#AmharaRegion
እስካሁን ከህወሓት ነፃ ስለሆኑ አካባቢዎች በኢትዮጵያ ፌዴራሉ መንግስት ፣ በአማራ ክልል መንግስት እና በየአካባቢው አስተዳደሮች እንዲሁም በተቋማት ደረጃ ሪፖርት የተደረጉ፦
- በተለያዩ አካባቢዎች የጅምላ ግድያዎች ተፈፅመዋል ለአብነት ሰሜን ሸዋ አንፆቂያ ፣ ጋሸና፣ ኮምቦልቻ፣ ውጫሌ አካባቢዎች በዋናነት ይጠቀሳሉ።
- ከፍተኛ የሆነ ሲቪሎች ላይ ያነጣጠረ የንብረት ዘረፋ ተፈፅሟል። ለአብነት ሆቴሎች ፣ የንግድ ቦታዎች በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።
- የላሊበላ ኤርፖርት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።
- የደሴ ሆስፒታልን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የጤና ተቋማት ተዘርፈዋል፤ ወድመትም ደርሶባቸዋል። ለአብነት ዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመት ደርሶበታል። ሌላ በደ/ወሎ ብቻ 103 ጤና ጣቢያዎች እና 9 ሆስፒታሎች ዝርፊያ እና ውድመት ደርሶባቸዋል።
- ከ4 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ወድመዋል፤ የወደሙ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም 11 ቢሊዮን ብር እንደሚጠይቅ ተገልጿል።
- የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ዘረፋ እንዲሁም ውድመት ደርሶበታል። ለአብነት ከ251 በላይ የደንበኛ ንብረት የያዙ ኮንቴነሮች ተዘርፈዋል።
- የሚዲያ ተቋማት የጥቃት ሰለባ ከሆኑት መካከል ናቸው ለአብነት የአማራ ኤፍ ኤም ደሴ 87.9 ውድመት ደርሶበታል።
- በርካታ የመንግስት የሆኑ ተቋማት ፣ ተሽከርካሪዎች ፣ የተከማቹ የህብረተሰቡ መረጃዎች ላይ ውድመት ደርሷል። በተጨማሪ ባንኮች ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ለአብነት ዳሸን፣ አቢሲኒያ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አማራ ብድርና ቁጠባ ውድመት ከደረሰባቸው መካከል ይጠቀሳሉ።
NB : ከላይ የቀረቡት ሪፖርት ከተደረጉት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው።
@tikvahethiopia

#Update
ተንታ፣ ማሻና ወግዲ ከተሞች ትላንትና እና ዛሬ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት መካነሰላምና ከላላ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳገኙ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#ATTENTION
" ዝናብ ሊዘንብ ባለመቻሉ ድርቁ ለ4 ወራት ሊራዘም ይችላል " - አቶ ቦሩ ጃርሶ
ቦረና ዞን ውስጥ የተከሰተው ድርቅ ለ4 ወራት ሊራዘም ስለሚችል ለእንስሳት ሀብቱ የማይቋረጥ ድጋፍና ክትትል እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
በዞኑ እስካሁን ድረስ ዝናብ እንዳልዘነበ ተነግሯል።
የቦረና ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቦሩ ጃርሶ የድርቁን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ በዞኑ የተከሰተው ድርቅ እስካሁን ድረስ በአካባቢው ዝናብ ሊዘንብ ባለመቻሉ ድርቁ ለአራት ወራት ሊራዘም ይችላል ብለዋል።
መንግሥትና ዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች እያደረጉት ባለው ድጋፍ የሰው ሕይወት ማዳን ቢቻልም ድርቁ በተለይ የእንስሳት መኖና ውሃ እጥረት በማስከተሉ በእንስሳት ላይ አደጋ ጋርጧል ሲሉ ተናግረዋል።
ድርቁ በዞኑ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ 84 ሺ እንስሳት መሞታቸውን፣ 100 ሺ የሚሆኑ እንስሳት በአሳሳቢ ደረጃ እንደሚገኙ አሳውቀዋል።
በቦረና ዞን ውስጥ የሚገኙት የእንስሳት ዝርያዎች የአገር ሀብት እንደመሆናቸው መጠን የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥታት አሁንም ትልቅ ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አቶ ቦሩ ጃርሶ ማኅበረሰቡ በአካባቢው ያለውን የዝናብ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ዝናብ ሳይዘንብ ለ4 ወራት ሊቆይ እንደሚችል እየተናገሩ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የቦረና እንስሳት ዝርያ በድርቁ ምክንያት የከፋ ጉዳት እንዳይደርስባቸው በአንድ ማዕከል ተለይተው ድርቁን የሚሻገሩበት ሁኔታ የሚፈጠርበት ሁኔታ እንዲመቻች መጠየቃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

#MoH
የጤና ባለሞያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከታህሳስ 21 እስከ ታህሳስ 27 ድረስ ይሰጣል።
በህክምና ፣ ነርሲንግ ፣ ጤና መኮንን ፣ ፋርማሲ ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኖሎጂ፣ ሚድዋይፈሪ፣ አንስቴዥያ፣ ዴንታል ሜድስን እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ ሙያዎች ተመርቀው የጤና ሚኒስቴር የሚሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ለተመዘገቡ የጤና ባለሙያዎች ፈተናው የሚሰጠው ከታህሳስ 21-27/2014 ዓ.ም ድረስ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ፥ ተፈታኞች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቦ የፈተናውን ፕሮግራም በቅርብ ቀን እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

4 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመሰረተ።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ ህገወጥ እስር በመፈፀምና በማስገደድ 260 ሺ ብር የተቀበሉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቷል፡፡
የዐቃቤ ሕግ ክስ እንደሚያስረደዳው ከሆነ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የአስተዳደር ልማት ዘርፍ በሹፌርነትና በጉዳይ አስፈጻሚነት የሥራ መደብ ላይ የሚሰሩት፦
1ኛ.ረ/ኢ/ር ፍቃዱ ዘዉዴ
2ኛ.ረ/ኢ/ር ይስሀቅ ዳካ
3ኛ.ረ/ኢ/ር ደሴ ደጆ ዳዊት ዳዲና በልዩ ወንጀል ተካፋይነት ግብረ አበር የሆነው ዳዊት ዳዲ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ዲያፍሪክ ሆቴል አካባቢ የግል ተበዳይ በባለቤትነት በሚያስተዳድረው የንግድ መደብር በመግባት 4ኛ ተከሳሽ የመረጃ መረብ ደህንነት አገልግሎት ባልደረባ በመምሰል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች የፌ/ፖሊስ አባልነታቸውን ሽፋን በማድረግ ምርመራ የማከናወንና ተጠርጣሪ የመያዝ የሥራ ድርሻ ሳይኖራቸውና ምንም አይነት ትዕዛዝ ሳይሰጣቸው የግል ተበዳይን በወቅታዊ ጉዳይ ትፈለጋለህ በማለት ለሥራ በተሰጣቸው መኪና ጭነውት ከወሰዱት በኋላ 1 ሚሊዮን ብር እንዲሰጣቸው ጠይቀው በኢዮጵያ ንግድ ባንክ ባልቻ አባ ነፍሶ ቅርንጫፍ 260 ሺ ብር ወደ 1ኛ ተከሳሽ የቁጠባ ሂሳብ እንዲያስገባ በማድረግ የተከፋፈሉ በመሆኑ በ1996 ዓ/ም የወጣዉን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ፣ 33ና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 881/07 አንቀፅ 9(2) ስር የተመለከተዉን በመተላለፍ በፈፀሙት ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
ተከሳሾች ዛሬ በችሎት ቀርበው ክሱ የተነበበላቸው ሲሆን በክሱ ላይ መቃወሚያ ካላቸው እንዲያቀርቡ ለመጠባበቅ ለታህሳስ 7/2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዟል፡፡
ምንጭ፦ፍትህ ሚኒስቴር

#Djibouti
በሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የተመራው የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ልዑክ ጂቡቲ ይገኛል።
ልዑኩ ሄሪቴጅ ኢንስቲትዩት በተባለው አለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ተቋም አማካኝነት በየአመቱ የሚያዘጋጀው መድረክ ላይ እየተሳተፈ ነው።
መድረኩ በዋናነት በምስራቅ አፍሪካ ወቅታዊ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና በቀጠናው ውህደት ላይ ትኩረቱ ያደረገ ሲሆን የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ናቸው በንግግር የከፈቱት።
የጅቡቲ እና የሶማሊያ ሪፐብሊክ ባለስልጣናት እንዲሁም የኬንያ የቀድሞ ጁብሊ ፓርቲ መሪ ሌሎች ሙሁራን ተገኝተዋል።
የዘንድሮው መድረክ "በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ያሉ ችግሮች የመረጋጋት ተስፋን ይጎትታሉ?" በሚል ርዕስ ነው የተካሄደ ሲሆን ከተለያዩ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የተውጣጡ እውቅ ምሁራን ፅሁፎች አቅርበው ውይይት ተደርጓል።
በመድረኩ በኢትዮጵያ ያለው ነባራዊ ሁኔታ በቀጠናው ያለው አንደምታ ተዳሷል።
የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ፥ " ወራሪውና አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ የከፈተው ወረራ ቀጠናውን ለማተራመስ የተነሳ ስለሆነ የቀንዱ ሀገራት በጋራ ሊመክቱ ይገባል " ብለዋል።
አክለው ፥ " ጠ/ ሚ ዐቢይ አህመድ በማንኛውም ሀገር ላይ ጣልቃ ገብነት እንዳይኖርና አሸባሪው ህወሓት በምስራቅ አፍሪካ ያደርግ የነበረውን ጣልቃ ገብነትና የማተራመስ ስትራቴጂን ተከላክለው መልካም የሆነ ጉርብትና በሀገራት መካከል እንዲኖር አድርገዋል " ብለዋል
በተጨማሪ በመድረኩ ላይ አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድና ልዑካቸው የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የኢትዮጵያውያን ብቻ ነው በማለት የኢትዮጵያን ድምፅ አሰምተዋል።

#Somalia
ለዓመታት በአልሸባብ ስር የነበሩ አካባቢዎች በዳናብ ኮማንዶዎች ነፃ መደረጋቸው ተሰምቷል።
በአሜሪካ የሰለጠኑት የሶማሊያ ጦር አባላት [ዳናብ] በሞቃዲሾ አቅራቢያ በታችኛው ሸበሌ ክልል የሚገኙ መንደሮችን ጨምሮ ጋምቤሬይ፣ ዳዋካሌ እና ጌዲያን ከአልሸባብ ነፃ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ከላይ የተጠቀሱትን አካባቢዎች አልሸባብ ለዓመታት ሲቆጣጠራቸው ነበር።
በሌላ በኩል የወታደራዊ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ የዘገበው ጋሮዌ ትላንት የዳናብ ኮማንዶዎች ታችኛው ሸበሌ ክልል ባካሄዱት የታቀደ የፀረ-አልሸባብ ዘመቻ በትንሹ 5 ታጣቂዎችን ገድለው መሸሸጊያ ቦታቸውን አውድመውታል።

ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 4 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 4,779 የላብራቶሪ ምርመራ 125 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 153 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

#UN
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ም/ቤት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ላይ በዚህ ሳምንት ልዩ ስብሰባ እንደሚያደርግ የተሰማ ሲሆን ም/ቤቱ ስብሰባውን የሚያደርገው ከአውሮጳ ህብረት የቀረበለትን አስቸኳይ ጥያቄ ከተቀበለ በኃላ መሆኑ ታውቋል።

#ETHIOPIA
የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤትን አንዳንድ ሀገራት ኢትዮጵያን በተመለከተ የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ ለማራመድ እየተጠቀሙበት ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህ ሁኔታ እጅግ እንዳሳዘነውም ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የተመድ የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተፈፅመዋል በተባሉ ጥሰቶች ላይ በጋራ ጥናትና ምርመራ አድርገው የጋራ ሪፖርት ማውጣታቸውን መግለጫው አስታውሷል።
መንግስት ይህ የድርጅቶቹ የጋራ ሪፖርት ውጤትን ተቀብሎ ከፍተኛ የሚኒስትሮች ግብረሃይል አቋቁሞ ምክረ ሀሳቦችን ለመተግበር እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል።
ይህ በሆነበት ሁኔታ አንዳንድ የUN የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሀገራት ኢትዮጵያን በተመለከተ የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ በመያዝና ይህንንም አጀንዳቸውን በምክር ቤቱ በኩል ለመፈፀም ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ልዩ ስብሰባ እንዲያደርግ በመጥራት ላይ መሆናቸውን አንስቷል።
ይህ ሁኔታ የኢትዮጵያን መንግስት በእጅጉ እንዳሳዘነው ነው ያስታወቀው።
ይልቁንም ም/ ቤቱ አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች የፈፀማቸውን እጅግ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አጀንዳ አድርጎ ሊወያይና ሊያወግዘው በተገባ ነበር ብሏል።
የምክር ቤቱ አባል ሀገራት ይህንን የተወሰኑ ሀገራትን የፖለቲካ ፍላጎት ያነገበን ልዩ ስብሰባ እና ውጤቱን በጥብቅ እንዲቃወሙ ሚኒስቴሩ በአጽንኦት ጠይቋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም አቀፉ ህግ መሰረት ሰብዓዊ መብቶችን ለማክበር፤ ለማስከበርና ለማሟላት ያለውን ቁርጠኝነት ለሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት አባላትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዳግም ለማረጋገጥ ይወዳል ሲል አስገንዝቧል።
ምንጭ፦የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር/ኤፍቢሲ

#America
" ህወሓት ወታደራዊ ዘመቻውን እንዲያስፋፋም ሆነ አዲስ አበባ እንዲገባ አሜሪካ በምንም ሁኔታ አበረታታ አታውቅም" - የአሜሪካ መንግስት
ከሰሞኑን የህወሓት ቡድን ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው በሰጡት ቃለ ምልልስ ወቅት ስለ አሜሪካ የተናገሩትን ንግግር በተመለከተ የአሜሪካ መንግስት ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ምላሽ ሰጥቷል።
አቶ ጌታቸው ረዳ በቃለ ምልልሱ ወቅት ፥ " የአሜሪካን አቋም ለመረዳት ከባድ ነው ። አንዳንዴ በሁለታችንም ላይ ማዕቀብ እንደሚጥሉ እያስፈራሩ ሰላም እንድናወርድ ይስገድዱናል፤ መልሰው ህወሓት አዲስ አበባ ከገባ ደም መፋሰስ ይኖራል ይሉናል ፤ በተመሳሳይ ጊዜ አዲስ አበባ የምትገቡ ከሆነ ሊፈጠር የሚችለውን ረብሻ ለማስቀረት እንዲቻል ሌሎች ፓርቲዎችን ጠርታችሁ አንድሁኑ ይሉናል፤ አሜሪካውያኑ ህወሓት አ/አ ቢገባ እንደድሮው ግትር ይሆናል የሚል ፍራቻ አላቸው ይሁን እንጂ አሜሪካ ውስጥ ያለው አስተሳሰብ ወጥ አለመሆኑን ማወቅ ጥሩ ነው " ሲሉ ነው የተናገሩት።
በዚህ ጉዳይ የአሜሪካ መንግስት ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል ፦
" ህወሓት ወታደራዊ ዘመቻውን እንዲያስፋፋ ሆነ ወደ አዲስ አበባ እንዲገባ አሜሪካ በምንም ሁኔታ አበረታታ አታውቅም።
እኛ ለሁሉም ወገኖች በአደባባይ ሆነ በግልም የአሜሪካ አቋም ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ግጭት ወታደራዊ መፍትሄ እንደሌለው በተደጋጋሚ ግልፅ አድርገናል።
የኛ ፍላጎት ህወሓት ለቆ እንዲወጣና ትግራይ ላይ ያለው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት የከበባ እግድ ሊባል የሚችል ሁኔታ አብቅቶ ማየት መሆኑን ልዩ ልዑኩ ፌልትማን ህዳር 14 አሳውቀዋል።
የእኛ ግብ ግጭቱ እንዲያቆም ፣ የመብቶች ጥሰት እና ሁከት እንዲያበቃ ፣ ድርድር ያለቅድመ ሁኔታ እንዲጀመር ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲኖርና ያንን ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታዎች እንዲመቻቹ፤ ሁሉን አቃፊ የሆነ ብሄራዊ ውይይት እንዲጀመር የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ብቸኛውም መንገድ ዴፕሎማሲ እንዲሆን መደገፍ ነው። "

#እንድታውቁት
በተሽከርካሪ የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ አተገባበር ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።
ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ከሌሎች ቅድመ-ሁኔታዎች በተጨማሪነት የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ የማስገጠምና በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት መገጠሙን የሚያረጋገጥ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ የነበራቸው መሆኑ ይታወቃል።
ይሁንና በአተገባበሩ ላይ እየታየ ያለውን ብልሹ አሰራር እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፈተሽ እና ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችል አሰራርና አደረጃጀት ተጠናቆ ተግባራዊ እስኪደረግ ድረስ እንዲሁም የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያው ሊገጠምባቸው የሚገባቸውን ተሽከርካሪዎች ዓይነትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በጥናት ምላሽ መስጠት የሚያስፈልግ በመሆኑ ለጊዜው አዲስ ተሽከርካሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገቡ ባለንብረቶች በማምኛውም ጊዜ መሳሪያውን መግጠም እንዳለባቸው እንዲያውቁት ተብሏል።
የግዴታ ስምምነት እየፈረሙና አስፈላጊ ሰነዶቻቸውን በአባሪነት እንዲያያይዙ ተደረጎም በተሽከርካሪዎቹ ላይ የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ መግጠም ሳያስፈልጋቸው አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሳውቋል።