TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tokyo2020 🇪🇹 #Ethiopia በ20 ኪ.ሜ የእርምጃ ውድድር ተወዳዳሪ የነበረችው አትሌታችን የኋላዬ በለጠ ውድድሯን አቋርጣለች። የኋላዬ በዓለም ሻምፒዮና ሁለት ግዜ ለንደን 2017 እና ዶሀ 2019 እንዲሁም በ 2016 የ ሪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክላ መሳተፏ የሚታወስ ነው። በዘንድሮው የ 20 ኪ.ሜ የእርምጃ ውድድር ሀምሳ ስምንት አትሌቶች መሳተፍ ችለዋል። @tikvahethsport
#Tokyo2020 🇪🇹 #Ethiopia

በ 5,000 ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ውድድር ዩጋንዳዊው ጆሽዋ ቼፕቴጌ የ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል።

ሀገራችንን ወክሎ በብቸኝነት የተወዳደረው አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ #አስረኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

ጆሽዋ ቼፕቲጌ የ5,000 ሜትር የቀነኒሳ በቀለን ሪከርድን ከአስራ አምስት ዓመት በኋላ የግሉ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ጆሽዋ ቼፕቲጌ በ ቶኪዮ ኦሎምፒክ የ10,000 ሜትር ውድድር ላይ ሲሳተፍ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወቃል።

በዛሬው የ5,000 ሜትር ውድድር ላይ ሁለት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለባህሬን በ ርቀቱ መወዳደር ችለዋል።

@tikvahethsport