TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WolaitaSodo : የዎላይታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት አንደኛ አስቸኳይ ጉባኤ በዎላይታ ጉታራ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህም አድስ መንግስት ምሥረታ በዞኑ የሚካሄድ ሲሆን የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጨምሮ የሌሎች የመንግሰት ኃላፊነት ሹመት ይፀድቃል።

@tikvahethiopia
#GamoZone : አቶ ብርሃኑ ዘውዴ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል።

የጋሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር መረሀ ግብር 9ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አስቸኳይ ጉባኤው አቶ ብርሃኑ ዘውዴን የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

ሹመቱን ተከትሎ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

@tikvahethiopia
#Awi : አቶ እንግዳ ደኛው የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ።

ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት 5ኛ ዙር 22ኛ መደበኛ ጉባዔ አቶ እንግዳ ደኛው የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል።

አቶ በላይነህ የኔሰው ደግሞ ምክትል አስተዳዳሪ እና የገጠር መሬት አስተዳደር መምሪያ ኃለፊ ሆነው ተሹመዋል።

መረጃው የአዊ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ ኢብራሂም ኡስማን የሶማሊ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ። አዲሱ የሶማሊ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው የመጀመሪያ አመት ጉባኤው ላይ አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፋራህን የሶማሊ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል። አቶ ኢብራሂም በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አማካኝነት ቃለመሃላ ፈፅመዋል። Photo Credit : SMMA @tikvahethiopia
#SomaliRegion : የሶማሊ ክልል ም/ቤት ሁለተኛ ቀን ውሎውን እያካሄደ ይገኛል።

ትላንት የክልሉ ፕሬዜዳንት ፣ ምክትል ፕሬዜዳንት ፣ አፈጉባኤ እና የምክትል አፈጉባኤ ሹመት በምክር ቤት ፀድቋል።

በመቀጠልም 2 የኦብነግ (ONLF) አባላት ያሉበት 27 የክልሉ ስራ አፅፈፃሚ አካላት ሹመት ፀድቆ ነበር።

በዛሬው የሁለተኛ ቀን ውሎ ምክር ቤቱ በክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ አቅራቢነት የተለያዩ ሹመቶችን አፅድቋል።

* አጠቃላይ በሶማሊ ክልል ምክር ቤት የፀደቁ ሹመቶች ከላይ ተያይዟል።

Credit : Somali Communication & SMMA

@tikvahethiopia
#Gambella : ትላንት በጋምቤላ ከተማ በ2 ባጃጅ ውስጥ አንድ የቡድን መሳሪያ (ላውንቸር)፣ አንድ ክላሽንኮቭ፣ 76 የዲሽቃ ጥይትና 705 የክላሽንኮቭ ጥይቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አሳውቋል።

የተያዙት ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ከጋምቤላ ከተማ 01 ቀበሌ ወደ 03 ቀበሌ ሲዘዋወር መሆኑንም ቢሮው ገልጿል።

የጦር መሳሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በህብረተሰቡ ጥቆማ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ነው ተብሏል።

አዘዋዋሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው የማጣራት ስራ እየተከናወነ መሆኑንም የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ በበኩሉ ፥ " ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ለኦነግ ሸኔ ተላላኪዎች በተለይም ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ብሎ ለሚጠራው ድርጅት ለማስተላለፍ ሲሞክር ነው የታያዘው" ብሏል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች "ላውንቸር" የቡድን መሳሪያ እንጂ በግለሰብ የሚያዝ እንዳልሆነ ፖሊስ አስረድቷል። ይህ መሳሪያ ምሽግ ለመስበር፣ ተሸከርካሪና ትልልቅ ህንፃዎችን ለማውደም የሚያገለግል ነው።

* በጋምቤላ ክልል ባለፉት 3 ወራት 61 ህገ ወጥ የጦር መሳሪያና በርካታ ተተኳሽ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል ከክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በተገኘው መረጃ።

Credit : ጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Bahirdar : በባህርዳር ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ህገ-ወጥ ሽጉጥ እንዲሁም የብሬን፣ የክላሸና የሽጉጥ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋለ። በባህር ዳር ከተማ ልዩ ቦታው ዳግማዊ ምንሊክ ክፍለ ከተማ ማርዘነብ ቀበሌ በተባለው ስፍራ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ፦ - 51 ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ህገ-ወጥ ሽጉጥ፣ - 2ሺ 1መቶ የብሬን ጥይት፣ - 69 የክላሽ ጥይት እንዲሁም 222 የሽጉጥ…
#Bahridar : በባህር ዳር ከተማ ከግለሰብ ቤት ውስጥ ህገወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ።

በዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ማር ዘነብ ቀበሌ ሲቱ ዋርካ አካባቢ በአንድ ተጠርጣሪ ቤት ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ፦
• 3676 የክላሽ ጥይት፣
• 1288 የመትረየስ ጥይት፣
• 3 ክላሽንኮፍ ጠመንጃ እና 20 የተለያዩ ሽጉጦች ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መያዙን የ9ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ክፍል አሳውቋል።

ፖሊስ ህገወጥ የጦር መሳሪያውን በድንገተኛ ፍተሻ ሊይዝ የቻለው ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሆኑን ገልጿል።

Credit : አማራ ፖሊስ

@tikvahethiopia
#KonsoZone : አቶ ዳዊት ገበየሁ የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል።

የኮንሶ ዞን የሽግግር ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ዳዊት ገበየሁ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

ሹመቱን ተከትሎ አቶ ዳዊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

@tikvahethiopia
#HalabaZone : ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሹመዋል፡፡

የሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 6ኛ ዓመት 4ኛ አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ሲሆን ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በትግራይ ክልል እና ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ፡፡ በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎችና በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወልዲያ የኒቨርሲቲ ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች…
የመምህራን ጉዳይ !

" በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጊዚያዊ ምደባ ይሰጣቸዋል " - ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ

በትግራይ ክልል የሚገኙ 4 ዩኒቨርሲቲዎች እና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ጉዳይን በተመለከተ ለትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ-ልማት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ጠይቀናል።

የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች እና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ተቋማቱ አዲስ አበባ ባላቸው የጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ አማካኝነት ደሞዝ እየተከፈላቸው መሆኑን ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ተናግረዋል።

እስከ ግንቦት 30/2013 ዓ.ም በሚሰሩበት ዩኒቨርሲቲ ደሞዝ የተከፈላቸው መምህራን አሁንም ክፍያ እየተፈጸመላቸው መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ በሥራ ላይ እንደነበሩ ማስረጃ ማሳየት ያልቻሉና ሚያዝያ/ግንቦት ደሞዝ ያልተከፈላቸው መምህራን፤ ሥራ ማቆማቸው ወይም ውላቸው መቋረጡ እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ደሞዝ እየተከፈላቸው ያሉ የአራቱ በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በተለይ የመምህራን እጥረት ባለባቸው የአገሪቱ ዩዩኒቨርሲቲዎች ጊዚያዊ ምደባ እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል።

More : https://t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#EZEMA : ዛሬ በኮንሶ ዞን የሽግግር ምክር ቤት እንዲሁም በጋሞ ዞን ምክር ቤት በነበረው ጉባኤ ላይ 2 የኢዜማ አባላት በዞን ስራ አስፈፃሚነት ሹመት ተሰጥቷቸዋል።

በኮንሶ ዞን የኢዜማ ፓለቲካ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አቤል ለሚታ የኮንሶ ዞን ወጣቶችና ስፓርት መምሪያ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

በጋሞ ዞን አስተዳደር ደግሞ አቶ መለሰ ጮራ የዞኑ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

@tikvahethiopia
ችሎት !

በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ዐቃቢ ህግ የሚያቀርባቸው ምስክሮች ስም ዝርዝር በመገናኛ ብዙሃን እንዲገለፅ ተወሰነ፡፡

ምስክሮቹ ከነገ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በግልፅ ችሎት እንዲመሰክሩ ተወስኗል፡፡

ይህ የተወሰነው የእነ እስክንድር ነጋን የዛሬ የጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም የክስ ቀጠሮ በተመለከተው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት መሆኑን አል ዓይን ዘግቧል።

ችሎቱ ዐቃቤ ሕግ በግልፅ ችሎት እንዲያቀርባቸው የታቀዱ ምስክሮች ስም ዝርዝር ለመገናኛ ብዙሃን እንዳይገለጽ ያቀረበውን የጽሁፍ አቤቱታ ውድቅ አድርጓል፡፡

በዐቃቤ ህግ ምስክርነት በግልጽ ችሎት የሚቀርቡ ዘጠኝ ምስክሮች ስም ዝርዝር ለመገናኛ ብዙሃን እንዲገለጽም ወስኗል፡፡ ውሳኔውን ተከትሎ የምስክሮቹ ስም ዝርዝር ይፋ ሆኗል፡፡

Credit : አል ዓይን

@tikvahethiopia