TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HalabaZone : ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሹመዋል፡፡

የሀላባ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 6ኛ ዓመት 4ኛ አስቸኳይ ጉባኤ እያካሄደ ሲሆን ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

@tikvahethiopia
#HalabaZone📍

ነፍሰ ጡር ሴት፣ ልጅ የተሸከመች እናትን ጨምሮ 7 ሰዎች በደራሽ ውሃ ተወሰዱ።

ትላንት በድንገት የተከሰተ ደራሽ ውሃ የብላቴ ወንዝን ሲያቋርጡ የነበሩ አንዲት ነፍሰ ጡር ሴትን ጨምሮ 7 ሰዎችን ወስዷል።

በሀላባ ዞን ከብላቴ ወንዝ ማዶ የሚገኙ የዌራ ወረዳ እና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ቀበሌያት ነዋሪ የሆኑ ግለሰቦች ትናንትና ልክ ከምሽቱ 4 ሠዓት አካባቢ ከፋማ ፏፏቴ በላይ የሚገኘውና በተለምዶ " ጣጤ ብላቴ " ተብሎ የሚጠራውን የወንዝ ውሃ አቋርጠው ሲሻገሩ በደራሽ ውሃ ተወስደዋል።

በደራሽ ውሃው ከተወሰዱት መካከል፦
👉 ነፍሰ ጡር ሴት፣
👉 ህፃን ልጅ የተሸከመች እናት
👉 የ9ኛ ክፍል ተማሪ የሚገኙ ሲሆን እስካሁን በሟቾች አስክሬን ዙሪያ የተገኘ የተጣራ መረጃ የለም።

የዌራ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ማህበረሰቡ ከበጋ ውጭ በማንኛውም ዝናብ የሚጥልበት ጊዜ በዚህ በኩል ከመሻገር እንዲቆጠብ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia