TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BREAKING

" ከፓርቲው ፕሬዝዳንት (የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ) ጀምሮ ወደ ግንባር ሄደን እኛ መስእዋት ሆነን ኢትዮጵያን ለማዳን ወስነናል " - ዶ/ር አለሙ ስሜ

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክሮ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት በውስጥም በውጭም የተከፈተባት ጥቃት የተቀናጀ መሆኑን ገልጾ፤ ሽብረተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህወሓትና ግብረአበሮቹ በኢትዮጵያ እስካሁን ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂ ናቸው፤ ተጠያቂነቱም ይረጋገጣል ብሏል።

ውጊያው አሁን ካለው የበለጠ ኪሳራ እንዳያደርስ ከነገ ጀምሮ ሁሉም የፀጥታ አካላት ወደተለየ እርምጃ እንደሚሸጋገሩ ተገልጿል።

ዶ/ር አብርሃም በላይ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ፥ " መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፀጥታ አካላት በቅንጅት ተዘጋጅተው ወደተለየ እርምጃ ይገባሉ ፤ ይህ ምንም ጥያቄ የለውም፤ ለውጥ ይኖራል " ብለዋል።

በተጨማሪ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በስብሰባው ላይ ከዚህ በኃላ ሁሉም አመራር በየጦር ግንባር እየተገኘ የህልውና አደጋውን ለመቀልበስ ከፊት ሆኖ እንደሚሰለፍ አሳውቋል።

ዶክተር አለሙ ስሜ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል፥ " የብልፅግና ስራ አስፈፃሚ ከፓርቲያችን ፕሬዜዳንት (ከሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር) ጀምሮ ወደ ግንባር መግባት እንዳለብን በእርግጥ ሌሎች ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ የተወሰነ የልማቱን ስራ ፣ የዲፕሎማሲውን ስራ፣ ከቢሮ የሚሰራውን ስራ እንድንሰራ ሌሎች ከዚህ ውጭ ያለን ከፓርቲያችን ፕሬዜዳንት ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጀምሮ ወደ ግንባር ሄደን እኛ መስእዋት ሆነን ኢትዮጵያን ለማዳን ወስነናል፤ ይሄንንም በተግባር ከነገ ጀምሮ በመንቀሳቀስ የምናሳየው ይሆናል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#BREAKING

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከነገ ጀምሮ ወደ ግንባር እንደሚዘምቱ አሳወቁ።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ዛሬ ምሽት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰራጩት ፅሁፍ ኢትዮጵያ አሁን እያደረገችው ያለው ትግል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግል ነው ብለዋል።

"ትግሉ ልጆቻችን ሀገር እንዲኖራቸው የሚደረግ ትግል ነው። ልጆቻችን ክብርና ነጻነትን ለብሰው፣ በዓለም አደባባይ በኩራት ቀና ብለው እንዲሄዱ የሚደረግ ትግል ነው፤ በዓለም ላይ በክብር የምንጠራበት ስም እንዲኖረን የሚደረግ ትግል ነው። መኖር ወይም አለመኖራችንን የሚወስን ትግል ነው። ያለ ጥርጥር ግን እናሸንፋለን። ኢትዮጵያን ጠርቶ መሸነፍ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው" ነው ሲሉ ገልፀዋል።

"ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው" ያሉት ዶ/ር ዐቢይ፥ " ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ" ብለዋል።

ዶ/ር ዐቢይ፥ "የእኛ መዝመት የሚፈጥረውን ክፍተት ከግንባር የቀሩት በሙሉ ዐቅማቸው ሸፍነው ይሠራሉ" ያሉ ሲሆን "በግንባር ያልተሰለፉ የክልልና የፌደራል አመራሮች ከመቼውም ጊዜ በላይ የልማትና አስተዳደር ሥራዎችን በሙሉ ዐቅማቸው ይከውናሉ" ብለዋል።

"ጎልማሶች በዘዴና በብልሃት አካባቢያቸውን እየጠበቁ፣ አረጋውያን እናትና አባቶች በጸሎት እየተጉ፣ ሁሉም ሰው ተባብሮ የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያረጋግጣል" ያሉት ዶ/ር ዐቢይ "ከዚህ በኋላ በሩቁ ተቀምጠን ተቺና አራሚ የምንሆንበት ጊዜ አይደለም። መደረግ ያለበትን እኛው ራሳችን እናድርገው። ለኢትዮጵያ ከእኛ በላይ ከየትም አይመጣም" ሲሉ ገልፀዋል።

* ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#Update

የአብኑ አመራር ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር አብረው እንደሚዘምቱ አሳወቁ።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መከላከያን በግንባር ሆነው ለመምራት ከነገ ጀምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እንደሚዘምቱ ካሳወቁ በኃላ የአብን አመራር እና የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንደሚዘምቱ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ፥ " ለአገር አንድነትና ለሕዝብ ደኅንነት የምንሰስተው ሕይወት የለምና እኛም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንዘምታለን። ሕዝቤ ሆይ ተከተል " ሲሉ ነው በገፃቸው ላይ ያሰፈሩት።

@tikvahethiopia
" አዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በአስተማማኝ ሰላም ላይ ይገኛል " - ዶ/ር ቀነዓ ያደታ

ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ላደረጉ የአፍሪካ የኤዢያና ፓስፊክ ሀገራት አምባሳደሮች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ተደረገ።

በመድረኩ ላይ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ፤ የከተማዋን ሰላምና መረጋጋት ለማስቀጠል የከተማው የፀጥታ ሀይል ከፌዴራል ፖሊስ ፣ ከሪፐብሊካን ጥበቃ ሃይል ፣ከኦሮሚያ ፖሊስ እና ከሌሎች የፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ጋር በመሆን በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል።

ከ27 ሺህ በላይ ወጣቶች እንዲሁም ህዝባዊ ሰራዊት የአካባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታን የሚያስከብሩ አደረጃጀቶች እስከ ታችኛው የብሎክ መዋቅር ድረስ በመደራጀት ወደ ስራ መግባታቸውን ገልፀው በአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ በአስተማማኝ ሰላም ላይ መሆኗን አስረድተዋል።

በምዕራባዊያን ሚዲያዎች የሚነዙትን የፕሮፖጋንዳ እና የሽብር ወሬ መሬት ላይ ካለዉ የከተማዋ የተረጋጋ ሰላም ጋር ፍፁም የሚጋጭ በመሆኑ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባው ዶ/ር ቀነዓ ያደታ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መረጃውን ያገኘ ነው ከAAPS ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል ዛሬ እና ነገ ይመሰረታል። 5 ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ ሆነው የሚያቋቁሙት የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ዛሬና ነገ በሚካሄዱ መርሀ ግብሮች 11ኛው ክልል ሆኖ በይፋ ይመሰረታል፡፡ ለክልሉ ምስረታ ከአምስቱ ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ የተውጣጡ የሥራ ሃላፊዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ ከትላንት ምሽት ጀምራ የክልል እና የፌደራል እንግዶች ለክልሉ…
#Update

ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በሀገራችን 11ኛው የክልል መንግሥት በይፋ ይመሰረታል።

11ኛው የክልል መንግሥት ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በቦንጋ ከተማ ይመሰረታል።

በቦንጋ እየተካሄደ በሚገኘው የክልል ምስረታ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ እንግዶችና ከ6ቱም መዋቅሮች የተገኙ የህዝብ ተወካዮች፣ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የሃይማኖት አባቶችና ምሁራን እንዲሁም ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

#SRTA

@tikvahethiopia
" እስካሁን ወደላሊበላና ኮምቦልቻ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ የጠየቀ አንድም የዓለም አቀፍ ተቋም የለም "– አቶ ምትኩ ካሳ

የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ላሊበላ እና ኮምቦልቻ አየር ማረፊያዎች የሰብዓዊ ድጋፍ በረራ ፍቃድ ቢሰጥም እስካሁን ድረስ ድጋፍ ለማድረስ የጠየቀ አንድም የዓለም አቀፍ ተቋም እንደሌለ የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ አሳወቁ።

ኮሚሽነሩ ይህ ያሳወቁት ለኢፕድ በሰጡት ቃል ነው።

" በአካባቢዎቹ ለአምስት ወራት ያህል ድጋፍ ያላገኙና እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች አሉ" ያሉት አቶ ምትኩ ካሳ፥ " መንግሥት ሁኔታዎችን ሲያመቻች ገብተው ሰብዓዊ ድጋፍ የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት ወደተግባራዊ እርምጃ አልገቡም" ብለዋል።

በሰሜን እና ደ/ወሎ አካባቢዎች ከተፈናቀሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ባለፉት ወራት እርዳታ ሳይቀርብላቸው የቆዩ ከ4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች እንደሚገኙ ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል።

ዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅቶች ወደአካባቢዎቹ እርዳታ ጭነው ቢሄዱና ሰብአዊ ድጋፍ ቢያቀርቡ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን መታደግ የሚቻልበት አማራጭ መኖሩንም አሳውቀዋል።

የዓለም አቀፍ ተቋማት ጦርነት እየተካሄደባቸው በማይገኙ ቦታዎች ላይ ገብተው ድጋፍ የማቅረብ ኃላፊነት አለባቸው ያሉት አቶ ምትኩ የሚሠሩት ሥራ የሰብዓዊነት ዓላማ እስካለው ድረስ የእራሳቸውን መለያ እና አርማ አድርገው ድጋፍ ለማድረግ ወደየስፍራዎቹ መግባት ይችላሉ ሲሉ ገልፀዋል።

አማራና አፋር ክልሎች ያለው የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች ድጋፍ የሚጠበቀውን ያህል እንዳልሆነ የገለፁት አቶ ምትኩ፥ "ችግሩን ለመፍታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት ከየተቋማቱ ጋር ተደጋጋሚ ውይይት አድርገናል። በዚህ መነሻነት ለውጦች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል" ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ በይፋ ተመስርቷል። 11ኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል ህገ መንግስትም በምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል። የምክር ቤቱ አባላትም ቃለ መሀላ ፈፅመዋል። ምንጭ፦ የዳውሮ ዞን የመን/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው   @tikvahethiopia
#Update

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስራ ቋንቋ አማርኛ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።

የዞን መዋቅሮች ደግሞ የራሳቸውን ቋንቋ እንደሚገለገሉ ተገልጿል።

የስልጣን እርከን ፍትሃዊነትን በተመለከተ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ፣ አፈጉባኤየክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳትና የብሄረሰብ ምክር ቤት አፈጉባኤ በአንድ ጊዜ ከተመሳሳይ ብሄር እንዳይሆኑ ተቀምጧል።

የስልጣን ገደብም የተቀመጠ ሲሆን÷ በተለያየ ምክነያት ከጊዜያቸው ቀድሞ ሊለቁ መቻላቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ረጅም ጊዜ ቢቆዩ ከ10 ዓመት እንዳይበልጥ ተመላክቷል።

የብዝሓ ማዕከል ወይንም ዋና ከተማ እንዲኖርም ተደንግጓል፣ የትኞቹ ከተሞች እንደሚሆኑ በዝርዝር ህግ በም/ ቤት እንዲወሰንም በህገ መንግስቱ መጠቀሱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopoa
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ ወንድሙ ኩርታ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና አፈጉባኤ ፤ ወይዘሮ ገነት መንገሻ ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል። ሁለቱም አፈ ጉባኤዎች ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። @tikvahethiopia
#Update

ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል ም/ርዕስ መስተዳደር ሆነው ተሾሙ።

ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ በክልልና በሀገር ደረጃ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች የሰሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የውሃና መስኖ ሚንስቴር ዴኤታ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።

ም/ርዕስ መስተዳደሩ በጉባኤው አባላት ፊት ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

@tikvahethiopia