TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተመልከቱ⬆️

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ #የናይጄሪያ ዜጎች ንብረታቸው እንዴት እንደወደመባቸው ተመልከቱ። #SOUTHAFRICA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ እስካሁን ከ80 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሏል። #ደቡብ_አፍሪካ #SouthAfrica
#SouthAfrica

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በአንድ ቀን 1,134 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 19,137 ደርሰዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የሰላሳ (30) ሰዎች ህይወት አልፏል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ሶስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ (369) ደርሷል።

በደቡብ አፍሪካ አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተይዘው በተደረገላቸው ህክምና ያገገሙ ሰዎች 8,950 ናቸው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#SouthAfrica

የደቡብ አፍሪካ ሆስፒታሎች በሳምንታት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሊጨናነቁ እንደሚችሉ የአገሪቱ ከፍተኛ የክትባት ባለሙያ መናገራቸውን #ቢቢሲ አስነብቧል።

በአሁኑ ሰዓት ኬፕታውን የሚገኙ ሆስፒታሎች ከአቅማቸው በላይ መሙላታቸውን ገልፀው በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በመላ አገሪቱ እየጨመረ መሆኑን ገልፀዋል። በምስራቃዊ ኬፕታውን አሁን ያለው ሁኔታ ከሕክምና ተቋማቱ አቅም በላይ ሆኗል።

ፕሮፌሰሩ አክለውም በምስራቃዊ ኬፕታውን የተከሰተው ለሌሎችም ትምህርት መሆን እንዳለበት እንዲሁም ቀሪው የአህጉሪቱ ክፍልም እንዲሁ ሊጠቃ እንደሚችል ግንዛቤ መውሰድ እንዳለበት አስረድተዋል።

ማንኛውም ሰው አፍሪካ ወጣት ዜጎቿ በርካታ በመሆናቸው ከኮሮና ቫይረስ ጠንካራ ክንድ ትተርፋለች ብሎ የሚያስብ ከሆነ ከንቱ ምኞት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Ethiopia🇪🇹 vs #SouthAfrica🇿🇦

ነገ የሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ብሄራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን ጋር ይፋለማል።

ጨዋታው በውቢቷ ባህርዳር ከተማ ነው የሚካሄደው።

ለዚሁ ጨዋታ የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን አባላት ዛሬ 28/01/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ሲል ባህርዳር ደርሰዋል።

የሀገራችን ብሄራዊ ቡድን አባላት ዛሬ ከረፋዱ 3:30 ጀምሮ የመጨረሻ ልምምድ በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም አድርገዋል።

ከነገው ጨዋታ ጋር በተያያዘ የብሄራዊ ቡድናችን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ዛሬ አመሻሽ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሠጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቲክቫህ ኢትዮጵያ (ስፖርት) በኩል ደግሞ ተጨማሪ መረጃዎች ማግኘት ትችላላችሁ : https://t.iss.one/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x

#ምንጊዜም_ኢትዮጵያ❤️

@tikvahethsport @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NO_MORE በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን #NO_MORE የሚለውን አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ እንቅስቃሴን በዛሬው እለት ተቀላቅለዋል :: የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ በሚገኘው) የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለውን ጫና ለመቃወም እንደሆነ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ገልፀዋል :: የዛሬው ሰልፍ…
#SouthAfrica

ባለፈው ሳምንት በ22/11/2021 በአለም አቀፍ ደረጃ ለተጠራዉ #Nomore ንቅናቄ ምላሽ በመስጠት በበብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ኤንባሲ ደጃፍ ላይ ተቃውሞ ማሰማታቸው የሚታወስ ነው።

ዛሬ በድጋሚ በደቡብ አፍሪካ እና አካባቢዉ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሐይማኖት አባቶች፣ የሲቪክ መሐበር አመራሮች እና ሌሎች አፍሪካዊያን የኢትዮጵያ ወዳጆች የተሳተፉበት ሰልፍ ተካሂዷል።

በሰልፋ ላይ የዉጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ የዉስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባታቸዉን እንዲያቆሙ የተጠየቅ ሲሆን በተለይም የተሳሳቱና አላማቸዉ ሐገር ማወክን ያደረጉ ዘገባዎችን የሚያሰራጩ ሚዲያዎችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሰልፈኞቹ አሳስበዋል።

የዛሬውን ሰልፍ የተባበሩት ኢትዮጵያ መሀበረሰብ መሀበር ያዘጋጀው ሲሆን ማህበሩ ከዘር ከፖለቲካ ከሃይማኖት የፀዳ እና በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ሀገር ወዳዶች የመሠረቱት ማህበር ነው።

በዛሬው ሰልፍ ላይ ኤርትራውያንን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሐገራት ዜጎች ተሳትፈዋል።

FAYA(Tikvah-family )
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia
#SouthAfrica

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

ፕሬዜዳንቱ በመግለጫቸው በኦሚክሮን ቫይረስ ሳቢያ ለ4ኛ ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተመታቸው ደቡብ አፍሪካ ቁጥራቸው የበዛ ህሙማንን ለመቀበል ሆስፒታሎችዋን እያዘጋጀች መሆኑን አስታውቀዋል።

በደቡብ አፍሪካ ወደ 2 ሺህ 300 የነበረው እለታዊው የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቁጥር እየጨመረ መጥቶ ባለፈው ዓርብ ከ16 ሺህ በላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንት ራሞፎሳ ኮቪድ-19ን አስመልክቶ በየሳምንቱ በሚወጣው የዜና መጽሄት “በሃገሪቱ የኦሚክሮን ቫይረስ በአብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል መነጋገሪያ የሆነ ይመስላል” ካሉ በኋላ ሰዎች እንዲከተቡ አሳስበዋል፡፡

በቂ ክትባት መኖሩን ጠቅሰው ብዙ ሰዎች እየተከተቡ በሄዱ ቁጥር ብዙ የንግድ አገልግሎቶች እየተከፈቱ ይመጣሉ ማለታቸውን ቪኦኤ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#SouthAfrica

ከሰሞኑን በደቡብ አፍሪቃ " የ2024 ምርጫ " ተደርጎ ነበር።

በምርጫው ማንም አሸናፊ አልሆነም።

የዘንድሮ ምርጫ ገዢው ፓርቲ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት / ANC / 40.18 በመቶ ድምጽ በማግኘት ቀዳሚ ቢሆንም መንግሥት መመስረት የሚያስችለውን ድምጽ ግን አላገኘም።

ፓርቲው በ30 ዓመታት የመሪነት ታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አብዛኛውን የምክር ቤት መቀመጫ ተነጥቋል።

በዚህም መንግሥት ለመመስረት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች መጣመር ግድ ይለዋል።

ፓርቲው ምክር ቤቱ ካለው 400 መቀመጫዎች 159 ብቻ ነው ያሸነፈው።

የወቅቱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ መንግሥት ለመመስረት #ከተቃዋሚዎች ጋር እንደሚነጋገሩ አመልክተዋል።

በምርጫው 87 መቀመጫዎችን ያሸነፈው የመሃል ቀኝ ዘመሙ ዴሞክራሲያዊ ጥምረት (DA) ነው።

ከገዢው ፓርቲ ጋር ጥምር መንግሥት ለመመስረት የሚያስችል ንግግር ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

ሶስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የቀድሞ ፕ/ት ጃኮብ  ዙማ ፓርቲ MK ሲሆን ከገዢው ፓርቲ ጋር የመነጋገር ፍላጎት ቢኖረውም " ራማፎዛ ሥልጣን ላይ እያሉ ንግግር አላደርግም " ማለቱን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

በዘንድሮ ሀገር አቀፍ ምርጫ እጅግ በርካታ #ወጣቶች ድምፅ መስጠታቸው የተሰማ ሲሆን ገዢውን ፓርቲ የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቤት /ANC/ በድምጻቸው #ቀጥተውታል

ለዚህ ደግሞ  ፦
- የከፋ ሙስና
- የመልካም አስተዳደር ችግር
- ስራ አጥነት መፋፋት
- የወንጀል መባባስ ... ዋነኞቹ ምክንያቶች እንደሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethiopia