንት በሽር አልአሳድን አገዛዝ ያስወገዱት የታጠቁት ተቃዋሚዎች አልአሳድ ሀገር ጥለው መጥፋታቸውን ገልጸዋል። የሶሪያ ተዋጊዎች በደማስቆ የሚገኘውን የአውሮፕላን ማረፊያን ከመቆጣጠራቸው ጥቂት ጊዜ በፊት በሶሪያ አየር ክልል ውስጥ የአንድ አውሮፕላን እንቅስቃሴ ተመዝግቧል። የIL76 አውሮፕላን የበረራ ቁጥሩ ' የሶሪያ አየር 9218 ' ከደማስቆ የተነሳ የመጨረሻ በረራ…
#SYRIA : የ24 ዓመታት የአልአሳድ አገዛዝ እንዴት ተገረሰሰ ?

በፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ላይ እ.ኤ.አ. በ2011 / ከዛሬ 13 ዓመት በፊት ነው ህዝባዊ አመጽ የተነሳው።

ከዛ ጊዜ አንስቶ ሀገሪቱ መረጋጋት አልቻለችም።

ታጣቂዎች በየቦታው ተነሱ ሀገሪቱ የከፋ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ገባች።

ይኸው 13 ዓመታት በሆነው የማያባራ እልቂት በርካታ ህጻናት፣ እናቶች፣ ወጣቶች ፣ አዛውንቶች ተቀጥፈዋል።

ሀገሪቱ እንዳልነበር ሆና ወድማለች።

ሶሪያ ዳግም ከወደቀችበት አዘቅት ለመውጣት ዘመናት የሚያስፈልጋት ሆናለች።

በዚህ 13 ዓመታትን በቆየው የእርስ በርስ ጦርነት የውጭ ሀይሎች እነ ሩስያ፣ ኢራን፣ አሜሪካ ፣ ቱርክ ... እጃቸው አለበት።

የውጭ ኃይሎቹ እንደግፈዋለን የሚሉትን ኃይል በማገዝ እልቂቱን እንዳያባራ አድርገዋል።

ምንም እንኳን በሀገሪቱ ያሉ የታጠቁ ተቃዋሚዎች የአላሳድን አገዛዝ ለመገርሰስ ሲዋጉ ፣ የተለያዩ ቦታዎችን ሲይዙ ለዓመታት ቢቆዩም የሰሞኑን ከፍተኛ ፍጥነት የታየበት ድንገታዊ ጥቃት ግን " ድራማዊ " ተብሎለታል።

ካለፈው ሳምንት አንስቶ ተጣቂዎቹ በተለያየ የሀገሪቱ አቅጣጫ በከፈቱት መጠነ ሰፊ ጥቃት የሶሪያ ጦር ፈራርሷል።

ወታደሮች ሀገር ጥለው ሸሽተዋል ፤ የአላሳድ መቀመጫ ደማስቆን ጨምሮ ትልልቅ እና ቁልፍ የሚባሉ ከተሞች በፍጥነት በታጠቁት ተቃዋሚዎች እጅ ወድቀዋል።

የአላሳድ ደጋፊ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ሩስያ በጦር አውሮፕላኖች ታግዛ ጭምር ለአላሳድ ድጋፍ ብታደርግም ፤ ኢራንም አለሁ " አግዛለሁ " ብትልም አገዛዙን ከውድቀት አልታደጉም።

ተንታኞች የአሳድ ጦር ኃይሎች በዝቅተኛ ደሞዝ እና በመኮንኖች መካከል በተንሰራፋው ሙስና የተነሳ የውግያ ሞራላቸው ተንኮታኩቷል ብለዋል።

ምንም እንኳን በቅርቡ ለሰራዊቱ የ50 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ ቢደረግም ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሊፈጠር ባለመቻሉ አገዛዙ ፈርሷል።

በአላሳድ ስር ሲዋጉ የነበሩ ወታደሮች ልብሳቸውን እያወለቁ ሲቪል መስለው ሲሸሹ ታይተዋል።

አላሳድም ሀገር ጥለው ጥፍተዋል። የት እንዳሉ አይታወቅም።

ቀጣዩ የሶሪያ ዕጣፋንታ ምንድነው ? ጁላኒ ማናቸው ?

አሁን ወደፊት ወጥተው የሚታዩት የቀድሞ ' አል-ኑስራ ' መሪ አሁን ደግሞ ሃያት ታህሪር አል-ሻም (ኤችቲኤስ) የተባለው የታጠቀ ኃይል መሪ አቡ መሀመድ አል ጁላኒ ናቸው።

በበላይነት የታጣቂዎቹን እንቅስቃሴ እያስትባበሩ ያሉት እሳቸው እንደሆኑ ተነግሯል።

ኑስራን ከመመስረታቸው በፊት ኢራቅ ውስጥ ለ #አልቃይዳ ተዋግተዋል። ወደዛ የሄዱት የአሜሪካን ወራር ተከትሎ ነው።

እኚህ ሰው ለ5 ዓመታት በአሜሪካ እስር ቤት አሳልፈዋል።

የአላሳድን አገዛዝ ለመጣል እንቅስቃሴ ሲጀመር በአልቃይዳው መሪ አቡ ባከር አል ባግዳዲ አማካኝነት የአልቃይዳ ህዋስ እንዲኖር  ለማድረግ ታስበው ወደ ሶሪያ ተልከዋል። (IS በኢራቅ በኃላ ISIS የሆነው)

አሜሪካ በ2013 አል-ጁላኒን በአሸባሪነት ፈርጃቸዋለች።

እ.ኤ.አ. 2016 ላይ ከአልቃይዳ መፋታታቸው ከተነገር በኃላ ሃያት ታህሪር አል-ሻም የተሰኘውን ቡድን ይዘው መጥተዋል።

ከአልቃይዳም ሆነ ከሌላ ቡድን መፋታታቸው ተነገረ በኃላ የሶሪያ ኢስላሚክ ሪፐብሊክን የመመስረት ዓላማ አንግበው አላሳድን ሲዋጉ ቆይተዋል።

ይኸው የጁላኒ ቡድን አሁን የአላሳድን አገዛዝ በመጣል ትልቁን ድርሻ እንደያዘ ነው የተነገረው።

አቡ መሀመድ አል ጁላኒ ከአላሳድ መገርሰስ በኃላ በሰጡት ቃል ፤ ሁሉም የመንግስት ተቋማት በይፋ ተላልፈው እስኪሰጡ / ርክክብ እስኪደረግ ድረስ በአላሳድ ጠቅላይ ሚኒስትር ቁጥጥር ስር እንደሚቆዩ ይፋ አድርገዋል።

ጠ/ሚኒስትር መሀመድ ጋዚ አል ጃላሊ በሰጡት መግለጫ ፥ በደማስቆ ቤታቸው እንደሚቆዩ እና የህዝብ ተቋማት ስራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሽር አላሳድ ማን ናቸው ?

° እድሜያቸው 59 ነው። የተወለዱት ደማስቆ።
° ከህክምና ትምህርት ቤት ተመርቀዋል። ለንደን ውስጥ በኦፕታሞሎጂ ስፔሻላይዝድ አድርገዋል።
° የወንድማቸውን በመኪና አደጋ መሞት ተከትሎ ወደ ሶሪያ መጥተዋል።
° እኤአ 2000 ላይ ነው የአባታቸውን ሃፊዝ አላሳድን መሞት ተከትሎ ወደ አገዛዝ የመጡት። አባታቸው ከ1971 አንስቶ ሀገሪቱን ሲመሩ ነበር።
° ወንድማቸው ባሴል አላሳድ የአባታቸውን ስልጣን ይረከባሉ ተብሎ ቢጠበቅም በመኪና አደጋ በመሞታቸው በሽር አላሳድ ስልጣኑን መያዝ ችለዋል።
° የስልጣን ዘመናቸው ከ2011 በኃላ በጦርነት ተሞላ ነው።

አሁን ከሀገር ፍረጥጠዋል የተባሉት አላሳድ በበርካታ የየሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ኬሚካል ጦር መሳሪያ በመጠቀም፣ እና በሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ይከሰሳሉ።


🚨በሶሪያ የ13 ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት ከ350 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሞቱ ሪፖርቶች ያሳያሉ። ሚሊዮኖች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃዎቹን ከሮይተርስ ፣ አልጀዚራ ፣ ዋሽንግተን ፖስት ፣ከፍራንስ 24 ነው አሰባስቦ ያዘጋጀው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" አሳድ የሩስያን ድጋፍ በማጣታቸው ሶሪያን ለቀው ሸሽተዋል " - ትራምፕ

ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ የሩስያን ድጋፍ በማጣታቸው ሀገራቸውን ጥለው መሸሻቸውን ገለጹ።

ይህን ያሉት ' ትሩዝ ' በሚሰኘው ማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ ነው።

" አሳድ ሄዷል " ያሉት ትራምፕ " ጠባቂው በቭላድሚር ፑቲን የሚመራው ሩስያ፣ ሩስያ፣ ሩስያ ! ከዚህ በላይ እሱን (አሳድን) ለመጠበቅ ፍላጎት አልነበረውም " ሲሉ ገልጸዋል።

የትራምፕ ሀገር አሜሪካ በርካቶች ባለቁበት የባለፉት 13 ዓመታት የሶሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ወቅት ሶሪያ ውስጥ ናት።

ሀገሪቱ ዋና አላማ ብላ የገባችው ' ISIS 'ን ለማፅዳት ቢሆንም በቀድሞ ፕሬዜዳንት ኦባማ ሰዓት " አሳድ መሄድ አለበት / ከአገዛዙ መወገድ አለበት " የሚል አቋም በይፋ ይንፀባረቅ ነበር።

እኤአ በ2013 ኦባማ እስራኤልን ሲጎበኙ ከቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋር ሆነው " አሳድ መሄድ አለበት አገዛዙ ማብቃት አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህም ባለፈ ፤ የአሳድን ተቃዋሚዎች በቁሳቁስ እና በስልጠና ድጋፍ ታደርግላቸው ነበር።

የፑቱን ሀገር ሩስያ የአላሳድን መንግሥት የምትደግፍ ሲሆን የአገዛዙ ጠላቶች ላይ እርምጃዎችን ስትወስድ ነበር።

#Syria

@tikvahethiopia