TIKVAH-ETHIOPIA
" በሚቀጥሉት 3 ወራት ዕጣ የወጣባቸውን 68 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች ለማስረከብ እየሰራን ነው " - የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን በሚቀጥሉት 3 ወራት ዕጣ የወጣባቸውን 68 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለዕድለኞች ለማስረከብ እየሰራ መሆኑን ለኢዜአ ገልጿል። ኮርፖሬሽኑ ዕጣ ወጥቶባቸው ወደ ባለዕድለኞች ያልተላለፉ 68 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በቀጣይ 3 ወራት…
" የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን በሚቀጥለው ወር ለማስረከብ እየሰራሁ ነው " - የአ/አ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሶስት ዓመት በፊት በተካሄደው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የወጣላቸውና በተለያዩ ምክንያቶች የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባለቤት የሆኑ ነዋሪዎችን ቤት በሚቀጥለው ወር ሙሉ ለሙሉ ለማስረከብ እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡
በሚቀጥለው ወር ወደ ቤታቸው ይገባሉ የተባሉት ከ63 ሺ በላይ የቤት ባለቤቶች ሲሆኑ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በ16 ሳይቶች የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አውራሪስ ከበደ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል፥ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ላይ ቅድመ ርክክብ ቢደረግም፣ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ባለመጠናቀቃቸው የቤት ባለቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተረክበውና አፅድተው አለመግባታቸውን አስታውቀዋል፡፡
እነዚህ የቤት ባለቤቶች በ13ተኛው ዙር የ20/80 ዕጣ፣ በሁለተኛው ዙር የ40/80 ዕጣ፣ እንዲሁም እንደ የልማት ተነሺነት ባሉ ልዩ ልዩ ምክንያቶች የቤት ባለቤት የሆኑ ናቸው፡፡
አቶ አውራሪስ፥ የቤት ባለቤት ከሆኑት ውስጥ እያፀዱ ያሉና መኖር የጀመሩ እንዳሉ ተናግረው ፤ ብዙዎቹ ግን ቤታቸውን ሙሉ ለሙሉ አለመረከባቸውን አስታውቀዋል፡፡
ነዋሪዎቹ ቤቶቹን ላለመረከባቸው ምክንያት የሆነው ቤቶቹ ሙሉ ለሙሉ ተገንብተው አለማለቃቸው ብቻ ሳይሆን እንደ ውኃ፣ መብራትና መንገድ ያሉ የመሠረተ ልማት አቅርቦቶች አለመዘርጋታቸው እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
እነዚህን ቀሪ ሥራዎች አጠናቆ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲገቡ ማድረግ በኮርፖሬሽኑ የ100 ቀናት ዕቅድ ውስጥ ያለ መሆኑ ያስረዱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ 100 ቀናት የሚጠናቀቀው ጥር 10 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሆነ መግለፃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።
@tikvahethiopia

#HappeningNow
" አዲስ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ትውልድ "
ሴንተር ፎር አድቫንስመንት ኦፍ ራይትስ ኤንድ ዴሞክራሲ (ካርድ) “የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አዲስ ትውልድ’’ በሚል ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል።
ዛሬ የሚመረቁት 364 የሚሆኑ የመንግሥትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ፅንሰ ሐሳቦችን፣ የሥርዓተ ፆታ እኩልነት፣ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲሁም የመሰብሰብና የመደራጀት መብቶች ላይ ሥልጠናዎችን ወስደነዋል።
በዛሬው ዕለት በኢንትር ላግዠሪ ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የሰብዓዊ መብት ፌስቲቫል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱኳን ሚዴቅሳ ተገኝተዋል።
መርኃግብሩን የካርድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር በፍቃዱ ኃይሉ በንግግር ከፍተዋል።
🔴 Live : https://fb.watch/9Rmjulyc8J/

ቱርክ ለሶማሊያ የድሮን ድጋፍ አደረገች።
ቱርክ ለሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የወታደራዊ መሳሪያ መለገሷን ጋሮዌ ዘግቧል።
ቱርክ ያደረገችው የሰው አልባ አውሮፕላኖች ወይም ድሮን ድጋፍ ሲሆን ድሮኖቹ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ለሀገሪቱ መሰጠታቸው ተሰምቷል።
ዶሮኖቹ የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ለአፍሪካ ቀንድ ትልቅ ስጋት የሆኑትን የአልሸባብ ታጣቂዎችን ለመዋጋት ይጠቅማሉ ተብሏል።
ቱርክ ላለፉት በርካታ አመታት የሶማሊያን ጦር ስታሰለጥን እና ስታስታጥቅ ቆይታለች ፤ አሁንም ለሀገሪቱ ጦር ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች።

#WFP
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ያቋረጠውን ድጋፍ ከቀናት በኃላ እንደሚጀመር አሳውቋል።
ድርጅቱ በአማራ ክልል የነፍስ አድን ምግብ እርዳታ ማድረግ መቀጠሉን ገልጿል።
በሰ/ጎንደር 470,000 ሰዎች በደሴ/ኮምቦልቻ 172,000 ሰዎች በJEOP በኩል መድረሱን አሳውቋል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፤ በዘረፋ እና በደህንነት ማጣት ምክንያት ባለፈው ሳምንት አቋርጦት የነበረውን ድጋፍ በሚቀጥሉት ቀናት ለመቀጠል ተስፋ እንደሚያድረግ ገልጿል።

" ከደቡብ ሱዳን በኩል የሚመጣ ኢትዮጵያን ለመጉዳት ያለመ እንቅስቃሴ አሁንም ሆነ ወደፊት አይኖርም " - ዶ/ር ሪያክ ማቻር
በደቡብ ሱዳን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደር ነቢል መህዲ ከደቡብ የሱዳንን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሪያክ ማቻር ጋር በሁለቱ ሀገራት በጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ዶ/ር ሪያክ ማቻር በኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን እና መካከል ያለውን ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ ግንኙነት አውስተው የደ/ሱዳን ህዝብ በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ የኢትዮጵያ መንግስታት ለሰጡት ያልተቋረጠ ድጋፍ ምስጋናው ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለው ለኢትዮጵያ ሰላም መስፈን ሀገራቸው ቁርጠኛ አቋም እንዳላት ጠቁመው፣ ከደቡብ ሱዳን በኩል የሚመጣ ኢትዮጵያን ለመጉዳት ያለመ እንቅስቃሴ አሁንም ሆነ ወደፊት እንደማኖር ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።
አምባሳደር ነቢል መህዲ በበኩላቸው ፥ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ በተለይ የህወሃት ወራሪ ሀይል በደረሰበት ምት ከያዛቸው ቦታዎች እየወጣ እንደሆነ ፤ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ለማድረስ እየተደረገ ያለውን ጥረት እንዲሁም የህወሃት ወራሪ ሀይል ይዟቸው በነበሩ ቦታዎች የፈጸማቸውን አሰቃቂ ጭፍጨፋን በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
አንዳንድ የምዕራባውያን የመገናኛ ብዙሃን ሀሰተኛ ዘገባዎች በማሰራጨት የአገሪቱ እና የአመራሩን ገጽታ ለማጠልሸት የጀመሩትን ስራ እየገፉበት እንደሆነ አምባሳደር ነቢል ማብራራታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

#Update
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በኮቪድ-19 ሳቢያ የሰው ሞት አልተመዘገበም።
ከተደረገው 3,452 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 115 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በኮቪድ-19 ሳቢያ የሰው ሞት አልተመዘገበም።
ከተደረገው 3,452 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 115 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow " አዲስ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ትውልድ " ሴንተር ፎር አድቫንስመንት ኦፍ ራይትስ ኤንድ ዴሞክራሲ (ካርድ) “የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አዲስ ትውልድ’’ በሚል ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል። ዛሬ የሚመረቁት 364 የሚሆኑ የመንግሥትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ፅንሰ ሐሳቦችን፣ የሥርዓተ ፆታ እኩልነት፣ ሐሳብን በነጻነት…
ፎቶ : ዛሬ ሴንተር ፎር አድቫንስመንት ኦፍ ራይትስ ኤንድ ዴሞክራሲ (ካርድ) “የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አዲስ ትውልድ’’ በሚል ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።
በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱኳን ሚዴቅሳ እንዲሁም የህግ አማካሪ እና ጠበቃ አመሃ መኮንን ተገኝተው ለተመራቂዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የብሄራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ መግቢያ ፈተና ነገ ይሰጣል።
ነገ ሰኞ ታህሳስ 4/2014 ዓ/ም የህክምና ስፔሻሊቲ መግቢያ ፈተና የሚሰጥ ሲሆን ፈተናው በአማራ ክልልም የሚሰጥ ይሆናል።
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ለኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ፅፎ በነበረው ደብዳቤ አሸባሪው ህወሓት ወረራ በፈፀመት ወቅት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ ፈተናውን ለመፈተን ተመዝግበው በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ጠቅላላ ሀኪሞች ላይ ጫና በመፈጠሩ መግቢያ ፈተናው ለመፈተን ስለሚቸገሩ እንዲራዘም ወይም ሌላ የተለየ አማራጭ እንዲፈለግላቸው ጠይቆ ነበር።
ጤና ሚኒስቴር በደብዳቤ በሰጠው ምላሽ የመግቢያ ፈተናው ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው የፈተና አስተባባሪዎች በአስራ ስምንቱ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተሰማርተው ፈተናውን ለመስጠት በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን በመገለፅ ፈተናውን ለማራዘም እንደሚቸገር አሳውቋል።
በዚህም የነገው ፈተና በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ በአማራ ክልል ጨምሮ የሚሰጥ ይሆናል።
ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እና ለፀጥታ ኃይል አባላት በክልሉ ውስጥ የህክምና አገልግሎት በመስጠት ምክንያት በወጣው መርሃግብር የመግቢያ ፈተናውን መፈተን የማይችሉ ሀኪሞች ካሉ ጤና ሚኒስቴር በሚደርሰው ማረጋገጫ አማካኝነት ሌላ ፈተና አዘጋጅቶ እንደሚያስፈትን አሳውቋል።

የአሜሪካ መግለጫ ...
ትላንት ለሊት ላይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ስለ ኢትዮጵያ ጉዳይ በቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ አማካኝነት አንድ መግለጫ አውጥቶ ነበር።
ይኸው መግለጫ በአማራ እና አፋር ክልሎች በትግራይ ኃይሎች ተፈጽመዋል የተባሉ " ያልተረጋገጡ " የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የንብረት ውድመቶች እጅግ አሳሳቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ነው።
አሜሪካ በአማራ እና አፋር ክልሎች በትግራይ ኃይሎች ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን፣ አስደንጋጭ የጭካኔ ድርጊቶችንና በሕዝብ መሠረተ ልማቶች ላይ የተፈጸሙ ውድመቶችን በተመለከተ እየወጡ ያሉ " ያልተረጋገጡ " ሪፖርቶች ያሳስበኛል ብላለች።
በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በሙሉ በንጹሃን ዜጎች ላይ የኃይል እርምጃዎችን ከመወሰድ መቆጠብ አለባቸውም ይላል መግለጫው።
ቃል አቀባዩ ፕራይስ ፥ " የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት እነዚህን ሪፖርቶችን በመመርመር ትክክለኛነታቸውን እንዲያጣሩ እና ጥፋተኛ የሆኑትን ተጠያቂ ለማድረግ ሁሉን አካታች እና ግልጽ ሥርዓት እንዲከተሉ እንጠይቃለን" ብለዋል።
አሜሪካ ፥ ይህ ጦርነት እንዲቋጭ የመጀመሪያው፣ የመጨረሻው እና ብቸኛው አማራጭ የዲሎማሲያዊ መንገድ ብቻ ነው ለዚህ ደግሞ በድጋሚ ድጋፋችንን እንገልፃለን ብላለች።
ከዚህ በተጨማሪ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ እንዲያበቃ ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድርድር እንዲጀመር፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እንዲኖር እና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ አቅርባለች።
* መግለጫው ከላይ ተያይዟል።