TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" አሁን ላይ ግጭቱ ቆሟል ሕዝብ የማወያየትና የሞቱትን የመቅበር ስራ ሲሰራ ነዉ የዋለው " - የደራሼ ወረዳ ነዋሪዎች
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ በጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ ከመጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ሕይወት መጥፋቱና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸዉን የአከባቢውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መናግራቸው ይታወሳል።
በወረዳዉ የሀይ'በረና እና ኦኖታ አከባቢ ነዋሪዎች ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ግጭቱ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አከባቢው በመግባቱ መቆሙን ተናግረዋል።
በግጭቱ ምክንያት ሕይወታቸዉን ያጡትን የመቅበርና ሕዝቡን የማረጋጋት ስራ እየተሰራ መዋሉንም ገልጸዋል።
" የሞተዉ ሰዉ ቁጥር በጣም ብዙ ነዉ አስከሬናቸው እየተፈለገ ያሉም አሉ " ያለን አንድ የአከባቢው ነዋሪ " የተቃጠለዉ ቤት ብዛት ከቁጥር በላይ ነዉ " ሲሉ ሁኔታዉን አብራርተዋል።
" የኛ ሁለት አጎቶች እስካሁን የገቡበት አልታወቀም፣ ልክ ግጭቱ እንደቆመ ቤተሰብ እያፈላለግን ነዉ " ያለን ሌላኛዉ አስተያየት ሰጪ " አሁን እየመሸ ስለሆነ የምናገኝ አይመስለንም፣ ሞተዉ ይሁን በህይወት ያሉ ፈጣሪ ነዉ የሚያዉቀዉ " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነዋሪዎችን ሃሳብ ተከትሎ በድጋሚ ወደ ጋርዱላ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ብርሃኑ ኩናሎ ደዉሎ የነበረ ሲሆን ሕዝብ እያወያዩ ብቻ እንደሆነ በመግለፅ ከዚህ ያለፈ መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia

😢519❤117😭90🕊83🤔65🙏51😡40😱14🥰12💔10👏2
" እየተስተጋባ የሚገኘው የጤና ባለሙያዎች ድምፅ የሁላችንም ድምፅ ነዉ " - የጤና ባለሙያዎች ማህበራት
⚫️ " ባለፉት ዓመታትም እንደዚሁ የጤና ባለሙያዎች ቅሬታ እየተስተጋባ መልሶ የሚቀዘቅዝበት ሁኔታ አለ !! "
ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየታየ የሚገኘውን የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ቅሬታን አስመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎችን እና የጤና ባለሙያዎች ማህበራትን አነጋግሯል።
የጤና ባለሙያዎቹ እንዲፈቱላቸው በሚፈልጓቸው ጉዳዮች ላይ ድምጻቸውን እያስተጋቡ ይገኛሉ።
➡️ " ሕይወት ስናድን ኖረናል አሁን ግን እኛን መታደግ ይገባል ! "
➡️ " ለጤና ባለሙያዎች የሚከፈለው ደመወዝ ስራና ድካማችንን የሚመጥን አይደለም ! "
➡️ " እኛ ከጎረቤት ሀገራትንና ሙያዉ ከሚፈልገዉን የደመወዝ መጠን አንፃር ሳይሆን የሚያስፈልገንን አድርጉልን ነዉ ያልነዉ ! "
➡️ " ሕይወት የሚታደጉ የጤና ባለሙያዎች ለራሳቸዉ የጤና ኢንሹራንስ የላቸዉም ! "
➡️ " የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በአግባቡ ይከፈሉ ! "
➡️ " የተራበ ሐኪም የሚሰጠዉ የጤና አገልግሎት መቼም ዉጤታማ አይሆንም ! "
➡️ " የጠየቅነዉ በአግባቡ ሕይወት እንድንታደግ እኛን ታደጉን ብለን ነዉ ! "
➡️ " የጤና ባለሙያ እየራበው፣ እየጠማው፣ ለቤት ኪራይ የሚከፍለው ሳይኖረው እና ጤናዉ እየታወከ እንዴት የሌላዉን ጤና ይጠብቃል ? "
➡️ " በርካታ ሐኪሞች ሌላዉን ለማዳን ሲሉ ጤናቸዉን አጥተዋል ብዙዎችም ቤተሰቦቻቸውን በትነዉ ሞተዋል ዳሩ ግን ለነሱም ሆነ ለቤተሰቦቻቸው ኢንሹራንስ የለም ! "
የሚሉት የጤና ባለሙያዎች እያሰሙት ካለው ድምጽ መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ነርሶች ፣ አዋላጆችና ላብራቶሪ ባለሞያዎች የጤና ማህበራት ጉዳዩን በማህበራዊ ሚዲያዎች መመልከታቸዉን ገልፀዉ " ጥያቄዉን የምንጋራዉ ነዉ " ብለዋል።
ባለሞያዎቹ " ለጤና ዘርፉ ተገቢው ትኩረት ባለመሰጠቱ የሚፈለገዉ ዉጤት እየተመዘገበ አይደለም፤ ለአብነትም ከነርስ የጤና ሙያ መስክ በ100 ሺህ የሚቆጠሩ ባለሙያዎች ቢኖሩም ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካቶች መስኩን እየለቀቁ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
አክለውም ፤ " በሀገራችን ሁሉንም የጤና ባለሙያ ዘርፎች ያካተተ አንድ የጋራ ማህበር አለመኖሩ ለችግሮች ፈጣንና የማያዳግሙ ዉሳኔዎች እንዳይሰጡ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል " ብለዋል።
በዝርዝር ያነሱት ሃሳብ ምንድነው ?
" ከዚህ ቀደም ወደ ዉጪ ሀገራት ይደረግ የበረዉ የባለሙያዎች ስደት አሁን አሁን ሙያ በመቀየር ሀገር ዉስጥ ሆኗል።
በቅርቡ በፀደቀዉ የጤና ፖሊሲ ላይ የጤና ባለሙያዎች የጤና መድህን ድርሻ መንግስት እንዲሸፍን ቢወሰንም በቂ ካለመሆኑም በላይ አፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ክፍተት አለ።
የጤና ባለሙያዎች በሚሰሩባቸዉ የጤና ተቋም ሳይቀር ከፍለው እንዲታከሙ ነዉ የሚደረገዉ ፤ ይህ ሙያዉንም ባለሙያዉንም እየጎዳው ነዉ።
በርካታ የጤና ባለሙያዎች በስራ ላይ እያሉ በሚደረሰባቸው የጤና፣ የስነ አዕምሮና አካላዊ ጉዳቶች የሕክምናና የማካካሻ ድጋፎችን አያገኙም።
ጤናን ከተቀዳሚ የሀገሪቱ ፖሊሲዎች አንዱና ዋነኛዉ ነዉ በምትል ሀገር በጤና ባለሙያዎች ላይ የሚስተዋለዉን የደሞዝ፣ የጤና ኢንሹራንስና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ጉዳይ በመንግስት በኩል ተገቢው ትኩረት አላገኘም።
ባለፉት ዓመታትም እንደዚሁ የጤና ባለሙያዎች ቅሬታ እየተስተጋባ መልሶ የሚቀዘቅዝበት ሁኔታ አለ።
በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መንግሥት የጤና ባለሙያዎች ሕይወት የሚታደጉ እንደመሆናቸዉ መጠን ተመጣጣኝ የደመወዝ ክፍያ፣ ሙሉ የጤና ኢንሹራንስና ነፃ የጤና መድህን አገልግሎት ሊያሰጣቸዉና ጥቅማ ጥቅሞቻቸዉን ማስከበር ሲገባዉ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በበዓላት የሚሰሩባቸዉን የትርፍ ሰዓት ክፍያቸዉን ጭምር በሚከለክሉና በግዳጅ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚደረጉባቸዉ አከባቢዎች ላይ የመፍትሔ እርምጃ አለመዉሰዱ ችግሩን አባብሶታል " ብለዋል።
እንደ መፍትሔ በጠቆሟቸው ሃሳቦች ምን አሉ ?
🔴 ለጤና ባለሙያዎች ስራቸዉን የሚመጥን የደመወዝ ማስተካከያ ቢደረግ እና የጤና ኢንሹራንስ ለጤና ባለሙያዎችና ለቀጥተኛ ተጎጂ ቤተሰቦቻቸው ቢሰጥ።
🔴 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቢፀድቅም አፈፃፀም ላይ ሰፊ ክፍተቶች ስላሉ የጤና መድህን አገልግሎትን ያለ ገደብ እንዲያገኙ ቢደረግ።
🔴 በትርፍ ሰዓት ክፍያ ጉዳይ ፈጣን እንዲሁም የማያዳግም ዉሳኔ ቢሰጥ።
🔴 በጤና ባለሙያዎች ማህበር በኩል በልዩነት አንድ የጋራ ማህበር አልያም " የጤና ባለሙያዎች ካዉንስል ቢቋቋም " በዘርፉ በየጊዜዉ የሚነሱ ችግሮችን በዘላቂነት እንዲፈቱ ያደርጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
⚫️ " ባለፉት ዓመታትም እንደዚሁ የጤና ባለሙያዎች ቅሬታ እየተስተጋባ መልሶ የሚቀዘቅዝበት ሁኔታ አለ !! "
ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየታየ የሚገኘውን የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ቅሬታን አስመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎችን እና የጤና ባለሙያዎች ማህበራትን አነጋግሯል።
የጤና ባለሙያዎቹ እንዲፈቱላቸው በሚፈልጓቸው ጉዳዮች ላይ ድምጻቸውን እያስተጋቡ ይገኛሉ።
➡️ " ሕይወት ስናድን ኖረናል አሁን ግን እኛን መታደግ ይገባል ! "
➡️ " ለጤና ባለሙያዎች የሚከፈለው ደመወዝ ስራና ድካማችንን የሚመጥን አይደለም ! "
➡️ " እኛ ከጎረቤት ሀገራትንና ሙያዉ ከሚፈልገዉን የደመወዝ መጠን አንፃር ሳይሆን የሚያስፈልገንን አድርጉልን ነዉ ያልነዉ ! "
➡️ " ሕይወት የሚታደጉ የጤና ባለሙያዎች ለራሳቸዉ የጤና ኢንሹራንስ የላቸዉም ! "
➡️ " የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ክፍያና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በአግባቡ ይከፈሉ ! "
➡️ " የተራበ ሐኪም የሚሰጠዉ የጤና አገልግሎት መቼም ዉጤታማ አይሆንም ! "
➡️ " የጠየቅነዉ በአግባቡ ሕይወት እንድንታደግ እኛን ታደጉን ብለን ነዉ ! "
➡️ " የጤና ባለሙያ እየራበው፣ እየጠማው፣ ለቤት ኪራይ የሚከፍለው ሳይኖረው እና ጤናዉ እየታወከ እንዴት የሌላዉን ጤና ይጠብቃል ? "
➡️ " በርካታ ሐኪሞች ሌላዉን ለማዳን ሲሉ ጤናቸዉን አጥተዋል ብዙዎችም ቤተሰቦቻቸውን በትነዉ ሞተዋል ዳሩ ግን ለነሱም ሆነ ለቤተሰቦቻቸው ኢንሹራንስ የለም ! "
የሚሉት የጤና ባለሙያዎች እያሰሙት ካለው ድምጽ መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ነርሶች ፣ አዋላጆችና ላብራቶሪ ባለሞያዎች የጤና ማህበራት ጉዳዩን በማህበራዊ ሚዲያዎች መመልከታቸዉን ገልፀዉ " ጥያቄዉን የምንጋራዉ ነዉ " ብለዋል።
ባለሞያዎቹ " ለጤና ዘርፉ ተገቢው ትኩረት ባለመሰጠቱ የሚፈለገዉ ዉጤት እየተመዘገበ አይደለም፤ ለአብነትም ከነርስ የጤና ሙያ መስክ በ100 ሺህ የሚቆጠሩ ባለሙያዎች ቢኖሩም ከጊዜ ወደ ጊዜ በርካቶች መስኩን እየለቀቁ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
አክለውም ፤ " በሀገራችን ሁሉንም የጤና ባለሙያ ዘርፎች ያካተተ አንድ የጋራ ማህበር አለመኖሩ ለችግሮች ፈጣንና የማያዳግሙ ዉሳኔዎች እንዳይሰጡ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል " ብለዋል።
በዝርዝር ያነሱት ሃሳብ ምንድነው ?
" ከዚህ ቀደም ወደ ዉጪ ሀገራት ይደረግ የበረዉ የባለሙያዎች ስደት አሁን አሁን ሙያ በመቀየር ሀገር ዉስጥ ሆኗል።
በቅርቡ በፀደቀዉ የጤና ፖሊሲ ላይ የጤና ባለሙያዎች የጤና መድህን ድርሻ መንግስት እንዲሸፍን ቢወሰንም በቂ ካለመሆኑም በላይ አፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ክፍተት አለ።
የጤና ባለሙያዎች በሚሰሩባቸዉ የጤና ተቋም ሳይቀር ከፍለው እንዲታከሙ ነዉ የሚደረገዉ ፤ ይህ ሙያዉንም ባለሙያዉንም እየጎዳው ነዉ።
በርካታ የጤና ባለሙያዎች በስራ ላይ እያሉ በሚደረሰባቸው የጤና፣ የስነ አዕምሮና አካላዊ ጉዳቶች የሕክምናና የማካካሻ ድጋፎችን አያገኙም።
ጤናን ከተቀዳሚ የሀገሪቱ ፖሊሲዎች አንዱና ዋነኛዉ ነዉ በምትል ሀገር በጤና ባለሙያዎች ላይ የሚስተዋለዉን የደሞዝ፣ የጤና ኢንሹራንስና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ጉዳይ በመንግስት በኩል ተገቢው ትኩረት አላገኘም።
ባለፉት ዓመታትም እንደዚሁ የጤና ባለሙያዎች ቅሬታ እየተስተጋባ መልሶ የሚቀዘቅዝበት ሁኔታ አለ።
በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መንግሥት የጤና ባለሙያዎች ሕይወት የሚታደጉ እንደመሆናቸዉ መጠን ተመጣጣኝ የደመወዝ ክፍያ፣ ሙሉ የጤና ኢንሹራንስና ነፃ የጤና መድህን አገልግሎት ሊያሰጣቸዉና ጥቅማ ጥቅሞቻቸዉን ማስከበር ሲገባዉ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በበዓላት የሚሰሩባቸዉን የትርፍ ሰዓት ክፍያቸዉን ጭምር በሚከለክሉና በግዳጅ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚደረጉባቸዉ አከባቢዎች ላይ የመፍትሔ እርምጃ አለመዉሰዱ ችግሩን አባብሶታል " ብለዋል።
እንደ መፍትሔ በጠቆሟቸው ሃሳቦች ምን አሉ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1.77K👏258💔45😢40🙏32😡19😭18🕊11🤔10🥰6😱1
" ለመንገድ ስራ የተከማቸ አፈር በህፃናት ላይ ተደርምሶ የአንድ ታዳጊ ሕይወት አጥፍቷል " - የወላይታ ከተማ ፖሊስ
በወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ለመንገድ ስራ ተብሎ የተከማቸ አፈር በአካባቢው ሲጫወቱ የነበሩ ሕፃናት ላይ ተደርምሶ የአንድ ታዳጊ ሕይወት ማለፉን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሀብታሙ አስፋዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አደጋዉ የተከሰተው በትናትናዉ ዕለት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አከባቢ መሆኑን የገለፁት አዛዡ በስፍራው የነበሩት ከ7 እስከ 9 ዓመት የዕድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ ሶስት ሕፃናት እንደነበሩ ተናግረው ሕይወቱ ካለፈዉ ታዳጊ በስተቀር በሌሎቹ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን ገልጸዋን።
ሕፃናቱ እየተጫወቱ የነበረበት ቦታ ለአደጋ ተጋላጭ መሆን እየጣለ ካለዉ ከባድ ዝናብ ጋር ተዳምሮ ለአደጋዉ መከሰት መንስኤ ሆኗል ሲሉ አስረድተዋል።
ምክትል ኮማንደር ሀብታሙ አስፋው ፥ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንደሚሰራና በሶዶ ከተማ አስተዳደር የዉስጥ ለዉስጥ የአስፋልት መንገድ ስራ እያከናወነ የሚገኘዉ የቻይና ተቋራጭም አደጋ ሊያስከትሉ በሚችሉ ቦታዎችን ጥበቃ እንዲያስቀምጥ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ አስታዉቀዋል።
ከአደጋው ጋር ተያይዞ በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ከአስር በላይ ሕፃናት ሕይወት እንዳለፈ ተደርጎ የሚሰራጨዉ መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ ያሉት ፖሊስ አዛዡ እንደዚህ ዓይነት መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

😢515😭237❤92🕊33🙏23💔20😱6😡5🥰3
" በስህተት ወደ አካውንቴ የገባልኝን 3.5 ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ መልሻለሁ " - አቶ በህጉ ወ/ሚካኤል
በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስህተት ወደ አካዉንቱ የገባን 3.5 ሚሊዮን ብር ተመላሽ ያደረገ ግለሰብ ምስጋና እየተቸረው ይገኛል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ በስም ተጠቃሹን ግለሰብ አግኝቶ ያነጋገራቸው ሲሆን የባንክ ባለሙያ አስተያየት እና ምክርም ጠይቋል።
በስህተት የገባላቸዉን 3.5 ሚሊዮን ብር የመለሱት አቶ በህጉ ወ/ሚካኤል ምን አሉ ?
" ከባንክ ወደ ባንክ በሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉር ሂደት በተፈጠረ ስህተት ከሌላ ግለሰብ ወደ አካዉንቴ የገባን 3.5 ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ ተመላሽ አድርጊያለሁ።
እኔም የስራ ሰዉ ነኝ እንደዚህ አይነት ክስተት ልያጋጥመኝ ይችላል፤ ስለዚህ ገንዘቡ የኔ ስላልሆነና ለባለቤቱ መመለስ ስላለብኝ ሳላቅማማ መልሻለሁ " ሲሉ ጉዳዩን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
አቶ በህጉ አክለዉም " ብዙ ሰዎች ሞኝ እንደሆንኩ፣ መመለስ እንዳልነበረብኝና ብመልስም ከላዩ ቀንሼ መሆን እንደነበረበት አስተያየት ሲሰጡ ሰምቻለሁ፤ ዳሩ ግን ቅድም እንዳልኩት የኔ ያልሆነ ነገር የኔ አይደለም፤ በተለይም እኔም በቢዝነስ አለም ዉስጥ እንዳለ ሰዉ ነግ በኔ እንደሆነ በመረዳት ማድረግ ያለብኝ ነዉ ያደረኩት "ብለዋል።
የአዋሽ ባንክ ባለሙያ ስለሁኔታዉ ምን አሉ ?
የአዋሽ ባንክ ፊንፊኔ ቅርንጫፍ ኦፕሬሽንናል ማናጀር አቶ ፉፋ አሰፋ ስለ ጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ " ከባንክ ወደ ባንክ በሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉር አቶ ቦንሳ ታደለ የተባሉ የባንካችን ደንበኛ ከአንዱ ባንክ አካዉንት ወደ ሌላ ባንክ አካዉንት በአካል ተገኝተዉ በማንዋል ፅፈዉ ሂሳብ ሲያስተላልፉ አንድ ቀጥር ተሳስተዉ ፅፈዉ በመስጠታቸዉ 3.5 ሚሊዮን ብር ወደ አቶ በህጉ ወ/ሚካኤል አካዉንንት ተላልፏል " ሲሉ ገልፀዋል።
ባንኩ ለአቶ በህጉ በመደወል ሁኔታውን ማስረዳቱንና አቶ በህጉም ተባባሪ በመሆን ለባለቤቱ ገንዘቡን ተመላሽ ማድረጋቸውን አስታውቋል።
ለሁሉም የባንክ ተጠቃሚዎች የባንክ ባለሙያዉ ምን አሉ ?
" ከባንክ ወደ ባንክ በሚደረግ የገንዘብ ዝዉዉር ሂደት ይህ ዓይነቱ አጋጣሚ የመፈጠር ዕድሉ ሰፊ ነዉ። ሁሉም ሰዉ በብር ዝዉዉርና አጠቃላይ በባንክ አጠቃቀም ወቅት ተገቢዉ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት " ሲሉ አሳስበዋል።

👏3.05K😭488❤341🙏176😡136🤔49💔34🥰33🕊31😱25😢11
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" ከታሰሩት 14 ባለሙያዎች 7ቱ ሲፈቱ 7ቱ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ " - የጤና ባለሙያዎች
" የ4 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ተከፍሎን ስራ ጀምረናል፤ በወረዳዉ ስራ ሲዘጋ መክፈል የተለመደ ነው !! "
ከ6 እስከ 9 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ምክንያት ሥራ ማቆማቸውንና 14 ሰዎች መታሰራቸውን በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ የሚገኘዉ ሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሞያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።
ጤና ባለሙያዎቹ ዛራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከታሰሩት 14 ባለሙያዎች 7ቱ ሲፈቱ 7ቱ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
ካልተከፈለዉ የ9 ወራት ዉዝፍ ዉስጥ የ4 ወራት ክፊያ መፈጸሙን ተከትሎ ሥራ መጀመራቸውን የገለጹት ባለሞያዎቹ " የትርፍ ሰዓት ስራ ከቆመ በኋላ ክፍያ መፈፀም በወረዳዉ የተለመደ ጉዳይ ነዉ " ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ከታሰሩ 5ኛ ቀናቸዉን የያዙት የታሰሩ የጤና ባለሙያዎች " እንዲፈቱ በተደጋጋሚ እየጠየቅን ነዉ ያሉት ሰራተኞቹ እስካሁን ግን ግልፅ ምክንያት አልተነገረንም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሎካ አባያ ወረዳ አስተዳዳሪና ፖሊስ አዛዥን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። በጉዳዩ ላይ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆኑ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

😭339😡81❤76😢18🕊16🙏14😱7🥰3🤔2
" ሚስቱን ገድሎ ሊሰወር የሞከረዉ ግለሰብ በፖሊስና በሕብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ሊዉል ችሏል " - የጋሞ ዞን ፖሊስ
በአርባ ምንጭ ከተማ ባለቤቱ ገድሎ ሊሰወር የነበረ ግለሰብ መያዙን ፖሊስ ገልጿል።
የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ሬታ ተክሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመዉ አርባ ምንጭ ከተማ ወዜ ቀበሌ ግድብ ሠፈር ነው።
ኮማንደር ሬታ ፤ የገዛ ባለቤቱን በመሳሪያ ተኩሶ በመግደል ሊሰወር የሞከረዉ ተጠርጣሪ በሕዝቡና በፖሊስ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል።
ተጠርጣሪው አቶ ነብዩ ጌታቸው ኤፍሬም እንደሚባልና ከሟች ጋር በትዳር ዓለም አብረዉ እንደነበሩ በመካከላቸዉ በነበረው አለመግባባት ሟች ወላጆቿ ጋር በመሄድ ላለፉት 5 ወራት ከቤተሰቦቿ ጋር ትኖር እንደነበር ገልፀዋል።
በትናትናዉ ዕለት ተጠሪጣርዉ አስቦና አቅዶ ጧት 4 ሰዓት ገደማ " ላናግርሽ እፈልጋለሁ " በማለት ካስጠራት በኋላ ሰዉ የማያይበትን ሁኔታ በማመቻቸት በሽጉጥ አንገቷ ስር ደቅኖ ተኩሶ እንደ ገደላት አስረድተዋል።
በኃላም ለመሸሸግና ለመሰወር ሲሞክር በፖሊስ ክትትልና በሕብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ተጠርጣሪዉና ሟች በትዳር አብረዉ በነበሩበት ወቅት አንድ ልጅ አፍርተዉ እንደነበርም የፖሊስ መረጃ ያመለክታል።
ተጠርጣሪዉ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመበትን ሽጉጥ ወንዝ ዉስጥ እንደጣለ ቢገልፅም ፖሊስ ባደረገዉ ማጣራት ከደበቀበት በኤግዚቢትነት ይዞታል።

😭2.49K💔316❤186😡111🕊86😢60🙏49😱41🤔32👏26🥰13
TIKVAH-ETHIOPIA
" ለ ' ምርመራ ' በሚል ተወስደዉብን የቆዩ የግል ስልኮቻችንና ኮምፕዩተሮቻችን ተመልሰዉልን ክሳችንም እንዲቋረጥ ተደርጓል " - ታስረዉ የተለቀቁ የገዜ ጎፋ ነዋሪዎች ➡️ " ክሳቸዉ እንዲቋረጥ የተደረገዉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የዞኑ ተወላጅ አመራሮችና ምሁራን ባካሄዱት የልማት ዉይይት እና የይቅርታ መድረክ ምክረ ሃሳብ ነዉ " - የዞኑ ፍትሕ መምሪያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ…
" በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ዳግም የመሬት ናዳ እና ጎርፍ ተከስቶ በሰዉና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል " - የአከባቢው ነዋሪዎች
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከሰሞኑ በአከባቢያቸዉ ነፋስ ቀላቅሎ እየጣለ ያለዉ ከባድ ዝናብ የመሬት ናዳ እና ጎርፍ በማስከተሉ በሰዉ ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል።
ከሚያዚያ 9/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በአከባቢዉ እየጣለ ያለዉ ዝናብ በተለይም ፦
- ጎሬ ኦዳ፣
- ጃዉላ ዉጋ ማሽታሌ፣
- ኤላ፣
- አማሮ ሻጌ፣
- ቡልቂ በተባሉ አከባቢዎች ባስከተለዉ ከባድ ነፋስ፣ ከፍተኛ የዉሃ ሙላት እና የመሬት መንሸራተት የ3 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ4 በላይ ቤቶች በመሬት ናዳዉ መስመጣቸዉንና፤ የእርሻ ማሳዎች እንዲሁም የቤት እንስሳት ጭምር በመሬት መንሸራተቱ መወሰዳቸዉን ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።
በወረዳዉ ሰሞኑን በተከሰተዉ ዳግመኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በጎዶ አንደኛ ትምህርት ቤት እና በአንድ የሃይማኖት ተቋም ግቢ ተጠልለው እንደሚገኙ የሚናገሩት ነዋሪዎቹ የዝናብ ሁኔታዉ ቀጣይነት ያለዉ ስለሚመስል አሁንም ከፍተኛ ስጋት ዉስጥ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
" በወረዳዉ የዛሬ ዓመት በተከሰተዉ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን መሉ በሙሉ መልሶ የማደራጀቱ ስራ ባልተጠናቀቀበት ይህ መከሰቱ ስጋታችንን ከፍ ያደርገዋልም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገራቸዉ የገዜ ጎፋ ወረዳ አደጋ ስጋት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማስረሻ ማናዬ በበኩላቸው በአካባቢው እየጣለ ባለዉ ከባድ ዝናብ በወረዳዉ አራት ቀበሌያት በሰዉ፣ በንብረትና በቤት እንስሳት ላይ ጉዳት ማድረሱን አስታዉቀዋል።
ተጨማሪ አደጋዎች እንዳይከሰቱ የወረዳዉ መንግስት በልዩ ተኩረት እየሰራ ነዉ ያሉት አቶ ማስረሻ ጉዳት የደረሰባቸውን ነዋሪዎች የማቋቋም ስራም እንደሚሰራ ገልፀዋል።
ባሳለፍነዉ ዓመት በአከባቢዉ የተከሰተዉ መሰል የመሬት መንሸራተትና ናዳ ምክንያት በርካታ ሰዎች መሞታቸዉ የሚታወስ ሲሆን አሁንም ድረስ በአከባቢው በስጋት የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ሙሉ በሙሉ መልሶ የማቋቋም ስራዉ አለመጠናቀቁን በቅርቡ የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

😢773😭358❤141🙏79💔49🕊26🤔20😱18😡17🥰9
" ላሟ ጅራት አልባ ጉማሬ መሰል ጥጃ ነው የተገላገለችው። ጥጃዉ ወዲያዉ ሲሞት ላሟም በማግስቱ ሞታለች " - ነዋሪዎች
🔴 " እኔ ስደርስ ባየሁት ነገር በጣም ደንግጫለሁ ! " - የአከባቢው እንስሳት ሀኪም
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ገዜ ከንቾ ቀበሌ አንዲት ላም ጉማሬ መሰል ጥጃ ከሰዓታት ምጥ በኋላ በሰዎች እርዳታ ብትገላገልም ጥጃዉ ወዲያዉኑ መሞቱንና ላሟም በማግስቱ ሕይወቷ ማለፉን የላሟ አሳዳጊና የአካባቢው ነዋሪዋች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የላሟ አሳዳጊ አቶ ኢሳያስ አልፋቴ ስለ ጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ " ላሚቷ ከዚህ ቀደም ሶስት ዙር ወልዳ ነበር። በአሁኑ ዙር ሆዷ ያለ ልክ ከፍ ብሎ ነበር ፤ የመዉለጃዋ ጊዜ ሲደርስም እንቅስቃሴዋ ዘገምተኛ ነበር " ሲሉ ገልጸዋል።
" በዕለቱ ለመዉለድ መቃረቧን ተከትሎ እንደሁልጊዜው ሁሉ በሰላም ትወልዳለች ብለን ብንጠብቅም ከ5 ሰዓታት በላይ ምጧ በመቀጠሉ ስጋት ስለያዘን ለአከባቢው የእንስሳት ሐኪም ደዉለን ሁኔታዉን አስረድተን ነበር ነገር ግን ባለሙያዉ በቅርበት ስላልነበር በቶሎ አልደረሰልንም ኋላም ላሟ በመዳከሟ የአከባቢው ሰዎች 'የወጣዉን እግር አስረን እንጎትት' በማለታቸዉ ጥጃዉ ተጎትቶ ከወጣ በኋላ ወዲያው ሞቷል " ሲሉ ተናግረዋል።
ጉማሬ መሰሉ ጥጃ ክብደቱ በግምት 50ኪሎ ግራም በላይ ነዉ ያሉን የአካባቢው ነዋሪዌች በማግስቱም ላሚቷም መሞቷን ገልፀዋል።
" እኔ ስደርስ ባየሁት ነገር በጣም ደንግጫለሁ " ያለን በአከባቢዉ የእንስሳት ሐኪም ሕዝቅያስ ሀብታሙ " የተወለደው ጭራ አልባና ከጥጃ ይልቅ ጉማሬ የሚመስል ፍጥረት ነዉ " ብለዋል።

😱514😭175❤100🤔67😢26🙏23🕊10💔10👏9🥰8
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ ከትርፍ ሰዓት ክፊያ ጋር በተያያዘ ሁለት ሳምንት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ የቆዩ የጤና ባለሙያዎች በዋስ መፈታታቸዉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከስፍራዉ አረጋግጧል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከሚያዚያ 8/2017 ዓ/ም ጀምሮ 14 የጤና ባለሙያዎች ታስረዉ የነበረ ሲሆን 7ቱ ከቀናት እስር በኋላ ተለቀዉ 7ቱ እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ በሀንጣጤ ከተማ ፓሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የቆዩ ቆይተዋል።
ዛሬ እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ መደረጉን የዓይን እማኞች ተናግረዋል።
በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በሚገኘዉ ሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያሉ የጤና ባለሙያዎች ከ6 እስከ 9 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ከወረዳ እስከ ክልል መዋቅር አሳዉቀዉ የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆማቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳዉቀዉ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም በጉዳዩ ዙሪያ ከእስር ተፈቱ የተባሉ የጤና ባለሙያዎችን ለማግኘት ያደረገዉ ሙከራ አልተሳካም።
ጉዳዩን አሁንም በቅርበት የምንከታተል ይሆናል።

😡318😭86❤47🕊14🙏10😢8🥰5💔1
" ያለ ቅድመ ሁኔታ ከስራ መስመር እንድንወጣ መደረጉ ለዘርፈ ብዙ ችግር ዳርጎናል " - የኤሌክትሪክ ባጃጅ አሽከርካሪዎች
" በመንግስት አበረታችነት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በብድርና በዋስትና ጭምር አዉጥተን በቅርቡ የገዛናቸዉ የኤሌክትሪክ ባጃጆች በአስፓልት መንገዶች እንዳሰሩ ተደርገዋል ፤ ይህም ለዘርፈ ብዙ ችግር ዳርጎናል " ሲሉ በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ አሽከርካሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
እያንዳንዳቸው በ1 ሚሊዮን 2 መቶ ሺ ብር ገዳማ የሚገዙ 140 በላይ ባጃጆች በከተማው እንደሚገኙ የሚገልፁት አሽከርካሪዎቹ ያለ አንዳች ዉይይትና ቅድመ ሁኔታ ካሳለፍነዉ አርብ ጀምሮ " በአስፋልት መንገዶች እንዳይሰሩ ተብለናል " በሚል የትራፊክ ፖሊሶችና የመንገድ ደህንነት አስከባሪዎች የእንቅስቃሴ ገደብ እንደጣሉባቸው አስረድተዋል።
አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ የኤሌክትሪክ ባጃጅ አሽከርካሪ አስቀድሞ የቤንዚኑን ባጃጅ ይሰራበት እንደነበርና እሱን ሽጦ የወላጆቹን የቤት ካርታ በማስያዝ የኤሌክትሪክ ባጃጅ መግዛቱን ገልጾ ወደ ስራ ከገባ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ " በአስፋልት መንገድ መስራት አትችሉም " ተብለን ከስራ መስመር እንድንወጣ ተደርገናል ብለዋል።
ሌላኛዉ ቅሬታ አቅራቢ ደግሞ " ባጃጁን የገዛሁት መንግስት ለጭስ አልባ ሞተሮች የሰጠዉን ትኩረት በሚገባ ካጠናሁ በኋላ ነዉ በድንገት የተወሰደዉ እርምጃ እጅግ አሳዝኖናል " ሲል ተናግሯል።
ከባጃጅ ግዢዉ በተጨማሪ ለ3ኛ ወገን 12 ሺ ብር ገደማ፣ 2 ፐርሰንት ተብሎ ደግሞ 21 ሺ ብር እና ለታርጋ 10 ሺ ብር ከእያንዳንዱ ባጃጅ ለመንግስት ገቢ አድርገናል የሚሉት አሽከርካሪዎቹ " ከተማዉንና ዘመኑን የሚመጥን ትራንስፖርት ነዉ " ስንባል ቆይተን በድንገት ከመስመር ዉጡ መባላችን ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ዳርጎናል ብለዋል።
በባጃጅ ስራዉ
- ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ፣
- ያስያዙትን የቤት ካርታ ለማስለቀቅ በየቀኑ ገንዘብ በባንክ ገቢ የሚያደርጉ
- ባጃጅ በዕቁብ ብር ገዝተዉ የቀን እቁብ የሚጥሉ፣
- ልጆች የሚያስተምሩ
- ቤተሰብ እጃቸዉን የሚጠብቅና ልዩ ልዩ የግዴታ ወጪዎች ያለባቸዉ አሽከርካሪዎች ይበዛሉ የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለከተማዉና ለክሉም መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሄደን ይኸን ሁሉ ገልፀን ብናመለክትም ተገቢውን ምላሽ አላገኘንም ብለዋል።
አንዳድ የመስሪያ ቤቶቹ ባለሙያዎች " ለምን ዉስጥ ለዉጥ እየሰራችሁ ጥያቄ አትጠይቁም " ይላሉ ነገር ግን የባጃጁ ስሪት ለኮብል ስቶን (የድንጋይ ንጣፍ) መንገድ ፍፁም የማይሆንና በቀናት ዉስጥ 'ሲልድ ባትሪዉንና ዲናሞዉን' ከጥቅም ዉጪ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ከሀዋሳ ከተማ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊና ምክትል ኃላፊዉ መረጃ ለማግኘት ያደረገዉ ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።
ምላሻቸዉን ስናገኝ የሚናካትት ይሆናል።

😡386😢93❤68💔18🙏15🤔14😭13🕊6🥰2