TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሪፖርት

Afar Region | Conflict Situation

የአፋር ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ህወሓት በክልሉ ላይ በፈፀመው ወረራ በ4 ዞኖች (21 ወረዳዎች) 377,000 ሰዎች መፈናቀላቸውን እና በአሁን ሰዓት በክልሉ 1.3 ሚሊዮን ህዝብ ለችግር ተጋልጧል ሲል አሳውቋል።

- በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከ376,502 በላይ ተፈናቃዮች አሉ።

- ከ205,178 በላይ ሰዎች ከአውሲራሱ፣ ከብላቲራሱ፣ ከፋንቲራሱ እና ከሃሪራሱ ዞኖች አዲስ ተፈናቃዮች ናቸው።

- ከፍተኛ ቁጥር ያለው አዲስ ተፈናቃይ የተመዘገበው ከጭፍራ (42156)፣ አዳአር (33,696)፣ ዳዌ (30,000)፣ ሃዳሌላ (21,000)፣ ሳማሮቢ (18,000) እና ተላሌክ (23,288) ነው። (እኤአ በህዳር 2021)

- መፈናቀሉ አሁንም በአውሲራሱ፣ ቀብላቲራሱ፣ ፋንቲ ራሱ እና ሃሪራሱ ዞኖች እንደቀጠለ ነው።

- በአጠቃላይ በግጭት ምክንያት የተከሰተው ሰብአዊ ቀውስ በአፋር ክልል 21 ወረዳዎች ውስጥ ወደ 1.3 ሚሊዮን ሰዎችን ለችግር አጋልጧል።

(የአፋር የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል)

@tikvahethiopia
#Update

በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ግጭት አውድ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ የተቋቋመው የሚኒስቴሮች ግብረ-ሀይል ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

ግብረ ኃይሉ ዛሬ በይፋ ስራ መጀመሩን አሳውቋል።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
" የሰላዮች ልዑካን እንጂ ታዛቢዎች አልነበሩም " - ኒኮላስ ማዱሮ

በዓለም ላይ አነጋገሪ ከሚባሉት የሀገራት መሪዎች አንዱ የሆኑት የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ትላንት በሀገራቸው ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ቀርበው የሰጡት ቃል መነጋገሪያ ሆኗል።

በቬንዝዌላ ባለፈው ሳምንት ክልላዊ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን ፕሬዜዳንት ማዱሮ ይህንን ምርጫ ለመታዘብ የተላኩትን የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን አባላትን “ሰላዮች” ሲሉ ጠርተዋቸዋል።

የማዱሮ ይህን ውግዘት ያሰሙት ታዛቢዎቹ በአራት አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቃዋሚ እጩዎች የተሳተፉበት ምርጫ ካለፉት አመታት በተሻለ ሁኔታ የተካሄደ ነበር ካሉ በኃላ ነው።

ይሁን እንጂ በምርጫው በአስተዳደራዊ ምክንያቶች በእጩዎች ላይ የዘፈቀደ እገዳዎች፣ የምርጫ ማእከላት መዘግየቶች እና "በዘመቻው ውስጥ የመንግስት ሀብቶችን መጠቀምን" በተመለከተ ያሉ ክፍተቶችን ታዛቢዎቹ አንስተዋል።

የገዢው ሶሻሊስት ፓርቲ መሪ ማዱሮ " የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች የምርጫውን ሂደት ለማበላሸት ፈልገው አልቻሉም " ብለዋል ።

ማዱሮ ፥ " የሰላዮች ልዑካን - ታዛቢዎች አልነበሩም! በነጻነት በሀገሪቱ ዙሪያ እየተዘዋወሩ የሀገሪቱን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ህይወት እየሰለሉ ነበር" ሲሉ ተደምጠዋል።

በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በተላለፈው ስርጭት ፕሬዜዳንት ማዱሮ ምርጫው "እንከን የለሽ፣ ቆንጆ" ነበር ብለዋል።

የታዛቢ ልዑኩ ለፕሬዜዳንቱ ውግዘት ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠም።

@tikvahethiopia
" በአንዳንድ አካባቢዎች የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ አምራች ኢንዱስትሪዎችን አይመለከትም " - የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ አምራች ኢንዱስትሪዎችን እንደማይመለከት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ ገለጸ።

አሁን ላይ ባለው ሀገሪቱን የማዳን ግዳጅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቢታወጅም በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ገደቡ ተግባራዊ አይደረግም ተብሏል።

ይህ የሆነው በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ ገደቡን ተግባራዊ ማድረግ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ጫና ስለሚያሳድር እንዲሁም ኢንዱስትሪዎችን ወደ ኪሣራ ስለሚያስገባቸው መሆኑ ተገልጿል።

የተቀመጠው ሰዓት እላፊ ገደብ ሁሉንም አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደማይመለከት ታውቆ ኢንዱስትሪዎቹ አስፈላጊ የሆነ የራሳቸውን የጥበቃ ስርዓት ከወትሮው በተለየ መልኩ አጠናክረው መደበኛ ስራቸውን በተለመደው ሁኔታ እንዲቀጥሉ ተጠቁሟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NO_MORE በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን #NO_MORE የሚለውን አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ እንቅስቃሴን በዛሬው እለት ተቀላቅለዋል :: የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ በሚገኘው) የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለውን ጫና ለመቃወም እንደሆነ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ገልፀዋል :: የዛሬው ሰልፍ…
#SouthAfrica

ባለፈው ሳምንት በ22/11/2021 በአለም አቀፍ ደረጃ ለተጠራዉ #Nomore ንቅናቄ ምላሽ በመስጠት በበብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሐገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ኤንባሲ ደጃፍ ላይ ተቃውሞ ማሰማታቸው የሚታወስ ነው።

ዛሬ በድጋሚ በደቡብ አፍሪካ እና አካባቢዉ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሐይማኖት አባቶች፣ የሲቪክ መሐበር አመራሮች እና ሌሎች አፍሪካዊያን የኢትዮጵያ ወዳጆች የተሳተፉበት ሰልፍ ተካሂዷል።

በሰልፋ ላይ የዉጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ የዉስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባታቸዉን እንዲያቆሙ የተጠየቅ ሲሆን በተለይም የተሳሳቱና አላማቸዉ ሐገር ማወክን ያደረጉ ዘገባዎችን የሚያሰራጩ ሚዲያዎችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሰልፈኞቹ አሳስበዋል።

የዛሬውን ሰልፍ የተባበሩት ኢትዮጵያ መሀበረሰብ መሀበር ያዘጋጀው ሲሆን ማህበሩ ከዘር ከፖለቲካ ከሃይማኖት የፀዳ እና በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ሀገር ወዳዶች የመሠረቱት ማህበር ነው።

በዛሬው ሰልፍ ላይ ኤርትራውያንን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሐገራት ዜጎች ተሳትፈዋል።

FAYA(Tikvah-family )
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፥ የኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዪ ሀገራትን የገንዘብ ኖቶች ለማባዛት በዝግጅት ላይ የነበሩ የካሜሮን እና የኮትዲቭዋር ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

ግለሰቦቹ በጋራ በመሆን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አማዶ የእንግዳ ማረፊያ ውስጥና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አዲስ ብራይት የእንግዳ ማረፊያ ውስጥ የገንዘብ ኖቶችን በማዘጋጀት ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።

የግለሰቦቹን ህገወጥ እንቅስቃሴ ሲከታተል የነበረዉ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተጠርጣሪዎቹን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥቆማ በመስጠት ነው በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ ያስደረገው።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሲዉሉ ፦
- 107 ሺህ 330 ትክክለኛ የኢትዮጵያ ብር፣
- የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣
- ባለ 200 በርካታ ፎርጅድ የኢትዮጵያ ብሮች፣
- ዱቄት መሳይ ኬሚካል፣
- ፈሳሽ ኬሚካሎች፣
- የወረቀት መቁረጫ፣
- በርካታ ቾክ፤ በርካታ ወረቀት፣
- 9 ሞባይል ስልኮች እና ሌሎች ቁሳቁሶች መያዛቸዉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

Credit : #ENA

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 10 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 4,753 የላብራቶሪ ምርመራ 84 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 299 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#Russia

የዓለም ሃያላን ሀገራት የላቀ የጦር መሳሪያ ለመስራት እየተሯሯጡ በሚገኙበት በዚህ ሰዓት ሩሲያ ሌላኛውን የተሳካ ዚርኮን ሃይፐርሶኒክ ኩሩዝ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን ዛሬ አስታውቃለች።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሙከራውን በማጠናቀቅ ተልዕኮ ከአድሚራል ጎሮሽኮቭ የጦር መርከብ የተወነጨፈው የዚርኮን ሚሳኤል 400 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ኢላማውን በተሳካ ሁኔታ እንደመታ ገልጿል።

ሩሲያ፣ አሜሪካ፣ ቻይና እና ፈረንሳይ ተመሳሳይ ሙከራ ሲያደርጉ ነው የቆዩት።

የሩሲያ ፕሬዜዳንት ፑቲን እኤአ የካቲት 2019 በሰጡት መግለጫ በባህር ሆነ በምድር በ1000 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለ ኢላማ መምታት የሚችል መሳሪያ እየተገነባ መሆኑ አስታውቀው ነበር።

የዛሬው የሩሲያ ሙከራ የመጣው ቻይና ባለፈው ሃምሌ ያደረገችው ሙከራ ከድምፅ ፍጥነት በላይ 5 ጊዜ እጥፍ የሚፈጥን መሆኑን የምዕራባውያን ምንጮች ከዘገቡ በኃላ መሆኑን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ እና ዘ ሞስኮ ታይምስ ዘግበዋል።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መልዕክታቸውን ያስተላለፉበት ቦታ።

@tikvahethiopia