TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BRICS

በ5 ሃገሮች (ብራዚል ፣ ህንድ  ፣ ቻይና ፣ ሩስያ ፣ ደቡብ አፍሪካ) የተመሠረተው የብሪክስ ቡድን መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንደሚሰበሰቡ ተዘግቧል።

መሪዎቹ በዚህ ስብሰባቸው ላይ ምጣኔኃብት ተኮር ሆኖ የተፈጠረውን ቡድን ወደ ጂዖ-ፖለቲካ ኃይልነት በመቀየር ‘የምዕራባውያኑን ተፅዕኖ ለመገዳደር ያስችለናል’ የሚሉትን መላ ሳያበጁ እንደማይቀር እየተነገረ ነው።

በስብሰባው ላይ ከመሥራች አባል ሃገሮቹ የብራዚል፣ የህንድ፣ የቻይናና የደቡብ አፍሪካ መሪዎች በአካል እንደሚሳተፉና የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲን ግን እንደማይገኙ ታውቋል።

ፑቲን ዩክሬን ውስጥ " የጦር ወንጀል ፈፅመዋል " በሚል በተገኙበት እጃቸው እንዲያዝ ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ከጥቂት ወራት በፊት ማዘዣ ማውጣቱ ይታወሳል።

ስብሰባው በተጨማሪም እያደገ ከመጣው ቡድኑን የመቀላቀል ጥያቄ አንፃር በተለይ የአፍሪካ ሃገሮችን በማቀፍ ለመስፋፋት በሚችልበት ሁኔታ ላይም ይወያያል ተብሏል።

#ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል ጥያቄ በይፋ ካስገቡ ሃገሮች መካከል ነች። (ለማስታወሻ https://t.iss.one/tikvahethiopia/79372?single)

የዓለም አካሄድ ‘ለአሜሪካና ለባለጠጋ አጋሮቿ ፍላጎት ያደላ ነው’ የሚለው ቅሬታ ለብሪክስ መፈጠር ዋና ምክንያት ነው።

መረጃው የቪኦኤና ሮይተርስ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ። በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው 15ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ አርጀንቲና፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን በአዲስ አባልነት መቀበላቸውን ታውቋል። BRICS በብራዚል፣ ሩስያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ህንድ ምጣኔኃብት ተኮር ሆኖ የተፈጠረው ቡድን ነው። አሁን…
#BRICS

BRICS ዛሬ አዳዲስ አባል ሀገራትን መቀበሉን አሳውቋል።

እነዚህም ፦

🇪🇹 #ኢትዮጵያ
🇦🇷 አርጀንቲና
🇪🇬 ግብፅ
🇮🇷 ኢራን
🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ናቸው።

አዳዲሶቹ አባል አገራት ከጥር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀላቀሉ  የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ተናግረዋል፡፡

የሀገራችን ኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የBRICS ጉባኤ ኢትዮጵያን በአባልነት ተቀብሎ ማፅደቁን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት ፤ " ይህ ለሀገራችን ታሪካዊ ሁነት ነው " ብለዋል። " ኢትዮጵያ ሁሉን አካታች ለሚሆን የበለፀገ የዓለም ስርዓት መስፈን ከሁሉም ጋር ለመስራት ሁሌም ዝግጁ ናት " ሲሉም ገልጸዋል።

BRICS አዳዲስ አባል ሀገራትን መቀበሉን ተከትሎ አጠቃላይ አባላቱ አስራ አንድ (11) ይሆናሉ።

እነሱም ፦
🇧🇷 ብራዚል
🇷🇺 ሩስያ
🇮🇳 ህንድ
🇨🇳 ቻይና
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇦🇷 አርጀንቲና
🇪🇬 ግብፅ
🇪🇹 ኢትዮጵያ
🇮🇷 ኢራን
🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ናቸው።

@tikvahethiopia
ቱርክ #ኢትዮጵያም ያለችበትን የBRICS ስብሰብ ትቀላቀል ይሆን ?

ባለፈው ሳምንት የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የBRICS አባሏን ቻይናን ጎብኝተው ነበር።

በጉብኝታቸው ወቅት ከቻይና ባለስልጣናት ጋር መክረዋል።

በወቅቱ ሀገራቸው ቱርክ የBRICS ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተጠይቀው ፥ " በእርግጥም #እንፈልጋለን። ለምን አንፈልግም ? " ብለዋል።

" በእርግጥም ፤ የBRICS አባል መሆን እንፈልጋለን " ያሉት ፊዳን " ስለዚህ በዚህ አመት እንዴት እንደሚሄድ እናያለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ነገር ከመናገር ግን ተቆጥበዋል።

አናዱሉ እንደዘገበው ደግሞ ቱርክ የBRICS  አባላት ሀገራትን ትብብር እየተመለከተች ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሁለት ቀን በፊትም ወደ ሩስያ አቅንተው ከBRICS አባሏ ሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዝግ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በBRICS አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል።

ፑቲን ከሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ስብሰባ ቱርክ ስብስቡን ለመቀላቀል (አብሮ ለመስራት) ያሳየችውን ፍላጎት በደስታ ተቀብለው ፤ ወደ ስብስቡ እንድትቀላቀል ሙሉ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

የቱርክ መንግሥት BRICS'ን ለመቀላቀል ርምጃ ይወስድ እንደሆነ እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም። ከዚህ ቀደም በይፋ ስብሰቡን ለመቀላቀል ያለውን ፍላጎት በይፋ አሳውቆ አያውቅም።

ቱርክ የ #NATO አባል ሀገር እንደሆነች ይታወቃል።

#BRICS+ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሩስያ ፣ የብራዚል ፣ የቻይና ፣ የህንድ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የኢራን ፣ የግብፅ ፣ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ስብስብ ነው።

#BRICS
#Turkey
#China
#Russia

@tikvahethiopia
#Ethiopia #UAE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ማዕከላዊ ባንክ የተፈራረሙት ስምምነት ምንድነው ?

1ኛ. በኢትዮጵያ ብር እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ (UAE) ድርሀም መካከል የምንዛሬ ልውውጥ ለማድረግ ተስማምተዋል።

ይህ ስምምነት 46 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር እና 3 ቢሊዮን UAE ድርሃም በማዕከላዊ ባንክ በኩል ለመቀያየር / ለመለዋወጥ ያመቻችላቸዋል።

ዓላማው ፦
° በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የፋይናንስ እና የንግድ ትብብርን ለመደገፍ ነው።
° ድንበር ተሻጋሪ ግብይቶችን የበለጠ ውጤታማ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ነው።

2ኛ. ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ/UAE በራሳቸው ገንዘብ (በብር እና ድርሃም) ለመገበያየት የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራርመዋል።

ዓላማው ፦
° የንግድ ልውውጦችን በራሳቸው (በሁለቱ ሀገራት ገንዘብ) ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል።
° የፋይናንስ እና የባንክ ትብብርን ያጠናክራል።
° የፋይናንስ ገበያዎችን ያዳብራል።
° የሁለትዮሽ ንግድን ያመቻቻል።
° የቀጥታ ኢንቨስትመንት ያበረታታል።
° የሙያ እና መረጃ ልውውጥ እንዲኖር ያመቻቻል።

3ኛ. የክፍያ እና የመልዕክት መለዋወጫ ስርዓቶችን ለማገናኘት የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈራርመዋል።

ዓላማው ፦
° ድንበር ተሻጋሪ የገንዘብ ልውውጦችን ውጤታማነት ያሳድጋል።
° በፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ እና በማዕከላዊ ባንኮች ዲጂታል ምንዛሬዎች ላይ ትብብር እንዲደረግ ይረዳል።
° በክፍያ መድረክ አገልግሎቶችና በኤሌክትሮኒክ ስዊች በኩል ትብብር ያደርጋሉ። በክፍያ ስርዓቶቻቸው በኩል ኢቲስዊች እና ዩኤኢስዊች እንዲሁም በመልእክት መላላኪያ ስርዓቶች በሀገራቱ የቁጥጥር መስፈርቶች በማገናኘት ትብብር ያደርጋሉ።

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) በአሁን ሰዓት ጠንካራ ከሚባሉ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር አንዷ ናት።

ሁለቱም የ #BRICS+ አባል ሀገራት እንደሆኑም ይታወቃል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያሰባሰበው ከብሔራዊ ባንክ እና ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ማዕከላዊ ባንክ ነው።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቱርክ #ኢትዮጵያም ያለችበትን የBRICS ስብሰብ ትቀላቀል ይሆን ? ባለፈው ሳምንት የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የBRICS አባሏን ቻይናን ጎብኝተው ነበር። በጉብኝታቸው ወቅት ከቻይና ባለስልጣናት ጋር መክረዋል። በወቅቱ ሀገራቸው ቱርክ የBRICS ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተጠይቀው ፥ " በእርግጥም #እንፈልጋለን። ለምን አንፈልግም ? " ብለዋል። " በእርግጥም ፤ የBRICS…
#BRICS+

የNATO አባል ሀገሯ ቱርክ የBRICS አባል ለመሆን ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች።

ቱርክ የBRICS አባል ለመሆን በይፋ ማመልከቻ ማቅረቧን የቱርክ ገዥ ፓርቲ ቃል አቀባይ ኦመር ሴሊክ አረጋግጠዋል።

ቃል አቀባዩ " ፕሬዝደንታችን የBRICS አባል መሆን እንደምንፈልግ ደጋግመው ተናግረዋል። ጉዳዩ በሂደት ላይ ነው " ብለዋል።

" በአባልነት ሂደት ላይ ያለውን እምርታ ለህዝብ እናሳውቃለን " ሲሉም ተናግረዋል።

ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም የBRICS+ ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ማሳወቋ የሚዘነጋ አይደለም።

ቱርክ የ #NATO አባል ሀገር እንደሆነች ይታወቃል።

#BRICS+ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሩስያ ፣ የብራዚል ፣ የቻይና ፣ የህንድ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የኢራን ፣ የግብፅ ፣ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ስብስብ ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BRICS+

16ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በሩሲያ ይጀመራል።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ለመሳተፍ ካዛን ከተማ ገብተዋል።

ከኢትዮጵያ መሪ በተጨማሪ ፥
- የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን
- የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬድራ ሞዲ
- የደቡብ አፍሪካው ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሩስያ፣ ካዛን ገብተዋል።

የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ እንዲሁም የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ፣ ሌሎችም መሪዎች እና የሀገራት ተወካዮች ወደ ሩስያ እያቀኑ ይገኛሉ።

Video Credit - RT

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BRICS+ 16ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በሩሲያ ይጀመራል። የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ለመሳተፍ ካዛን ከተማ ገብተዋል። ከኢትዮጵያ መሪ በተጨማሪ ፥ - የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን - የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬድራ ሞዲ - የደቡብ አፍሪካው ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሩስያ፣ ካዛን ገብተዋል። የቻይናው…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ካዛን ፦ ከ16ኛው የ #BRICS+ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሀገራት መሪዎች የተናጠል ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪም ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፦
° ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ፕሬዜዳንት  ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን ፣
° ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ
° ከኢራን ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዥሺካን ... ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

ቪድዮ ፦ አርቲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ካዛን ፦ ከ16ኛው የ #BRICS+ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የሀገራት መሪዎች የተናጠል ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል። በተጨማሪም ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ፦ ° ከተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) ፕሬዜዳንት  ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን ፣ ° ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ…
#BRICS+

በሩስያ፣ ካዛን ሲካሄድ የቆየው የBRICS+ አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።

ስብስቡ 13 ሀገራትን በአጋር (ፓርትነር) አድርጎ ተቀብሏል።

ሀገራቱን የBRICS አጋር (ፓርትነር) አድርጎ የተቀበለው በ2024 ምንም አይነት አዲስ ሙሉ አባል ሀገር ላለመቀበል በመወሰኑ ነው።

13ቱ ሀገራት ወደፊት የስብሰቡ ሙሉ አባል ሀገር ለመሆን እንደሚሰሩ ነው የተነገረው።

የBRICS+ ሙሉ አባል ሀገራት እነማን ናቸው ?

🇧🇷 ብራዚል
🇷🇺 ሩስያ
🇮🇳 ሕንድ
🇨🇳 ቻይና
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇪🇹 ኢትዮጵያ
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ
🇮🇷 ኢራን
🇪🇬 ግብፅ ናቸው።

አሁን BRICS+ን በአጋርነት (ፓርትነር) ሆነው የተቀላቀሉት እነማን ናቸው ?

🇩🇿 አልጄሪያ
🇧🇾 ቤላሩስ
🇧🇴 ቦሊቪያ
🇨🇺 ኩባ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇰🇿 ካዛኪስታን
🇲🇾 ማሌዢያ
🇳🇬 ናይጄሪያ
🇹🇭 ታይላንድ
🇹🇷 ቱርክ
🇺🇬 ዩጋንዳ
🇺🇿 ኡዝቤኪስታን
🇻🇳 ቬዬትናም ናቸው።

በካዛኑ የBRICS+ የመሪዎች ጉባኤ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ፣ የቬንዝዌላው ፕሬዜዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ተገኝተው ነበር።

የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ካዛን ተገኝተው ነበር። ሳዑዲ ምንም እንኳን በይፋ የBRICS ስብስብን ባትቀላቀልም በተጋባዥ ሀገርነት ትሳተፋለች።

የሌሎች ሀገራት መሪዎችና ተወካዮችም በካዛን ተገኝተው ነበር።

#BRICSSummit #Russia

@tikvahethiopia