TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Syria : የ24 ዓመታት የፕሬዜዳንት በሽር አልአሳድን አገዛዝ ያስወገዱት የታጠቁት ተቃዋሚዎች አልአሳድ ሀገር ጥለው መጥፋታቸውን ገልጸዋል። የሶሪያ ተዋጊዎች በደማስቆ የሚገኘውን የአውሮፕላን ማረፊያን ከመቆጣጠራቸው ጥቂት ጊዜ በፊት በሶሪያ አየር ክልል ውስጥ የአንድ አውሮፕላን እንቅስቃሴ ተመዝግቧል። የIL76 አውሮፕላን የበረራ ቁጥሩ ' የሶሪያ አየር 9218 ' ከደማስቆ የተነሳ የመጨረሻ በረራ…
#SYRIA : የ24 ዓመታት የአልአሳድ አገዛዝ እንዴት ተገረሰሰ ?

በፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ላይ እ.ኤ.አ. በ2011 / ከዛሬ 13 ዓመት በፊት ነው ህዝባዊ አመጽ የተነሳው።

ከዛ ጊዜ አንስቶ ሀገሪቱ መረጋጋት አልቻለችም።

ታጣቂዎች በየቦታው ተነሱ ሀገሪቱ የከፋ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ገባች።

ይኸው 13 ዓመታት በሆነው የማያባራ እልቂት በርካታ ህጻናት፣ እናቶች፣ ወጣቶች ፣ አዛውንቶች ተቀጥፈዋል።

ሀገሪቱ እንዳልነበር ሆና ወድማለች።

ሶሪያ ዳግም ከወደቀችበት አዘቅት ለመውጣት ዘመናት የሚያስፈልጋት ሆናለች።

በዚህ 13 ዓመታትን በቆየው የእርስ በርስ ጦርነት የውጭ ሀይሎች እነ ሩስያ፣ ኢራን፣ አሜሪካ ፣ ቱርክ ... እጃቸው አለበት።

የውጭ ኃይሎቹ እንደግፈዋለን የሚሉትን ኃይል በማገዝ እልቂቱን እንዳያባራ አድርገዋል።

ምንም እንኳን በሀገሪቱ ያሉ የታጠቁ ተቃዋሚዎች የአላሳድን አገዛዝ ለመገርሰስ ሲዋጉ ፣ የተለያዩ ቦታዎችን ሲይዙ ለዓመታት ቢቆዩም የሰሞኑን ከፍተኛ ፍጥነት የታየበት ድንገታዊ ጥቃት ግን " ድራማዊ " ተብሎለታል።

ካለፈው ሳምንት አንስቶ ተጣቂዎቹ በተለያየ የሀገሪቱ አቅጣጫ በከፈቱት መጠነ ሰፊ ጥቃት የሶሪያ ጦር ፈራርሷል።

ወታደሮች ሀገር ጥለው ሸሽተዋል ፤ የአላሳድ መቀመጫ ደማስቆን ጨምሮ ትልልቅ እና ቁልፍ የሚባሉ ከተሞች በፍጥነት በታጠቁት ተቃዋሚዎች እጅ ወድቀዋል።

የአላሳድ ደጋፊ ከሆኑ ሀገራት አንዷ ሩስያ በጦር አውሮፕላኖች ታግዛ ጭምር ለአላሳድ ድጋፍ ብታደርግም ፤ ኢራንም አለሁ " አግዛለሁ " ብትልም አገዛዙን ከውድቀት አልታደጉም።

ተንታኞች የአሳድ ጦር ኃይሎች በዝቅተኛ ደሞዝ እና በመኮንኖች መካከል በተንሰራፋው ሙስና የተነሳ የውግያ ሞራላቸው ተንኮታኩቷል ብለዋል።

ምንም እንኳን በቅርቡ ለሰራዊቱ የ50 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ ቢደረግም ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሊፈጠር ባለመቻሉ አገዛዙ ፈርሷል።

በአላሳድ ስር ሲዋጉ የነበሩ ወታደሮች ልብሳቸውን እያወለቁ ሲቪል መስለው ሲሸሹ ታይተዋል።

አላሳድም ሀገር ጥለው ጥፍተዋል። የት እንዳሉ አይታወቅም።

ቀጣዩ የሶሪያ ዕጣፋንታ ምንድነው ? ጁላኒ ማናቸው ?

አሁን ወደፊት ወጥተው የሚታዩት የቀድሞ ' አል-ኑስራ ' መሪ አሁን ደግሞ ሃያት ታህሪር አል-ሻም (ኤችቲኤስ) የተባለው የታጠቀ ኃይል መሪ አቡ መሀመድ አል ጁላኒ ናቸው።

በበላይነት የታጣቂዎቹን እንቅስቃሴ እያስትባበሩ ያሉት እሳቸው እንደሆኑ ተነግሯል።

ኑስራን ከመመስረታቸው በፊት ኢራቅ ውስጥ ለ #አልቃይዳ ተዋግተዋል። ወደዛ የሄዱት የአሜሪካን ወራር ተከትሎ ነው።

እኚህ ሰው ለ5 ዓመታት በአሜሪካ እስር ቤት አሳልፈዋል።

የአላሳድን አገዛዝ ለመጣል እንቅስቃሴ ሲጀመር በአልቃይዳው መሪ አቡ ባከር አል ባግዳዲ አማካኝነት የአልቃይዳ ህዋስ እንዲኖር  ለማድረግ ታስበው ወደ ሶሪያ ተልከዋል። (IS በኢራቅ በኃላ ISIS የሆነው)

አሜሪካ በ2013 አል-ጁላኒን በአሸባሪነት ፈርጃቸዋለች።

እ.ኤ.አ. 2016 ላይ ከአልቃይዳ መፋታታቸው ከተነገር በኃላ ሃያት ታህሪር አል-ሻም የተሰኘውን ቡድን ይዘው መጥተዋል።

ከአልቃይዳም ሆነ ከሌላ ቡድን መፋታታቸው ተነገረ በኃላ የሶሪያ ኢስላሚክ ሪፐብሊክን የመመስረት ዓላማ አንግበው አላሳድን ሲዋጉ ቆይተዋል።

ይኸው የጁላኒ ቡድን አሁን የአላሳድን አገዛዝ በመጣል ትልቁን ድርሻ እንደያዘ ነው የተነገረው።

አቡ መሀመድ አል ጁላኒ ከአላሳድ መገርሰስ በኃላ በሰጡት ቃል ፤ ሁሉም የመንግስት ተቋማት በይፋ ተላልፈው እስኪሰጡ / ርክክብ እስኪደረግ ድረስ በአላሳድ ጠቅላይ ሚኒስትር ቁጥጥር ስር እንደሚቆዩ ይፋ አድርገዋል።

ጠ/ሚኒስትር መሀመድ ጋዚ አል ጃላሊ በሰጡት መግለጫ ፥ በደማስቆ ቤታቸው እንደሚቆዩ እና የህዝብ ተቋማት ስራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሽር አላሳድ ማን ናቸው ?

° እድሜያቸው 59 ነው። የተወለዱት ደማስቆ።
° ከህክምና ትምህርት ቤት ተመርቀዋል። ለንደን ውስጥ በኦፕታሞሎጂ ስፔሻላይዝድ አድርገዋል።
° የወንድማቸውን በመኪና አደጋ መሞት ተከትሎ ወደ ሶሪያ መጥተዋል።
° እኤአ 2000 ላይ ነው የአባታቸውን ሃፊዝ አላሳድን መሞት ተከትሎ ወደ አገዛዝ የመጡት። አባታቸው ከ1971 አንስቶ ሀገሪቱን ሲመሩ ነበር።
° ወንድማቸው ባሴል አላሳድ የአባታቸውን ስልጣን ይረከባሉ ተብሎ ቢጠበቅም በመኪና አደጋ በመሞታቸው በሽር አላሳድ ስልጣኑን መያዝ ችለዋል።
° የስልጣን ዘመናቸው ከ2011 በኃላ በጦርነት ተሞላ ነው።

አሁን ከሀገር ፍረጥጠዋል የተባሉት አላሳድ በበርካታ የየሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ኬሚካል ጦር መሳሪያ በመጠቀም፣ እና በሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ይከሰሳሉ።


🚨በሶሪያ የ13 ዓመታት የእርስ በርስ ጦርነት ከ350 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሞቱ ሪፖርቶች ያሳያሉ። ሚሊዮኖች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ተሰደዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃዎቹን ከሮይተርስ ፣ አልጀዚራ ፣ ዋሽንግተን ፖስት ፣ከፍራንስ 24 ነው አሰባስቦ ያዘጋጀው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia