TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተቃውሞ ሰልፎች ፦

በ27 የተለያዩ ዓለም አቀፍ ከተሞች በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገ ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ ተደረገ።

በዓለማ አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያን በ27 ከተሞች የአሜሪካ መንግስት እና አንዳንድ የምእራባዊያንን መንግስታት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ያሉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና የሚቃወም ሰልፍ አድርገዋል።

በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ " ኋይት ሃውስ ቤተ መንግስት " በርካቶች የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍም ተካሂዷል። በዚሁ ሰልፍ ሽብረተኛ ተብሎ የተፈረጀውን ህወሓት መደገፍ የአፍሪካ ቀንድን እና መላ አህጉሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል አካሄድ መሆኑን የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር እንዲገነዘብ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።

በእስራኤልና እንግሊዝ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ብዛት ያለው ህዝብ በመሳተፍ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የሀሰት ዘገባ እና መንግስታት በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣ መንግስትን ለመጣል የሚያደርጉትን ጥረት ክፉኛ ኮንነዋል።

ሰልፈኞቹ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችን በመከፋፈል ላይ የተመሰረተ ፖሊሲዋን እንድታርም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያን እጅ ለመጠመዘዝ የሚደረግ ሙከራ የአፍሪካን ነጻነት መግፈፊያ ዳግም የቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ አካል በመሆኑ “#NoMore” በሚለው መሪ መፈክራቸው ተቀባይነት እንደሌለው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ሶሻል ሚዲያ

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል ዛሬ እና ነገ ይመሰረታል።

5 ዞኖችና አንድ ልዩ ወረዳ በጋራ ሆነው የሚያቋቁሙት የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ዛሬና ነገ በሚካሄዱ መርሀ ግብሮች 11ኛው ክልል ሆኖ በይፋ ይመሰረታል፡፡

ለክልሉ ምስረታ ከአምስቱ ዞኖች እና አንድ ልዩ ወረዳ የተውጣጡ የሥራ ሃላፊዎች እና የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

ከትላንት ምሽት ጀምራ የክልል እና የፌደራል እንግዶች ለክልሉ ምስረታ ቦንጋ ከተማ እየገቡ ይገኛሉ።

በነገው እለት የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ህገ መንግስት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዕለቱ የአዲሱ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይመረጣል፡፡

በተያያዘ ልዩ ልዩ አዋጆች እና ህጎች ይፀድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የከፋ ዞን መንግስት ኮምዩኒኬሽን ሀላፊ አቶ መስፍን ተስፋዬ አሳውቀዋል።

Credit : ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ወታደሮች ትልካለች ?

" ከዚህ ክፉ ሀሳብ ቢታቀቡ ይሻላቸዋል " - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ከሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የጆ ባይደን አድተዳደር በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ሁኔታ ጋር በተያየ ወደ ኢትዮጵያ ወታደሮችን ሊልክ ነው ፤ ወታደሮችን ሊያስገባ ነው የሚሉ የተለያዩ መረጃ ሲናፈሱ ነበር።

በዚህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን አስተያየት የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ አሜሪካ ወታደር ታስገባለች ለሚባለው ጉዳይ ለምን ? የሚለው ጥያቄ ምላሽ የለውም ብለዋል።

አምባሳደሩ ፥ " በዚህ ሰዓት ኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ ጫና ለማሳረፍ ፣ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያሳስባቸው ምንም ነገር የለም፤ የአሜሪካን ጥቅም ህዝብም የሀገርን ጥቅም የሚጠብቅ አይደለም። ሁለቱንም ሀገሮች ግንኙነት ቁመናን የሚለካም አይደለም። እብደት ካልሆነ በስተቀር " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው " ህዝባችን እያለ ያለው የኛ ጉዳይ ፣ የኛ ህልውና ፣ የኛ ነፃነት ሁሉ ነገር በእጃችን ነው ያለው እንጂ በእነሱ እጅ አይደለም ያለው ፣ በሌሎች እጅ አይደለም ያለው፤ በማንም እጅ ሊሆን አይችልም። ይህንን ህዝቡ በአንድ ትልቅ ድምፅ እየተናገረ ነው " ብለዋል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሰላሙን ጉዳይ በተመለከተም ፥ "ይሄ ሀገር ተጭኖበት ካልሆነ በስተቀር ለሰላም ሁል ጊዜ የቆመ ህዝብ እና መንግስት ነው ፤ መንግስት ለሰላም ከአንዴም ሁለቴ እርምጃዎችን የወሰደበት ሁኔታ ነው ያለው። መጥተው እዚህ ስለ ሰላም የሚያወሩትም ሰዎች ስለሰላም ምንም አዲስ ነገር እየነገሩን አይደለም ይሄ የህዝባችን ፍላጎት ነው እሱ። ህዝባችን ለምንድነው የሚጭኑብን እያለ ነው፤ ግን ከህልውናችን በላይ ምንም ነገር የለም የሚል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

አምባሳደር ዲና ፤ [ አሜሪካኖቹ ወደ ኢትዮጵያ ወታደር የማስገባት ] እርምጃ ባይገቡበት ይሻላል ያሉ ሲሆን እነሱ ገብተው ሰላም የፈጠሩበት ሀገር ብዙም የለም ብለዋል።

" እዚህ በአካባቢያችን ሊቢያን፣ የመንን ፣ ሶሪያን ፣ ኢራቅን ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና ራቅ ያሉ የኤዥያ ሌሎች ሀገራትን አይተናልና የሚፈጥሩት ነገር የለም። ይልቁን የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነትና የቆየ ግንኙነት ማበላሸት ነው የሚሆነው ይሄን መላልሰው ቢያስቡበት እና ከዚህ ክፉ ሀሳብ ቢታቀቡ ይሻላል " ብለዋል አምባሳደር ዲና።

@tikvahethiopia
ኤጀንሲው የሰነድ ማረጋገጫ ማህተም አሰራርን ቀየረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ እየተበራከተ የመጣውን ሰነድ አስመስሎ የመስራት ወንጀል ለመቀነስ ኤጀንሲው በሚሰጣቸው የልደት፣ የጋብቻ ፣ የፍቺ ፣ የያላገባ እንዲሁም ሌሎች ማስረጃዎች አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረውን የማረጋገጫ አሰራር በዘመናዊ አሰራር በመተካት ፎርጀሪ እያደረሰ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳት ለመቀነስ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ተቋሙ በዋና መስሪያ ቤት የሚሰጠውን ለፖስፖርት አገልግሎት፣ ለውጭ ሃገራት የቪሳ ጥያቄ ፣ ለተለያዩ የውጭ እና የሃገር ውስጥ ጉዳዮች የሚውሉ ማስረጃዎች የሚረጋገጥበትን የቀድሞ የማህተም አሰራር በማስቀረት በውጭ ሃገር አሰርቶ ባስገባው ዘመናዊ የሆሎግራም ማረጋገጫ አሰራር ከዛሬ ህዳር 13 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመተካት ተግባራዊ ያደርጋል።

ይህ አሰራር ከፖስፖርት እና ከውጭ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በየቦታው ተመሳስሎ በመስራት ለማለፍ የሚሞከሩ ሌብነቶች ኤጀንሲውን እንዳያልፉ እገዛ የሚያደርግ እንደሚሆን ታምኖበታል።

በተያዘው በጀት ተቋሙ የሚሰጣቸውን ሰርተፍኬቶች የደህንነት ደረጃ ከፍ ለማድረግ አዲስ የPersonalization ቴክኖሎጂ ባላቸው ፕሪንተሮች ለመተካት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ምንጭ፦ ወ/ኩ/ም/መ/ኤጀንሲ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ዴንማርክ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ርዳታ ተጨማሪ 4.5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች።

አዲሱ አስተዋፅኦ የኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ፈንድ በኢትዮጵያ በጣም ለተቸገሩ ሰዎች ህይወት አድን ሰብአዊ ርዳታ ለመስጠት የሚረዳ ነው።

በሌላ በኩል የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርገውን የ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚቀጥል ዛሬ ገልጿል።

USAID በአፋር፣ በአማራ፣ በትግራይ ክልሎችና በሌሎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች የህይወት አድን ሰብአዊ ድጋፉን እንደሚቀጥል አሳውቋል።

አሜሪካ በጤናና በትምህርት በኢትዮጵያ የምታደርገው ኢንቨስትመንት እንደሚቀጥል አሳውቃለች።

ከኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ጋር እየተሰጠ ላለው ምላሽ የምናደርገው ድጋፍና የኮቪድ ክትባት ልገሳውም ይቀጥላል ብላለች። ከግጭቱ በኋላ ሀገሪቷ እንድታገግም የያዝነው ዕቅድ ሁሉ አይቆምም ፣ ይቀጥላል ስትልም ገልጻለች።

የአሜሪካ ኤምባሲ ክፍት ነው ፣ የአሜሪካ ህዝብም የኢትየጵያን ህዝብ በሚያስፈልገው ሁሉ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቃለች።

ምንጭ፦ Embassy of Denmark in Ethiopia & US EMBASSY AA

@tikvahethiopia
#NO_MORE

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን #NO_MORE የሚለውን አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ እንቅስቃሴን በዛሬው እለት ተቀላቅለዋል ::

የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ (ፕሪቶሪያ በሚገኘው) የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረገች ያለውን ጫና ለመቃወም እንደሆነ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ገልፀዋል ::

የዛሬው ሰልፍ የተጠራው በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሲሆን የሰልፉ አላማም #NOMORE በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ በተመሳሳይ ቀን የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ አንዱ አካል ነው በማለት የሰልፉ አስተባባሪዎች አስታውቀዋል ::

እዚህ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ ከጠዋቱ ጀምሮ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ግዛቶች በተዘጋጁ ትራንስፖርቶች ወደ ጆሃንስበርግ ያቀኑ ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያን እና አንዳንድ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት በርካታ ዜጎች በሰልፉ ላይ ተሳትፈዋል ::

በሰልፉ ላይ የተኙት በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በአሜሪካ መንግስት እና በምዕራቡ አለም ሚዲያዎች ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞ አሰምተዋል ::

በተጨማሪ :-

November 29 ደግሞ በተባበሩት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር አስተባባሪነት የተጠራ የተቃውሞ ሰልፍ በድጋሚ በደቡብ አፍሪካ እንደሚኖር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ::

ፎቶ ፦ የኛ ሰው ሚዲያ እና ከማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የተሰባሰበ

FAYA (Tikvah-family )
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia