TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተቃውሞ ሰልፎች ፦

በ27 የተለያዩ ዓለም አቀፍ ከተሞች በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ ተደረገ።

በዓለማ አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያን በ27 ከተሞች የአሜሪካ መንግስት እና አንዳንድ የምእራባዊያንን መንግስታት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ያሉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና የሚቃወም ሰልፍ አድርገዋል።

በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ " ኋይት ሃውስ ቤተ መንግስት " በርካቶች የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍም ተካሂዷል። በዚሁ ሰልፍ ሽብረተኛ ተብሎ የተፈረጀውን ህወሓት መደገፍ የአፍሪካ ቀንድን እና መላ አህጉሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል አካሄድ መሆኑን የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር እንዲገነዘብ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።

በእስራኤልና እንግሊዝ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ብዛት ያለው ህዝብ በመሳተፍ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የሀሰት ዘገባ እና መንግስታት በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣ መንግስትን ለመጣል የሚያደርጉትን ጥረት ክፉኛ ኮንነዋል።

ሰልፈኞቹ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችን በመከፋፈል ላይ የተመሰረተ ፖሊሲዋን እንድታርም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያን እጅ ለመጠመዘዝ የሚደረግ ሙከራ የአፍሪካን ነጻነት መግፈፊያ ዳግም የቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ አካል በመሆኑ “#NoMore” በሚለው መሪ መፈክራቸው ተቀባይነት እንደሌለው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ሶሻል ሚዲያ

@tikvahethiopia
#NO_MORE

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን #NO_MORE የሚለውን አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ እንቅስቃሴን በዛሬው እለት ተቀላቅለዋል ::

የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ በሚገኘው) የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለውን ጫና ለመቃወም እንደሆነ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ገልፀዋል ::

የዛሬው ሰልፍ የተጠራው በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሲሆን የሰልፉ አላማም #NOMORE በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ በተመሳሳይ ቀን የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ አንዱ አካል ነው በማለት የሰልፉ አስተባባሪዎች አስታውቀዋል ::

እዚህ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ ከጠዋቱ ጀምሮ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ግዛቶች በተዘጋጁ ትራንስፖርቶች ወደ ጆሃንስበርግ ያቀኑ ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያን እና አንዳንድ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት በርካታ ዜጎች በሰልፉ ላይ ተሳትፈዋል ::

በሰልፉ ላይ የተኙት በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በአሜሪካ መንግስት እና በምዕራቡ አለም ሚዲያዎች ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞ አሰምተዋል ::

በተጨማሪ :-

November 29 ደግሞ በተባበሩት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር አስተባባሪነት የተጠራ የተቃውሞ ሰልፍ በድጋሚ በደቡብ አፍሪካ እንደሚኖር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ::

ፎቶ ፦ የኛ ሰው ሚዲያ እና ከማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የተሰባሰበ

FAYA (Tikvah-family )
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia
የተቀጣጠለው የ #NoMore ንቅናቄ ፦

አሜሪካንን ጨምሮ ሌሎች የምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና በሀገራቱ ሚዲያዎች የሚሰራውን የኢትዮጵያን ህዝብ የማሸበር የሀሰተኛ መረጃ ዝውውር በመቃወም በተለያዩ ሀገራት #NoMore በሚል በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኤርትራ ዜጎች የተቀውሞ ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

ትላንት እሁድ እንዲሁም ቅዳሜ በአይርላንድ (ደብሊን ፣ ኮርክ፣ ጋልዌይ) ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ኖርዌይ፣ ጣልያን የተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል።

በተጨማሪ በአሜሪካ ነጩ ቤተ መንግስት መቀመጫ ዋሽንግቶን ዲሲ ትላንት የተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ የውሥጥ ጉዳዮች እጇን እንድትሰበስብና በሀገሪቱ ያሉት ሚዲያዎች በሀሰተኛ መረጃ ህዝብን ከማሸበር እንዲታቀቡ ተጠይቋል።

#NoMore ዘመቻ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያው ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች እየተሳተፉበት ሲሆን ከነዚህ መካከል በጉልህ የሚጠቀሱት የቻይና ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው።

የቻይና መንግሥት ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ ዌንቢን ፣ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሁዋን ቹኒንግ፣ በሊባኖስ የቻይና ኤምባሲ ኮንሱላር ካኦ ይ የ #NoMore በቃ ንቅናቄ ድጋፋቸውን በይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ያንፀባሩቁ ናቸው።

ባለስልጣናቱ፥ " O ዴሞክራሲ፤ በስምሽ ስንት ወንጀሎች ተፈጸመ "ብለዋል።

ባለስልጣናቱ ከመልእክታቸው ጋር ያያዙት ምስል " ለUS ኢምፔሪያሊዝም ቀጣዩ ማን ነው?" የሚል ሲሆን አፍጋኒስታን፤ ኢራቅ፤ ሊቢያ እና የመን ወድመዋል፤ ማነው ተረኛው? "ሲልም ያጠይቃል።

ከፖለቲካ ሰዎች በተጨማሪም ሴኔጋላዊ-አሜሪካዊው ዓለም አቀፍ ድምፃዊ ኤኮን #NoMore ንቅናቄን ተቀላቅሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NO_MORE በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን #NO_MORE የሚለውን አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ እንቅስቃሴን በዛሬው እለት ተቀላቅለዋል :: የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ በሚገኘው) የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለውን ጫና ለመቃወም እንደሆነ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ገልፀዋል :: የዛሬው ሰልፍ…
#SouthAfrica

ባለፈው ሳምንት በ22/11/2021 በአለም አቀፍ ደረጃ ለተጠራዉ #Nomore ንቅናቄ ምላሽ በመስጠት በበብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ኤንባሲ ደጃፍ ላይ ተቃውሞ ማሰማታቸው የሚታወስ ነው።

ዛሬ በድጋሚ በደቡብ አፍሪካ እና አካባቢዉ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሐይማኖት አባቶች፣ የሲቪክ መሐበር አመራሮች እና ሌሎች አፍሪካዊያን የኢትዮጵያ ወዳጆች የተሳተፉበት ሰልፍ ተካሂዷል።

በሰልፋ ላይ የዉጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ የዉስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባታቸዉን እንዲያቆሙ የተጠየቅ ሲሆን በተለይም የተሳሳቱና አላማቸዉ ሐገር ማወክን ያደረጉ ዘገባዎችን የሚያሰራጩ ሚዲያዎችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሰልፈኞቹ አሳስበዋል።

የዛሬውን ሰልፍ የተባበሩት ኢትዮጵያ መሀበረሰብ መሀበር ያዘጋጀው ሲሆን ማህበሩ ከዘር ከፖለቲካ ከሃይማኖት የፀዳ እና በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ሀገር ወዳዶች የመሠረቱት ማህበር ነው።

በዛሬው ሰልፍ ላይ ኤርትራውያንን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሐገራት ዜጎች ተሳትፈዋል።

FAYA(Tikvah-family )
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Video : የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትላንት ለስራ ጉብኝት በሄዱበት ካንሳስ ከተማ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዜዳንት ትራምፕ ደጋፊዎች ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።

የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የሚያካሂደውን እንቅስቃሴ አጥብቀው ተቃውመዋል።

ተቃዋሚዎቹ ፥ " የጆ ባይድን አስተዳደር ሽብርተኛውን የህወሃት ቡድን የመደገፍ እንቅስቃሴውን ሊያቆም ይገባል፣ የኢትዮጵያን ዴሞክራሲ ለማጥፋት የሚያካሄደው ጣልቃ ገብነትም ሊቆም ይገባል #NoMore” ብለዋል።

በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ፣ ገለልተኛና ነጻ መንግስት አለን ጣልቃ ገብነቱ እንዲቆም እናሳስባለን ሲሉም የሰልፉ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

የትራምፕ ባንዲራ የያዙ ወደ ደርዘን የሚጠጉ ሰዎችም ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን ፤ በፕሬዚዳንት ባይደን በደቡብ ድንበር አያያዝ፣ አሜሪካ ከአፍጋኒስታን መውጣት እና በ COVID-19 የደህንነት ጥንቃቄዎች ጉዳይ ተቃውሞ አሰምተዋል።

Video Credit : KMBC

@tikvahethiopia