TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቱርክ #ኢትዮጵያም ያለችበትን የBRICS ስብሰብ ትቀላቀል ይሆን ?

ባለፈው ሳምንት የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን የBRICS አባሏን ቻይናን ጎብኝተው ነበር።

በጉብኝታቸው ወቅት ከቻይና ባለስልጣናት ጋር መክረዋል።

በወቅቱ ሀገራቸው ቱርክ የBRICS ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ተጠይቀው ፥ " በእርግጥም #እንፈልጋለን። ለምን አንፈልግም ? " ብለዋል።

" በእርግጥም ፤ የBRICS አባል መሆን እንፈልጋለን " ያሉት ፊዳን " ስለዚህ በዚህ አመት እንዴት እንደሚሄድ እናያለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ነገር ከመናገር ግን ተቆጥበዋል።

አናዱሉ እንደዘገበው ደግሞ ቱርክ የBRICS  አባላት ሀገራትን ትብብር እየተመለከተች ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሁለት ቀን በፊትም ወደ ሩስያ አቅንተው ከBRICS አባሏ ሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በዝግ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በBRICS አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል።

ፑቲን ከሚኒስትሩ ጋር በነበራቸው ስብሰባ ቱርክ ስብስቡን ለመቀላቀል (አብሮ ለመስራት) ያሳየችውን ፍላጎት በደስታ ተቀብለው ፤ ወደ ስብስቡ እንድትቀላቀል ሙሉ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

የቱርክ መንግሥት BRICS'ን ለመቀላቀል ርምጃ ይወስድ እንደሆነ እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም። ከዚህ ቀደም በይፋ ስብሰቡን ለመቀላቀል ያለውን ፍላጎት በይፋ አሳውቆ አያውቅም።

ቱርክ የ #NATO አባል ሀገር እንደሆነች ይታወቃል።

#BRICS+ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሩስያ ፣ የብራዚል ፣ የቻይና ፣ የህንድ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የኢራን ፣ የግብፅ ፣ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ስብስብ ነው።

#BRICS
#Turkey
#China
#Russia

@tikvahethiopia