TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Free_Nazrawit_Abera!!

መንግስት በቻይና መንግስት እፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ እስር ላይ የምትገኘውን ናዝራዊት አበራን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ከfbc ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ መንግስት #ጓንዡ_ግዛት በሚገኘው ማረሚያ ቤት የምትገኘውን የናዝራዊት አበራን ጉዳይ #በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ተናግረዋል።

በስፍራው በሚገኘው የኢፌዴሪ ቆንስላ ፅህፈት ቤት ሰራተኞችም ናዝራዊት በምትገኝበት ማረሚያ ቤት ሶስት ጊዜ በመሄድ ያለችበትን ሁኔታ ተመልክተዋል ነው ያሉት።

መንግስትም ዜጋውን የመከታተል መብቱን ተጠቅሞ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ጠቅሰው፥ ተጠርጣሪዋን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ እየተናፈሱ ያሉ ወሬዎች #ሃሰት መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።

በተለይም ከተጠረጠረችበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ #የሞት_ፍርድ_ተፈርዶባታል በሚል እየተናፈሰ ያለው ወሬ ሃሰት መሆኑንም ገልጸዋል።

ተጠርጣሪዋ አሁን ላይ በማረሚያ ቤት የምትገኝ ሲሆን አቃቤ ህግም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ክሱን ካቀረበ በኋላ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት አምርቶ #እንደሚወሰንም አስረድተዋል።

መንግስት አሁን ላይ እንደ ዜጋ መጠየቅ የሚችለውን እያደረገ ሲሆን፥ ትክክለኛ ፍርድ እንድታገኝ ክትትል ይደረጋልም ነው ያሉት።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tijvahethiopia
#ናዝራዊት_አበራ

እፅ በማዘዋወር #ተጠርጥራ ቻይና ጉዋንዡ እስር ቤት የምትገኘው #ኢትዮጵያዊቷ ናዝራዊት አበራ ከወር በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረቧንና የመጨረሻውን ፍርድ እየተጠባበቁ እንደሆነ እህቷ #ቤተልሔም_አበራ ለቢቢሲ ገለፁ።

ናዝራዊት አበራ በቻይና በእፅ ዝውውር ተጠርጥራ በቁጥጥር ሥር መዋሏ ከተሰማ ስድስት ወራቶች አልፈዋል።

አንድ ሰው እፅ ሲያዘዋውር ከተገኘ #የሞት ፍርድ እንዲበየንበት የሚያዘው የቻይና ህግ በናዝራዊት ላይ ተግባራዊ ይሆናል በሚል በቤተሰቦቿ፣ በቅርብ ዘመዶቿ እንዲሁም በበርካታ ሰዎች ዘንድ ስጋትን አሳድሯል።

የቢቢሲን ዘገባ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/NA-07-22
#Ethiopia

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃለማርያም ሀገር ጥለው ከወጡ ዛሬ ድፍን 33 ዓመት ሆኗቸዋል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪ ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ/ም ነው ከሀገር የወጡት።

የድርግ ውድቀትን እና የ #ኢህአዴግ ወደ አዲስ አበባ መቃረብን ተከትሎ ከሀገር እንደወጡ የሚነገርላቸው ኮ/ሌ መንግሥቱ ኃለማርያም በአንድ ወቅት ፤ " እኔ ኮብልዬ አልወጣሁም " ሲሉ ነበር ቃላቸውን የሰጡት።

ኬንያ የሄዱትም ' #አሰብ ' በሻዕብያ በመያዙ ለመልሶ ማጥቃት የሚሆን ሌላ በር እንዲኖር ከኬንያ፣ ከጅቡቲ እና ሰሜን ሶማሊያ መንግስታት ጋር ለመነጋገርና ለመመለስ እንደነበረና ይህም ጥብቅ ሚስጥራዊ ጉዞ እንደሆነ ተናግረው ነበር።

ጥዋት 2:20 ወደ ኬንያ ጉዞ እንደጀመሩ እዚህ ስብሰባ መጀመሩና ኬንያ እንዳሉ ከቀን 7:00 ሰዓት ከስልጣን እንደወረዱ እንደሰሙ ገልጸው ነበር።

በራሳቸው አንደበትም ፥ ምንም አይነት #ገፊ ምክንያት በሌለበት በአሻጥር ከሀገር እንዲወጡ መገደዱን ነው በአንድ ወቅት ሲናገሩ የተደመጡት።

ዛሬ ላይ ሀገር ጥለው ከወጡ 33 ዓመት የደፈናቸው ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም በዚምባቡዬ ውስጥ ይኖራሉ።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዜዳት ከዓመታት በፊት ፦
° በዘር ማጥፋት ፣
° በግድያ፣
° ከህግ ውጪ ሰዎችን በማሰር
° ንብረትን በመውረስ ጥፋተኛ ተብለው በሌሉበት #የሞት ፍርድ ተወስኖባቸዋል።

@tikvahethiopia
#Adama

ተከሳሽ ቶሎሳ ወይም ፍቅሩ አሸናፊ ይባላል።

በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍል ከተማ በተለምዶ ደካ አዲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል።

ተከሳሹ እናቱን በስለት (ቢላዋ) በአሰቃቂ ሁኔታ ወግቶ ነው ህይወታቸውን እንዲያጡ ያደረገው።

ተከሳሹ ድርጊቱን የፈጸመው #በቁማር_የተበላዉን ገንዘብ እናቱ ያላቸውን ንብረት በመሸጥ እንዲተኩለት ለማድረግ ሲል እየደበደበ ያሰቃያቸው እንደነበር ዐቃቤ ሕግ በማስረጃ አረጋግጧል።

በዚህ ብቻ ያላበቃው ተከሳሽ ሚያዚያ 21/ 2016 ዓ/ም ጠዋት በአሰቃቂ ሁኔታ የእናቱ ህይወት እንዲያልፍ በማድረጉ ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

ጉዳዩን የተመለከተው የአዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።

በተከሳሹ ላይ የተጣለው #የሞት_ፍርድ በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሲጸድቅ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#ሞት_ተፈርዶበታል !

ከአባቱ ጋር በገባበት " #የጥቅም_ግጭት " መላው ቤተሰቦቹን በጥይት ገድሎ ሊጨርስ የነበረው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተፈረደበት።

ተከሳሽ ከፍታ ካፋላ ይባላል።

በጋርዱላ ዞን የሃይበና ቀበሌ ነዋሪ ነው።

ግለሰቡ ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ሠገን ገነት ቀበሌ በመሄድ በ4 ቤተሰቦቹ ላይ የጥይት እሩምታ ይከፍታል።

በዚህም ሶስቱን ሲገድል አንዱን አቁስሏል።

በጥይት እሩምታ የገደላቸው ፦
- #አባቱ
- #እናቱ
- #አጎቱ ሲሆኑ የመቁሰል አደጋ የደረሰበት የ9 አመት ታናሽ ወንድሙ ነው።

ግለሰቡ ይህን ፈጽሞ ከአካባቢዉ ቢሰወርም የጸጥታ ኃይሉ ከማህበረሰቡ ጋር ተባብሮ ባደረገዉ ክትትል ከ5 ወራት በኋላ ሊያዝ ችሏል።

ፖሊስም ስራውን አጠናቆ ለፍርድ ቤት አቅርቧል።

ተከሳሹም ፤ ከወላጅ #አባቱ ጋር በገባበት ' የጥቅም ግጭት ' ምክኒያት ወንጀሉን እንደፈጸመ ለፍርድ ቤቱ አምኖ ቃሉን ሰጥቷል።

ይህም ቃሉም ከቀረበበት የሰውና የሰነድ ማስረጃ ጋር ተዳምሮ የፍርድ ሂደቱን ቀላል እንዳደረገዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

በዚህም በኃላ ጉዳዩን ሲመረምር የነበረዉ የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተከሳሽ ከፍታ ካፋላ #በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።

በተከሳሹ ላይ የተጣለው #የሞት_ፍርድ በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሲጸድቅ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia